Tuesday, October 30, 2012

ሲኖዶሱ በሰባተኛ ቀን ውሎው ቃለ ጉባኤ ላይ ሲጨቃጨቅ ዋለ

Click here to read in PDF:sinodos 7
ሲኖዶሱ በትናንትናው ዕለት በነበረው ስብሰባ ቃለጉባኤ ሲያስነብብ እና ሲጨቃጨቅበት ውሏል፡፡ አቃቤ መንበሩ አቡነ ናትናኤል የባንዲራ ቀን ለማክበር ሄደው ስለነበር ስብሰባው የተካሄደው እሳቸው በሌሉበት ነበር፡፡ ቃለጉባኤው ሲነበብ ካነጋገሩት ነገሮች መካከል ዋነኛው የአሜሪካው ጉዳይ ነበር፡፡ ያጸደቁትን እና የሚተዳደሩበትን ህግ የማያውቁ የሲኖዶሱ አባላት የአርባ ምንጩ አቡነ ኤልያስ መሪነት እኛ የወሰንነው ሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ ይነሳ ብለን ነው ለምንድን ነው የማይነሳው? ብለው ህገ ደንቡ በማይፈቅድላቸው ጉዳይ ሙግት ጀመሩ፡፡
ነገሩ ወደ ጭቅጭቅ በማምራቱም አቡነ ናትናኤል ባሉበት በዛሬው ዕለት እንደገና እንዲታይ ተወስኗል፡፡ እንደገና ይታይ ሲባልም በክብረ መንገስት ሕዝብ ተዋርደው እና አንገታቸውን ደፍተው የወጡት አቡነ ዮሴፍ ጉዳዩን ደግመን የምናየው ከሆነ የምናየው አቡነ ፋኑኤል በሌሉበት መሆን ነው ያለበት ቢሉም አቡነ ፋኑኤል ግን እስከ አሁን ድረስ የማንም ሀገረ ስብከት ጉዳይ በሲኖዶስ ሲታይ ሊቀ ጳጳሱ ባለበት ነው የኔ ጊዜ ለምንድን ነው የምወጣው? የአቡነ ገብርኤል ጉዳይ የታየው እሳቸው ባሉበት ነው ስለዚህ እኔ ባለሁት ነው የሚታየው በማለት መልሰዋል፡፡


ህጉ የሚለው የሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ የሚነሳው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ካላመነበት ብቻ ነው ነው፡፡ ጌታቸው ዶኒ አዋሳ ስራ አስኪያጅ በነበሩበት ጊዜ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ጠንካራ እምጃዎችን መውሰድ በመጀመራቸው ማኅበርዋ ስለተቆጣች እነ ደጀ ሰላም አቡነ ገብርኤል አልፈልገውም ብለው ማንሳት መብታቸው ነው፡፡ እንኳን ሌላ ጳጳስ ፓትርርኩም አያገባቸውምም ሲል መጻፉዋ እና አቡነ ገብርኤልም ይህን ጠቅሰው ጌታቸው ዶኒን ማስነሳታቸው ይታወሳል፡፡ አሁን የአቡነ ፋኑኤል ጊዜ ሲኖዶሱ በማያገባው ገብቶ መዘባረቁ እያስገረመን ነው፡፡ ነው ጳጳሳቱ የሚተዳደሩበትን ህግ እንደፈለጉ ለማሽከርከር ሲሉ በጉናጫቸው ላይ ነው ይዘው የሚዞሩት ያሰኛል፡፡ በማይመለከታቸው ጉዳይ ጣልቃ መግባት ህግ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጠቅመው ከሆነ ሊጠቀስ የሚጎዳው ከሆነ ደግሞ እየተሻረ የሚሄደውስ እስከ መቼ ነው?
የካህሳይ መጽሐፍ ጉዳይ እስካሁን እንዳቃጠላቸው አለ፡፡ ቃለ ጉባኤው ላይ የካህሳይ ስም ሲነሳ የተንዘፈዘፉት ጳጳሳት ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ካህሳይ ጉድለታችንን ገልጧል፡፡ እንዴት መኖር እንዳለብን ለህዝብ አሳይቷል፡፡ በሚሎ ሰንካላ ምክንያት ልባቸው በቂም እና በበቀለኛነት ስሜት እንዲህ መንገብገባቸው በእውነት እነዚህ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ አንብበው ያውቃሉ ወይ? ያደጉትስ ምን እያደረጉ ነው? አንድ ሰው ለምን የአኗኗራችንን ምሥጢር ገለጠው ተብሎ እንዲህ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? አልተበደሉም እንጂ ተብድለው እንኳ ቢሆን ስለይቅርታ ያላቸው ግንዛቤ ምንድን ነው? በእውነት የክርስቶስ ተከታዮች ናቸው የሚሉት ጥያቄዎች ለብ ኖሯቸው ሊመልሱዋቸው የሚገቡ ጥቆዎች ናቸው፡፡
የአክሱም ጉዳይ እንደገና የጭቅጭቅ ርዕስ ሆኗል፡፡ አቡነ ሰላማ እና አቡነ ናትናኤል አሰላ ላይ የቆየ ጸብ ስላላቸውም ነገሩ እንዲባባስ ምክንያት መሆኑ ይወራል፡፡ የሆነ ሆኖ አክሱሞች በትናንትናው ዕለትም በስብሰባው ላይ ተገኝተው አቡነ ሰላማን መልሳችሁ ከላካችሁብን ለሚፈጠረው ችግር ሁሉ ባለዕዳው ሲኖዶሱ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡ ሲኖዶሱ ግን አቡነ ሰላማ ይመለሱ ብለናል እኮ ቢልም አክሱሞች ግን ብታስበብቡት ይሻላችሁዋል ብለናችኋል አክሱምን የሚመለከት ጳጳስ ማስቀመጥ የሚችለው ፓትርያርክ ስለሆነ ሌሌቻችሁ አያገባችሁም አሁን ባለው ሁኔታ ጉዳዩ የአቡነ ናትናኤል ጉዳይ ነው አቡነ ሰላማ አይመለሱብን ብለዋል፡፡ ለማኅበረ ቅዱሳን ብዙም ያልተመቹት እና እንዲሾሙ ሲስደርግም አሻንጉሊት ሊያደርጋቸው የነበረውን እቅድ ያፈራረሱት አቃቤ መንበሩ ቃለ ጉባኤው ላይ ፊርማዬን የማኖረው ሲኖዶሱ ከአክሱም ጉዳይ ላይ የማያገባው መሆኑን አምኖ ሲቀበል ነው ብለዋል፡፡
ስብሰባው በዛሬው እለት ቀጥሎ በነገው ዕለት እንደሚያበቃ ይጠበቃል፡፡



1 comment: