Sunday, October 28, 2012

ለቅዱስ ፓትሪያሪክ መርቆሪዎስ


በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
በለሱንየጠበቀፍሬዋንይበላል፥ጌታውንምየሚጠብቅይከብራል!
ቅድመ ሐተታ
በይድረስ የተጻፈውን ደብዳቤ ከመልዕክቱ ተቀባይ ከቅዱስ ፓትሪያሪኩ አልፎ ለአንባቢያን በግላጭ ማቅረብ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ቅዱስነታቸው ፊት ለፊት አፍጥጦ የሚጠብቃቸው በሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ቅራኔ ከዚህም አልፎ የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን  "ልክ ለሌለው" የመከፋፈልና የመለያየት፤ ማንም እንዳሻው እየተነሳ በራሱ አለቃ የሚሆንበት ሥርዓት አልበኝነት/ጋጠወጥነት ያነገሰ አሳፋሪ ገጽታ ለማስቆምም ሆነ አሁን ካለበት ሁኔታ ተባብሶ እንዲቀጥል ለማድረግ ሁለቱም አካላት የሚያሳዩት/የሚያንጸባርቁት አቋም በሌላ አገላለጽ በሚያስተላልፉት ውሳኔና በሚወስዱት እርምጃ በቀጥታ ቀዳሚ ተጠቃሚም ሆነ ተጎጂ የሆነውን የቤተ እምነቱ ተከታይ (ምእመናን) በመሆናቸው በዚህ ጉዳይ ማለትም እርቀ ሰላሙን በማውረድ ረገድ ማን ምን እያደረገ እንዳለ መጠነኛ ግንዛቤ ይኖረውና ያውቅም ዘንድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው።


የመልዕክቱ ይዘትና ውሱንነት በተመለከተ
ቅዱስ ፓትሪያሪኩ እንደ አባትና የበላይ መንፈሳዊ መሪ ቅድስት ቤተ- ክርስቲያን እየታማሰችበት በምትገኘው ጉዳይ ላይ ህውከቱና የመለያየት ክፉ መንፈስ ለማስወገድ ሲባል በሚወስዱት ቀጣይ እርምጃዎች ጥንቃቄ በተሞላበትና ከምንም በላይ ደግሞ ከሰላቢዎች ሴራና ደባ ራሳቸውን ይጠብቁ ዘንድ በዚህ ሁሉ ሂደትም የሚሆነውን ሁሉ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የማንም ጥቅም ለማስከበር ሲባል የቅድስት ቤተ- ክርስቲያን ጥቅም ብቻ በማስቀደም ይሆንና ይደረግ ዘንድ የክርስትና መነሻና መደምደሚያ፣ በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ስልጣን የመጨረሻው እርከን የሆነው ቃል (መጽሐፍቅዱስ) ተመርኩዞ ለምክርና ለተግሳጽ ተጻፈ።
ቅዱስነትዎ!  ምህረትና እውነት ፍቅር ቸርነትም በሞላው ጌታ ሰላምዎ ይብዛ በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ሰላም እሎታለሁ።
ቅዱስነትዎ!  ለረጅም ዘመናት እትብትዎ ተቆርጦ ከተቀበረባት፣ ተወልደው ካደጉባት ሀገር እንዲሁም ያገለግሉት ዘንድ ከተሾሙበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ርቀው በብዙ ወጀብና አውሎ ነፋስ ሳይበገሩ ለዚህ ሁሉ ዘመናት በአገልግሎትዎ  "ይድፋ"  ባይ በማይገኝበት ህይወትዎ ላሳዩት ጽናትና ትዕግስት በታናሽነቴ ቡራኬዎ ይድረሰኝ ስል በረከትዎንና ይሁንታዎትን ተቀብዬ ወቅታዊ የቤተ- ክርስቲያናችን ሁኔታ በማስመልከት በመንፈስ ቅዱስ በልጅነት መንፈስና በክርስቶስ ኢየሱስ ዝቅ ባለ የትህትና ልብ እንደሚከተለው ሃሳቤን አካፍሎት ዘንድ ወደድኩ።
ቅድስነትዎ!  ጠቢቡ በምሳሌው  "በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል!”  እንዲል  በእውነቱ ነገር እግዚአብሔር ስለመጠበቅ ለእርስዎ የሚነገር ሆኖ ሳይሆን ቢሆንም ግን ከሳለፉት ረጅም የእንግድነት ኑሮ የተነሣ ሥጋ በሥጋ ማንነት ማውጠንጠኑ አይቀርምና አፋፍ ላይ በደረሰው ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ውሳኔዎ " እስከ ዛሬ ዕለት ድረስ የሚጡበትን መንገድ" ጠብቀው ራስዎን ለቅድስት ቤተክርስቲያን ጥቅምና ለሚመሩት ምእመን ያሎትን ታዛዥነትና የአደራ ሃላፊነት  እስከ መጨረሻ ሰዓት ድረስ በማሳየትና በመጠበቅ ከሚበረው ባቡርና ከሚወርደው ወራጅ እግርዎትን ይጠብቁና የነገሮች አመጣጥ በማጤን ምላሽ መስጠት ይቻልዎትም ዘንድ  ዓይንዎና ጆሮውን በእግዚአብሔር መንበር ላይ ጥለው ይቆሙ ዘንድ ነው። የእርስዎ ብቻ መቅረት፣ የአብሮ አደጎችዎትን በአጸደ ሥጋ አለመኖር፣ በሚገኙበትን አከባቢም ሆነ በሌሎች የአብያተ ክርስቲያን የስራ አፈጻጸም ድክመትና ብልሹ አሰራር ተማረውና ተሰላችተው ዛሬ ላይ ደርሰው የቁዘማ ህይወት ውስጥ ገብተው ልቦትን የሚያነቅሉበት ምንም ዓይነት ምክንያትም ሊኖር አይገባምና በዚህ ረገድም የገዛራ ስዎትን ቀዳዳ ለሌሎች አጀንዳ ማርኪያ ሆኖ እንዳይገኝም ላነቃቃዎት እወዳለሁ።
ቅድስነትዎ!  መገኛዎትን ሳይመለከት ራሱን ታምኖ የጠራዎት፣ የሾምዎት፣ የቀባዎት፣ ያከበርዎት፣ በፊቱና በሕዝብ ፊትም ይቆሙና ይሻገሩ ዘንድ የመረጥዎት እግዚአብሔር እስከ ዕለተ ዕረፍትዎ ድረስ በክብርና በላቀ ማዕረግ ይጠብቅዎት ዘንድ የታመነ ለመሆኑ እኔ አልለወጥም ያለ፣ በክንዱ ታላቅን ነገር የሚያደርግ፣ ለስራ የተዘረጋች እጁን ያጥፍ ዘንድ ይቻለው የሌለ እግዚአብሔር ዕድል ፈንታው ለሆነለት ለያዕቆብ ቤት "እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ ስሙኝ  እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፥ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ"  እንዲል እንደተገረው በየትም ስፍራ በየትኛውም ሁኔታ የሚያከብሮትና ከሰው እልፎ ሳር ቅጠሉ ለክብሩ ማቆም የሚቻለው እግዚአብሔር  ብቻ አይተው እጅዎትን መምታት ይሆንሎት ዘንድ ላሳስቦት እወዳለሁ።
ቅድስነትዎ!  ቀደም ስል እንደገለጽኩት ስጋ መንፈስ ካልገራውና ካልመራው የራሱ ባልሆነ ነገር ላይ በስርቆት አሻግሮ ማየቱ አይቀርምና የቅዱስ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ስርዓት አይተውም ሆነ ሰምተው " እኔስ ነገ ምን ይገጥመኝ ይሆን?" በማለት በድንዎትን የሚጥሉበት ስፍራ ሊያሳስቦት አይገባም። ከዚህም የተነሳ የሚቀለብሱት አቋምም ሆነ የቤተ- ክርስቲያን ጥቅም አሳልፈው በመስጠት የራስዎትን ነገር በማስቀደም የሚወስዱት ውሳኔ ሊኖር እንደማይችል ተስፋ አደርጋለሁ።
ቅድስነትዎ!  የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ካሌብ በቀረቡ ጊዜ ካሌብ "እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ። ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደነበርሁ፥ ዛሬ ጕልበታም ነኝ ጕልበቴም በዚያን ጊዜ እንደነበረ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።"  እንዲል ዛሬም የሚያረጅ ጨርቅ እንጂ የሚያረጅ ቅባት እንደሌለ በመገንዝብ  "አሁንስ ደክሜአለሁ፣ ምን ቀረኝ ሀገሬ ልግባ"  በማለት ይህን ሕዝብ በትነው መልካም በሚመስል ዳሩ ግን ትክክል ባልሆነ ሽምገላ ተታለው ፌትዎትን በእግዚአብሔር ላይ እንዳይመልሱም እማጸኖታለሁ።
ቅድስነትዎ!  በዋናነት አጀንዳው የቅድስት ቤተክርስቲያን አጀንዳ እንደ መሆኑ መጠን ከማንኛውም አንጻራዊ የሆነ አካሄድና የባላንጣ አስተሳሰብ ካለው አካል ጋር በግልዎ/በተናጠል የሚያደርጉት ማንኛውም ዓይነት ግኑኝነት ለጠላት በርን የመክፈት ያክል ለአደጋ የሚያጋልጥ፣ የዕርቀ ሰላሙን ሂደት የሚያደናቅፍ፣ እውነትንየ ሚያጨልማና የሚሸረሽር ተገቢ ያልሆነ ይልቁንስ አፍራሽድ ርጊት አውቀው ከእንዲህ ዓይነት በጥሩ ዕቃ የተዘጋጀ መርዝ/ወጥመድ ራስዎትን ይጠብቁና ይታቀቡ ዘንድ በድጋሜ ላሳስብዎት እወዳለሁ።
በመጨረሻ በአጽንዖት የማመላክቶት ነጥብ ቢኖር በድጋሜ  እርስዎን ብቻ ላይ በማተኮ ርበተናጠል ለማነጋገር የተፈለገበትና የሚፈለግበት ጉዳይ "እሳቸው በባሌም በቦሌም ብለን አባብለን ወደሀገር ቤት  እንዲገቡ ያደረግን እንደሆ ነሌሎች ማድሮውንም አንፈልጋቸውም፣ አዳዲሶቹም እንደ ሆኑ በአንዲት ጀንበር መሻራቸው አይቀርም፣ ፓትሪያሪኩን ተከትለው የሚገቡ ወዶ- ገብችም የተገኙ/ያሉ እንደሆነ አስገብተን (ወደ አገር ቤት ማለት ነው)  እንደቁሰዋለን"  በሚል ስሌት ከጀርባው ያለውን የድውያን ፖለቲካዊ ብልጠት በመንቃት በግል/በተናጠል የጀምሩት ማንኛውም ዓይነት ግኑኝነት በቅድስትቤተ-ክርስቲያን አንድነትና በምእመናን ሞራላዊ ህይወት ላይ የሚያስከትለውን ግልጽ የሆነ አደጋ ከወዲሁ አርቀው በመመልከት የጀመሩትን ግኑኝነት ዋል- ይደርሳ ይሉ ያቆሙ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እጠይቆታለሁ። በበር የማይገባ እሱ ሊገድል ሊያጠፋና ሊያርድ የሚመጣ ሌባ ነውና።
ቡራኬዎ ይድረሰኝ!

/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
United States of America

No comments:

Post a Comment