Monday, November 5, 2012

የግብጽ ቤተክርስቲያን አቡነ ቴዎድሮስ ሁለተኛን 118ኛዋ ፓትርያርክ አድርጋ ሾመች


read in PDF:
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ አቡነ ቴዎድሮስ ሁለተኛ በመባል የግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አዲሱ ፓትርያርክ ሆነው በትናንትናው ዕለት በመንፈስ ቅዱስ ተመረጡ፡፡ ለምርጫው የመጨረሻ እጩ ከነበሩት ከሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት እና ከአንድ መነኩሴ መሀል የመንፈስቅዱስን ሞገስ ያገኙት አቡነ ቴዎድሮስ ህዳር 9 ቀን በፓትርያርክነት ይቀባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ  በዕጣ ፓትርያርክ መሾም የጀመረችው በ18ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ የእግዚአብሐየር ፈቃድ ሆኖ ከ6 ዓመት ያልበለጠ ልጅ ዓይኑ በጨርቅ ታስሮ ባወጣው ዕጣ የተመረጡት አቡነ ቴዎድሮስ ሁለተኛ የ60 ዓመት አዛውንት ናቸው፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የምርጫው ዕለት የልደታቸው ቀን የሆነው አቡኑ የሁኔታው መገጣጠም ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1997 በጵጵስና የተቀቡት አቡነ ቴዎድሮስ ከካይሮ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በመንፈሳዊ አባትነታቸው የተመሰገኑ እና የቤተክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስም ሙሉ ድጋፍ ያላቸው አባት ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment