Saturday, March 24, 2012

አቡነ ሳሙኤል ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ውስጥ ሽምቅ ውጊያ መጀመራቸው ተሰማ


በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ለጳጳሳት ማረፊያ በተሰራው ህንጻ ውስጥ ሳይሆን፣ ተምረው ባላለፉበት በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ የሚኖሩት የልማት ኮሚሽን የበላይ ጠባቂ አቡነ ሳሙኤል ከማህበረ ቅዱሳን የተሀድሶ መናፍቃንን ዘመቻ ለመከላከል በሚል ከሰበሰበው ገንዘብ ላይ እንደተለቀቀላቸው በሚታመነው ገንዘብ አንዳንድ የኮሌጁን ተማሪዎች በማባበልና ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው የሚባሉ ተማሪዎችን በመዋጋት በውስጣቸው ተዳፍኖ አልወጣላቸው ያለውን መፈንቅለ ፓትርያርክ እንደገና ለመሞከር ሽምቅ ውጊያ መጀመራቸው ተሰማ፡፡

አቡነ ሳሙኤል ከማህበሩ ጋር በመቀናጀት ለጀመሩት ሽምቅ ውጊያ አንዱ የቤት ስራቸው በኮሌጁ ውስጥ ከዚህ ቀደም በደጀሰላም ድረገጽ ላይ ወጥቶ የነበረውና ማህበረ ቅዱሳን ‹‹ተሀድሶ ናቸው ይባረሩልኝ›› ብሎ ያለባለቤትና አድራሻ የላከውንና በኮሌጁ አስተዳደር ውድቅ የተደረገውን ክስ እንደአዲስ ማንቀሳቀስና የተባሉትን ደቀመዛሙርት ከኮሌጁ ማስወጣት ነው፡፡ ከሰሞኑም ያው ስም አጥፊ ደብዳቤ እንደ ተለመደው ያለባለቤትና አድራሻ ተልኮ ለኮሌጁ አስተዳደር ከደረሰ በኋላ ፍሬከርስኪ ሆኖ በመገኘቱ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ምክንያቱም ባለቤት የለውም አድራሻም የለውም፡፡

Wednesday, March 21, 2012

የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ ደጀ ሰላም ለምን ተቀዛቀዘ?


ማህበረ ቅዱሳን በስዉር የሚፈልገውን እያጻፈ ቤተክርስቲያናችንን ሲበጠብጥ የነበረው ደጀሰላም ድረገጽ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያስተዋል ነው። ለምን ተቀዛቀዘ? ለሚለው ግን ድረገጹ የሚያቀርባቸው ምክንያቶች ውሃ የሚያነሱ ሆነው አልተገኙም። ከምክንያቶቹ አንዱ ከስሜ የተወሰነ ፊደል እየገደፉና እየጨመሩ የተለያዩ ድረገጾች በስሜ ተከፍተዋል የሚል ነው። ይሁን እንጂ ድረገጹ በርካታ ተገዳዳሪና ወደረኛ የሆኑ ድረገጾች ተከፍተው አፉን ማዘጋት ስለቻሉ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ደጀሰላም ያለ ተቀናቃኝ ብቻውን ድረገጽን የተቆጣጠረበትና እውነትን ሀሰት፣ ሀሰትን እውነት እያለ የሚዘላብድበት፣ አላማውን የተቃወሙ ብጹዓን አባቶችን ስም ሲያጎድፍ የነበረበት፣ በብዙ መንፈሰዊ ችግሮች ውስጥ የተዘፈቁና እርሱን የደገፉትን ሁሉ ሰማይ ላይ የሰቀለበት ዘመን ስላበቃና አማራጭ ድረገጾች የእርሱን ድብቅ ገመና አደባባይ ላይ በማስጣት እውነትን መመስከር ስለጀመሩ ነው። በተጨማሪም የማህበረ ቅዱሳን ፖለቲካዊ አጀንዳ ስለ ተነቃበትና የመንግስትን ትኩረት ስለሳበ የፖለቲካዊ ስሜቱ ማስተንፈሻ የሆነው ደጀሰላም ለጊዜው ራሱን ደበቅ ለማድረግ በሚል ማህበሩ አዲስ በከፈታቸው በአንድ አድርገንና በገብርሄር ላይ ግልጽ ፖለቲካ የሚንጸባረቅባቸውን፣ መንግስትንና ህዝብን ለማጋጨት ጥረት የሚያደርጉ፣ ህዝቡን ከቤተክርስቲያን አባቶች ጋር ለማናከስ የሚቀሰቅሱ ዘገባዎችን በስፋት እያወጡ ይገኛሉ።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአሁኑ ሰዓት ድረገጹ ተቀዛቅዞ የሚገኘው ድረገጹን ከማህበረ ቅዱሳን በተመደበ በጀት በዋናነት ሲያንቀሳቅስ የነበረው ሱራኤል ወንድሙ አሜሪካ መግባቱን ተከትሎ ነው። ለደረገጹ የሚሆኑ ወሬዎችን በመቃረም ለማህበሩ በሚጠቅም ሁኔታ እያዛቡና እያዛነፉ የሚሰልቁት ቱሪስት ሆቴል፣ ምርፋቅ እና ሶመሰ ካፌና ሬስቶራንቶች የማይጠፋው የድራፍት ጠጪዎች ቡድን ነው። የዚህ ማፍያ ቡድን አባላት ሰብሳቢያቸው ሱራፌል ወንድሙ፣ ጳውሎስ /መረዋ/ መልክአ ስላሴ፣ በመሰሪነቱ የሚታወቀው ዳንኤል (ዴራ) ተስፋዬ ሞሲሳ፣ ሰለሞን (የአዲሱ ሚካኤል) ምክትል ሰባኬ ወንጌል፣ ወንድወሰን፣ እና ሌሎች ያሉበት ስብስብ ነው።

Tuesday, March 20, 2012

ዛሬም ያልተፋቱት ኢትዮጵያና ግብፅ


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ግብጻውያንና የዓባይ ወንዝ፡-
ከቤተ ጳውሎስ ድረገጽ የተወሰደ 
ከትላንት በስቲያ በሥጋ የተለዩን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ሀገር የሆነችው ግብጽ የረጅም ጊዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያላት አፍሪካዊት ሀገር ናት፡፡ እጅግ የዳበረ የሥነ ሕንጻ፣ የሥነ ጽሑፍ፣ የፍልስፍና ማዕከል፣ በዓለማችን ከሚገኙት ታላላቅ ሥልጣኔዎች ተብለው ከሚጠቀሱት ከፋርስ (ፐርሺያ)፣ ከባቢሎን፣ ከአሴርያውያን፣ ከግሪክ፣ ከሮማ፣ ከቻይና፣ ከደቡብ አሜሪካዎቹ ከአዝቴክስና ከኢንካ እንዲሁም ከእኛዋ አክሱም ሥልጣኔ ጋር በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ ሀገር ናት፡፡
በዓለማችን የመጀመሪያ እንደሆነ የሚነገርለትና በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ የፍልስፍና፣ የታሪክ፣ የጥበብ፣ የአልጄብራና ጆሜትሪ፣ የሥነ ፈለክ፣ የሕክምና እና የመሳሰሉ የጥንት የብራና ጥቅልሎችን የያዘውና ግሪካዊው አሌክሳንደር ዘግሬት ግብጽን በወረረ ጊዜ ለቃጠሎና ለመዘረፍ የበቃው ቤተ መጻሕፍት አቻና ወደር የሌለው እንደነበር የግብጽን ሥልጣኔና ታሪክ የሚያጠኑ ምሁራን (Egyptologists) ይናገራሉ፡፡ እንደውም እንደ አንዳንድ አፍሪካውያንና አፍሪካ አሜሪካውያን ምሁራን ለግሪክ ሥልጣኔ ትልቅ መሠረት የጣለው ከዚሁ ከግብጻውያን ቤተ መጻሕፍት በተዘረፉት የዕውቀትና የጥበብ ምንጮች በሆኑት የብራና መጻሕፍቶች እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡
በሃይማኖትም ረገድ ግብጽ እስራኤል ጋር ባላት ታሪካዊ ትስስር የተነሣም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፊ ቦታ ተሰጥቷት የተተረከላት ሀገር ናት፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በሕጻንነቱ ወራት ከእናቱ ጋር ወደ ግብጽ ተሰዶ እንደነበረ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል፡፡ ግብጻውያን የክርስትና ሃይማኖትን በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ አማካኝነት በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን እንደተቀበሉ የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ የመጀመሪያው የግብጽ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክም ይኸው ቅዱስ ማርቆስ እንደሆነ የግብጻውያን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል፡፡ ዛሬ በሥጋ የተለዩንም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳም በቅዱስ ማርቆስ መንበር 117ኛው ፓትሪያርክ ነበሩ፡፡

Saturday, March 17, 2012

ሰበር ዜና፡- ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ አረፉ


              የግብፅ አርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑት  ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ በተወለዱ በ88 ዓመታቸው ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ.ም. አረፉ። ዜናው በሰበር ዜና በቢቢሲና በአልጃዚራ ሲነግር በርካቶችን ወደ ሀዘን ድባብ ጨምሮዋል። ቅዱስነታቸው በግብፅ ህዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ አባት ነበሩ። የእረፍታቸውም ዜና በሁላችንም ዘንድ ከፍተኛ ሀዘንን ፈጥሮዋል።


   ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ መስከረም 26 1916 ዓ.ም. ተወለዱ። በታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ1949ዓ.ም. ያገኙ ሲሆን በሰንበት ት/ቤት መምህርነትም አገልግለዋል። በ1942 ዓ.ም. ከመንፋሳዊ ኮሌጅ ተመርቀው በአዲስ ኪዳን መምህርነት አገልግለዋል።በ1946 ዓ.ም. የመነኮሱ ሲሆን በመስከረም 20 1953 ዓ.ም. ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ተብለው የጵጵስናናን ማዕረግ ተቀብለዋል። በህዳር 4 1964 ዓ.ም. ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ተብለው በመንበረ ማርቆስ ላይ 117ኛ ፓትርያርክ ሆነው ተሹመዋል። ላለፉት 40 ዓመታትም የተሠጣቸውን መንፈሳዊ አደራ በብቃት ተወጥተዋል።

    ብጹዕነታቸው ከ100 በላይ መጽሓፍትን የጻፉ ሲሆን በመልካም ስነ ምግባር በብቁ እረኝነት ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ተወጥተው አልፈዋል።

የሰማዩ አምላክ ነፍሳቸውን በእቅፉ ያስቀምጥልን

በዚህስ አትበለጡ

/ከጌድዮን/

ዘመኑ የውድድር ዘመን አይደል! የፉክክር የሩጫ፣ የትግል፣ የእሽቅድምድም፣ የንፅፅር፣ የእኔ እበልጥ የእኔ እበልጥ አይነት የጥርስ መሰበር፣ ዘመን ማንም ከማንም አንሶ ላለመገኘት እልክ አስጨራሽ ፍልሚያ የሚደረግበት መድረክ፡፡ የምድራችን መርህ አለመበለጥ ነው ከቶስ ትግሉ ውስጥ የሌላ ዳር ቆሞ የሚታዘብ ጉልበት እስኪርድ፣ ላብ እስኪፈስ ደም ስኪንጠባጠብና አጥንት እስኪሰበር የሰው ልጅ በምድሪቱ መድረክ ላይ ከሁሉ ልቆና ገዝፎ ለመታየት የሚያደርገውን የፍጻሜ ጦርነት እንደተራ ጉዳይ ቆጥሮ የራሱን ኑሮ ብቻ የሚያስታምም ይኖር ይሆን? ወንድሜ ዘመኑ አለመበለጥን ነው የሚሰብክህ፡፡ ከነተረቱስ አለመቀደም ነው አይደል የሚለው? ሌላው ቀርቶ ታላቁ መጽሐፍ ‹‹የአንዱ ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ክብር ይበልጣል›› ይል የለ፡፡ እዚያም ታላቅ የውድድር መድረክ መኖሩ መች ይቀራል፤ መልኩንና ጠባዩን ቢቀይር እንጂ!

ለመሆኑ እናንተ የማታወቁት የትግል የውድድርና የፍልሚያ መድረክ አይኖር ይሆን? እውነት እላችኋለሁ፡፡ በሔዳችሁበት በደረሳችሁበት አደባባይ ሁሉ አንገት ለአንገት የሚተናነቅ፣ ሞቼ እገኛታለሁ እንጂ! ካንተ አላንስም አይነት ፍልሚያ ይጠብቃችኋል፡፡ ዝግጁ ካልሆናችሁ ዛሬም ለሌላ ትግልና ትንቅንቅ ትሰናዱ ዘንድ ሹክ እላችኋለሁ፡፡ ለነገሩ እናንተም ሆነ እኔ የማናውቀው የትግልና የፉክክር መድረክ የቱ ይሆን? አርሴና ማንቼ፣ ኃይሌና ቴርጋት፣ ጥሩነሽና መሰረት፣ ማድሪድና ባርሴሎና፣ ቡናና ጊዮርጊስ ሞሪኖና ቬንገር፣ ታይሰንና ዳግላስ፣ አሜሪካና ቻይና፣ ጃፓንና ኮሪያ፣ እስደራኤልና አረብ፣ ሪፓብሊክና ዴሞክደራት፣ ኢህአዲግና ቅንጅት፣ በአሉ ግርማና ሀዲስ አለማየሁ፣ ፀጋዬ /መድህንና መንግሥቱ ለማ፣ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲና ቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ፣ ቀሲስ እገሌና ቀሲስ እገሌ፣ / እገሌና / እገሌ፣ ዘማሪት እገሊትና ዘማሪት እገሊት፣ እንትን ማኅበርና እንትን ማኅበር፣እንደሀገርም፣ እንደህዝብም፣ እንደማኅበረሰብም፣ እንደተቋምም እንደ ግለሰብም ትውልድ ፍጻሜና መቋጫ በታጣለት እልክ አስጨራሽ ፉክክር ውስጥ ወድቋል፡፡

Friday, March 16, 2012

ማህበረ ቅዱሳን በተሀድሶ ዘመቻ ስም ከሰበሰበው ገንዘብ የድርሻውን ያገኘው “ወልደ ዘርአ ያዕቆብ” ማን ያዘዋል ባለ መኪና ሆነ


ነጭ በነጭ ለብሶ አራት ኪሎን ሲያካልል የሚውለውና በጠቅላይ ቤተክህነትና በአዲሰ አበባ ሀገረ ስብከት ከቢሮ ቢሮ እየተዘዋወረ ወሬ በማቀባበል ስራ ፈቶ ስራ በማስፈታት የሚታወቀው አቶ ማንያዘዋል መኪና መግዛቱ ተሰማ፡፡ ከወዲያ ወዲህ ወሬ የሚያመላልሰው እንዲያው ጥሎበትና አመል ሆኖበት ብቻ ሳይሆን፣ ማህበረ ቅዱሳን የሰጠው ተልእኮም ስለሆነ ነው፡፡ በባለፈው ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የጳጳሳቱን ጉዳይ ማህበሩ በእርሱ ላይ ጥሎ እንደነበረና እርሱም ተልእኮውን በተገቢው መንገድ መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ ያቀረበውን በወረቀት የሰፈረ የስም ማጥፋት ክስ ለጳጳሳቱ ያደለውም ይኸው የማህበሩ ወሬ አቀባባይ ማን ያዘዋል ነው። በዚህ ጸባዩና ከቢሮ ቢሮ እየተዘዋወረ ከፎቅ ፎቅ እየወጣ እየወረደ ስራ በማስፈታቱና በሌላም ለጊዜው ባልተገለጸ ምክንያት ቤተክህነት ግቢ እንዳይደርስ እስከ መከልከል ደርሶ ነበር፡፡

ግለሰቡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልማት ኮሚሽን ሠራተኛ የነበረ ሲሆን፣ ከመዞርና ወሬ ከማመላለስ በቀር ሌላ ሞያ ስለሌለው ከስራ መባረሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ይሁን እንጂ ከቀድሞ ጀምሮ ተጨማሪ ደመወዝ ይሰጠው የነበረው ማህበሩ በአሁኑ ሰአትም ክፍያውን እንደቀጠለ ሲታወቅ፣ በአሁኑ ጊዜ እንደ ቢሮ መዋያው በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የነገረመለኮት ምሩቃን ቢሮ ውስጥ መሆኑ ታውቋል፡፡ 

Wednesday, March 14, 2012

ማህበረ ቅዱሳንና አንዳንድ ቅጥረኛ ጳጳሳቱ የሲኖዶስን ውሳኔዎች በስልት እየሸረሸሩ ይገኛሉ


ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካል ነው፡፡ እርሱ ለሚወስነው ውሳኔ ተገዢ መሆን ደግሞ የግድ ነው፡፡ ይህን ጥሶ መልካም በማድረግ ስም የሲኖዶስን ውሳኔ መጣስ ግን፣ አጋግን ከነነፍሱ ማርኮና ለሰቡት እንስሳት ሳስቶ እነርሱን ለመስዋእት በማቅረብ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት እንደሞከረው እንደ ሳኦል መሆን ነው፡፡ ሳሙኤል በእግዚአብሔር ቃል ምን አለው? “በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል። ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።” (1ሳሙ. 15፡22-23)፡፡ ዛሬም ማህበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን ይህንና ያን አደረኩ ቢል፣ ፖለቲካውን ለማሳካት እንጂ እግዚአብሔር የሚከብርበት ቤተክርስቲያንም የምትደሰትበት አይደለም፡፡

ማህበረ ቅዱሳንን ከጨዋታ ውጪ እያደረጉት የነበሩትን የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እንዳይሰብኩና እንዳያገለግሉ ማዕቀብ እንዲጣልባቸው ብዙ ገንዘብ አፍስሶ በድምፅ ብልጫ ያስወሰነውና ራሱንም ያገደውን ውሳኔ፣ በየአካባቢው በሚያስነሳው ሁከት ምክንያት የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ኮሚቴ በየጊዜው የሚወስናቸውን ውሳኔዎች ሁሉ እየጣሰና፣ በጥቅማ ጥቅምና በገንዘብ የታወሩ፣ እንዲሁም አደባባይ ላይ የተሰጣውን ነውራችሁን እሸፍንላችኋለሁ በሚል መደለያ የያዛቸው ጳጳሳቱም ሲኖዶስ ላይ የወሰኑትን ውሳኔያቸውን እንዲጥሱ እያደረገ ይገኛል፡፡ አቡነ ገብርኤል ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ሀዋሳ ላይ በቅርቡ ያዘጋጁት ጉባኤ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ መጋቢት 2/2004 ዓ.ም ወደ በኬ ያዘጋጀውና ‹‹ሀዊረ ህይወት›› የተሰኘ ጉዞና በበኬ ደብረ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ያዘጋጀው ጉባኤ፣ ከህገ ወጥና አጉራ ዘለል ከተባሉ ሰባክያን መካከል ብርሃን አድማስና ሌሎችም ህገወጦች የሰበኩበት ጉባኤ ‹‹ሰፈር በመለወጥ›› የሲኖዶስን ውሳኔ የሸረሸሩበት ጉባኤ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይህም በህጋዊ መንገድ ያጡትን በህገወጥ መንገድ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ ይህም የማን አለብኝነት እንቅስቃሴ ከግንቦቱ የሲኖዶስ ስብሰባ በፊት እንደተለመደው ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳትና አባቶችን በመከፋፈል ተጠቃሚ ለመሆን መቋመጣቸውን ያስረዳል፡፡

Tuesday, March 13, 2012

ነጭ ለባሹ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሠራዊት አቡነ ገብርአልን ለማስወገድ የመከረ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ


  • በሀዋሳ የተሰደዱት ምዕመናንና ምዕመናት ላይ አስቸኳይ ርምጃ ለመውሰድ ዝቷል

"ማኅበረ ቅዱሳን" የልዩ ልዩ የጥዋ ማኅበራት ሰብሳቢዎችን (ሙሴዎችን) እና የሀዋሳ ማዕከል ኃላፊዎችን ያካተተ ነጭ ለባሽ "ማኅበረ ቅዱሳን" ሠራዊት ባደረገው ድንገተኛ አስቸኳይ ስብሰባ፣ አቡነ ገብርአልን ለማስወገድ ሤራ መቋጨቱን ውስጥ ዐዋቂ ምንጮች ከወደ ሥፍራው መረጃ አድርሰውናል፡፡ ትላንት ከምሽቱ 1200 እስከ 300 ሰዓት  በሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የክርስትና ማጥመቂያ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደው ስብሰባ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ይትባረክ ታጠቅ ተገኝተዋል፡፡

መልአከ ብርሃን ይትባረክ ታጠቅ "ማኅበረ ቅዱሳን" አባልና "ማኅበሩ" ልሳን የሆነው የስምዓ ፅድቅ ጋዜጣ ተከፋይ ዐምደኛ መሆናቸው ሲታወቅ "ማኅበረ ቅዱሳን" በድርጅታዊ አሠራር አቡነ ገብርኤልን ካስመጣ በኋላ ለሥራ አስኪያጅነት አጭቶ ያሾማቸው ምርጥ "ማኅበረ ቅዱሳን" ተላላኪ ናቸው፡፡

በዚህ መሠረት ይትባረክ ታጠቅ በስብሰባው ላይ ተገኝተው ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸው ማጠቃለያም እርሳቸው የሚፈርሙትን አቡነ ገብርኤል እየሻሩባቸው፣ ቀጣሁ ያሉትን እየማሩባቸው፣ ሻርኩ ያሉትን እየሾሙባቸው፣ አባረርኩ ያሉትን እያመጡባቸው በየዕለቱ የሚፈርሙትን ውሳኔ ፍጹም በተቃራኒው መንገድ እየቀለበሱባቸው መቸገራቸውን ገልጸው፣ ትዕግሥታቸው ፈጽሞ ማለቁንና ሥራቸውን ለቀው አቡነ ገብርኤልን ከማያዩበት የትኛውም ቦታ ለመሄድ መወሰናቸውን እልህና እንባ በተናነቀው ስሜት አብራርተዋል፡፡