Wednesday, March 21, 2012

የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ ደጀ ሰላም ለምን ተቀዛቀዘ?


ማህበረ ቅዱሳን በስዉር የሚፈልገውን እያጻፈ ቤተክርስቲያናችንን ሲበጠብጥ የነበረው ደጀሰላም ድረገጽ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያስተዋል ነው። ለምን ተቀዛቀዘ? ለሚለው ግን ድረገጹ የሚያቀርባቸው ምክንያቶች ውሃ የሚያነሱ ሆነው አልተገኙም። ከምክንያቶቹ አንዱ ከስሜ የተወሰነ ፊደል እየገደፉና እየጨመሩ የተለያዩ ድረገጾች በስሜ ተከፍተዋል የሚል ነው። ይሁን እንጂ ድረገጹ በርካታ ተገዳዳሪና ወደረኛ የሆኑ ድረገጾች ተከፍተው አፉን ማዘጋት ስለቻሉ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ደጀሰላም ያለ ተቀናቃኝ ብቻውን ድረገጽን የተቆጣጠረበትና እውነትን ሀሰት፣ ሀሰትን እውነት እያለ የሚዘላብድበት፣ አላማውን የተቃወሙ ብጹዓን አባቶችን ስም ሲያጎድፍ የነበረበት፣ በብዙ መንፈሰዊ ችግሮች ውስጥ የተዘፈቁና እርሱን የደገፉትን ሁሉ ሰማይ ላይ የሰቀለበት ዘመን ስላበቃና አማራጭ ድረገጾች የእርሱን ድብቅ ገመና አደባባይ ላይ በማስጣት እውነትን መመስከር ስለጀመሩ ነው። በተጨማሪም የማህበረ ቅዱሳን ፖለቲካዊ አጀንዳ ስለ ተነቃበትና የመንግስትን ትኩረት ስለሳበ የፖለቲካዊ ስሜቱ ማስተንፈሻ የሆነው ደጀሰላም ለጊዜው ራሱን ደበቅ ለማድረግ በሚል ማህበሩ አዲስ በከፈታቸው በአንድ አድርገንና በገብርሄር ላይ ግልጽ ፖለቲካ የሚንጸባረቅባቸውን፣ መንግስትንና ህዝብን ለማጋጨት ጥረት የሚያደርጉ፣ ህዝቡን ከቤተክርስቲያን አባቶች ጋር ለማናከስ የሚቀሰቅሱ ዘገባዎችን በስፋት እያወጡ ይገኛሉ።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአሁኑ ሰዓት ድረገጹ ተቀዛቅዞ የሚገኘው ድረገጹን ከማህበረ ቅዱሳን በተመደበ በጀት በዋናነት ሲያንቀሳቅስ የነበረው ሱራኤል ወንድሙ አሜሪካ መግባቱን ተከትሎ ነው። ለደረገጹ የሚሆኑ ወሬዎችን በመቃረም ለማህበሩ በሚጠቅም ሁኔታ እያዛቡና እያዛነፉ የሚሰልቁት ቱሪስት ሆቴል፣ ምርፋቅ እና ሶመሰ ካፌና ሬስቶራንቶች የማይጠፋው የድራፍት ጠጪዎች ቡድን ነው። የዚህ ማፍያ ቡድን አባላት ሰብሳቢያቸው ሱራፌል ወንድሙ፣ ጳውሎስ /መረዋ/ መልክአ ስላሴ፣ በመሰሪነቱ የሚታወቀው ዳንኤል (ዴራ) ተስፋዬ ሞሲሳ፣ ሰለሞን (የአዲሱ ሚካኤል) ምክትል ሰባኬ ወንጌል፣ ወንድወሰን፣ እና ሌሎች ያሉበት ስብስብ ነው።

ይህ የጠጪዎች ቡድን፣ ከዚህ ቀደም የሰባኪዎች ህብረት በሚል ለመሰባሰብ ሞክሮ የነበረ ሲሆን፣ ፋንቱ ወልዴ ከአሜሪካ 40 ሺህ ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለቡድኑ መስጠቷ ታውቋል። ሲሰርቅ አንድ የሆነ ሲካፈል እንደሚጣላ ሁሉ፣ በመጣው ብር ዙሪያ ጠብና ክርክር ተነስቶ እንደነበረና በገንዘብ ፍቅር ተነድፎ የሚገኘው ጳውሎስ በቂ ገንዘብ አላገኘሁም በሚል ከቡድኑ መለየቱን ለአንዳንዶች እያስወራ ይገኛል። ይሁን እንጂ የክፋት ስራ ከቡድኑ ጋር ስለሚያገናኘው ተመልሶ አንድ የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ በቅርብ የሚያውቁት ይመሰክራሉ።

የድረገጹ ዋና ጦማሪ የነበረው የነገረ ሰሪው ጋዜጠኛ የሱራፌል ወንድሙ ወደአሜሪካ መግባት ለድረገጹ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል። ስለዚህ ደጀሰላም በወለዳቸው ሌሎቹ ድረገጾች ለጊዜውም ቢሆን ስሙን ቀይሮና በፖለቲካው ፍጹም ተጠምቆ ሽብር መንዛቱን ቀጥሏል። “ዋልድባ በመንግስት ተደፈረ ተነሱ”፣ “በጎንደር የአብነት ትምህርት ቤት ተቃጠለ ተነሱ”፣ “ዝቋላ እየተቃጠለ ነው ተነሱ” በማለት በግልጽ ፖለቲካዊ አጀንዳውን በሃይማኖት ሽፋን ለማስፈጸም እየተራወጠ ይገኛል። ይሁን እንጂ ሁሉንም ነገር ህዝቡ እየታዘበ ስለሆነ የማህበረ ቅዱሳን ፖለቲካዊ ቅስቀሳ የትም አይደርስም። ምናልባት ገመዱን ለማሳጠር ምክንያት እንዳይሆነው ነው የብዙዎች ስጋት። ከዚህ ሁሉ በተቃዋሚ ፖለቲከኛነት በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ቢንቀሳቀስ ለቤተክርስቲያኗ እረፍት፣ ለማህበሩም ነጻነት ይሆን ነበር።

18 comments:

  1. Tasafralachihu betam betam enante ahun kristian tibalalachihu? mahibere kidusanin yemitiweksu????? kemewgiaw biret gar bititagel bante yibisibihal yemilewin asibachihu yihe ye aganint weriachihun akumu!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. አረባክህ ማቅ ነዋ ክርስቲያን? እናንተ ስትወቅሱ ልክ ሌላው ሲወቅሳችሁ ስህተት የሚሆነው ለምንድን ነው? ይልቅ ቤቱ ባዶ ነው ብላችሁ በተክርስቲያንን መቦጥቦጥ አቁሙ

      Delete
  2. ሊበጠብጡ ኖሯል "ደጀ ሰላም" ብለው በር የከፈቱት? ታዲያ "ደጀ-ብጥብጥ" ቢሉት አይሻልም ኖሯል?

    እናንተሳ፦ እንዲህ ልትኰንኑ ኖሯል "ዐውደ ምሕረት" የሠየማችኹት? ታዲያ ለምን "ዐውደ ምኵናን" አትሉትም?

    ReplyDelete
    Replies
    1. በሬ ወለደ ወሬ ስለሚያወራ ነዋ ባልቤቶቸም እኮ ሳይነቃ አውራ ነው ያሉት እሱ ደግሞ ወሬ በየት አለፈ እያለ ለአድመኛነቱን፣ለጠቡ፣ለክርክሩ ማጋጋያ ወሬ ይፈበርካል ወንጌል መማርና ማወቅ ይሻለው ነበር ስርአት እንኩዋን የለውም ሲሳደብ ጎዳና ላይ የወጡት ልጆች እንኳን ጋሽዬ እትዬ ይላሉ እሱ አባቶችን አንኳን ሲሳደብ አያፍር ለአነጋገሩ ስርአት የለው ለኦርቶዶክስ ሐይማኖት የተቆረቆረ የማስመሰል ድብቅ ሴራው ተጋለጠ እራሱ ይህ ንግግር የሚገኘው በልምድ እንዳየነው ወይ ከመናፍቅ ጉባዬ አለያም ከጫትና ከተለያዩ ሱስ ቤቶች ነው አማኝ አይሳደብም አባቶችን ያከብራል ይሄ ግን ግብረግብነት የጎደለውና ስራአተ አልበኝነትን ለማበረታታት የተከፈተ ወረኛ ወረኛ ወረኛ ከዚያም ባላይ ነው፡፡
      እግዚያብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቧን የባርክ !!!!!!!!

      Delete
  3. it is because dejeselam has achieved its mission ( tehadiso menafkan has now defeated in every corner of the country). so, no more information!!!!!!

    ReplyDelete
  4. Kenat selhone endeh yemiadergachu ayferedebachehum menem betaworu mahbere kidusan serawen yeseran menfesawi kinat kentachehu endenesu bethonu yeshalacheual enante belo kerstian.

    ReplyDelete
  5. Ahun Gena gebagn Yeenante Ajenda, Leka bebetechristian sim yebeg lemd yelebesachu tekulawoch nachihu "Tehadiso", Minim sira satiseru bewere bicha yalachu nachu.... ahu gena gebagn!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. mk sineka lenante thadesonet new aydel? chefenoche. mk ena ablatu yehelemawe melektegoche nahu

      Delete
  6. new ende mk eko enawkewalen besega temesereto besega sera lesera yemil boletikega deregit new

    ReplyDelete
  7. bertulenma abo. endihe newe engi yeenersun mister meglet.

    ReplyDelete
  8. ድሮስ ደጀ ሰላም እኮ እየተበላ እየተጠጣ የወሬ ቦታ እንጂ ለሌላ ነገር ሲውል አይቸ አላውቅም

    ReplyDelete
  9. በሬ ወለደ ወሬ ስለሚያወራ ነዋ ባልቤቶቸም እኮ ሳይነቃ አውራ ነው ያሉት እሱ ደግሞ ወሬ በየት አለፈ እያለ ለአድመኛነቱን፣ለጠቡ፣ለክርክሩ ማጋጋያ ወሬ ይፈበርካል ወንጌል መማርና ማወቅ ይሻለው ነበር ስርአት እንኩዋን የለውም ሲሳደብ ጎዳና ላይ የወጡት ልጆች እንኳን ጋሽዬ እትዬ ይላሉ እሱ አባቶችን አንኳን ሲሳደብ አያፍር ለአነጋገሩ ስርአት የለው ለኦርቶዶክስ ሐይማኖት የተቆረቆረ የማስመሰል ድብቅ ሴራው ተጋለጠ እራሱ ይህ ንግግር የሚገኘው በልምድ እንዳየነው ወይ ከመናፍቅ ጉባዬ አለያም ከጫትና ከተለያዩ ሱስ ቤቶች ነው አማኝ አይሳደብም አባቶችን ያከብራል ይሄ ግን ግብረግብነት የጎደለውና ስራአተ አልበኝነትን ለማበረታታት የተከፈተ ወረኛ ወረኛ ወረኛ ከዚያም ባላይ ነው፡፡
    እግዚያብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቧን የባርክ !!!!!!!!

    ReplyDelete
  10. ሀይለሚካኤል ዘ5April 3, 2012 at 9:28 PM

    ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ለመፎካከር ብዙ ይቀራችኋል ይልቁንም መሃበሩን ደግፋችሁ ብትንቀሳቀሱ ይሻላችሁ ነበር፡፡ ለማንኛውም አምላክ ልብ ይስጣችሁ!!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ወይ በሳቅ መሞት ኪኪኪኪ ማህበሩ እኮ ሽብርተኛ ሆነ አይ የአምላክ ስራ ተመስገን !!!!!!

      Delete
  11. ወሬያችሁ ሁላ ብጣም ተራ ነው፡፡ዝም ብሎ አሉባልታ ነገር ነው ፡፡ምናለ ባትሆኑ እንኴን ከርስቲያንያዊ ለማስመሰል ብትሞክሩ፡፡ እናንተ ስለ ማህበረ ቅዱሳን ለማውራት ገና ብዙ ይቀራችኌል!!!!

    ReplyDelete