Saturday, March 17, 2012

ሰበር ዜና፡- ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ አረፉ


              የግብፅ አርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑት  ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ በተወለዱ በ88 ዓመታቸው ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ.ም. አረፉ። ዜናው በሰበር ዜና በቢቢሲና በአልጃዚራ ሲነግር በርካቶችን ወደ ሀዘን ድባብ ጨምሮዋል። ቅዱስነታቸው በግብፅ ህዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ አባት ነበሩ። የእረፍታቸውም ዜና በሁላችንም ዘንድ ከፍተኛ ሀዘንን ፈጥሮዋል።


   ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ መስከረም 26 1916 ዓ.ም. ተወለዱ። በታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ1949ዓ.ም. ያገኙ ሲሆን በሰንበት ት/ቤት መምህርነትም አገልግለዋል። በ1942 ዓ.ም. ከመንፋሳዊ ኮሌጅ ተመርቀው በአዲስ ኪዳን መምህርነት አገልግለዋል።በ1946 ዓ.ም. የመነኮሱ ሲሆን በመስከረም 20 1953 ዓ.ም. ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ተብለው የጵጵስናናን ማዕረግ ተቀብለዋል። በህዳር 4 1964 ዓ.ም. ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ተብለው በመንበረ ማርቆስ ላይ 117ኛ ፓትርያርክ ሆነው ተሹመዋል። ላለፉት 40 ዓመታትም የተሠጣቸውን መንፈሳዊ አደራ በብቃት ተወጥተዋል።

    ብጹዕነታቸው ከ100 በላይ መጽሓፍትን የጻፉ ሲሆን በመልካም ስነ ምግባር በብቁ እረኝነት ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ተወጥተው አልፈዋል።

የሰማዩ አምላክ ነፍሳቸውን በእቅፉ ያስቀምጥልን

1 comment:

  1. Amen!! ታላቅ የቤ/ክ አባት ተለዩን ነፍሳቸውን ከቅዱሳን አበው ጋር ይደምርልን

    ReplyDelete