Wednesday, March 14, 2012

ማህበረ ቅዱሳንና አንዳንድ ቅጥረኛ ጳጳሳቱ የሲኖዶስን ውሳኔዎች በስልት እየሸረሸሩ ይገኛሉ


ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካል ነው፡፡ እርሱ ለሚወስነው ውሳኔ ተገዢ መሆን ደግሞ የግድ ነው፡፡ ይህን ጥሶ መልካም በማድረግ ስም የሲኖዶስን ውሳኔ መጣስ ግን፣ አጋግን ከነነፍሱ ማርኮና ለሰቡት እንስሳት ሳስቶ እነርሱን ለመስዋእት በማቅረብ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት እንደሞከረው እንደ ሳኦል መሆን ነው፡፡ ሳሙኤል በእግዚአብሔር ቃል ምን አለው? “በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል። ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።” (1ሳሙ. 15፡22-23)፡፡ ዛሬም ማህበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን ይህንና ያን አደረኩ ቢል፣ ፖለቲካውን ለማሳካት እንጂ እግዚአብሔር የሚከብርበት ቤተክርስቲያንም የምትደሰትበት አይደለም፡፡

ማህበረ ቅዱሳንን ከጨዋታ ውጪ እያደረጉት የነበሩትን የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እንዳይሰብኩና እንዳያገለግሉ ማዕቀብ እንዲጣልባቸው ብዙ ገንዘብ አፍስሶ በድምፅ ብልጫ ያስወሰነውና ራሱንም ያገደውን ውሳኔ፣ በየአካባቢው በሚያስነሳው ሁከት ምክንያት የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ኮሚቴ በየጊዜው የሚወስናቸውን ውሳኔዎች ሁሉ እየጣሰና፣ በጥቅማ ጥቅምና በገንዘብ የታወሩ፣ እንዲሁም አደባባይ ላይ የተሰጣውን ነውራችሁን እሸፍንላችኋለሁ በሚል መደለያ የያዛቸው ጳጳሳቱም ሲኖዶስ ላይ የወሰኑትን ውሳኔያቸውን እንዲጥሱ እያደረገ ይገኛል፡፡ አቡነ ገብርኤል ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ሀዋሳ ላይ በቅርቡ ያዘጋጁት ጉባኤ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ መጋቢት 2/2004 ዓ.ም ወደ በኬ ያዘጋጀውና ‹‹ሀዊረ ህይወት›› የተሰኘ ጉዞና በበኬ ደብረ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ያዘጋጀው ጉባኤ፣ ከህገ ወጥና አጉራ ዘለል ከተባሉ ሰባክያን መካከል ብርሃን አድማስና ሌሎችም ህገወጦች የሰበኩበት ጉባኤ ‹‹ሰፈር በመለወጥ›› የሲኖዶስን ውሳኔ የሸረሸሩበት ጉባኤ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይህም በህጋዊ መንገድ ያጡትን በህገወጥ መንገድ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ ይህም የማን አለብኝነት እንቅስቃሴ ከግንቦቱ የሲኖዶስ ስብሰባ በፊት እንደተለመደው ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳትና አባቶችን በመከፋፈል ተጠቃሚ ለመሆን መቋመጣቸውን ያስረዳል፡፡

እነርሱን በመቃወም የታወቁት፣ ተሀድሶ እየተባለሉ ሲብጠለጠለሉ የነበረውና በፖለቲካው ቋንቋ ግለሂስ አድርገው ወደእነርሱው የተመለሱት መጋቤ ሀዲስ እሸቱም በጉባኤው ላይ የማህበሩ ሰው መሆናቸውን አስመስክረዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በማህበረ ቅዱሳን ክስ የተመሰረተባቸው የቤተክርስቲያን ልጆችና የራሱ የማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ እንዲታይና ለግንቦቱ ስብሰባ እንዲቀርብ ወስኖ እያለና በተገቢውና በተለመደው የቤተክርስቲያን አሰራር ውግዘት ሳይተላለፍ ማህበሩ በጥቅም በተጋጫቸው አገልጋዮች ላይ የለጠፈውን ተሀድሶ መናፍቃን የሚለው ስድብ እንዲቆም በቅዱስ ፓትርያርኩ መመሪያ ተሰጥቶ እያለ፣ እነዚህን ውሳኔዎችና መመሪያዎች በመጣስ፣ የሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ቀውስጦስ ተሀድሶ በሚል ሲደነፉ መዋላቸው ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ እነዚህ አባቶች በዱርዬዎችና በነፍሰገዳዮች የሚመሩትና የሚስቱት እስከመቼ ይሆን? ከዚህ ቀደም አቡነ ፊልጶስ በማህበሩ ሰዎች ምልጃ የዘመድኩንንና የደስታን ወንጀል ለመሸፈን ሞክረው የማያዋጣ ሲሆን ከመዋረድ ለጥቂት ተርፈው ክሱ ቀጥሎ ዘመድኩንን ወኅኒ አወረደው፡፡

የማህበረ ቅዱሳን ድረገጽ አንድ አድርገን እንደዘገበው አቡኑ በጉባኤው ላይ ሞቅታ ተሰምቷቸው ‹‹በጣም ደስ ብሎኛል ይህን በማየቴ ፤ ይህን ያህል ምዕመን የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ እንዲህ ተሰብስቦ ማየት ደስ ያሰኛል ፤ እናንተ ከውስጥ ጠላት ጋር በብርታት እየተዋጋችሁ ይህን ማዘጋጀታችሁ ያስመሰግናችኋል ፤ ምግባችንን በልተው እኛው ቤት ተምረው ከተነሱብን ጠላቶች ጋር በመታገል ይህን ነገር ማድረጋችሁ ያስመሰግናችኋል ፤ የውጭ ጠላት ጋር መታገል ከባድ አይደለም ፤ ከወዳጅ ጠላት ያድናችሁ ፤ ይህች ቤተክርስያን በደሙ የዋጃት ስለሆነች ጠባቂዋ እሱ ነው ፤ እነዚህ የውስጥ ጠላቶች እንደ እግዚአብሔር ቸርነት ይከስማሉ እመኑኝ፤ እኔ ከዚህ በኋላ አልሰጋም ፤ ልጆች በአባቶች እግር ተተክተዋል ፤ አንዳንዴ ሳስበው ይህች ቤተክርስትያን የወደፊት እድሏ ምንድነው ብዬ እጨነቅ እጠበብ ነበር፤ አሁን ግን አልሰጋም፤ ተስፋዬም በእናንተ ስራ ለምልሟል ብለዋል››

እነዚህ ጳጳሳት አይሳካላቸውም እንጂ ቤተክርስቲያኗን ለፖለቲከኛው፣ ለነጋዴው፣ ለወንጀለኛው ማህበር ለማስረከብ የራሳቸውን ውሳኔ በራሳቸው እስከ መሻር መድረሳቸው ትልቅ ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል፡፡ ከልምድ እንደታየው ነገ ደግሞ በዚህ አቋማቸው መገኘታቸው አጠራጣሪ ነው፡፡ ማህበሩ ግን ለጊዜውም ለዜና ፍጆታ የሚውል ነገር አግኝቷል፡፡ የእርሱ ትርፍ ያ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማህበሩ በቅርቡ በብሄራዊ ሙዚየም አዳራሽ ባዘጋጀው ድብቅ ስብሰባ ላይ ጎላ ብለው ያልወጡ ሰባክያንንና ዘማሪዎችን ጠርቶ ለማወያየትና በእርሱ መንገድ እንዲጓዙ ለማድረግ ያግባባ ሲሆን፣ በአንዳንዶቹ በኩል ግን ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ዋናው ተቃውሞ ማህበሩ ለእርሱ ሰላም መስሎ በታየው ጊዜ የኮሌጅ ደቀመዛሙርትን በጭፍን ተሀድሶ መናፍቃን እያለ ሲገፋና ግንኙነቱን ሲሻክር ይቆይና በእርሱ ላይ ሁሉም ሲነሳበት ደግሞ ሰላማዊ መስሎ ለመቅረብና እርቅ ለመፍጠር ይሞክራል፡፡ ይህ ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ እንጂ መንፈሳዊ ህይወት አይደለም፡ ስለዚህ ማህበሩ ራሱን ሊያስተካክል ይገባል ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

ማህበሩ ራሱን ከውድቀት ለማዳን ሲል በየአዳራሹ መሰብሰቡ ቅዱስ ተግባር ነው፡፡ ሌሎች ህይወትን ለማዳን ሲሰበሰቡ ግን ተሀድሶነትና መናፍቅነት ነው፡፡ መቼ ይሆን ማህበረ ቅዱሳን ከዚህ ያረጀ አስተሳሰቡ የሚወጣው?

2 comments:

  1. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete
  2. እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን እሺ የተዘጉ አብያተ ቤ/ክን ሲያስከፍት፣ ለተጎዱ ሲረዳ፣ የአባቶቹን ትምህርት ጠንቅቆ ሲያውቅ፣ በአለም ሁሉ ፀጋው በዝቶለት ሲገንን፣ በስርዓት ሲሄድ፣ እንደ ማንም መናፍቅ ሳይልከሰከስ አረ ምኑ ቅጡ መልካም ሥራው ብዙ ነው ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ በማታውቁጥ እየቀባጠራችሁ የማህበሩን ስም ለማጥፋት አትነሱ እግዚአብሔር ይደግፈዋል ሕዝብም አውቆታል በፊት የሚቃወሙት እንኳን ከማህበሩ ወዲያ እምነት፣መልካምነት ለአሳር ብለዋል እንግዲህ ምን ትሆኑ!!!!ተሐድሶዎች ተው::
    ድሮም የበጎ ነገር ተቃራኒ አለው እሱም ሰይጣን ነው:: ሰይጣንም ስራውን የሚያከናውነው በማደሪያወቹ ነው:: ማደሪያወቹም እናንተ ናችሁ:: ማህበረ ቅዱሳን ቤ/ክርስቲያን እውቅና የሰጠችው በህጓና በስርዓቷ የሚጓዝ ታማኝ አገልጋይና የቁርጥ ቀን ልጀ ነው:: ቤ/ክርሰቲያን ስተፈርስ፣ ገዳማትና አድባራት ሲበተኑ፣ የአብነት ት/ርት ቤት ሲዳከምና ሲጠፋ ማየት የሚፈልጉ ፀረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አንጃዎች መሆናችሁ በጽሁፋችሁ ይታወቃል::

    ReplyDelete