Wednesday, February 19, 2014

ቋሚ ሲኖዶሱ መጋቢ ሐዲስ በጋሻው አገልግሎቱን እንዲቀጥል ፈቀደ


በማህበረ ቅዱሳን ውል አልባ ክስ አገልግሎቱን አቋርጦ የነበረው መጋቤ ሐዲስ በጋሻው አገልግሎቱን እንዲቀጥል ተፈቀደ። ማኅበረ ቅዱሳን በአንካሳ ልቡ እያነከሰ ወንድሞችን ከቤተክርስቲያን ጠራርጎ የማስወጣት ዘመቻው አካል የሆነው የበጋሻው ክስ አቅሙ የሰለለ እና የምንፍቅናን ምንነት ያላገነዘበ መሆኑ ታውቆ አገልግሎቱ እንዲቀጥል መደረጉ ለእውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ትልቅ ድል ነው።
አሁንም ማኅበሩ ይህን እፍረቱን ተመለክቶ ወንድሞችን ማሰደዱን መክሰሱን ትቶ በእውነት ለቤተክርስቲያን የሚጠቅማትን ነገር ብቻ ላይ ቢያተኩር ይገባዋል እንላለን።
አሊያ የእውነተኛው ከሳሽ እና የሀሰት አባት የሆነው የዲያቢሎስ ደቀ መዝሙር እንደሆነ ይቀጥላል።

Thursday, January 23, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን በአዲሱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መዋቅራዊ ለውጥ ምክንያት እየደረሰበት ያለው ተቋሞ ተጋግሎ ቀጥሏል፡፡

REadin PDF:

በየሆቴሉ በድብቅ ይሰበሰባሉ ሲባሉ የቆዩት የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አለቆች በገሀድ በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ተሰብስበው ፓትርያርኩንና አንዳንድ የማኅበሩን ደጋፊ ሊቃነ ጳጳሳት አስጠነቀቁ፡፡ ጥያቄዎቻችን ምላሽ የማያገኙ ከሆነ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር በጥቁር ራስ (መነኮሳት ባልሆኑ) ሰዎች እንዲካሄድ በሕጋዊ መልኩ እንደሚጠይቁ አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ሰራተኞች ቤተክርስቲያኒቱ የአሰራር ለውጥ እንደሚያስፈልጋት አምነው ለውጡ ሁለንተናዊና መላውን የቤተክህነቱ ክፍል ሊያቅፍ እንደሚገባ ሕጉም ከዋናው ከሕገ ቤተክርስቲያን መጀመር እንዳለበትና በየደረጃው ደንቦችና መመሪያዎች ሊወጡ እንደሚገባው አስረድተው ይህንን የሚሰራው አካልም ከቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከሊቃውንት ጉባዔ፣ በየደረጃው ከሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ሰራተኞች ፣ ከገለልተኛ ባለሙያዎች ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተወጣጣ ኮሚቴ መሰራት እንደሚገባው አስምረውበታል፡፡
ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጥያቄያችሁ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ትኩረት ይፈልጋል  በማለት ኮሚቴ እንዲቋቋም ፈቅደዋል በቤተክህነቱ አዳራሽ መሰብሰብ እንደሚችሉ አረጋግጠውላቸዋል፡፡
ስብሰባው ያበሳጫቸው አቡነ እስጢፋኖስ ግለቱ ከብዷቸው ወደ አሜሪካ እንደሚሄዱ ተናግረዋል፡፡

Friday, January 17, 2014

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በህዳር 12 ከተሰበሰበ ገንዘብ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ተመዘበረ፡፡

በደብረምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የደብሩ አስተዳዳሪ የዓመት ፍቃድ በመሆናቸው በቆጠራው ላይ ስላልተገኙ ይህንንም እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠርና የሰበካ ጉባዔ ምክትል ሊቀ መንበር ስልክ ተደውሎላቸው ቆጠራውን አቋርጠው በመውጣታቸው የደብሩ ዋና ጸሐፊ መ/ስ አብርሃም አቧይ  የወረዳው ስራ አስኪያጅ የአባ አእምሮ የቅርብ ዘመድ ከወረዳ የተወከሉት ወ/ሮ አባይ እና የሀገረ ስብከቱ ጸሐፊ ወ/ሮ አዲስ ዓለም እንዲሁም በአዲስ አበባ ሙስናና ዘረፋን በማበረታታት እነ የካ ሚካኤልን እንዳያገግሙ አድርጎ በዘረፋ ባዶ ያስቀራቸው በአዲስ አበባ ከተማ ለተለያዩ የውጪ ሀገር ኗሪዎች 7 ፎቅ ቤቶችን በተለያዩ አካባቢዎች  ሰርቶ የሚያከራየው ቀድሞ አለቃ የአደራው ንጉሤ ሴት ልጅ  ወ/ት እጸገነት አደራው በገንዘብ ያዥነት እንዲሁም በካቴድራሉ መልካም ሰው በመምሰል ለሁሉ ወዳጅ የሆነው አቶ ፋንታሁን ምረቴ እና ሊቀ ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ በጋራ ዘረፋውን ማከናወናቸው ታውቋል፡፡

Friday, October 18, 2013

ይድረስ ለአቶ ተመስገን ደሳለኝ፡ ፋክት ወይስ ፕሮፖጋንዳ?

በቅድምያ “ቀጣዩ የኢሕአዴግ ዒላማ ማኅበረ ቅዱሳን ይኾን?” [ፋክት መጽሔት፤ ቁጥር 14 መስከረም 2006 ዓ.ም] ሲሉ ባልዋሉበት አልያም በሽፍጥነት የሐሰት ምስክርነታቸውን ለሰጡ/ለጻፉ ግለሰብ ራሴን ላስተዋውቅ። ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል እባላለሁ። ከልጅነት እስከ እውቀት ያደግኩት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ነው። ራሱን “ማኅበረ ቅዱሳን” እያለ የሚጠራ መንፈሳዊ መልክ ያለው መሰሪ – ጸረ ሀገር፣ ጸረ ትውልድና ጸረ ቤተ ክርስቲያን ቡድን ተገንዞ ከተቀበረበት መቃብር ቀስቅሰው ሊነግሩን እንደቃጣዎት ዓይነት ሳይሆን “ማህበረ ቅዱሳን” ማለት ሰይጣን ራሱ በቁሙ የሚመለክበት፣ የሚዘከርበትና የሚታሰብበት የሲዖል ተረፈ ምርት ለመሆኑ በህይወቴ የማውቀው ሰው ነኝ። ሕገ መንግሥታዊ የመማር መብቴ ተጥሶ ለዓመታት ከለፋሁበት የትምህርት ገበታዬ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ያለ ስሜ ስም ተለጥፎብኝ እንድባረር የተደረግኩ፣ ከአንድም ሁለቴ በአንድ የክስ መዝገብ ለከፍተኛ እንግልትና ለእስር የተዳረግኩ፣ በሞትና በህይወት መካከል የተገረፍኩና በመጨረሻም አገሬን ለቅቄ በስደት ምድር በኬንያ ለሁለት ዓመት ከአምስት ወር ያለ ምንም የህይወት ዋስትንና እርዳታ የተንገላታሁ የሰው ሚስት ሳማግጥ ተገኝቼ ይመስሎታል? ከነተረቱ “ያልተነካ ግልግል ያውቃል” ነው የሚባለው። ለመሆኑ እርስዎ ስለ “ማኅበረ ቅዱሳን” ያልሆነውን ነው! በማለት ይህን ያህል ለማለት የደፈሩ እንደ አንድ የማኅበሩ አባል በጋዜጠኝነት ስም የአባልነት ግዴታዎ መወጣትዎ ነው ወይስ ነኝ እንደሚሉት “በጋዜጠኝነትዎ” ነው? ቁምነገሩ ያለው ወዲህ ነው። “ቀጣዩ የኢሕአዴግ ዒላማ ማኅበረ ቅዱሳን ይኾን?” ሲሉ በጻፉት ጽሑፍ በጋዜጠኝነትዎ እንዳልነቅፎት፥ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ሰርተው ያለ ተጠያቂነት ለመኖር ይሻሉ? 
እንግዲያውስ በጋዜጠኝነት የሥራ መስክ ይሰማሩ።

Thursday, October 17, 2013

ማኅበረ ቅዱሳን በአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በደረሰበት ተቃውሞ ተወካዮቹ ስብሰባ ረግጠው ወጡ

ምንጭ- አባ ሰላማ
32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ከየሀገረ ስብከቱ የተወከሉ የአህጉረ ስብከቶች ሥራ አስኪያጆች፣ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎችም በተገኙበት ጥቅምት 3/2006 ዓ.ም ተጀምሯል፡፡ በስብሰባው ላይ ከየአህጉረ ስብከቶች በመጡ ሥራ አስኪያጆች የሥራ ሪፖርት እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን ውይይትም እየተደረገ ነው፡፡

 በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የካህናት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ሊቀ ካህናት ኃይለ ስላሴ ዘማርያም ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን ምን ያህል አስጊ ኃይል እንደ ሆነና ከተለያዩ የንግድ ተቋማቱ የሚሰበስበውንና በቤተክርስቲያን ስም ከአገር ውስጥና ከውጭ የሚሰበስበውን ገንዘብም ኦዲት እንደማይደረግ የገለጹ ሲሆን፣ በዚህም ማቅ ኪራይ ሰብሳቢ ድርጅት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 በትናንትናው ዕለት ደግሞ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ – ወሊሶ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መልአከ ገነት አባ አፈወርቅ ዮሐንስ በሀገረ ስብከታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በዓመቱ ከገጠሟት ችግሮች መካከል ዋና አድርገው የጠቀሱት ማኅበረ ቅዱሳንን ሲሆን፣ ማኅበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ ቤተ ክርስቲያኗ የራሷ መተዳደሪያ ቃለ አዋዲ እያላት ቃለ ዐዋዲውን አሻሽሎ ሌላ መተዳደሪያ በማውጣትና የቤተክርስቲያንን መዋቅር በማዳከምሕዝበ ክርስቲያኑ ፐርሰንት እንዳይከፍሉና ሕዝቡ ለማኅበሩ በአባልነት ተመዝግቦ ለማኅበሩ እንዲከፍል በመቀስቀስ በቤተ ክርስቲያን ላይ ደባ መፈጸሙን ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም የሀገረ ስብከቱ የሆነውን ሱቅ እንደማንኛውም ምእመን ተከራይተው ኪራይ አንከፍልም በማለት ማመጻቸውንና ሕዝብን ማነሳሳታቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ማኅበሩ እንደ ትልቅ ስልት የያዘው የሕዝብ ተመራጭ በመምሰል በሰበካ ጉባኤ፣ በሰንበት ትምህርት ቤቶች በልማትኮሚቴና በስብከተወንጌል ኮሚቴነት በመግባት የበላይ መመሪያን አለመቀበልንና መዋቅር ማዳከምን ነው ብለዋል፡፡ ለማሳያነትም በወንጪ፣ በወሊሶ፣ በሰበታ አዋስ ወረዳ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሕዝብን የመከፋፈልና የማሳመፅ ድርጊት በመፈጸም ላይ መሆናቸውን በማስረጃ አስደግፈው አጋልጠዋል፡፡ ከዚህም ሌላ በ11ዱ ወረዳዎች ኔትዎርክ በመዘርጋት የራሳቸውን ሥራ በመተው በሀገረ ስብከቱ ላይ ሰዎችን በማደራጀት ላይ እንደሚገኙ በማስረዳት ቅዱስ ሲኖዶስ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

Thursday, September 26, 2013

ከሰማይ ወረደ በተባለው መስቀል ላይ ሳይንሳዊ ምርመራ ማድረግ ክልክል ነው ተባለ

ነገሩ “በሃይማኖት ጉዳይ ሳይንስ ጣልቃ አይገባም” የሚል ቃና ያለው ይመስላል

ከሰሞኑ ከሰማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል ከዘገቡት የፕሬስ ውጤቶች መካከል አንዱ የሆነው አዲስ አድማስ ጋዜጣ በመስከረም 11/2006 ዓ.ም. እትሙ ላይ “ከሰማይ ወረደ ለተባለው መስቀል የሳይንስ ምርመራ አይፈቀድም ተባለ” የሚል ርእስ ይዞ በድጋሚ ወጣ፡፡ ጋዜጣው እንደ ዘገበው መስቀሉ ከሰማይ ወርዷል ለሚለው የብዙዎች ጥርጣሬ ማረጋገጫ መስጠት እንዲቻል “ወረደ” በተባለው መስቀል ሳይ ሳይንሳዊ ምርመራ ይደረግ ዘንድ ስለመጠየቁ ሐሳብ ቀርቦ እንደሆን የተጠይቁት፣ መልስ የሠጡትና የዚህ “ተአምር ብቸኛ የዓይን ምስክር የሆኑት” መጋቤ ሐዲስ ፍስሃ እስካሁን “ከሰማይ የወረደውን መስቀል” አድናቂዎች እንጂ ምርምር እናካሂድ የሚል ጥያቄ ያቀረቡ ምሁራን አለመኖራቸውን ጠቅሰው ጥያቄውን የሚያቀርቡ ቢኖሩ ግን “የማይሞከር ነው” ሲሉ ተከላክለዋል፡፡


ይህ “ተአምር” ለሳይንሳዊ ምርምር ክፍት እንዳይሆን መከልከሉ ሰዎች በጉዳዩ ላይ ከፊት ይልቅ እንዲጠራጠሩ ሰፊ በር የሚከፍት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ይሁን እንጂ “ያደረገችውን ታስታውቅ ከወደ ደረቷ ትታጠቅ” እንዲሉ መጋቤ ሐዲስ ፍስሀ ያደረጉትንና የሆነውን ስለሚያውቁ “የማይሞከር ነው” በሚል “በሃይማኖት ጉዳይ ሳይንስ ጣልቃ አይገባም” አይነት መከራከሪያ አቅርበው ለምርምር በሩ ዝግ መሆኑን ፈርጠም ብለው ተናግረዋል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ “ወረደ” የተባለውን መስቀል ሳይንስ ቢያረጋግጠው ከሰማይ የወረደ እስከሆነ ድረስ ምንም የሚያስፈራ ነገር አይኖርም ነበር፡፡ ነገር ግን አስቀድመን በእርግጠኛነት እንደተናገርነው መስቀሉ ከምድር የተገኘ ስለሆነ “ከቶም አይሞከርም” ብለው “የነገርኳችሁን ማመን እንጂ መመርመር አትችሉም” የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ይህ ግን ትክክል አይደለም፡፡

Monday, August 5, 2013

በእጅ አዙር የቤተክርስቲያኒቱን መዋቅር መቆጣጠር የሚፈልገዉ የጸሐፍት ፈሪሳዊያን ጥርቅሙ ማህበረ ቅዱሳን በአሰበ ተፈሪ ድብቅ ሴራዉ ተጋለጠ

Read In PDF: Asebeteferi
 ከመሪጌታ የሻውወርቅ
ሐራ ዘተዋህዶ በተባለዉ የማህበረ ቅዱሳን መርዝ መርጫ ድረ ገጽ ላይ በምእራብ ሐረርጌ በአሰበ ተፈሪ ቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ዉስጥ ከእሁድ ሰንበት ቅዳሴ በኋላ ምእመኑና ማህበረ ካህናቱ የሰበካ ጉባኤ አባላት ምርጫን ለማከናወን በሐገረ ስብከቱ ተይዞ የነበረዉን ፕሮግራም ሰንበት ት/ቤት አባላት ነን ከሚሉ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ የማህበረ ቅዱሳን አመራሮችና በጣት በሚቆጠሩ ግለሰቦች የተፈጠረዉን ከኦርቶዶክሳዊ አማኝ ስነምግባር ዉጪ የሆነዉን ሁከት እንደለመደዉ ማህበሩ በአንድ የማህበረ ናታኒም የተሰራ ተንኮል እንደሆነና ከዚሁም ጋር የሐገረ ስብከቱን ስራ አስኪያጅና ጸሀፊ ለመወንጀል የታሰበበት ጽሁፍ አስነበበን፡፡

ያሳዝናል እድሜ ልኩን እንደ ግብር አባቶቹ ጸሐፍት ፈሪሳዊያን/ቤተ አይሁድ/ ለጥፋት የተቋቋመ ማህበር፡፡ መቼ ይሁን እዉነቱን እዉነት ሐሰቱን ሐሰት የሚለዉ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሐፍት ፈሪሳዊያን ተይዞ ሊቀ ካህን ሐና ጋር በቀረበበት ግዜ አንድ ክስተት ተከሰተ ይሄዉም ሊቀ ካህኑ ሐና ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀዉ፡፡ አምላካዊ መልሱ በግልጥ ለአለም ተናገርኩ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት  በቤተ መቅደስና በምኩራቦች በግልጽ አስተማርኩኝ በስዉርም ምንም አልተናገርኩም፡፡ ስለምን ትጠይቀኛለህ; የሰሙትን ጠይቅ እነርሱ እኔ የተናገርኩትን ያዉቃሉ አለዉ፡፡ በዚህ ግዜ ግን አንድ አሳዛኝ ክስተት ተከሰተ የሊቀ ካህኑ ሎሌ የነበረ አገልጋይ ኢየሱስ ክርስቶስን ለምን እንዲህ አይነቱን መልስ ለሊቀ ካህኑ ትመልሳለህ ብሎ ጌታን በጥፊ መታዉ፡፡ እጅግ የሚገርመዉ አምላካዊ መልሱ ነዉ፡፡ ኢየሱስም መልሶ #ክፉ ተናግሬ እንደሆንሁ ስለ ክፉ መስክር መልካም ተናግሬ ከሆነ ግን ስለምን ትመታኛለህ አለዉ፡፡$ የዮሀንስ መንጌል ምእራፍ 18፤19-23  ይህንን ጥቅስ የወሰድኩበት አንድ ምክንያት አለኝ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን እንደ ምሰሶ ደግፎ ይዞ እንደቆመ ራሱን ይቆጥራል' እርሱ እንጂ ሌላ መንፈሳዊ ማህበር ለቤተክርስቲያኒቱ እንደማያስፈልግ ያዉጃል፡፡ 

Thursday, May 9, 2013

አድብቶ ነዳፊው ዳንኤል ክብረት የአውስትራሊያ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለመሆን እየሞከረ ነው


(http://awdemihreet.blogspot.com/)ባለሁለት ሚስቱ እና ፈቱ ዳንኤል ክብረት ያፈረሰ ሰው የሚገባውን ማርገጃ አድማቂነት እምቢኝ ብሎ ባልተማረው ትምህርትና በማይመልሰው ተሰጥኦ “ዲያቆን” ተብሎ ለእርሱ ብጤ ጨዋ ማኅበርተኞቹ “ሊቅ” ሆኖ እና “ሊቅ” ተሰኝቶ ከእውነተኛ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትና አባቶች ሸሽቶ እንደ እርሱ በሁለት ሀሳብ በገንዘብ እና በዝሙት ከሚያነክሱ አባ አብርሃም እና አባ ኤዎስጣጢዎስን ከመሰሉ ግለሰቦች ተጠግቶ በአድርባይ ብዕሩ እነዚህን የጉድ ሙዳዮች እየሸላለመ የነበረበት ሁኔታ አልበቃ ብሎት አሁን ደግሞ የአውስትራሊያ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ለመሆን ደፋ ቀና እያለ ነው፡፡
ማህበርዋን በዋና ጸሐፊነት በመራባቸው ረጅም አመታት ከየዋኃን አባላት ከሚሰበሰበው ገንዘብ እና ከቤተክርስቲያን የድርሻውን ወስዶ በሲኤምሲ ሁለት ቤቶችን የሰራው እና እና ከጊፍት ሪል እስቴት አንድ ቤት በመግዛት የሦስት ቤቶች ባለቤት የሆነው ዳንኤል ክብረት አሁን ደግሞ ሌላ ሦስት ቤት የሚሰራበትን ገንዘብ ከቤተክርስቲያን ለመዝረፍ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህንን ለማሳካት በሲአይኤ ወኪልነት በሚታወቀው እና እንደ እባብ ልስልስ ገላውን እያሳየ የተንኮል ድሩን በሚያደራው እና በቅርቡ የማኅበሩን አንጃ በሀሳብ የተቀላቀለው  በአቶ ባያብል አማላጅነት ጉዳዩ መስመር የያዘለት የመሰለው ዳንኤል ለቅርብ ወዳጆቹ የአውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የመሆኑ ጉዳይ ያለቀለት መሆኑን ሲናገር ተሰምቷል፡፡ በዚህም ተቋርጦ የነበረው የዳንኤል እና የባያብል ፍቅር የታደሰ መስሏል፡፡