Monday, October 22, 2012

የሲኖዶሱ የዛሬ ቀን ውሎ

Read in PDf:Day 0ne
  • 21 አጀንዳዎችን መርጧል በ5 ተወያየቶ ጨርሷል
ሲኖዶሱ በዛሬው ዕለት ስብሰባውን የጀመረ ሲሆን  በዛሬው እለት ስብሰባውን በአጀንዳ ቀረፃ እና በተቀረጹት አጀንዳዎች ላይ በመወያያት አሳልፎዋል፡፡
በስብሰባው ላይ ከተነሱት አጀንዳዎች መካከል
·        የቤተክርስቲያኒን ህግጋት ማሻሻል
·        የፓትርያርክ ምርጫን ኅግ ማውጣት
·        ለአቃቤ መንበሩ ህግ ማውጣት
·        የቁልቢ ገብርኤል ጉዳይ
·        የእርቁ ጉዳይ
·        የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይ
·        የቤቶች አስተዳደር
·        የወደፊት እቅድ


·        የሽልማት አሰጣጥን በተመለከተ
·        የቤተክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረት አጠባበቅ
·        ገዳማት አስተዳደርንና መምሪያውን በተመለከተ
·        አብነት ት/ቤቶችን በተመለከተ
·        ልማት ኮሚሽንን እና ህጻናት አስተዳደርን በተመለከተ
·        ዝውውር የጠየቁ ሊቀ ጳጳሳት ካሉ
·        የጠቅላይ ቤተክህነት አሰርርን በተመለከተ
ዋና ዋናዎቹ አጀንዳዎች ናቸው፡፡
ከነኚህ ውስጥ 5ቱን ተነጋግረው የጨረሱ ሲሆን ሌሎቹ በይደር ተላልፈዋል፡፡
የቤተክርስቲያኒቱ ሕገ ደንብ ይሻሻል የሚለው አጀንዳ ባለፈው ግንቦት ተነስቶ በማኅበረ ቅዱሳን አዝማችነት በፍጹም አይሆንም በሚል ከፍተኛ ሙግት አስነሰቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ማኅበሩ ለራሱ በሚመች መንገድ ለማስተካከል አጀንዳው እንዲያዝ አስደርጓል፡፡
የአቃቤ መንበሩ ህግም ቢሆን ያስፈለገው አቡነ ናትናኤል እንደተፈለገው ለማኅበሩ እና ለቡድን ስምንት አልታዘዝ በማለታቸው እሳቸውን በህግ አስሮ ከዚህች ማለፍ አይችሉም ብሎ  ለማስቀመጥ ነው፡፡
በትናንትናው እለት እንኳ በቀድሞው የጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ አበባው ይግዛው ቀብር ላይ አቡነ ገብርኤልን  እና አቡነ ኤልሳዕን መገሰጻቸው ብዙም አልተወደዳለቸውም፡፡ እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ ጉባኤ ወቅትም ከዚህ በፊት ለሲኖዶስ ስብሰባ ገንዘብ ሲጠየቁ እንቢኝ አሻፈረኝ ይሉ የነበሩት እና አሁን ቀደው የማይጨርሱትን ገንዘብ አንድ ሚሊየን ብር ለስብሰባው የፈቀዱትን አቡነ ሳሙኤል በሀገረ ስብከቱ ስብሰባ ወቅት እንደ ደቦል አንበሳ ወዲያ እና ወዲህ ሲሉ በአቃቤ መንበሩ በመገሳጻቸው የሚታሩበትን ህግ ለማውጣት እንደ ተጨማሪ ግብአት ሆኗል፡፡
ማኅበሩ ከስብሰባው በፊት ባሉ ቀናቶች ህግ በማውጣት ስራ ተጠምዶ የነበረ መሆኑ ሲታወቅ ማቅ ያዘጋጀው ህግ አለምንም ማሻሻያ አንዲጸድቅ ህልመያርኩ ማንያዘዋል እና ባልደረቦቹ ስብሰባውን በሪሞት ኮንትሮል እየተቆጣጠሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

1 comment: