Monday, October 15, 2012

በጉጂቦረና ሀ/ስብከትሥር የምትገኛው የሻኪሶ ምስራቀ ፀሐይ ቤ/ክ ያለችበት ሁኔታ

gugi borena church
ከፍርዱ ወልደነጎድጓድ
      ይህቺ ቤ/ክ ከተቆረቆረች 70 አመትአስቆጥራለች ታድያ በነዚህ አመታት ውስጥ በእሾህ አጠገብ እንደበቀለች ቁልቋል እየደማች  የከረመች ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ሰሞኑን የአውደ ምህረት ብሎግ በጉጂ ቦረና ሀ/ስብከት ያለበት ሁኔታ በሰፊው ዘግባለች ነገር ግን ያገረ ስብከቱ ችግር መነሻ የሻኪሶ ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው የሻኪሶ ቅ/ማርያም ሰበካጉባኤ የተመረጠው በ1984ዓ/ም ነው በወቅቱ ሀገረ ስብከቱ የነበረው በሐዋሳ ነው፡፡ ሊቀ ጳጳሱም አቡነ በርተሎሚዮስ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜ የሻኪሶ ቅ/ማርያም አስተዳዳሪ የነበሩት አባ ብርሃነ ስላሴ የአሁኑ አቡነ ዲዮስቆሮስ ናቸው እኚህ አባት ከዘዋይ እንደመጡ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ፍቅር ነበራቸው፡፡ ብዙዎችን ከባዕድ አምልኮ መልሰዋል፡፡ በ2004 በየካቲት 4 የተመረቀው ህንፃ ቤተክርስቲያንን መሰረት ያስጀመሩት እሳቸው ነበሩ፡፡ በኃላ ግን እጅግ የሆነ ፈተና ተነሳባቸው፡፡ በማ የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም? በአቡነ በርተሎሚዮስ ተቀምጦ ከአንድም ሶስት ጳጳሳት በሀገረ ስብከቱ ላይ ሲቀያየሩ በኃላም ሀገረ ስብከቱ በሁለት ስራ አስኪያጅ ሲመራም በመጨረሻ በአቡነ ሳዊሮስ የወረደው ሰበካ ጉባኤ ነው ይህ ሰበካ ማን ነው? ማህበረ ቅዱሳን በ1983 በብላቴ ጦር ማሰልጠኛ ተመስርቶ ወደ ተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ላይ መርዙን ሲረጭ ወዲያውኑ ነው የማቅ ህዋስ በሻኪሾ የተገኘው ምክንያቱም የደርግ መንግስት የአሁኑ ሜድሮክ ጎልድ የቀድሞ ለገደንቢ ወርቅ ልማት ድርጅትን ሲከፍት በተለያዩ ፊልድ ቀጥሮ ያመጣቸው ሰራተኞች የማኅበሩ አባል በመሆናቸው ነው፡፡

እኚህ አባትን የተሀድሶ ቀንደኛ መሪ ናቸው በማለት ህዝቡን በማነሳሳት ምዕመኑ ድንጋይ አንስቶ እስከ መደብደብ ማረፊያ ቤታቸውን ከአንድም ሁለቴ አሰብረው አዘርፈዋቸዋል ሀገሩንም ለቀው እንዲሄዱ ተደርገዋል ዛሬ ታዲያ እንደዛ ኢሰብአዊ ድርጊት የፈጸሙባቸውን ማህበር ለምን ተለጠፉ? እውነት ለመናገር ሰውየውም ተሀድሶ አይደሉም ነገር ግን የማይካድ ሐቅ አላቸው በወቅቱም ማረፊያ ቤታቸው መቃብር ቤት ስለነበር አጥሚት ወይም ፍትፍት ይዛ የመጣት ኮረዳ ሳያማግጡ አይሸኟትም የማህበረ ቅዱሳን አባል ከሆነች ሴት የ18 ዓመት ወንድ ልጅ አላቸው ማህበረ ቅዱሳንም ይህንን ገበና ጠንቅቆ ስለሚያውቅ  ወየውልህ ገበናህን እንገልጥልሃለን እያሉ ስለሚያስፈራቸው ህሊናቸውን ለመሸጥ ተገደዋል፡፡ ማህበረ ቅዱሳንም እርሳቸው እንደተባረሩ የማቅ ሳንባዎች እንደፈለጉ መተንፈስ ጀመሩ እራሳቸው ሰበካ ጉባኤ እራሳቸው ማህበረ ቅዱሳን ህንፃ አሰሪ እራሳቸው ሰንበት ት/ቤት እራሳቸው ወረዳ ቤተ ክህነት በመሆን የቤተ ክርስተያን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ማዋል ጀመሩ፡፡
ጳጳስ ወይም ከሀገረ ስብከት እንግዳ መጣ ሲባል ጎማ ስር ምንጣፍ እያነጠፉ በሜድሮክ ገስት ሐውስ ውስጥ በማስተኛት ዳጎስ ያለ ገንዘብ ሰተው በመሸኘት አባቶችም የህዝቡን እንባ መመልከት አልቻሉም ህዝቡ ሰሚ አቶ ለ17 ዓመት ቆይቷል፡፡ በዚያን ጊዜ ሲያምር ተክለ ማርያም  ከዝዋይ እንደመጣ በዱቁና ተቀጥሮ እየሰራ በትርፍ ሰዓቱ ፎቶ እያነሳ የሚኖር ሰው ነበር፡፡ ይህ ግለሰብ በወቅቱ ማህበሩ እንደ አቡነ ዲዮስቆሮስ የተሃድሶ ታርጋ ከተለጠፈባቸው የአሁኑ የማቅ ፈረስ አንዱ ነበር፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ከፍተኛ እንግልት አድርሰውበታል፡፡ በወቅቱ ጓደኞቹ ተነጋግረው በወረዳው ስር ወደ ምትገኘው መጋዶ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንዲቀጠር ተደረገ ከዛም በወቅቱ ሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዲሜጥሮስ ተቀይረው እንደመጡ በሰዎች ከፍተኛ ተጋድሎ ወደ ቅዱስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲገባ ተደረገ፡፡ ሲያምር የአሁኑ ጋዳፊ የቀድሞ ምስኪን ሾፋ አጣቢ (የወርቅ እጣቢ አጣቢ)  ከኮሌጅ ተመርቆ ሲወጣ እንደ እድል ሆኖ ይዞ የወጣው ወንጌልን ሳይሆን የይሁዳ ከረጢት ነው፡፡ ከረጢቷን አንግቦ እያለ አቡነ ሳዊሮስ በሃገረ ስብከቱ ላይ ተመደቡ ሲመጢ በቂቤ አንደበቱ በለሰለሰ በእባብ ቆዳው ተጠጋቸው ሊቀ ጳጳሱም ቆዳውን አይተው የጉጂ ቦረና ሊበን ሃገረ ስብከት የስብከት ወንጌል ኃላፊ አድርገው ሾሙት፡፡ እሱም የተሰጠውን የወንጌል ኃላፊነት ወደ ጎን ትቶ ከቲዎሎጂ ይዞ በወጣው በይሁዳ ከረጢት ገንዘብ መሰብሰብ ጀመረ አቡነ ሳዊሮስም በሃገረ ስብከቱ ላይ ታላቅ የወንጌልን ችቦ አቀጣጠሉ ህዝቡም የዘመናት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጀመረ በዚያን ጊዜ የሲያምር እንቅስቃሴ አልዋጥላቸው ያላቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ለሊቀ ጳጳሱም ቀርበው ቢያስረዱም  በወቅቱ ሊመስላቸው አልቻለም፡፡
በዚህ ሁኔታ እያለ ነው እንግዲህ 2001 ዓ/ም በአቡነ ሳዊሮስ ትዕዛዝ በሻኪሶ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን መስከረም ወር ላይ በሻኪሶ ወርቅ ነጋዴዎች እስፖንሰር አድራጊነት ታላቅ ጉባኤ ተካሄደ፡፡ የጉባኤው ፍፃሜ ላይ ህዝቡ ሊቀ ጳጳሱን አንድ ጥያቄ ጠየቀ እኛ ወንጌል እንፈልጋለን ይህ ሰበካ ጉባኤ ከቃለ አዋዲ ውጪ ለ17 ዓመት ተቀምጧል የወንጌል እንቅፋት ስለሆነ ይውረድልን ብሎ ጮኸ ሊቀ ጳጳሱም የህዝቡን ጥያቄ ወዲያውኑ በመመለስ ከደርግ መንግስት እኩል ስልጣን ላይ የነበረውን ሰበካ ጉባኤ አወረዱት፡፡ ህዝቡም በደስታ እንባ ተራጨ፡፡ ማቅም እንደፈለገ ሲፈነጭበት የነበረውን እርስቱን አጣ እንዳበደ ውሻ መሮጥ ጀመረ፡፡ በወቅቱ የሃገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ የነበሩት ብረሃኑ ካሳ ለቀው ሄዱ፡፡ አቡነ ሳዊሮስ ሲያምርን ከስብከተ ወንጌል ኃላፊነት አንስተው ስራ አስኪያጅ አደረጉት፡፡ ባጎረስኩ እጄ ተነከስኩ እንዲሉ ዛሬ ስማቸውን እያጠፋ ይገኛል፡፡
ማቅም የሆዱን በሆዱ ይዞ ሳለ አቡነ ሳዊሮስ ተቀይረው ወደ ወሊሶ ሲሄዱ ምቹ ጊዜን የሚጠብቀው ማቅም ይሁዳ ጌታውን በ30 ብር እንደ ሸጠ ሁሉ ሲያምር እጅ ላይ የይሁዳ ከረጢት ስላየ በወቅቱ ሰርግ ስለነበረበት አስታከው ከረጢቱ ውስጥ 20,000 ብር ወሸቁለት በወቅቱ ገንዘቡን ካሰባሰቡለት ሰዎች መካከል
1. ልንገረው መኮንን(መፃጉ)
2. ወርቅነህ ተክለሚካኤል (በ1997 በሻኪሶ ወረዳ የቅንጅት ተዋካይ የነበሩ በወቅቱ የፖለቲካ ኪሳራ የደረሰባቸው አሁን ፊታቸውን ወደ ግንቦት 7 የፖለቲካ ድርጅት የተቀላቀሉ አሁን ደግሞ  በቤተህርስቲያን ከነ አቡነ ገብርኤል ጋር በመሆን ህዝቡን ግራ ባጋባት ላይ የሚገኙ ግለሰብ ናቸው) 3.ሊቀትጉሐን ኪዳኔአባዲ  ናቸው፡፡
ሲያምርም የጳጳሱን ቦታ ደርቦ በመያዝ በኪራይ ሰብሳቢነት ተዘፈቀ ማቅም አፈር ልሶ መነሳት ጀመረ፡፡ የሻኪሶ ሰበካ ጉባኤ የወረደው አላግባብ ነው ሰበካው የተመረጠው አላግባብ ነው አስተዳዳሪውም ሙስሊም ናቸው የወረዳው ሊቀ ካህን ተሃድሶ ነው፡፡ በማለት ማወክ ጀመሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን ለ17 ዓመት እንደ ትኋን ተጣብቀውባት የቤተክርስቲያንን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ሲያውሉ የነበሩ ናቸው፡፡ ለአብነት ጥቂቶቹን እንመልከት
ሀ). ሊቀ ትጉኃን ኪዳኔ አባዲ ይህ ግለሰብ ሻኪሶ የመጣው በ1985 ዓ/ም ነው እንደመጣ በጭቃ መምረግ ስራ የሚተዳደር ግለሰብ ነበር በአላት ሲሆን ቅኔ ማህሌት ቆሞ ሲወጣ ደጀ ሰላም ቁራሽ የሚወረውርለት ምስኪን ሰው ነበር፡፡ ቀስ እያለ ከማቅ አባል ከተቀላቀለ በኃላ ማህበሩ በአባ ዲዮስቆሮስና በሲያምር ላይ ዘመቻ ሲከፍት የጦሩ መሪ በመሆን ካስወገዷቸው በኃላ ማቅ ለውለታው ሲል ወዲያውኑ
1.   የወረዳው ምክትል ሊቀ ካህን
2.   የሰበካ ጉባኤ ሊቀ መንበር
3.   የወረዳው የኤች አይ ቪ ኤድስ ካውንስለር
4.   የወረዳው የኤች አይ ቪ ኤድስ ገንዘብ ያዥ
5.   በወረዳው የሚገኙ የዘጠኙ አብያተ ክርስቲያና የልማት ኮሚቴ ሊቀ መንበር
6.   በወረዳው የሚገኙ የዘጠኙ አብያተ ክርስቲያና የልማት ኮሚቴ ገንዘብ ያዥ
7.   በወረዳው የሚገኙ የዘጠኙ አብያተ ክርስቲያናት ካሃናት ቅሬታ ሰሚ በማድረግ በአንድ ቂጡ ሰባት ወንበር ላይ እንዲቀመጥ አደረጉት፡፡
ከዚያም የሜድሮክ የሰራተኛ ማህበር አባላት የማህበረ ቅዱሳን አባላት ስለ ነበሩ ሜድሮክ ጎልድ አስቀጠሩት ብዙም ሳይቆይ በሻኪሶ ከተማ ውስጥ ከ100,000 ሺህ እስከ 120,000 ሺህ የሚገመት ሱቅ ከፈተ መቀሌ ከተማ ግራወንድ ፕላስ 3 ፎቅ ሰርቷል፡፡ በተለምዶ አባ ዱላ የሚባለውን ሚኒባስ ገዝቷል፡፡ በ2004 ዓ/ም የተመረቀው ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ከሙገር ፋብሪካ  2000 ኩንታል ተፈቅዶ ስራ ላይ የዋለው 250 ኩንታል ብቻ ነው፡፡ ቀሪው የት ሄደ ብትሉግራወንድ ፕላስ ስሪ የታነፀበት በማን ይመስላችኃል፡፡
ለ). አቶ፡- በላይ ሸጋው ኃላፊነቶቹ
የህንፃው ግዢ
የሰበካው ሂሳብ ሹም
የማቅ ፀኃፊ
የሰንበትብ ት/ቤቱ ስራ አመራር
በዱከም ከተማ ጂ ፕላስ 2 መኖሪያ ቤት ያለው የሻኪሶ ዲሃስፖራ በመባል የሚታወቅ ሰው ነው፡፡
ሐ). አቶ፡-ገ/ጊዮርጊስ ቀለታ
የወረዳው የማህበረ ቅዱሳን ሊቀ መንበር
 የህንፃው ሂሳብ ሹም
የሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት ክፍል
በአዲስ አበባ ሃና ማርያም ሰፈር ግራወንድ ፕላስ 2 መኖሪያ የሰራ ቤተል ወይራ ሰፈር አካባቢ ለሚስቱ በ200,000 ሱፐር ማርኬት ከፍቷል፡፡ ከሜድሮክ ጎልድ ሰራተኞች በሙስና ቦታ አዶስ አበባ አሰጣችኃለሁ በማለት ከ12 ሰዎች ከየ አንዳንዳቸው 10,000 ብር በድምሩ 120,000 ብር  ክዷቸዋል ላብነት እነዚህን ጠቀስን እንጂ ብዙዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ናቸው እንግዲህ ለቤተ ክርስቲያኗ ቆመንላታል የሚሉት ለ17 ዓመት ቆይተው ሲወርዱ በቤተክርስቲያኑ አካውንት ውስጥ አስረክበው የወረዱት 82 ሺህ ብር ብቻ ነው፡፡ሲወርዱ እንኳን ኦዲት እንዳይደረጉ በሲያምርና በሊቀ ስዩማን ልሳነ ወርቅ ሁንዴ ተዋናይነት አልተደረጉም፡፡ ሲያምርም ተው ባይ አጣ፡፡ ስለዚህም ሻኪሶ ቅ/ማርያም ቤተ ክስርቲያን ቅፅር ጊቢ የሚረዱ 20 አዛውንቶች 13 የኤች አይ ቪ ህሙማን 18 ወላጅ አልባ ህፃናት በድምሩ 51 አባላት የሚመጣውን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው አውለውታል፡፡
መ)ዲያቆን ተስፋዬ ኃይሌ ለኤች አይ ቪ ኤድስ ህሙማን የምክር አገልግሎት የተገዛውን ማውንቴን ሳይክል ለልጁ አበርክቶለታል አዲሱ ሰበካ ጉባኤ በገንዘብ በኩል ጠንቃቃ ስለነበር ሊያምር አንድ ዘዴ ከማቅ አባላት ጋር ፈጠረ ሰበካው ገንዘብ በልቷል ብላችሁ ህዝቡን ቀስቅሱ ሰበካውን እናወርደዋለን ይልና በተባለው መሰረት የማቅ ቅጥረኞት እንደ ፖሊዮ ክትባት ቤት ለቤት ቀስቅሰው ህዝቡ ውስጥ ውዥንብርን ፈጠሩ፡፡ ወዲያውኑ ሲያምር ከሀገረ ስብከት ኦዲተሮችን ልኮ ከተመረጡ አንድ አመት ያልሞላቸውን ሰበካ ጉባኤ ኦዲት እንዲደረጉ አደረገ 17 ዓመት የቆዩትን እንዳይደረጉ አድርጎ በአንድ ዓመት ያልሞላውን ሰበካ እንዲደረጉ ማድረጉ ግርምትን ይፈጥራል፡፡  አዲሱ ሰበካ ጉባኤ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የካህናትን ደሞዝ ከቀድሞ በሶስት እጥፍ አሳድጎ ለቤተ ክርስቲያኗ ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ 12 ሱቆችን ገንብቶ በወር በ6000 ብር  አከራይቷል ስንዴ፤ በቆሎ ፤ጤፍ በመዝራት  ተጨማሪ ገቢ ፈጥሯል፡፡ በቤተክርስቲያኑ አካውንት ላይ 560,000 ሺህ ብር በላይ ተቀማጭ አላቸው ይህንን ፈጣን ለውጥ የተመለከተ ምዕመን ማለትም ከቃድሞ 17 ዐመት ካገለገሉት የማቅ የጉጂ ዞን ቀይ የደም ስር ካሆኑት ይልቅ አሁን ያሉት ኮሚቴዎች ቤተክርስቲያንንና አገልጋዮችዋን በከፍተኛ ሁኔታ እያገለገሉ በመሆናቸው እንዲሁም የቤተክርስትያኒቱን ገቢ ከቀድሞ በአመት ሲሰላ ከ300 እጥፍ በላይ በማሳደጋቸው ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ አመራ ቅዱስ ሲኖዶስም የችግሩ አሳሳቢነት በመመልከት አጣሪ ልኮ አጣሪዎቹ አጣርተው ከተመለሱ በኃላ ቅዱስ ሲኖዶስ ሲያምር ተ/ማርያምን በቅያሪ ወደ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ቢቀየርም አሻፈረኝ በማለት እያወከ ይገኛል፡፡ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ተሹመው የመጡትን ስራ አስኪያጅ ከማህበሩ ጋር በመሆን እያስደበደበ በመጡበት እግራቸው እንደመለሱ ያደረገ ነው፡፡አሁንም ሁከትን እየፈጠረ ይገኛል ይህ ህገወጥ የሆነ ግለሰብ የዞኑ አስተዳዳሪ የዞኑ ፀጥታ ዘርፍ የዞኑ ፍትህ ቢሮ የዞኑ ፖሊስ ይህን ግለሰብ እንዲያስታግሱ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በተደጋጋሚ የፍትህ ያለ ቢልም የዞኑ ባለስልጣናት በኪራይ ሰብሳቢነት ተዘፍቀው ከማህበረ ቅዱሳን በሚሾጎጥላቸው ዳጎስ ያለ ገንዘብ የህዝቡን ጩኸት ሰሚ አቷል ዞኑንን መንግስት አልባዋ ባድማ አድርገዋታል ይህንን ጉዳይ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትንም በግልባጭም አሳውቀናል ህዝቡ መንግስት ላይ ጥርጥር እያሳደረ ይገኛል የፌደራል መንግስት በገዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል በመጨረሻም ከተቆረቆች 70 ዓመት ካስቆጠችው ቤተ ክርስቲያን ከወረደው ሰበካ ከማቅ ፀኃፊ  በአቶ በላይ ሸጋው እጅ ያላስረከቡት 723 ግራም ወርቅ በእጁ ይገኛል፡፡ ከህንፃው ስራ የቀረ 96,000 ብር አቶ፡- ገብረ ጊዮርጊስ ገለታ እጅ በዲያቆን ተስፋዬ ኃይሌና በኪዳኔ አባዲ በመርጌታ ሰለሞን የኤች አይ ቪ ኤድስ ህሙማን መርጃ በሶስቱ ስም 45,000 ብር ይገኛል፡፡ የግፍ ቀንበር የከበደው ሕዝብ አዲሱን ነፍጠኛ ማቅን ለመቋቋም በከፍተኛ ተነሳሽነት ላይ ይገኛል፡፡ መነግስትም በቤተክርስቲን በኩል ማቅን ታክኮ የመጣውን የነፍጠኛ ስርዓት እንዲያስታግስልን እንጠይቃለን፡፡
ሰላመ እግዚዝብሔር አይለየን
 
 

1 comment:

  1. ዐውደ ምሕረቶች ምሕረት ያውርድ! ለቤተ ክርስቲያን እና ለእውነት ስትሉ
    የምትጽፉት ማስገንዘቢያ ጽሑፍ የምታቀርቡት የሓሳብ ድጋፍ ግሩም ነውና ጠንክሩ
    ተረፈ ይሁዳና ብዙ አስመሳይ ፈሪሳውያን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ተሰግስገዋል፤
    እናም ንግር ወኢታምም ተናገር ዝም አትበል ይላልና እስክመጨረሻው ልናውቅባቸው
    ይገባል፤ የፈጣሪ ኃይል ከሁላችን ጋር ይሁን!

    ReplyDelete