Friday, October 26, 2012

አራተኛው ቀን የሲኖዶሱ ስብሰባ

Click here to read in PDf: sinodos day 4
  • ·       ተስፋዬ ከምክትል ስራ አስኪያጅነቱ እንዲነሳ ተወስኗል
  • ·       ሰለሞን ቶልቻ ከገዳማት አስተዳደር ይነሳ ተብሏል
  • ·       እስክንድር ከህዝብ ግንኙነት ይነሳል
  • ·       ለግብጽ ቤተክርስቲያን የፓትርያርክ ምርጫ አምስት ጳጳሳት እንዲሄዱ ተወስኗል
  • ·       አቡነ ሰላማ የአክሱም ህዝብን የደረሰባቸውን ተቃውሞ ለማስተባበል ጉዳዬ ይታልኝ ቢሉም ሰሚ አላገኙም

በዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ በርካታ ጉዳዮች የታዩ ሲሆን የጠቅላይ ቤተክህነቱ ምክትል ስራ እስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ሁለት ስልጣን ደራርቦ መያዙ አግባብነት ስለሌለው በአንዱ ስልጣን በቤቶች አስተዳደር ብቻ ተወስኖ እንዲቀመጥ እና ከጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅነቱ እንዲነሳ ተወስኗል፡፡
ተስፋዬ ከቦታው እንዲነሳ የተወሰነበት ተጨማሪ ምክንያት ደግሞ ጠቅላይ ቤተክህነቱ በአቶ መመራት የለበትም የሚል ተጨማሪ ምክንያት በመቅረቡ ነው፡፡ አቶ ተስፋዬ የቤተክነቱ ትምህርት ስለሌለው እና የቤተክነትን ቋንቋ በብቃት ስለማያውቅ አንዳንድ ጉዳዮችን በአቶ ደንብ ማስተናገዱ ቅር  እንዳሰኛቸው ያልደበቁ ጳጳሳት ነበሩ፡፡

የገዳማት መምሪያን በመምሪያ ኃላፊ ደረጃ ይመራ የነበረው ሰለሞን ቶልቻም እንዲሁ ከስልጣኑ እንዲነሳ ሲኖዶሱ ወስኖበታል፡፡ ስለገዳማት አኗኗር አወቃቀርና የትምህርት ሁኔታ ምንም የማያውቅ ሰው ገዳማትን በጥቁር እራሱ መምራቱ አግባብ አይደለም ተብሎ ከስልጣኑ እንዲነሳ ተወስኖበታል፡፡ በተቻለ መጠን የገዳማትን መምሪያ ከመነኩሴ ውጭ ባይሾምበት ጥሩ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡
የጳጳሳቱ ተቃውሞ በከፍተኛ ደረጃ የተሰማው ግን የህዝብ ግንኙነት ነኝ ብሎ እንጥጥ ፍርጥ እያሉ በመንበረ ፓትርያርኩ ጊቢ በሚንጎማለለው በእስክንድር ላይ ነው፡፡ ብጹአን አባቶች ሕዝብ ግንኙነት ለመሆኑ ምንድን ነው ስራው? ቤተክርስቲያን ስራዋ ሕዝብን ከወንጌል ጋር ማገናኘት አይደለም ወይ? ሌላ ምን ተልዕኮ አላት? ሲሉ ከጠየቁ በኃላ ለዚህ ስራ የወንጌል መምህር እንጂ ሌላ አያስፈልገንም ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ስለዚህም አቶ እስክንድር ቦታውን መልቀቅ አለበት በማለት ወስነዋል፡፡
ለግብጽ የፓትርርክ ምርጫ ላይ እንዲገኙ እና በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ስም ድምጽ እንዲሰጡ አቡነ ገሪማ አቡነ አረጋዊና አቡነ ገብርኤል የሚገኙበት የ5 ጳጳሳት ልኡካን ቡድን ተመርጧል፡፡
በዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ ለየት ብሎ ብዙዎችን ያስደመመው የአቡነ ሰላማ ሁኔታ ነው፡፡ ብጹዕነታቸው በአክሱም ምዕመናን እና ካህናት የደረሰባቸውን ተቃውሞ እና ካሁን በኃላ ስለማንፈልግዎ ተመልሰው አይምጡብን የሚል ሀሳብ በእጅጉ አበሳጭቷቸው የኔ ጉዳይ ያለ አጀንዳ በሰበር ይታይልኝ ቢሉም ሲኖዶሱ ግን የእርስዎ ጉዳይ በአስተዳደር ነው የሚታየው ሲል ተቃውሞዋቸዋል፡፡
የአክሱም ምዕመናን በአቡነ ሰላማ ላይ ተቃውሞ ካሰሙበባቸው ምክንያቶች አንዱ በቤታቸው በሚያድርጉት ማጥመቅ ነው፡፡ መነኩሴ ሆነው ከመነኩሴም ጳጳስ እንዴት ቤታቸው ያጠምቃሉ? ተገቢም አይደለም በማለት ነው፡፡
የስብከተ ወንጌል መምሪያን ጨምሮ የአጠቃላይ መምሪያዎች አሰራር እና አወቃቀር ድክመት ስለሚታይበት ይሻሻል የሚል ሀሳብ ተነስቶም በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በኩል የማሻሻያ ሀሳብ እንዲቀርብ ተወስኗል፡፡ በዚኅም ማህበረ ቅዱሳን ከፓትርያርክ ምርጫ በፊት ከቃለ አዋዲው ጀምሮ ሁሉንም የቤተክህነት ህጎች መመሪያዎች እና መተዳደሪያ ደንቦች ለማሻሻል ያለውን ፍላጉት አሳክቷል፡፡ በዚህ ስራው ቤተክርስቲንዋን ጠቅልሎ በማህበሩ ጉያ ውስጥ እንዴት እንደሚስቀምጣት እቅዱን የሚያሳካበት መንገድ ይነድፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የእግዚአብሔር መንጋ በሚሰበሰብባት ቤተክርስቲን የተለያያ ታርጋ እየለጠፈ መንጋውን ለመበተን ቆርጦ የተነሳው እና መንፈሳዊነት የአስተዳደር ቦታን መቆጣጠር የሚመስለው  ማኅበረ ቅዱሳን አስተዳደር መምሪያውን ለመቆጣጠር ከሚነድፍበት እቅድ ከሚያጠፋው ጊዜና ከሚሸርባቸው ሴራዎች 2 በመቶውን እንኳ ቀንሶ የምዕመናንን ፍልሰት እንዴት ማቆም እንችላለን የሚል ጥያቄ ቢጠይቅ ኖሮ ወንጌል በማስተማር የሚል ትክክለኛ መልስ ማግኘት በቻለ ነበር፡፡
ነገር ግን እንደጭቃ ሹም ምእመኑን አስጨንቆ ከመግዛት ውጭ ሌላ መንፈሳዊነት እንደሌለ የሚያስበው ማቅ የምእመናኑን ፍልሰት ቁም ነገሬ ማለት ከተወ ቆይቷል፡፡ ይልቅስ አጠናሁ ፈተፈትኩ እያለ የምንቆርበው ማኅሌት የሚቆምልን የሚቀደሰው ሱባኤ የሚያዘው በተሃድሶ እጅ ነው፡፡ ከቤተክርስቲኑ ህዝብ 85% ተሀድሶ ነው፡፡ መናኒያኑ ገዳምያኑ ሁሉ ተሃድሶዎች ናቸው፡፡ ጥናቴ ይህን ያረጋግጣል በማለት በቤተክህነት አዳራሽ ከየሀገረ ስብከቱ የተሰበሰቡ ካኅናት ፊት እንደ ድል ዜና በማውራት
ጊዜ የለም እንጂ ጊዜማ ቢኖር
ሁሉንም አብርሬ ባዶ አስቀር ነበር
የሚል የሞኝ ዘፈን እየዘፈነ ይገኛል፡፡ የአሁኑ ጊዜ የቤተክርስቲያን ትልቁ አደጋ የምእመናን ፍልሰት ሆኖ ሳለ እሱ የሚቆምበትን መንፈሳዊ መንገድ ከማሰብ ይልቅ ዛሬም 85% ኦርቶዶክሳዊን አጥንቼ አወኩ በማለት ተሀድሶ ነህ አበርሀለሁ እያለ ይገኛል፡፡
ማኅበሩ በዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንኳ አባቶች “ቤተክርስቲያን ስራዋ ሕዝብን ከወንጌል ጋር ማገናኘት አይደለም ወይ? ሌላ ምን ተልዕኮ አላት? ሲሉ ከጠየቁ በኃላ ለዚህ ስራ የወንጌል መምህር እንጂ ሌላ አያስፈልገንም” በማለት የተናገሩትን ሰምቶ ቢሆን ኖሮ ለስንት አይነት ችግሮች ቋሚና ዘላቂ መፍትሔ ባገኘ ነበር፡፡ ከላይ ከሰማይ ካልታደሉ ቢደላደሉም ለውጥ የለው፡፡

2 comments:

  1. good job guys very good

    ReplyDelete
  2. kikiki masaregiyahe mahebere kidusan newe ayedele!!! alegebahem enji ke namelake sera ga atetageem nebere betekirstiyan netsa eyewetache newe...menafeqe hula teterarego ezawe adarashu yeheadale

    ReplyDelete