Sunday, October 21, 2012

የአባ ናትናኤል ጉዳይ

  • ከእስር ከተፈቱ ሳምንት ሆኗቸዋል
  • ለእስር ያበቃቸው ዋነኛው ምክንያት ማኅበረ ቅዱሳን በደብሩ የሚካሄደውን ግልጽ ጨረታ አጭበርብሮ ለማሸነፍ በመፈለጉ ነው፡፡
የአየር ጤና ኪዳነ ምህረት / አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ናትናኤል መላኩ ባለፈው ጥቅምት 2 2005 ዓ.ም. በአዋሳ ፖሊሶች አማካኝነት ታስረው የተወሰዱ ቢሆንም ባለፈው ሳምነት እሁድ እሳቸውን ለማሳሰር የሚያበቃ ምንም ምክንያት እንደሌለ ስለታመነበት ከእስር እንዲፈቱ ተደርገዋል፡፡ ከአዋሳ ሀብታሞች እና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ተሻርከው እንዲታሰሩ ያደረጉት ፖሊሶችም በድረጊታቸው በክልል መንግስት ተገምግመው በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ታልፈዋል፡፡ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ የተባለው ፖሊስ ቁርጥራጭ ሳንቲም ተቀብሎ ንጹህ ሰው ለማሰር በመሞከሩ በራሱ ላይ ግለ ሂስ እንዲያደርግ የታዘዘ ሲሆን ከስራው መታገድም ያሳጋዋል፡፡
አባ ናትናኤል ለምን ታሰሩ?
አየር ጤና ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ከተሾሙ ጀምሮ ከስልጣናቸው ሊያስነሳቸው ትግል ሲያድርግ የነበረው እና ለኔ ያልታዘዘ ሁሉ ተሀድሶ ነው በሚል አባዜ የተመታው ማኅበረ ቅዱሳን አባ ናትናኤል እያደረጉት ባለው ስራ በደብሩ ካህናትና ምዕመናን ተቀባይነት እያገኙ በመምጣቸው እና በቦታው ላይ ማኅበሩ የቢዝነስ ኢምፓየር በማጣቱ የተነሳ እና ይልቁንም ባለፈው ሰኞ በደብሩ ይካሄድ የነበረው የ2.8 ሚሊየን ብር ጨረታ በእሱ ሰዎች አሸናፊነት እንዲጠናቀቅ በመፈለጉ ምክንያት ሐዋሳ ከተማ ካሉ ጀሌዎቹ ጋር ተነጋግሮ የሰራው ሴራ ቢሆንም የክልሉ መንገስት ተንኮሉን በመረዳቱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ በማዘዙ ባለፈው እሁድ ተፈትተው ጨረታው እሳቸው በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ ጨረታው የማኅበሩ ሰዎች እንዲሸንፉ ዝግ ጨረታ እንዲሆን ተፈልጎ የነበረ ቢሆንም ጨረታው ገልጽ ሆኖ አሸነፊም በግልጽ መታወቅ አለበት በማለታቸው ማኅበርዋም አስባው የነበረውን ሴራ ሳይሳካላት ቀርቷል፡፡ የእሳቸው እስር የመጣው እንግዲህ ጨረታው ዝግ እንዲሆን እና የማኅበሩ ሰዎች እንዲያሸንፉ ለማድረግ ነው፡፡ አልተሳካም እንጂ፤ እውነቱ ይሔ ሳለ አንድ አድርገን የተባለው የማቅ ብሎግ ግን በ170 ሺህ ብር ስርቆት ተከሰሱ ሲል አስነብቦናል፡፡ ቀድሞ መጮህ  የአላማው ማስፈጸሚያ መንገድ አድርጎ የተረዳው ማቅ አባ ናትናኤል ባልሰረቁት ገንዘብ ተከሰሱ ቢልም እውነታው ግን ከላይ የገለጽነው ነው፡፡
እሳቸው ከመጡ በኃላ ለማኅበሩ ሰዎች 3000 ብር ይከራይ የነበረውን የቤተክርስቲያኑን ቦታ አስለቅቀው 30000 ብር በግልጽ ጨረታ እንዲከራይ አድርገዋል፡፡ ይህም የአየር ጤና ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ምዕመን የሚረዳው ሀቅ ነው፡፡ ማኅበሩ በአቡነ ገብርኤል መኪና ከሞያሌ አዋሳ  ኮንትሮባንድ እየሰራ መንጀል እስፋፋ በሀገር ላይ ኪሳራ እያስከተለ እሱን የማይደግፉትንና ህጋዊ አሰራርን በሚያበረታቱት የቤተክርስቲን ልጆችን ግን በጨዋ አፉ ስማቸውን ያስጠፋል ጉቦ እየሰጠም ለማሳሳር ይሞክራል፡፡
አባ ናትናኤል ጸሎት በእንተ ማኅበረ ቅዱሳን የተባለ መጽሀፍ የጻፉ ሰው መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም ማኅበሩ ከፍተኛ ቂም ይዞባቸዋል፡፡ ቂሙንም ለመወጣት ከግብር አባቱ ከዲቢሎስ በተማረው መሰረት በርካታ የሀሰት ክሶችን እና ማስፈራሪያዎችን ቢደረድርም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

No comments:

Post a Comment