Friday, April 20, 2012

«አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት» የሚለው አባባል “ሕገ መንግሥት” ላይ ብቻ ሳይሆን በክርስትናም ላይ የተቃጣ የጸረ- ክርስቶሱ ሃሳዌ መሲህ አጀንዳ ነው!

                                         በዲ/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
       (ዲ/ን ሙሉጌታ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ተነባቢነት የነበረውና በብዙ እውነተኛ የሰነድ ማስረጃዎች የተደገፈው ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሠይጣን የሚለው መጽሐፍ ደራሲ ነው)

ለመግባባት ያክል የምዕራቡ ዓለም የዕድገትና የስልጣኔ ምስጢር በማውሳት ሐተታዬን ልጀምር:: ለብዙዎቻችን ግልጽ እንደሆነ የምዕራቡ አለም ፖለቲካ ከተቀረው የዓለማችን ክፍል የሕዝብ አስተዳደር የተለየና የላቀ የሚያደርገው ቢኖር የፖለቲካ መሪዎች አስተዋይነትና አርቆ አሳቢነት ለመሆኑ  አያከራክርም:: ለምሳሌ ያክል "የዲሞክራሲ" ተምሳሌት የሆነችውን ሃያልዋ ሀገረ አሜሪካ የወሰድን እንደሆን በተለይ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በየትኛውም መስክ ያለ ተቃናቃኝ በኢኮኖሚውም ሆነ በፖለቲካው መድረክ የበላይነትዋን  እንደያዘች የመዝለቅዋ ምስጢር ስልጣን ላይ የሚወጡትም ሆነ በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉትን የፖለቲካ መሪዎች ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ውጤት ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም:: ይህ ማለት ዲሞክራትም ይሁን የሪፐብሊካን ፓርቲ አቀንቃኝ ሀገራቸው አሜሪካ በዋናነት ልትከተለው በሚገባት ፖሊሲ ላይ የጎላ ልዩነት ቢኖራቸውም የአሜሪካን ሉዓላዊነት እንዲሁም የአሜሪካ ሕዝብ ጥቅም የመጣን እንደሆነ ግን አንዱን ከሌላውን መለየት ፈጽሞ አይቻለንም:: ሀገራዊ ጥቅም በተመለከተ ዲሞክራቱም ሪፖብሊካኑም አሜሪካዊ ነው!! እናማ ከየትም አቅጣ ቢመጡ ጽሐፉን ሲያነቡ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በሰከነ መንፈስና በተረጋገ ልብ እንደሚያነቡት ተስፋ አደርጋለሁ:: 

በያዝነው ሳምንት ከጥቂት ቀናቶች በፊት መሆኑ ነው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በፓርላማቸው ተገኝተው ካደረግዋቸው ንግግሮችና ከተወካዮቹም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ካነሱዋቸው ነጥቦች መካከል ሃይማኖትን በማስመልከት መንግስታዊ ትንታኔአቸውና አቋማቸውን ለፓርላማው ግልጽ አድርገዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ማህበረ ቅዱሳን" ከአልቃይዳ ጋር በማመሳሰልም ገልጸውታል:: እንግዲህ ይህን አገላለጽ/ንግግር ያዳመጠ ሰው አልቃይዳ ማለት ደግሞ ማን ነው? ምንስ ማለት ነው? ብሎ የሚጠይቅ አዋቂ ሊኖር እንደማይችል አምናለሁ::  

Thursday, April 19, 2012

ማህበረ ቅዱሳንና ሰለፊያ፤ ማን የማን ግልባጭ ነው?

Click here to Read in PDF

የማህበረ ቅዱሳን ሰለባ የሆኑ ብዙ የቤተክርስቲያን አባቶችና ልጆች ማቅን በአሸባሪነት ከፈረጁት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ ማቅ ግን እንዲህ የሚሉኝ ለቤተ ክርስቲያን ጥብቅና ስለቆምኩ ነው በሚል ራሱን ሲከላከል ቆይቷል። ማህበሩ አሸባሪ የመሆኑ ጉዳይም በአንዳንዶች ዘንድ እንደ ስድበ ሲቆጠር መቆየቱ ይታወሳል። ለማኅበሩ ይህ ስም የተሰጠው በከንቱ አልነበረም። ስራው በአክራሪ ሙስሊሞች ከሚካሄደው የበለጠ እንጂ ያላነሰ ሆኖ ስለተገኘ ነበር ይህ የግብር ስም የወጣለት።

 ዕድሜ የሰጠው ሰው ብዙ ያያልና ይኸው የማህበሩ የግብር ስም ከትናንት በስቲያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ጸድቋል። በማኅበሩ ሲገፉና ሲነቀፉ ለኖሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ይህ እንደ አንድ ትልቅ ድል የሚቆጠር ነው። እንኳንም በትክክል የወጣለት የግብር ስም በማኅበሩ ዘንድ እንደ ስድብ ከመቆጠር አልፎ ትክክለኛ የማህበረ ቅዱሳንን ማንነት የሚገልጥ ስም ሆኖ ተነገረ! ይህን የተናገሩት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትራችን መሆናቸው ትልቅ ግምት የሚሰጠው ብቻ ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን ከማሸበር አልፎ አገርንም ለማተራመስ ትልቅ አላማ እንዳለው በመንግስት በኩል የተደረሰበት መሆኑን ያመለክታል።   

በአሁኑ ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳን ማነው? ምንስ ነው የሚሰራው? አላማው ምንድነው ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ የሚፈልገው የህብረተሰብ ቁጥር እየበዛ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ሰለፊያን አስመለክተው ሲናገሩ ሰለፊያ የማኅበረ ቅዱሳን ግልባጭ መሆኑን በግልጽ ቋንቋ እንዲህ ሲሉ ነግረውናል። “አንዳንድ የሰለፊ እምነት ተከታዮች አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱትን ግልባጭ ሲያራምዱ ይታያሉ።” ማኅበረ ቅዱሳን ለክፋት መምህር እንጂ ደቀመዝሙር እንደማይሆን የተረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ማኅበረ ቅዱሳን ስልቶቹንና አካሄዱን ለሰለፊያ ማውረሱን በማያሻማ መንገድ ገልጸዋል፡፡
መቼም ማቅ የሚሰራውን ስራ አስተውሎ ያየ ሰው በማቅና በሰለፊያ(ወሀቢያ) መካካል ያለውን የመንፈስ አንድነት በቀላሉ ይረዳል። ለማስረጃ ያህል፡-

Tuesday, April 17, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን የጉዞ መርሀ ግብርና አንድምታው

ከተመሰረተ 20 ዓመት ከ7 ወር ከ23 ቀን የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ ዓመቱን በእግር ጉዞ ለማክበር መዘጋጀቱን በየስፍራው በለጠፈውና በየሚዲያው በሚያስነግረው ማስታወቂያ እየገለጸ ይገኛል። መስከረም 4 ቀን 1984 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገረው ማህበረ ቅዱሳን የተመሰረተበትን ቀን ሳይጠብቅና ከቀኑ ሰባት ወራትና 23 ቀናትን አሳልፎ 20ኛ ዓመቱን የምስረታ በዓል ማክበር ለምን አስፈለገው? የሚል ጥያቄን በብዙዎች ዘንድ ፈጥሯል።

ማኅበሩ የማያውቁትንና እርሱም በስም ብቻ ካልሆነ በቀር የማያውቃቸውን የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን ፎቶ ግራፍ የማስታወቂያው ማዳመቂያ ያደረገ ሲሆን፣ ብፁዕነታቸው የማኅበሩ መሥራች አባት ተደርገው እንዲቆጠሩ በስማቸው ብዙ ሲሰራ እንደቆየ ለማወቅ ተችሏል። ብፁዕነታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በ1982 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ሲሆን፣ ማኅበሩ የተቋቋመው ደግሞ ከ2 ዓመት በኋላ በ1984 ዓ.ም ነው።

Thursday, April 12, 2012

ማህበረ ቅዱሳን በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ላይ የስለላ መዋቅሩን ዘረጋ

Click here to read in PDF
    • “የቤተክርስቲያን አባቶች የጻፉትን መጻህፍትም ሆነ የቤተክርስቲያን አባቶችን መቶ በመቶ አንቀበልም። መቶ በመቶ የምንቀበለው መጽሐፍ ቅዱስንና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው።”                                                                               ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
ማኅበረ ቅዱሳን በየወሩ በሚያካሂደው የማኅበሩ አባላት የሆኑ አገልጋዮች ውይይት  ላይ የማኅበሩ አፍ ሆኖ በተለያዩ ቦታዎች እና አዳራሾች በግንዛቤ አስጨብጣለሁ ስም፣ ያለ አንዳች ማስረጃ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆችን “ተሀድሶ - መናፍቃን ናቸው” እያለ መግለጫ ሲሰጥ የነበረው ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ በቤተክርስቲያን ታሪክ «አውጣኪ መናፍቅ ነው» የተባለው ያለ ተጨባጭ ማስረጃ ነው ሲል ለአውጣኪ ተከላከለ።

የካቲት 29 2004 ዓ.ም. በአዲስ ቪው ሆቴል በተካሔደው በዚህ ወርሀዊ ጉባኤ ላይ ለጥናት የቀረበው ርዕስ “ቅድመ ኬልቄዶን ጉባኤ የኬልቄዶን ጉባኤ እውነታና ድኅረ ኬልቄዶን ጉባኤ” የሚል ሲሆን፣ የጽሁፉም አቅራቢ የማህበሩ ቀኝ እጅ ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ነው። የጥናቱ ዋና ትኩረት የአውጣኪና የፍላብያኖስን ጠብና የአውጣኪን መወገዝ የተመለከተ ነው። ያረጋል እንዳለው በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የተቻለውን ያህል ልዩ ልዩ መዛግብትን ለማገላበጥ የሞከረ መሆኑን ጠቅሶ፣ ከዚህም በመነሳት የደረሰበት ድምዳሜ “አውጣኪ የተወገዘው መናፍቅ ሆኖ ሳይሆን በወቅቱ ስልጣን ላይ በነበሩት በነፍላብያኖስ ጥላቻ ነው” የሚል ነው። ይህም እንደ ጥናቱ ባለቤት እንደ ያረጋል አመለካከት “በወቅቱ አውጣኪ ላይ የቀረበው ክስ በእምነት ሳይሆን በጥላቻ የቀረበ ነው። ከዚህም በመነሳት ክሱ መሠረታዊውን አጀንዳ የሳተ እና በሀይማኖት ሽፋንነት የቀረበ ነው ወደሚል ድምዳሜ ያደርሰናል።” ብሏል።

ያረጋል ይህንን ሀሳቡን ሲያጠናክር በዋነኛነት እንደ ምክንያት የሚከተለውን አቅርቧል፤ “አውጣኪን መናፍቅ የሚያደርግ አንድም መረጃ አልተገኘም። አውጣኪ የተወገዘው በትክክለኛ እምነቱ ነው። በገዳሙ ውስጥ በእውነተኛ እምነቱ እና በትክክለኛ የምንኩስና ህይወቱ ይኖር የነበረ ሲሆን፣ በጉባኤው ላይ የመገኘት ፍላጎት አልነበረውም። በጉባኤው ላይ ላለመገኘትም ሕመምና የተለያዩ ምክንያቶችን አቅርቦ እንደ ነበር ያካሄድኩት ጥናት ያስረዳል። ይሁንና ያኔ ስልጣን ላይ የነበሩት አካላት በግፍ በጉባኤው ላይ እንዲቀርብና ምንም አይነት ሀሳብ ሳያቀርብ ጥያቄም ሳይጠየቅ መልስም ሳይሰጠው መናፍቅ ነው ብለው ብዙ ጫና አድርገውበታል።” ሲል ለአውጣኪ ትክክለኛ መሆኑን ለማስረዳት ሞክሯል።

Saturday, April 7, 2012

የማህበረ ቅዱሳን ከፍተኛ “ግልጽ” አመራሮች “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ተለውጠውብናል” ሲሉ አማረሩ

Click here for PDF
  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም “ደግሞ ምን ልታደርጉ መጣችሁ?” ብለዋቸዋል 

በየድረገጾቹ ስማቸውን ክፉኛ እያብጠለጠለ፣ ከስልጣናቸውን እንዲለቁም ልዩ ልዩ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ እየነዛባቸው በህዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ እንዲጠሉ በማድረጉ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ማህበረ ቅዱሳን፣ በትናንትናው ዕለት ከፍተኛ አመራሮቹን ወደብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ልኮ እንደነበረ የቤተክህነት ምንጮቻችን ገለጹ። ማህበሩ ከመንግስት ፖለቲከኞች በኩል አለኝ የሚለውን አቶ ካሳሁንን ጨምሮ ሌሎቹንም የማህበሩን ስውር ሳይሆን ግልጽ አመራሮች ወደቅዱስነታቸው የላከው፣ ቅዱስነታቸውን ለመውቀስ ነው ተብሏል።

በዚሁ መሠረት አመራሮቹ ቅዱስነታቸው እንደ ከዚህበፊቱ እንዳልሆኑላቸውና እንደተለወጡባቸው፣ እየራቋቸውም መሆኑን በተለመደው መቅለስለስ ለቅዱስነታቸው ያስረዱ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት ለማህበሩ እንቅስቃሴ ከማንም በላይ የቅዱስነታቸው ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን አበክረው አስረድተዋቸዋል።

ቅዱስነታቸውም ከማህበሩ የቀረበባቸውን ወቀሳ ካዳመጡ በኋላ፣ “ለመሆኑ ምን ልታደርጉ መጣችሁ? በየዌብሳይቱ፣ በየጋዜጣውና በየመጽሄቱ ታስተላልፉት የነበረውን ሀሜታችሁንና ስድባችሁን ጨረሳችሁ ወይ? አሁን ደግሞ እኔን ይዛችሁ ምን ልትሰሩ አስባችሁ ነው የመጣችሁት?” በማለት ለማህበሩ አመራሮች ተግሳጽ አዘል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል። የማህበሩ የክፋት አሰራር በእርሳቸው ላይ ምንም ሊያደርጋቸው እንደማይችልና የቤተክርስቲያኒቱ መሪ አድርጎ ያስቀመጣቸው አምላክ ፍቅሩንና ጥበቃውን እንዳላራቀባቸውም ቅዱስነታቸው ሳያስገነዝቡ እንዳላለፉ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

Friday, April 6, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን አቡነ ፋኑኤልን “አወገዘ”

Click here to read in PDF
ውግዘት በኪሴ አለማወቅ በመቅደሴ፤ ተንኮል መነሻዬ ለግፍ መኖር መድረሻዬ እያለ የግብር አባቱን የዲያብሎስን ጸሎት ሳይታክት የሚጸልየው ማህበረ ቅዱሳን ከደርብ በላይ ተንጠራርቶ በጥቁር ራስ፣ ጳጳስ አውግዣለሁ አለ። 

“የሀገረ ስብከት መዋቅር ለድርድር አይቀርብም” በሚል ርእስ የማህበሩ የአሜሪካ ክንፎች ባወጡት ቅጥር ዘለል መግለጫ ለሊቀጳጳስ ለመታዘዝ የማይፈልጉ መሆናቸውንና የራሳቸውን የንግድና የፖለቲካ ስብስብ “ሀገረ ስብከት” ሲሉ በመጥራት ለድርድር እንደማያቀርቡት ተናግረዋል።

እንደ አበደ ውሻ በየእስቴቱ እየተክለፈለፈ ባልገባው ክርስትና ላይ በቅጡ በማያውቀው የቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ላይ ሲዘላብድ በመካሪ በአስመካሪ ተው ሲባል አልሰማ ያለውንና በአድመኝነቱ የታወቀውን መስፍን የተባለውን የድሮ ዶክተር የክብር «ክህነት» በመሻራቸው ማህበሩ ያለ መለኪያ የጠጣው አብሾ እብደቱን ቀስቅሶበት ታላቁን አባት አቡነ ፉኑኤልን በዘወርዋራ መንገድ አውግዣለሁ ማለቱ ብዙዎችን አስደንቆዋል።

Wednesday, April 4, 2012

በፎርጅድ ክህነት ሲያወናብድ የነበረው ማቁ ዶ/ር መስፍን ተገኝ “ክህነቱን” ተገፈፈ፣ ከአገልግሎትም ታገደ

 Click here for PDF
የማህበረ ቅዱሳን ዋናዎች ከሚባሉትና በሰሜን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመገንጠል “ቤተክርስቲያንን” እንደ ኪዎስክ እየከፈቱ በሰሜን አሜሪካ ቤተክርስቲያናችን እንድትከፋፈል ትልቅ ስራ እየሰሩ ካሉት ባለፎርጅድ ክህነት የማህበረ ቅዱሳን ሰዎች አንዱ የሆነው ዶ/ር መስፍን ተገኝ፣ ለጊዜው ከየት እንዳመጣው ያልታወቀው “ክህነቱ” መገፈፉን አባ ሰላማ ድረገጽ ዘገበ። ድረገጹ ይፋ ያደረገው የማገጃ ደብዳቤ አክሎም ዶ/ሩ የቤተክርስቲያን አባቶችንና ምእመናንን ለማለያየትና ለማጋጨት አድማ በማነሳሳትና በመቀስቀስ የተጠመደበትን “አገልግሎቴ” የሚለውን አጋንንታዊ ተግባሩን እንዳይቀጠል እግድ እንደጣለበት ይፋ አድርጓል። 

ዶ/ሩን ያገዱት ማህበረ ቅዱሳን ከምንኩስና እስከ ጵጵስና፣ ከሀዋሳ እስከ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ድረስ ያሳደዳቸው አሁንም የሚያሳድዳቸው ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው። ብፁዕነታቸው ከዚህ ቀደም ከሀዋሳ ለቀው በነበረበት ጊዜ የትኛው ሀገረ ስብከት ቢመደቡ ይሻላል ተብለው ቢጠየቁ፣ “ማህበረ ቅዱሳን የሌለበት” እንዳሉ ይነገርላቸዋል። ለዚያም ነው የሰዋስወ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ሆነው ተሾመው የነበረው። ከዚያም በሰሜን አሜሪካ የካሊፎርኒያና የዋሽንግተን ዲሲ ሊቀጳጳስ ሆነው ሲሾሙ ማህበረ ቅዱሳን ውጪ ባስቀመጣቸው ወኪሎቹ በእነ ዶ/ር መስፍንና በነብርሃኑ ጎበና የተለመደውን ተቃውሞ በማስነሳት በየድረገጾቹ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ያወጀባቸው መሆኑ ይታወቃል።

Monday, April 2, 2012

ከዋልድባው ጉዳይ በስተ ጀርባ የአቡነ ሳሙኤል እጅ እንዳለ እየተነገረ ነው


               Click here for PDF:Waldeba
           ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግስት ሊሰራ ያሰበውን የልማት ስራ መነሻ በማድረግና በሃይማኖታዊ ሽፋንነት በመጠቀም ማህበረ ቅዱሳን በውጪ ካሉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እያጋጋለ ካለው የፖለቲካ አጀንዳ ጀርባ አባ ሳሙኤል እንዳሉ እየተነገረ ነው። የቀድሞው የዋልድባ መነኩሴና የዛሬው የልማት ኮምሽን ጳጳስ አባ ሳሙኤል፣ በጉዳዩ ላይ የዋልድባን መነኮሳት በማነሳሳትና ከቪኦኤና ከሌሎችም አካላት ጋር የሚገናኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት፣ በሰልፍ መልክ ወደጠቅላይ ቤተክህነት እንዲመጡና ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ በማድረግ፣ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ለጳጳሱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ሲናገሩ ተሰምተዋል። ይህን እያደረጉ ያሉትም በአቡነ ጳውሎስ ላይ ተቃውሞ እንዲነሳ ለማድረግና ተቃውሞው ተጋግሎ ከቀጠለና እርሳቸውን በአመጽ ከመንበራቸው ማስነሳት ከተቻለ በእርሳቸው እግር እተካለሁ የሚል ቅዠት ስላላቸው ነው ይባላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ድጋፍ እየሰጣቸው ያለው ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ 

           ማህበረ ቅዱሳንንና አባ ሳሙኤልን ያገናኛቸው አጀንዳ ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን፣ የቤተመንግስቱንም የቤተክህነቱንም ስልጣን ጠቅልሎ መያዝ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። አባ ሳሙኤል ከልባቸው አልወጣ ያለውን ፓትርያርክ የመሆን ቅዠት ለማሳካት እየወደቁ እየተነሱ፣ የተለያዩ ክፍተቶችን እየተጠቀሙ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ላይ መፈንቅለ ፓትርያርክ ለማካሄድ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ የዋልድባን ጉዳይ ሽፋን በማድረግ እንደተለመደው አባ ጳውሎስን መታገላቸውን ቀጥለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ ከመንግስት ጋር ሳያጋጫቸው እንደማይቀር የአንዳንዶች ግምት ነው፡፡