Wednesday, April 4, 2012

በፎርጅድ ክህነት ሲያወናብድ የነበረው ማቁ ዶ/ር መስፍን ተገኝ “ክህነቱን” ተገፈፈ፣ ከአገልግሎትም ታገደ

 Click here for PDF
የማህበረ ቅዱሳን ዋናዎች ከሚባሉትና በሰሜን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመገንጠል “ቤተክርስቲያንን” እንደ ኪዎስክ እየከፈቱ በሰሜን አሜሪካ ቤተክርስቲያናችን እንድትከፋፈል ትልቅ ስራ እየሰሩ ካሉት ባለፎርጅድ ክህነት የማህበረ ቅዱሳን ሰዎች አንዱ የሆነው ዶ/ር መስፍን ተገኝ፣ ለጊዜው ከየት እንዳመጣው ያልታወቀው “ክህነቱ” መገፈፉን አባ ሰላማ ድረገጽ ዘገበ። ድረገጹ ይፋ ያደረገው የማገጃ ደብዳቤ አክሎም ዶ/ሩ የቤተክርስቲያን አባቶችንና ምእመናንን ለማለያየትና ለማጋጨት አድማ በማነሳሳትና በመቀስቀስ የተጠመደበትን “አገልግሎቴ” የሚለውን አጋንንታዊ ተግባሩን እንዳይቀጠል እግድ እንደጣለበት ይፋ አድርጓል። 

ዶ/ሩን ያገዱት ማህበረ ቅዱሳን ከምንኩስና እስከ ጵጵስና፣ ከሀዋሳ እስከ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ድረስ ያሳደዳቸው አሁንም የሚያሳድዳቸው ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው። ብፁዕነታቸው ከዚህ ቀደም ከሀዋሳ ለቀው በነበረበት ጊዜ የትኛው ሀገረ ስብከት ቢመደቡ ይሻላል ተብለው ቢጠየቁ፣ “ማህበረ ቅዱሳን የሌለበት” እንዳሉ ይነገርላቸዋል። ለዚያም ነው የሰዋስወ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ሆነው ተሾመው የነበረው። ከዚያም በሰሜን አሜሪካ የካሊፎርኒያና የዋሽንግተን ዲሲ ሊቀጳጳስ ሆነው ሲሾሙ ማህበረ ቅዱሳን ውጪ ባስቀመጣቸው ወኪሎቹ በእነ ዶ/ር መስፍንና በነብርሃኑ ጎበና የተለመደውን ተቃውሞ በማስነሳት በየድረገጾቹ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ያወጀባቸው መሆኑ ይታወቃል።

ሳኦል የዳዊት የእድሜ ልክ ጠላት እንደሆነ ሁሉ ማህበረ ቅዱሳንም የብፁእ አቡነ ፋኑኤል የእድሜ ልክ ሊባል ለሚችል ጊዜ ጠላታቸው ሆኖ እያሳደዳቸው የሚገኝ ሲሆን፣ በአሳዳጅነቱ ገፍቶበትና አሜሪካ ድረስ ተከትሎ ብዙ ሊዋጋቸው ሞክሯል። ግን አልተሳካለትም። በዚህ እጅግ የተበሳጨው ማህበሩ ለዶ/ሩ ተልእኮ ሰጥቶ የመጨረሻው የሚባለውን ጥይት ለመተኮስ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጪ መንቀሳቀሱ ታውቋል። ብፁዕነታቸውም “ቀሲስ” ተብዬውን ዶክቶር ከክፉ ድርጊቱ እንዲታቀብ ማስጠንቀቂያ መጻፋቸው ታውቋል። ዶክተሩ ግን በእንቢተኝነት የገፋባት ሲሆን ብጹዕነታቸውንም በመቃወም የቤተክርስቲያንን ቀኖና ጥሷል። በዚሁ መሠረት ፍትሕ መንፈሳዊን ጠቅሰው ባላቸው ስልጣንና የቤተክርስቲያን ታላቅ ሃላፊነት የዶክተሩን የመንደር ውስጥ ክህነት ገፈው ከአገልግሎት አግደውታል። 

በብፁዕነታቸው የተወሰደው ይህ እርምጃ እጅግ የሚደገፍ የሚበረታታና በህገ ቤተክርስቲያን የተፈጸመ በመሆኑም ተገቢ ነው። በአገር ውስጥም ቤተክርስቲያንን እያተራመሱና እያወኩ የሚገኙትን የመንደር ውስጥ ህግወጥ ተሿሚ የማህበረ ቅዱሳን “ዲያቆናት”፣ “ቀሳውስት” “ሊቀ ምንትሶች” ከየት እንደመጣ የማይታወቀውን ለቅዳሴ ሳይሆን ቤተክርስቲያንን ለማወክ ሽፋን ያደረጉትን “ሥልጣነ ክህነታቸውን” እና “ማእረጋቸውን” መግፈፍ የሚገባ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ። ማህበሩ ህዝቡን የሚያታልልበት አንዱ መንገድ ይህ ስለሆነ፣ ከየትም ያምጣው ከየት “ክህነትህ ህገወጥ ነው” ያለውን ሁሉ ከማጥቃት እንደማይመለስ ከዚህ ቀደም አባ ሠረቀን በመክሰስ ያሳየ መሆኑ የሚታወስ ነው። እንደ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እነዚህን በቤተክርስቲያን ስርአተ ትምህርት ውስጥ ሳያልፉና አፋቸውን በቤተክርስቲያን ቋንቋ ሳይፈቱ፣ ፎርጂድ ዲያቆናት ቀሳውስትና ሊቀ ምንትሶችን ማገድና አለን የሚሉትንና ምንጩ ያልታወቀውን “ስልጣነ ክህነት” መግፈፍ ያስፈልጋል።

14 comments:

  1. forged association forged kehenet and mafiya job. this is called mk

    ReplyDelete
    Replies
    1. and yet don't tell us about Kessiss Dr. Mesfin we know him and he is not like as you said, let God bless his job and outstanding believe in God forever.

      Delete
  2. ante yalezih inforemation yelehem lela yemetaqerebew????????

    ReplyDelete
  3. Ewunetim Awude Miheret. Yih Talak Sibiket new. Awude miheret MK kalarefe sew yasenakilal eyalin yasikemetinew document bemahiberu abalat lay bezih blog yiwotal erefuuuuuuuuuu belachew. Be ewunetu enkuan kahin mimen mehon ayichilum. Mimen lemehon amagne mehon silemiteyik...Please MK members in USA cool down ahun yenanite kifu zemen alikual EGZIABHER HIZIBUN YEMIASARIFIBET ZEMEN NEW. ANIGILETEW ZEMAWINETACHIHUN. eHITIMAMACH DEFRO YAMAGETE YETEKESESE KESIS TEBIYE usa YE mAHIBERU aMERAR usa ENDALE TAWIKALACHIHU????????wE WILL POST IT WITH EVIDENCE. Please lemengaw tetenkeku

    Tinant Zemari, Sebaki, Likawinte bete christian asadedachihu. Zare degimo ye sinodos Abal egziooooooooooooooooooooooooooooooooooo. Mesfin ayamiribihim neber khinetu wondime enkuanim kerebih. Eneziawim Abune Fanuel Gelageluh. Ahunim Birhanu Gobenan, Belachew Workun ena yared Gebre medhinim bigelagilochew eseyew bilew sunday school abal bihonu. Timihirtum yele, Tidarachewim lekhinet yemayihon, enersum set siamagitu yenoruuuuuuuuuuuu. Oh Geta hoy tegeletina talakinetih yitayyyyyyyy, Amennnnn!!!

    Ehite Mariam Negne, former MK and victim of these folks. Menfesawi mesilewigne keribe kibren yatahu Ehitachihu. Bene Sebeb Ehitem victim nat...Yih sim lematifat sayihon Enersum Selemiawikugne new Sira Amerar Tenegagirobet yalef new. Egzer lib Yistachew bekirbu bemetsehaf yigeletallllll. Yane Aba Fanuel Sayihonu Enersu Eyasirekebu nisiha yigebaluuuuu

    ReplyDelete
    Replies
    1. oooooooooweeeeeeeeeee make it fast pls we need to know it. this people are ugly arogants

      Delete
  4. ለመኾኑ እናንተስ "እስኪ አቡነ ፋኑኤል ያለፉበትን የቤተ ክርስቲያን ሥርዐተ ትምህርት ንገሩን" ብትባሉ የጽድቅ ባለቤት እግዚአብሔርን ሳታሳዝኑ የምትሰጡት መልስ ምንድር ነው? ለቀጠፋ ጥቅስ እንደኾነ ዛሬ ትንሽ ትልቁ ተክኖበታል። ወዳጆቼ ባኹኑ ጊዜ ቤተ ክሲያናችን የምትገኝበት የችግር አረንቋ ጥልቅ እና ሰፊ ነው። ከወዲያ ወዲህ ከወዲህ ወዲያ ደንጊያ መወራወር ሳይኾን ረጋ ብሎ ማሰብን ተቻችሎ መወያየትን ይጠይቃል። ባካችኹ፣ ባካችኹ፣ ባካችኹ። "አርመምኩ ለሠናይ" ብሎ አንገቱን ደፍቶ በሚኖር ምእመን ዐይንና ጆሮ አትጫወቱ፤ ልቡንም አታድሙት። ረ ስለ እግዚአብሔር! ረ ስለ ወላዲተ አምላክ!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ወንድም ይሔንን ምክር ለማቅ ብትሰጥ በእጅጉ ጥሩ ነው። በድረ ገጾቻቸው ውሸትን ሐሜትንና ተራ ስድብን የጀመሩት ያስፋፉትና እስካሁንም ያስፋፉት እነርሱ ናቸው። እነ አውደ ምህረትማ የሆነውን ሆነ የሚሉ ብሎጎች ናቸው። ይህም ቢሆን ማቅ በድረ ገጹ ሕዝብን ማደናገር ውሸቱንና ሐሜቱን ከተወ እውነትን ተመርኩዞም ቢሆን ምላሽ መስጠቱ የሚቀር ይመስለኛል። እነርሱ የሌለውን የሌላውን ገመና እናውጣ ስላሉ እኮ ነው የእነርሱ እውነተኛ ገበና መውጣት የጀመረው። ስለዚህ አጥብቀህ ማቅን ምከር እርሱ ከሰማህ እነ አውደ ምህረት የሚያስቸግሩህ አይመስለኝም። ማቅ ይጩህ እናንተ ዝም በሉ ግን አይሰራም።

      Delete
  5. እንደ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እነዚህን በቤተክርስቲያን ስርአተ ትምህርት ውስጥ ሳያልፉና አፋቸውን በቤተክርስቲያን ቋንቋ ሳይፈቱ፣ ፎርጂድ ዲያቆናት ቀሳውስትና ሊቀ ምንትሶችን ማገድና አለን የሚሉትንና ምንጩ ያልታወቀውን “ስልጣነ ክህነት” መግፈፍ ያስፈልጋል።

    ReplyDelete
  6. ይድረስ ለብጹ ቅዱስ አቡነ ፋኑኤል

    በቅርቡ ካህናትን ለማስፈራራት ተንሳስተው የጻፉትን ደብዳቤ ቁጥር ሀ\ስ\24\04 በተለያዩ ድረ ገጾች አይች አስተያየትና ጥያቄ ላቀርብ ክርስቲያናዊ በሆነ መንፈሳዊ ግዴታ ተገደድኩ።

    አይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቁንጮዎች፤ ምነው ቤተክርስቲያኒቱን ካለችበት ፈተና ለማውጣት ብትጥሩ።
    አሁን ይህ ድርጊት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ይጠቅማታል? ምእመናን አባትን በማክበርና የአዋሳውን ችግር ላለመድገም ብለን ዝም ብንል ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል
    እንደተባለው ጳጳሱ እየጮሁ አላስቀምጥ አሉን። ከእንግዲህስ ወዲያ ዝምታው እየከበደን ነው።

    ብጹእነትዎ እስኪ የሚከተሉት ጥያቄወች የእርስዎን መምጣት በጉጉት እየጠበቅን ላለነው ለምእመናን ይመልሱልን።


    ፩. ዛሬ እርስዎ ስልጣንዎን በመጠቀም እያስፈራሩአቸውና እየወነጅሉአቸው ያሉት ካህናት ከላይ በተዘረዘሩት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የእርስዎን መምጣት
    በጉጉት እየጠበቅን ያለነወችን ምእመናን አሰባስብው ቀደም ብሎ በብጹእ አቡነ አብረሃም የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ በተመሰረተው ሃገረ ስብከት
    ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና በመጠበቅ በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ስር በመሆን ምእመናን እንዳይበተኑና ቤተ ክርስቲያ
    እንዳትበደል በማገልገል ላይ ያሉ መሆናቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉን?
    እርስዎን ሊጠቅም የማይችል ድርጊት በእነዚህ አባቶች ላይ ባይፈጽሙ መልካም ነው።


    ፪. ለመሆኑ ይህንን ውሳኔ ሲወስኑ ከየትኛው መንበር ላይ ቁጭ ብለው ነው


    ፫. በብጹእ አቡነ አብረሃም መልካም አባታዊ መሪነት የተገዛውንና በቅዱስ ሴኖዶስ የሚታወቀውን የሃገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ለምን አልተረከቡም?


    ፬. በቅዱስ ሴኖዶስ የታወቁትንና ሊቀ ጳጳስ ተመድቦላቸው በብጹእ አቡነ አብረሃም ይተዳድሩ የነበሩትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አብያተ ክርስቲያናት ለምን አልተረከቡም?

    ፩ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ባልቲሞር

    ፪ ምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሌክሳንደሪያ

    ፫ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

    ፬ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ሉዊቪል

    ፭ አንቀጸ ምህረት በዓታ ለማርያም ሻርለት

    ፮ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አትላንታ

    ፯ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ወአቡነ አረጋዊ

    ፰ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ታምፓ

    ፱ ደብረ ዕንቁ ቅድስት ማርያም ሜምፊስ

    ፲ ደብረ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ካንሳስ ሲቲ

    ፲፩ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኦክላሆማ ሲቲ

    ፲፪ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ቨርጂኒያ

    ፲፫ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ቨርጂኒያ ቢች


    ፭. ለምንስ በቪ.ኦ.ኤ በሰጡት መግለጫ "አሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት መተዳደሪያ ደንብ የላቸውም፣ ሃገረ ስብከት የለም" አሉ?

    የእኛ የምንጠቀመው መተዳደሪያ ደንብ ቃለ አዋዲ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከቃለ አዋዲ የተለየ እርስዎ የሚያውቁት መተዳደሪያ ደንብ አውጥታለች?


    ፮. እርስዎ ከመምጣትዎ በፊት የሃገረ ስብከቱ አስተዳዳሪ የነበሩትን ብጹእ አቡነ አብረሃምን ለምን ሸሹ ለምን የርክክብ ስርአት አልተደረገም?

    ፯ በግንቦቱ የቅዱስ ሴኖዶስ ምላተ
    ጉባኤ ላይ ከብጹእ አቡነ አብረሃም ጋር በግንባር ለመወያየት ፈቃደኛ ነወት?


    ፰ በአሁኑ ሰዓት እርስዎ እየመራኋቸ ነው የሚሏቸውን አብያተ ክርስቲያናት ስምና ቦታ በዝርዝር ለምእመናን ቢያስረዱን?



    ቅዱስ እግዚአብሔር መልካም እረኛ የሚያደርግና መልካሙን መንገዱን እንዲገልጽልዎ እየጸለይኩ መልስዎን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
    ያቅርቡልኝ ስል በጥህትና እጠይቃለሁ።


    ግልባጭ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቁንጮ ለሆነው ቅዱስ ሴኖዶስ::

    ReplyDelete
  7. Mk stands for monkosat killer.

    ReplyDelete
  8. mk kefu zare new e/re yatefawe

    ReplyDelete
  9. Wushet !!!!!!!!!!!!! all you said is false ! even if you said ke kihnetu taged that is fine but you said Forged how come he was serving with out a licence tell me he is a doctor ! to be honest how come he cheat God be couse can do his bussines with proffission ! how come ? False False information turn to your hear my dear !

    ReplyDelete
  10. yeweshete kuate,beweshe satenailene teketachehuale

    ReplyDelete
  11. ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያናችን የመጨረሻው አካል ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በታወቀ መተዳደሪያ ደንብ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ያሰማራው እውተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ማኅበር ነው፡፡

    ReplyDelete