Saturday, April 7, 2012

የማህበረ ቅዱሳን ከፍተኛ “ግልጽ” አመራሮች “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ተለውጠውብናል” ሲሉ አማረሩ

Click here for PDF
  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም “ደግሞ ምን ልታደርጉ መጣችሁ?” ብለዋቸዋል 

በየድረገጾቹ ስማቸውን ክፉኛ እያብጠለጠለ፣ ከስልጣናቸውን እንዲለቁም ልዩ ልዩ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ እየነዛባቸው በህዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ እንዲጠሉ በማድረጉ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ማህበረ ቅዱሳን፣ በትናንትናው ዕለት ከፍተኛ አመራሮቹን ወደብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ልኮ እንደነበረ የቤተክህነት ምንጮቻችን ገለጹ። ማህበሩ ከመንግስት ፖለቲከኞች በኩል አለኝ የሚለውን አቶ ካሳሁንን ጨምሮ ሌሎቹንም የማህበሩን ስውር ሳይሆን ግልጽ አመራሮች ወደቅዱስነታቸው የላከው፣ ቅዱስነታቸውን ለመውቀስ ነው ተብሏል።

በዚሁ መሠረት አመራሮቹ ቅዱስነታቸው እንደ ከዚህበፊቱ እንዳልሆኑላቸውና እንደተለወጡባቸው፣ እየራቋቸውም መሆኑን በተለመደው መቅለስለስ ለቅዱስነታቸው ያስረዱ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት ለማህበሩ እንቅስቃሴ ከማንም በላይ የቅዱስነታቸው ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን አበክረው አስረድተዋቸዋል።

ቅዱስነታቸውም ከማህበሩ የቀረበባቸውን ወቀሳ ካዳመጡ በኋላ፣ “ለመሆኑ ምን ልታደርጉ መጣችሁ? በየዌብሳይቱ፣ በየጋዜጣውና በየመጽሄቱ ታስተላልፉት የነበረውን ሀሜታችሁንና ስድባችሁን ጨረሳችሁ ወይ? አሁን ደግሞ እኔን ይዛችሁ ምን ልትሰሩ አስባችሁ ነው የመጣችሁት?” በማለት ለማህበሩ አመራሮች ተግሳጽ አዘል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል። የማህበሩ የክፋት አሰራር በእርሳቸው ላይ ምንም ሊያደርጋቸው እንደማይችልና የቤተክርስቲያኒቱ መሪ አድርጎ ያስቀመጣቸው አምላክ ፍቅሩንና ጥበቃውን እንዳላራቀባቸውም ቅዱስነታቸው ሳያስገነዝቡ እንዳላለፉ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

በማህበሩ ቆስቋሽነትና በሃይማኖት ሽፋን በተለያዩ ቦታዎች የተነሳው ብጥብጥና ረብሻ በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ የተናገሩት ቅዱስነታቸው፣ እየሆነ ያለው ሁሉ እንደ ከዚህ በፊቱ በቸልታ የማይታለፍ መሆኑን ለአመራሮቹ ነግረዋቸዋል ተብሏል። “ትማራላችሁ፣ ትሻሻላላችሁ ብለን ነው እንጂ የምታደርጉት ነገር ሁሉ ከማንም የተሰወረ አይደለም።” ሲሉም ማህበሩ በስውር እየሰራ ያለውንና በቤተክርስቲያኒቱ ብሎም በአገር ላይ ብጥብጥ ለመፍጠር እየሄደበት ያለውን አደገኛ አካሄድ ሁሉ እንደሚያውቁ ገልጸውላቸዋል።

የማህበሩ ሰዎች ነጻ የሆኑ ሲመስላቸው ብቻቸውን ይሮጡ እንደነበርና እንደእባብ ያገኙትን ለመንደፍ እንደሚሽሎከለኩ የተነገራቸው ሲሆን፣ ከሚያደርጉት አንዳንድ ህገወጥ እንቅስቃሴ አንጻር ስርአት እንዲይዙ አስገዳጅ ሁኔታ ሲፈጠርባቸውና ከማንም እንዳልተሰወሩ ሲገባቸው፣ እንደማያዋጣቸውም ሲያውቁ ደግሞ ስልታዊ ማፈግፈግ በማድረግ እንደሚቅለሰለሱ፣ በዚህ መንገድ መጓዝ የትም እንደማያደርሳቸውና እንደማያዋጣቸው ተነግሯቸዋል ተብሏል።

ማህበረ ቅዱሳን “ድል የቀናው” ሲመስለው ቅዱስነታቸውን ከመዝለፍና ከማዋረድ እንደማይመለስ በየድረገጾቹም ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደሚከፍትባቸው ከዚህ ቀደም ካደረጋቸው ከፍተኛ ቅስቀሳዎች መረዳት ይቻላል። በዚህ ዓመት እንኳ “የአቡነ ጳውሎስ ገድል” እንዲሁም “የፓትርያርክ ጳውሎስ ቁማርና የቤተክርስቲያን ተስፋበሚሉ አርእስቶች “አንድ አድርገን” የተባለው የማህበሩ ድረገጽ ያወጣውን አባት አዋራጅ ጽሁፍ መጥቀስ ይቻላል።

ማህበረ ቅዱሳን ቀኑ የጨለመበት ሲመስለው ደግሞ እየተቅለሰለሰ ወደ ቅዱስነታቸው በመቅረብ የልቡን በልቡ ይዞ ለሚሠራው ስራ ቅዱስነታቸው ቀኝ እጃቸውን እንዲሰጡት ይማጸናል። ትናንት ያደረገው የዚህ አካሄድ አካል መሆኑ ታውቋል።

በዚህ ወቅት ማህበሩ ምን እያደረገ ነው? የሚለውን ለማወቅ ድረገጾቹን መጎብኘት ብቻ በቂ ነው። በዚህ ወቅት የዝቋላ ተራራ ተቃጠለ አገር ይያዝልኝ፤ ዋልድባ ተደፈረ አገር ይያዝልኝ እያለ በአሜሪካ ካሉ ስውር አመራሮች ጋር በመቀናጀት ሰፊ የፖለቲካና የንግድ ስራ እየሰራ ነው። የብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ትእዛዝ አልቀበል ብሎ በጥፋቱ ያገዱትን “የክብር ቄስ” የመስፍን ክህነት መገፈፉን ተከትሎ ብፁዕነታቸውን አውግዟል። በዚህ ነገሮችን ሁሉ አጡዞ ጫፍ ባደረሰበት ወቅት አመራሮቹ እየተቅለሰለሱ ወደ ቅዱስነታቸው የቀረቡት ታዲያ ከሰሞኑ አጠናክረው ከዘመቱበትና አጣብቂኝ ውስጥ ከገቡበት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው በስልት ለማምለጥ እንደሆነ ተገምቷል።

26 comments:

  1. Shame on you,
    Does "Ande Adirgen" belong to Mahibere Kidusan?

    You are false accuser, a wolf in a sheep skin.

    ReplyDelete
    Replies
    1. ከበደ ከ4ኪሎApril 8, 2012 at 8:11 AM

      አይደለም እንዴ? ውይ አላወቅንም ነበር እኮ!! ይልቅ ራስህን አታጃጅል። እውነቱን ውላችንም እናውቀዋለን። ለዛውም ለዛ ቢስ ብሎጉ ነው።

      Delete
  2. Gov. and betkinet must have taken series action to demolish mk last for ever. Ato. kasahun informed to all gov. official document to mk.he is uncle of kassuelala that why he got the position on the contaray he did not qualified to do the current position.

    ReplyDelete
  3. ማቅ የቤተክርቲያን ጠላት ነው።

    ReplyDelete
  4. እውነት ግን ምን ሊያደርጉ ሄዱ? እሳቸውን ከአባ ሳሙኤል ጋር በመሆን ለመጣል ደፋ ቀና የሚሉት እነርሱ ናቸው። ሌላ ሸር አስበው ይሆነናል እንግዲህ

    ReplyDelete
  5. simple and clear why you are against MK and exposing falasies which is very far from the fact. Even you can't have moral to say any thing about MK.
    You are false accuser, a wolf in a sheep skin.you are known from your speach, like your interest about today's church abuse.
    Say what you says
    God with MK

    ReplyDelete
  6. Betam yemtsazenu woregnoch nachehu dgmo betkrstian lemafres ytenesachehu sewoch endhonacheu kehunetacheu yastawokal enante eneman nachehu lebetkrstian men argachu new mahbere kedusanen yemtwoksut betam maferia nachu betekrstian yemades alamachu seltawokebachu yemthonuten atacheu lebona yestachehu BETAM GEN WOREGNOCH NACHEHU!!!!!!!!

    ReplyDelete
  7. ማኅበሩ ውስጥ ያሉ የተወሰኑ ሰዎች በጣም ቅናተኛና መሰሪ ናቸው ግዚያብሄር ይቅር ይበላቸሀው፡፡

    ReplyDelete
  8. don't be foolish any one can judge this and know the truth!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  9. Mastewal yerakachiw nachihu.And nitsuh sew kemebedel yerasin tfat amno memeles yetemerete new. yihuda tifatun amno nsaha bigeba noro yikifat tebabari balhone neber!!!!!!Egziabiher mastewalun yestachihu

    ReplyDelete
  10. who are you?you cant say any thing about mk.God bless mk.aglegelotachewen yetebek.lenanetem lebona yadelachu.

    ReplyDelete
  11. ማህበረ ቅዱሳን የተባለ ህገወጥ ፓርቲ ህገወጥነቱንና ዘረኝነቱን ያረጋገጠው በጣም የገረመኝ በስላሴ ቤተክርስትያን የሚገኘው የደርጉ ጳጳስ ሀውልት ቅርስ ብሎ ሲያስጠግነው ያቡነ ጳውሎስ ደግሞ ጣኦት እያለ ሲሰብክበት በገዛ ራሱ በፃፈው አንብቤ ነው፡፡ አረ ይከ ፓርቲ በተስክናችን ማተራመሱን ትቶ ካርድ ይዞ ምርጫ ቢቀሰቅስ ይሻለዋል፡፡ ለነገሩ በዴሞክራሲ መቸ ያምናል? ምንድን ነው እየሰራ ለው?ቤተከረርስትያን ለፀሎት የመጣውን ምእመን በጠበጠው እኮ አበው በቃዝም ትላላቹ?

    ReplyDelete
  12. ማህበረ ቅዱሳን የተባለ ህገወጥ ፓርቲ ህገወጥነቱንና ዘረኝነቱን ያረጋገጠው በጣም የገረመኝ በስላሴ ቤተክርስትያን የሚገኘው የደርጉ ጳጳስ ሀውልት ቅርስ ብሎ ሲያስጠግነው ያቡነ ጳውሎስ ደግሞ ጣኦት እያለ ሲሰብክበት በገዛ ራሱ በፃፈው አንብቤ ነው፡፡ አረ ይከ ፓርቲ በተስክናችን ማተራመሱን ትቶ ካርድ ይዞ ምርጫ ቢቀሰቅስ ይሻለዋል፡፡ ለነገሩ በዴሞክራሲ መቸ ያምናል? ምንድን ነው እየሰራ ለው?ቤተከረርስትያን ለፀሎት የመጣውን ምእመን በጠበጠው እኮ አበው በቃዝም ትላላቹ?
    ሁለቱም የጀሶ ሀውልቶች ጣኦት ከሆኑ አንድላይ ቅርስ ከሆኑ አንድላይ እንጂ በየተኛው አስተሳሰብ ነው የ 1ዱ ጣኦት ሆኖ የሌላው ቅርስ ሞሆነው? ይክ በዘረኝነት አስተሳሰብ ብቻ ነው፡፡ ማህበሩ እንደ መረጃ ያቀረበው በደርግ የነበሩ ሊቀጳጳስ በባዶ እግራቸው መሄዳቸሀውን ነው! ቡለተኛነትም ብር አለመቅጠራቸውን ነው! ይሁን እንጂ የዛኔ ዘመን ጥሩ በነበረበት ይሰበሰብ የነበረውን መባ የት ያደርጉት ነበር ተብሎ ቢጠየቅ መልሳቸው እዜር ይወቅ፡፡ በደርግ በውጫ ሰአት ክርስትያን የእስላም ስጋ ሊበላ በታወጀበት ብፁአን ጳጳሳት ሲሰዉም አገር ሲለቁም ተመቻችተው ተኝተው የነበሩ ጳጳስ ብፁእ መባላቸው ከፖለቲካ ውጪ ሌላ ምክንያት የነውም፡፡
    ደግሞም እኔ በባዶ እግር መሄዴ ብፁእ ሊያስብለኝ የሚችል ሀይማኖታዊ ይዘት የለውም፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Yihen Yetsafik betam bematawikew neger eyagacheh atikebatir.
      Yemayigenagn neger Atagenagn.
      Ke MK gare bicha bitiwekakes tiru new.
      Abune Teklehaimanoten keyet endemetu endet endeteshomu... bedenib atara...keza judge if you have right.

      Delete
    2. GETA ABZITO YIBARKH, AYEH YIH MAHBER YABEDA MAHBER NEW,

      we have to fight, for truth. this the group of devil mahber is a killer mahber.

      Delete
  13. All of you setasazenu.....

    ReplyDelete
  14. Plaese don.t campaign for mahber campaign for kidist tewahedo you mk yebetekiristianin kibir Atakalilu .

    ReplyDelete
  15. ከላይ ስለ ሐውልትና ስለ ሌባው ማቅ የፃፍከው ሰው፤ እጅግ በጣም ጥሩ አስተውለሃል። እግዚአብሔር
    ለሌሎችም ይህን ማስተዋል እንዲሰጣቸው እንመኛለን። አንተን ግን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ። አሜን።

    ReplyDelete
  16. ከላይ ስለ ሐውልትና ስለ ሌባው ማቅ የፃፍከው ሰው፤ እጅግ በጣም ጥሩ አስተውለሃል። እግዚአብሔር
    ለሌሎችም ይህን ማስተዋል እንዲሰጣቸው እንመኛለን። አንተን ግን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ። አሜን።

    ReplyDelete
  17. አመሰግናለሁ ስለሀውልቱ የፃፍኩት ነኝ፡ ብዙ ትዝብት ታዚቤ አለሁ እኔን ለማግኘት ከፈለጉ lovemetoo68@yahoo.com ብለው ተጨማሪውን ይፃፉልኝ

    ReplyDelete
  18. ነገሮችን ሁሉ አጡዞ ጫፍ ባደረሰበት ወቅት አመራሮቹ እየተቅለሰለሱ ወደ ቅዱስነታቸው የቀረቡት ታዲያ ከሰሞኑ አጠናክረው ከዘመቱበትና አጣብቂኝ ውስጥ ከገቡበት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው በስልት ለማምለጥ እንደሆነ ተገምቷል።
    ግምቱ ትክክለኛ ነው!!
    ቅዱስነትዎ ግን ከእነዚህ መሰሪዎች ይጠንቀቁ እነርሱ(ማ/ቅ) የዘረፉትንና ለአክስዮን ያደረጉትን የቤተክርስቲያን ሀብት ለቤተክርስቲያን ሳይመልሱ መለሳለስ አያስፈልግም፡፡
    ታሪክ ሰሪነትዎን በጥበብ ይቀጥሉበት!!!

    ReplyDelete
  19. ire yihe wisha yehone mahiber meche new arfo yemikemetew,one of the funny thind is hecall himself KIDUS but we know that this group is the sarvant of satan, even some times more than satan himself.

    i hate this the group of satan mahbere irkusan, not kidusan,

    please let me call this mahber"MAHBERE IRKUSAN"

    ReplyDelete
  20. በጣም ይገርማል!! እኔ ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ አቡነ ጳዉሎስን ለማታለል አስበዉ ከሆነ በጣም ተሳስተዋል የማህበራን ምንነትና ማንነት ምዕመኑ አሁን በግልፅ እየተረዳዉ ነዉ ፡፡ አይደለም እስቸዉን አፍንጫቸዉ ስር ያሉትን፤ ሌሎችንም ለማታለል መሞከራቸዉ ለሌሎች ያላቸዉን ንቀት አመልካች ነዉ፡፡

    ReplyDelete
  21. በጣም ይገርማል!! እኔ ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ አቡነ ጳዉሎስን ለማታለል አስበዉ ከሆነ በጣም ተሳስተዋል የማህበራን ምንነትና ማንነት ምዕመኑ አሁን በግልፅ እየተረዳዉ ነዉ ፡፡ አይደለም እስቸዉን አፍንጫቸዉ ስር ያሉትን፤ ሌሎችንም ለማታለል መሞከራቸዉ ለሌሎች ያላቸዉን ንቀት አመልካች ነዉ፡፡

    ReplyDelete