Friday, April 6, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን አቡነ ፋኑኤልን “አወገዘ”

Click here to read in PDF
ውግዘት በኪሴ አለማወቅ በመቅደሴ፤ ተንኮል መነሻዬ ለግፍ መኖር መድረሻዬ እያለ የግብር አባቱን የዲያብሎስን ጸሎት ሳይታክት የሚጸልየው ማህበረ ቅዱሳን ከደርብ በላይ ተንጠራርቶ በጥቁር ራስ፣ ጳጳስ አውግዣለሁ አለ። 

“የሀገረ ስብከት መዋቅር ለድርድር አይቀርብም” በሚል ርእስ የማህበሩ የአሜሪካ ክንፎች ባወጡት ቅጥር ዘለል መግለጫ ለሊቀጳጳስ ለመታዘዝ የማይፈልጉ መሆናቸውንና የራሳቸውን የንግድና የፖለቲካ ስብስብ “ሀገረ ስብከት” ሲሉ በመጥራት ለድርድር እንደማያቀርቡት ተናግረዋል።

እንደ አበደ ውሻ በየእስቴቱ እየተክለፈለፈ ባልገባው ክርስትና ላይ በቅጡ በማያውቀው የቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ላይ ሲዘላብድ በመካሪ በአስመካሪ ተው ሲባል አልሰማ ያለውንና በአድመኝነቱ የታወቀውን መስፍን የተባለውን የድሮ ዶክተር የክብር «ክህነት» በመሻራቸው ማህበሩ ያለ መለኪያ የጠጣው አብሾ እብደቱን ቀስቅሶበት ታላቁን አባት አቡነ ፉኑኤልን በዘወርዋራ መንገድ አውግዣለሁ ማለቱ ብዙዎችን አስደንቆዋል።

አሜሪካ ያለው የእነ ብርሃኑ ጎበና፣ ኤፍሬም እሸቴና መስፍን «ሚጢጢ ሲኖዶስም» አምስት ገጽ ሙሉ በጻፈው የውግዘት ደብዳቤው ብፁዕነታቸውን የተለያዩ የፍትሐ ነገሥትን አንቀጸች በመጥቀስ በሌላቸው ሥልጣን ግዝት መሰል የመልስ ምት ለመስጠት ሞክሯል። 

ሃሳቡ ፖለቲካ የሆነውና አወቃቀሩ ከሃይማኖት ድርጅት ይልቅ የንግድና የፖለቲካ ድርጅት የሚመስለው ማኅበረ ቅዱሳን ከግብር አባቱ ከዲያቢሎስ በተማረው መሠረት ማዘዝን እንጂ መታዘዝን ስለማይወድ አቡነ ፋኑኤል አሜሪካ ከተመደቡ ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የማጥላላት ዘመቻ በማድረግ ሥራ ተጠምዶ እንደቆየ ይታወቃል። አልተሳካለትም እንጂ በአሜሪካ የምትገኘውን ቤተ ክርስቲያን  ለመከፋፈል ያደረገው እንቅልፍ አልባ ጥረት ከሽፏል። 

“ክፉ በምን ተጠልፎ ይወድቃል ቢሉ በገዛ ሀሳቡ” እንደሚባለው፤ ለአቡነ ፋኑኤል አስቦት የነበረው መገለል በራሱ ላይ ሲደርስ በመስፍን ፊት አውራሪነት በየእስቴቱ እየዞሩ ብጹዕነታቸውን ለማስጠላት ቢፍጨረጨሩም ጥረታቸው አፈር መላስ ሆኖባቸው በየብሎጉ ጥላቻ መዝራቱን ቀጥለውበት እንደነበር አይዘነጋም። ነገሩን ሁሉ በጽሞና ሲከታተሉት የነበሩት አባታችንም ተደጋጋሚ ምክርና ተግሣጽ ለፊት አውራሪው መስፍን ቢሰጡትም ካፈርኩ አይመልሰኝ በማለት መደናበሩን ስላላቆመ ያቺኑ የሚመጻደቅባትን የክብር «ክህነቱን» በተሰጣቸው ሥልጣን መሠረት ለመግፈፍ ተገደዋል። 

 «አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ» (1ጴጥ. 2፡16) የሚለውን ጥቅስ በመጥቀስ ብጹዕነታቸውን ለመክሰስ የሞከረው የአሜሪካው ማቅ እንዲህ ያለውን ጥቅስ ለብጹዕነታቸው ከመጻፍ ይልቅ ለእኔ ብሎ ቢያነበው ይበልጥ ይጠቀም ነበር። አርነቱን ከ10 በላይ ብሎጎች ከፍቶ የእውነተኛ አባቶችንና የወንድሞችን ስም በሐሰት በየቀኑ ለማጥፋት እየተጠቀመበት ያለው ማቅ፣ አሁን አባሉ በጥፋቱ «የክብር ክህነቱ» መገፈፉን ተከትሎ ጉዳዩን አቡነ ፋኑኤልን ለማውገዝ መጠቀሙ አስገርሟል።

በአንድ ሌሊት ደርሰው የፍትሐ ነገሥት ሊቅ የሆኑት የተረት አባቱ ኤፍሬምና አንደበተ ለዛዛው ብርሃኑ የተለያዩ የፍትሐ ነገሥትን ጥቅሶች በመደርደር ውግዘት ባይ ነኝ መግለጫቸውን የጥቅስ ደብተር አስመስለውታል። ከሁሉ የሚገርመው ግን «ሁለት ጊዜ የተሾመ ይሻር እንዳልን ሳይሾም ሁለት ሚስት አግብቶ የተገኘ ተሿሚው ሿሚውም ይሻር፡፡» የሚለውን ለመሰረተ ቢስ ግዝታቸው መጥቀሳቸው ነው። ስለ ሁለት ሚስት ስለ ሁለት እጮኛ ከተለያየ ሴቶች ስለመውለድና አስገድዶ ስለ መድፈር ከማኅበረ ቅዱሳን  መሥራች አባላት በላይ ስሙ ሊጠራ የሚችል እንደሌለ እኛም እነርሱም እናውቀዋለን። መቼም ሰይጣን ሊገዛ ሲፈልግ በአንድ ነውር አስሮ መሆኑ እርግጥ ነው። (ይህን ርዕስ ወደፊት በስፋት እንመለስበታለን)

ሌላው የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ አንድ አድርገንም «የአቡነ ፋኑኤል ድርጊት ተወገዘ» በሚል ርዕስ በማስቀመጥ መግለጫውን ለማስተጋባት ሞክሯል። ተንጠራርቶ መንከስ ልማዱ የሆነው ማቅ ትናንት በሰባኪያንና በዘማሪያንን ላይ የጀመረውን ውንጀላና ክስ «ደረጃውን አሻሽሎ» ጳጳስ ወደ ማውገዝ አድርሶታል። እንዲህ የዕውር ድንበሩን እያስኬደ ሁሉን የሚያስነክሰው ጠባዩ ሀይ ባይ እንደሚስፈልገው ታዛቢዎች እየተናገሩ ነው።
ደብዳቤውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ 
  

7 comments:

  1. deneqe nwe bertulen. yehen awre agaletulen

    ReplyDelete
  2. Aye MK tasaferiYalese. Yegalemota SebaYese besegam benebsem eyetegelete new

    ReplyDelete
  3. “አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል” እንደሚባለው እያወቃችሁ እንዳላወቃችሁ ትሆናላችሁ፡፡አውሬ፣ሌባ፣ውሸታም … የሚሉት አገላለጾች ሁሉ ለማህበረ ቅዱሳን ሳይሆን ለእናንተ ይገባል፡፡ልቦና ይስጣችሁ…. የምትጽፉትን እወቁ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. ለማህበረ ቅዱሳንማ ሲያንሰው ነው ራሱን የሰደበ ነው ሰው ሲሰድብ ምን ይጠብቀኛል ብሎ ነው ሽቶ ሊቀባ ተረት ነው እግዚያብሄር ይይለት የቤተክርሰቲያን ጠላት ለዝናው የቆመ በሰው ጸጋ የሚቀና፡፡

      Delete
  4. AYi Mesfin. Endaw Ene Kalimerahuachihu. Lam Baliwalebet Kubet Lekema. Ebakih Wode Libih Temeles. Hagere Sibiket Ena Sunday School Yileyayal. Minale Endeguadegnochih atinteh Master bitiwosid. Beziach Begonderooo MD erasihin DR Eyalih Batikofes. Temar, Temar, Temar WOndime.Menosota Yalemuyah Gebite KIDASSIE - Tiz Yilihal Docteru Kidassie Mariamin Opration adderegat sitibal. Deacon Yechereselih. woy Difretiiiiiiiiii.

    Lela Kuankua atawikum ende TEHADISOOOOOOOOOOOOO. Kenante Yebelete Tehadisooo ABatochin Mitawogizu, Hulunim SIm Yemitisetooo. Ahun Enanite TEHADISOOO Yalalachihut Sebaki, Zemari, Memiria halafi, Likawint, Theologian, Papas, Pathrearch ere man kere? Yemahiberu Abalat Kalihonu. Zare Degimo Dn Hailegiorgis Teshome Sibal " TEHADISOO" ATafirum. Lemin Sibal, Mahiberun Gemigimo Kenante gar Mesirat Betechristianin Mafires new bilochih endetew Hulum betekhinet sew yemiawikew new. Le 14 ametat enaniten lemastekakel ke abatochi ena likawintu gar yelefa dink wondim new. Sile mahiberat, gilesebochin tarik Yemayawera vision yalew talak sew. Bekiribu tinish le anbabian yemihon enawotalen tebikun.

    Eg' r Zendowin Betelo Yitalew, Amen!

    ReplyDelete
  5. በእናንተ ጽሁፍ የሚታለል ማንም የለም፡፡የህጻን ስራ ነው እየሰራችሁ ያላችሁት

    ReplyDelete
  6. be enatachehu erse be erse eyeteblalan eyetewegagezen diablosen ena yeleloch mesakya kemenhon lemen tefat enkuan bensera yeker le EGZIABHER anbabalem!

    ReplyDelete