Tuesday, April 17, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን የጉዞ መርሀ ግብርና አንድምታው

ከተመሰረተ 20 ዓመት ከ7 ወር ከ23 ቀን የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ ዓመቱን በእግር ጉዞ ለማክበር መዘጋጀቱን በየስፍራው በለጠፈውና በየሚዲያው በሚያስነግረው ማስታወቂያ እየገለጸ ይገኛል። መስከረም 4 ቀን 1984 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገረው ማህበረ ቅዱሳን የተመሰረተበትን ቀን ሳይጠብቅና ከቀኑ ሰባት ወራትና 23 ቀናትን አሳልፎ 20ኛ ዓመቱን የምስረታ በዓል ማክበር ለምን አስፈለገው? የሚል ጥያቄን በብዙዎች ዘንድ ፈጥሯል።

ማኅበሩ የማያውቁትንና እርሱም በስም ብቻ ካልሆነ በቀር የማያውቃቸውን የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን ፎቶ ግራፍ የማስታወቂያው ማዳመቂያ ያደረገ ሲሆን፣ ብፁዕነታቸው የማኅበሩ መሥራች አባት ተደርገው እንዲቆጠሩ በስማቸው ብዙ ሲሰራ እንደቆየ ለማወቅ ተችሏል። ብፁዕነታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በ1982 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ሲሆን፣ ማኅበሩ የተቋቋመው ደግሞ ከ2 ዓመት በኋላ በ1984 ዓ.ም ነው።

«ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን ዕድገት አብረን እንስራ!» በሚል መሪ ቃል የእግር ጉዞውን ያዘጋጀው ማኅበሩ፣ መሪ ቃሉ «ለቤተክርስቲያን ዕድገት» ቢልም፣ ዕድገቱ በቤተክርስቲያን ስም ተነግዶ ለማኅበሩ እንጂ ለቤተክርቲያን አለመሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል። ማኅበሩ በዚህ ወቅት የእግር ጉዞውን ያዘጋጀው 20ኛ ዓመቴን ለማክበር ነው ቢልም፣ ከበስተጀርባው ብዙ ዐላማዎችን አንግቧል እየተባለ ነው። የምሥረታ ቀኑ ካለፈ ከ7 ወራት በኋላ 20ኛ ዓመቴን ላክብር ብሎ መነሳቱ በራሱ ያነጋግራል። ማህበሩ ግብር ከፋይ ያለሆነና በመንፈሳዊ ስም የሚያጭበረብር ስግብግብ ነጋዴ በመሆኑ አጋጣሚውን ለከፍተኛ ገቢ ማሰባሰቢያነት ሊጠቀምበት አቅዷልና እያንዳንዱ ተጓዥ ጉዞ ሰነድ የተባለውን በ100 ብር እንዲገዛ እያደረገ ነው። ለዚህም ከ21 በላይ የሆኑ ሰነዱ የሚሸጥባቸውን አድራሾች ያስተዋወቀ ሲሆን፣ እነዚህም የማኅበሩን የወረዳ ማእከላት፣ የግቢ ጉባኤያትንና የሰራተኛ ጉባኤያትን ሳይጨምር ነው።
የእግር ጉዞውን በተመለከተ ለሚመለከተው የቤተክህነትም ሆነ የመንግስት አካል አስቀድሞ አለማሳወቁን ምንጮቻችን ገልጸው፣ ምንአልባት ጉዞው እንዳይካሄድ ቢታገድ፣ የሰበሰበውን ገንዘብ ለማቅለጥ እንዲመቸው ይህን እንዳደረገ የሚናገሩ አሉ።
መስከረም ላይ ተመስርቶ ሳለ ሚያዝያ ላይ 20ኛ ዓመቱን ለማክበር የተነሳው ማኅበሩ፣ ይህን በአጋጣሚ እንዳላደረገውና አሁን ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚታየውን አንዳንድ ሁኔታ ተጠቅሞ የራሱን ጥቅም ለማስከበር እንደሆነ ተገምቷል። ከግንቦቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የእግር ጉዞው መካሄዱ ማኅበሩ በጉዞው የሚሳተፈውን ሰው የራሱ አባል እንደሆነ አድርጎ ለማሳየት፣ ብዙ ደጋፊ ሕዝብ አለኝ ለማለትና በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የተቻለውን ተጽእኖ ለማሳረፍ እንደሆነ እየተነገረ ነው። በተለይ በዚህ ስብሰባ እንዲታዩ በይደር በቆዩት አጀንዳዎች ላይ የእርሱን ጥቅም በሚያስከብር መልኩ እንዲወሰንለት ከዚህ ቀደም ብዙ ገንዘብ አፍስሶ አንዳንድ ብፁዓን አባቶችን እስከማሳሳት ደርሶ እንደ ነበር የሚታወስ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በቅርቡ ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ ማኅበሩ ያሰነሣውን አቧራ ይበልጥ ለማጫጫስና በአሜሪካ ወኪሎቹ በኩል ያስተባበረውን የተቃውሞ ሰልፍ በእግር ጉዞ ስም አገር ውስጥም በመድገም አጋጣሚውን ሊጠቀምበት እንደሚችል የብዙዎች ግምት ሆኗል።
ስለዚህ የሚመለከተው የቤተ ክህነት አካል ሁኔታውን በቅርብ እንዲከታተልና አስፈላጊውን ቁጥጥር እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን።

12 comments:

  1. min new MK lie zemetachihu ?? ???????????

    ReplyDelete
  2. የሌባ ሁሉም ስው ሌባ ይመስለዋል፡፡እኛ ብንሆን እንዲህ አድርገን ብሩን እንበላው ነበር ለማለት ይመስላል፡፡ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ፡፡ከእውነት ጋር መታገል ከባድ ስለሆነ ቢቀርባችሁ ይሻላል፡፡

    ReplyDelete
  3. Men agebachu enante betkrstian lemafres yetnsachu sewoch selaltsakalachu mahberun mekawom becha hone seracheu enante belo krstian.

    ReplyDelete
  4. Ahunima Mahibere Kidusan Ye poletika Dirgijt Mehonu tegeltsowl - teregagitsowal Mahibere Kidusan Menfesaw Mahiber Mesilog Abal Kehonku Berkata ametat honewgal Ahun gin tegeletse Yasazinal ethiopia yetegodachiw beasmesayoch new

    ReplyDelete
  5. Yemtgerm!!! Kebetekrstyan endalelih felatsa yezeh yeqomk,Atsirare betkirsteyan,kirsteyanochin yemtneqif. Kepoletekengochu atbal poletekan sayhon telachana alubaltan endehum mesertawe yehon chibt yalew neger atkebatir. Zim bleh yemtqebzbez tselaye senay neh. egzeabher yegestsachehu!

    ReplyDelete
  6. Please don't be the mouth of the EOTC enemy!

    ReplyDelete
  7. Your name is attractive and tel us that you are the member of EOTC, Your post tel us that you are the member of the enemy of our church!

    ReplyDelete
  8. ሌባ ሁሉም ሰው ሌባ ይመስለዋል፡፡ ይህ ያወራኸው ወሬ የማኀበረ ቅዱሳን ሳይሆን የእናንተና የአለቆቻችሁ ተግባር ነው፡፡ ምክንያቱም በተደጋጋሚ ታይታችኋል ለቤተክርስቲያን ማሰሪያ፣ ለሕክምና፡ ለእርዳታ፣ ለተቸገሩ፣ ለፈረሱ ቤተክርስቲያኖች እያላችሁ የግል ሃብት ስታካብቱ ፎቅ ሰትሰሩ፣ መኪና ሰትገዙ በቤተክርስቲያን ስም የተሰበሰበ ገንዘብ ስትቀራመቱ

    ማኀበረ ቅዱሳንማ የሚሰራውን እያያችሁ ነው እንደናንተ ስላለሆነ ከሆነ ያንገበገባችሁ የሰይጣን ሥራ አይስማማውምና እናንተንም እግዚአብሔር ከማኀበሩ ሕብረት ጋር እንዲቀላቅላችሁ በርትታችሁ ፀልዩ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Ke seytan gar hibret yalew seytan bicha new.

      Delete
  9. ye mogny zefen avevaye new alu hula mk mk keshemoch

    ReplyDelete
  10. አይ የሰው ነገር! ምነው አንዱ በጎ ሲሰራ ሌላው እንቅፋት ይሆናል፡፡ ምን ለማለት ፈልገህ ነው? እንዲህ አይነት አስተያየት ለመስጠት የፈለግከው? ቢሆንስ ኖሮ እንዴት አድርገን ቤተክርስቲያንን እናሳድጋት ማለት ነበረብህ አንተ ግን ‹‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ…››አባቶች እንደሚሉት ሆንክ፡፡ እግዚአብሔር ለሁላችንም ማስተዋሉን ያድለን፡፡ እግዚአብሔር ልቦና ይስጥህ!!

    ReplyDelete
  11. ለተዋሕዶ ልጆች ማንነታችንን ያሳወቁ፤ በክርስቲያናዊ ሕይወት እንድንኖር ያሳዩ፤ በኢትዮጵያዊነታችን ምንጊዜም እንድንኮራ ያደረጉ፧ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለመላው ዓለም ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ያሳወቁ ፧ለዚህ ትውልድ አዲስ ምእራፍ የከፈቱ፤ ማኅበረ ቅዱሳንን ጸንሰው እንዲወለድ መሠረት የጣሉ ቅዱስ አባት ናቸው።

    ReplyDelete