Friday, April 20, 2012

«አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት» የሚለው አባባል “ሕገ መንግሥት” ላይ ብቻ ሳይሆን በክርስትናም ላይ የተቃጣ የጸረ- ክርስቶሱ ሃሳዌ መሲህ አጀንዳ ነው!

                                         በዲ/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
       (ዲ/ን ሙሉጌታ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ተነባቢነት የነበረውና በብዙ እውነተኛ የሰነድ ማስረጃዎች የተደገፈው ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሠይጣን የሚለው መጽሐፍ ደራሲ ነው)

ለመግባባት ያክል የምዕራቡ ዓለም የዕድገትና የስልጣኔ ምስጢር በማውሳት ሐተታዬን ልጀምር:: ለብዙዎቻችን ግልጽ እንደሆነ የምዕራቡ አለም ፖለቲካ ከተቀረው የዓለማችን ክፍል የሕዝብ አስተዳደር የተለየና የላቀ የሚያደርገው ቢኖር የፖለቲካ መሪዎች አስተዋይነትና አርቆ አሳቢነት ለመሆኑ  አያከራክርም:: ለምሳሌ ያክል "የዲሞክራሲ" ተምሳሌት የሆነችውን ሃያልዋ ሀገረ አሜሪካ የወሰድን እንደሆን በተለይ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በየትኛውም መስክ ያለ ተቃናቃኝ በኢኮኖሚውም ሆነ በፖለቲካው መድረክ የበላይነትዋን  እንደያዘች የመዝለቅዋ ምስጢር ስልጣን ላይ የሚወጡትም ሆነ በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉትን የፖለቲካ መሪዎች ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ውጤት ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም:: ይህ ማለት ዲሞክራትም ይሁን የሪፐብሊካን ፓርቲ አቀንቃኝ ሀገራቸው አሜሪካ በዋናነት ልትከተለው በሚገባት ፖሊሲ ላይ የጎላ ልዩነት ቢኖራቸውም የአሜሪካን ሉዓላዊነት እንዲሁም የአሜሪካ ሕዝብ ጥቅም የመጣን እንደሆነ ግን አንዱን ከሌላውን መለየት ፈጽሞ አይቻለንም:: ሀገራዊ ጥቅም በተመለከተ ዲሞክራቱም ሪፖብሊካኑም አሜሪካዊ ነው!! እናማ ከየትም አቅጣ ቢመጡ ጽሐፉን ሲያነቡ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በሰከነ መንፈስና በተረጋገ ልብ እንደሚያነቡት ተስፋ አደርጋለሁ:: 

በያዝነው ሳምንት ከጥቂት ቀናቶች በፊት መሆኑ ነው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በፓርላማቸው ተገኝተው ካደረግዋቸው ንግግሮችና ከተወካዮቹም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ካነሱዋቸው ነጥቦች መካከል ሃይማኖትን በማስመልከት መንግስታዊ ትንታኔአቸውና አቋማቸውን ለፓርላማው ግልጽ አድርገዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ማህበረ ቅዱሳን" ከአልቃይዳ ጋር በማመሳሰልም ገልጸውታል:: እንግዲህ ይህን አገላለጽ/ንግግር ያዳመጠ ሰው አልቃይዳ ማለት ደግሞ ማን ነው? ምንስ ማለት ነው? ብሎ የሚጠይቅ አዋቂ ሊኖር እንደማይችል አምናለሁ::  

አልቃይዳ በብዙሐን የንጹሐን ዜጎች ደም ተጠያቂ: በደም የተነከረ መታወቂያ ያለው: መሰረተ ልማቶችን በቦንብ የሚያጋይ: በአጠቃላይ በንጹሃን ሰዎች፣ በልማት ተቋማት፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ንብረቶች ላይ ያነጣጠረ የሽብር ጥቃቶች የሚፈጽም ጸረ ልማትና በግርግር የሚያምን ሃላፊነት የጎደለው ሃይል ነው:: በአንጻሩ ደግሞ የቅዱሳን ማህበር ሲል ራሱን በቁልምጫ ቋንቋ የሚጠራ:
Ø ለነውሩ መንፈሳዊ ካባ ያጠለቀና የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ፥
Ø ታቦት ተቀርጾለት አምልኮ ብቻ የቀረው ለ20 ዓመታት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ስም ከእምነትዋ ተከታዮች አልፎ በሀገርና በትውልድ ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆና ተቀምጦ ይሄ ነው ተብሎ በቀላሉ የማይነገር ሀብት በሕገ ወጥ መንገድ ያግበስበሰና፥
Ø በብዙዎች የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ልጆች ደም የተጨማልቀ፥
Ø ከቤተ-ክርስቲያን አልፈው ለሀገር የሚተርፍ እውቀት ያላቸውና በጥበብ የተሞሉ የቤተ-ክርስቲያን ልጆች ለስደትና ለግዞት ህይወት የዳረገ: ሀገር ወልዳ እንዳልወለደች የወላድ መሃን ያደረገ፥
Ø የህልውናው ያክል ጸበኛ: አልታዘዝ ባይና አመጸኛ ትውልድ በማፍራት አቻ የማይገኝለት፥
Ø በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ታሪክ ምእመናን ከመሪዎች: አባቶች ከልጆች ጋር እንደ አንድ አካል መደማመጥ ይሳናቸው ዘንድ የአለመግባባትን መንፈስ ያስተጋባ፥
Ø የተለያዩ ያማሩ ስሞች ያሏቸው ድረ ገጾችን በመክፈት በቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ጭምር ሳይቀር  ጦርነት የከፈተ፥
Ø ለምንም ለማንም በማይበጁ ያልተጠኑና ቤተ-ክርስቲያን በሕግ የማታውቃቸው እንግዳ ትምህርት በማሰራጨት ሃይማኖትን የሚበዝር: ትውልድን የሚያደነዝዝ ሰላቢም ነው::
Ø በአጠቃላይ "ማህበረ ቅዱሳን" ክርስቲያናዊ ድርጅት ሳይሆን ጸረ-ክርስቶስ ወንጌል፣ የተደራጀ አጽራረ ጽድቅ፣ መከፋፈልንና ሁከት እንደ አጀንዳ ቀርጾ ነውጥን በመፍጠር ምኞቱን የሚያሳካ ሀገር በቀል የጥፋት ተልእኮ ያነገተ አውዳሚ ማህበር ነው:: 

ራሱን "ማህበረ ቅዱሳን" ሲል የሚጠራ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ጉያ ላይ ተወሽቆ በመንፈሳዊነት ስም ስለ ተቋቋመው መሰሪ ድርጅት በማስመልከት መንግስት የሀገርና የሕዝብን ሰላም የመጠበቅ ግዴታው ነውና በመግቢያዬ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማቸው ባደረገሩት ንግግር ላይ የሰይጣን ማህበር "ማህበረ ቅዱሳን" ለመግለጽ የተጠቀሙበት አገላለጽ እርምጃው ሀገራችንና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ማእከል ያደረገ እስከሆነ ድረስ እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የተናጋሪው ሃሳብና አቋም ሙሉ በሙሉ በመጋራት አንኳር አንኳር ነጥቦችን በማተኮር እንደሚከተለው ሐተታዬን ይዜ ቀርቤአለሁ::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ሃይማኖቶች የጽንፈኝነት ምልክቶች መታየታቸውን አውስተው በምሳሌነት ከጠቀሱት መካከል በአዲስ አበባ የተከበረውን የጥምቀት በዓልና  የማህበረ ቅዱሳን ጸረ-ሕገ መንግስታዊ  እንቅስቃሴው የገለጹት በእንዲህ ዓይነት መልኩ ነበር ጥምቀት ላይ ከነበሩ መፎክሮች አንዱ «አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት» የሚል  ነው::” የማህበሩ አፍራሽና ጸረ ሕገ መንግስታዊ ድርጊት ሲያስረዱ ምክንያታቸው እንደሚከተለው አቅርበዋል «አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት» የሚል ሕገ መንግስት የለንም:: አንድ ሀገር የፈለገውን ዓይነት ቁጥር ያለው ሃይማኖት ነው ህገ መንግስቱ የሚለው" ሲሉ:: እዚህ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ብቻ ጠቀሱ እንጂ "ማህበረ ቅዱሳን" የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ሰላምን የሚፈታተን: የሃይማኖት ነጻነትን የሚጻረር: የዜጎች ሰብዓዊ መብትን የሚጋፋ አቋሙን የሚያንጸባርቅባቸው አባባሎችና ትምህርቶች በርካታ ናቸው:: 

ያም ሆነ ይህ ግን በእኛ (በክርስቲያኖች) በኩል ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ ቢኖር መፈክሩ እውን ክርስቲያናዊ መፈክር ነው ወይ? ነገሩ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘንስ ሚዛን ይደፋል ወይ? «አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት!» ብሎ የሀዲስ ኪዳን ትምህርት/እምነት አለ ወይ? ነው:: መልሱ አጭር ነው መፈክሩም ክርስቲያናዊ አይደለም አጋፋሪዎቹም ክርስቲያን/የክርስቶስ ተከታዮች ሊሆኑ አይችሉም!! በዮሐንስ ወንጌል 13: 35 “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉተብሎ እንደተጻፈ አንድ ክርስቲያን የሚታወቀው በጸብ ጫሪነቱ: በተናዳፊነቱ: አልያም በነገር ሳይሆን የአንድ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ መለያው ፍቅር ነው! እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ የሚያስበው: የሚያሰላስለው ፍቅር ነው! ቋንቋውም ስራሁም ሁሉ ፍቅርና የፍቅር ውጤቶች ናቸው!  ፍቅር ካራሱ ጋራ: ፍቅር ከወገኖቹ ጋራ: ፍቅር ከጎረቤቱ: ፍቅር ከሚያምንም ከማያምንም ጋራ! ታድያ ይህ ራሱ የቅዱሳን ማህበር በማለት የሚጠራ ግብረ እኩይ ማህበር በቅርብም በሩቅም በዞረበት: በዋለበት: ባለፈበትና ጥላው ባጠላበት ስፍራ ሁሉ እነዚህ ነገሮች የውሃ ሽታ ናቸው:: 

በነገራችን ላይ «አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት» የሚለውን አባባል “ሕገ መንግስትን” ብቻ ሳይሆን ጸረ ክርስትና/የክርስትናን መልክ ለማጥፋትና ክርስትናን የጥላሸት ለመቀባት በሀዲስ ኪዳን ላይ የተቃጣ የጸረ- ክርስቶስ ሃሳዌ መሲህ አጀንዳ ነው:: እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ዓቢይ ነጥብ ቢኖር እግዚአብሔር በግርግር: በአመጽ: በአድመኝነት: የማይከብር መሆኑና አመጸኝነት ለባህሪው የማይስማማው: ምግባረ እኩይ ልጅ የሌለው ጻዲቅ አምላክ መሆኑ በግልጽ ሊታወቅና ሊሰመርበት ይገባል:: ጌታችን ኢየሱስ በማቴ 28: 19 ለደቀመዛሙርቱ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት” እንዲል “እያስተማራችኋቸው” አለ እንጂ ያልተጻፈ ቃል በቲሸርታችሁ ጽፋችሁ በታላቅ ጩኸትና ጭፈራ ዱላና ቆመጥም ይዛችሁ ተከታዮች አፍሩልኝ አላለም! እንዲህ ያለ እንቅስቃሴም ከክርስቲያናዊ ስነ ምግባር የወጣ ተግባር ብቻ ሳይሆን ሰይጣናዊም ነው::

በሌላ አገላለጽ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ናት! ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ ብቸኛ ጌትነትና አዳኝነት ቢያምንም ባያምንም ቢቀበልም ባይቀበልም ኢትዮጵያ ለዚህ ግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ ምድሩ: ኩራቱም ሀገሩም ናት::  ክርስትና አላምንም ያለ አንገቱን በስይፍ ቅላው የሚል ትምህርት የለውም! በአባባሉ ያልተስማማ: በነጻ ፈቃ የሚያምን: የሌላ እምነት ተከታይ ዜጋ የት ይሂድ ነው መልእክቱ? በምድሪትዋ የተወለደም ሁሉ ምድሪቱ እኩል ትደርሰዋለች! ወይ ጉድ! ክርስቲያን ወንጌልን የሚመሰክርበት: የእውነትን ቃል በፍቅር የሚያካፍልበት መንገድ ይፈጥራል ያበጃጃል እንጂ ያልደረሰበት ያልነካውን ሰው በቡጢ ለማለትና በማጮል ለጸብ: ለደምና ለሞት አይተናኮስም አይነካካም::

ኢትዮጵያዊነት የሰው ልጆች ከልደት በኋላ በአንድም በሌላም በሚይዙት/በሚያግኙት በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው። በሌላ መታወቂያም አይለካም! ይህን ሐቅ የማይቀበል ማንም ቢኖር ደግሞ ምድሪቱ ሀገሩ መሆንዋ ትቀርና  እስር ቤት ብትሆንበት ምን ይደንቃል? ይህ ደግሞ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እምነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሀገራዊ ጥቅም ማእከል ያደረገ አጀንዳ ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች እምነት ነው:: ቀድሞውኑ ማህበሩና አባላቶቹ በወንጌል እውነት ሲያምኑ አይደለም ወይ?

በመቀጠል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉት ይህንኑ ነበር እንደዚህ ዓይነት ነገር የሚናገሩና የሚያደርጉ ሰዎች ከግንዛቤ ችግር የተነሳ ሊሆን ስለሚችል በትምህርት ሊመለሱ እንደሚችሉ” ይላሉ:: "አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማ" ነው የሚባለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገራቸው በፖለቲካ ቋንቋ እየገለጡ/እያስረዱ ካልሆነ በስተቀር የ"ማህበረ ቅዱሳንና" ዓላማና ግብ አጀንዳ አንድና አንድ ነው ይኸውም የሀገሪቱ ስልጣን በመላ መቆጣጠር ነው:: እንስቃሴው በተመለከተ ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ ነው የሚለው እምነት ፍጹም ተቀባይነት የለውም ሊሆንም አይችልም::

እዚህ ላይ ማህበሩ በቤተ-ክርስቲያን ጥላ ስር ስለ ተጠለለ ብቻ ከቤተ-መንግስት አካባቢ መሰጠት የሚገባውን ስም አላገኘም:: ቁምነገሩ “ማህበረ ቅዱሳን” ብዙዎች እንደሚያውቁት ነጭ ነጠላ ለብሶ ሲያሸበሽብ መላእክት የሚያስቀና መሆኑ ሳይሆን “ማህበረ ቅዱሳን” ማለት  በሽብር ድርጊት ላይ የተሰማራ ሀገርንና ትውልድን የማተረማመስ አጀንዳ ያለው ስራ ፈቶ የተደራጀ የአቡጊዳ ሽፍታ ስብስብ መሆኑ በሀገሪትዋ ጠቅላይ ሚኒስትር በማያዳግም ቋንቋ በይፋ መገለጹ ያስማማናል::  የማህበሩ ቋንቋ እንደ ገደል ማሚቱ የሚያስተጋባ ብዙሐኑ የማህበሩ አባላት አንደሆነ ግን እውነትም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤ በእጅጉ የሚያጥረው ዜጋ ለመሆኑ አያጠያይቅም::

ይህ ሁሉ ካስረዱ በኋም በሃይማኖት ሽፋን ሌላ ተልእኮ ስለሚያራምዱ እንደ "ማህበረ ቅዱሳን" ያሉ ለሀገርም ለወገን የማይበጁ ኪሳራዎች ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ መንግስታዊ አቋማቸውን ሲገልጹ የዕብራውያን መጽሐፍ ጸሐፊ ለዕብራውያን ሰዎች ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ (ዕብ. 12: 15) ገልጾ መቆረጥ እንደሚገባ ሲል በጻፈው መንፈስ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የሃይማኖት አክራሪነት በአጭሩ መቀጨት ይኖርበታል” በማለት ንግግራቸውን ቋጭተዋል::

በመጨረሻ ኃይማኖታዊ ጽንፈኝነት ምን ማለት እንደሆነና አስከፊ ገጽታውን በማሳየት ለምን መወገድ እንዳለበትም ጥቂት ነጥቦችን በመዘርዘር ልለያችሁ::  
ü ጽንፈኞች ክፉኛ በጅምላዊ አስተሳሰብ የተለከፉ ከመሆናቸው የተነሳ እንደ አማኝ እግዚአብሔር ምን ያላል?  መጽሐፉስ? ማለት ቀርቶ ከእግዚአብሔርም ከቃሉም በላይ የሚከበሩና የሚፈሩ የድርጅቱ መሪዎች ስለሚሆኑ እገሌ ምን አለ? እየተባለ የጨለማ ቁራጭ የሲዖል አጋፋሪ ያለውን የአመጻ ቋንቋ እያስተጋባ ለጥፋት የሚሰለፍ ትውልድ ስለሚያፈራ::
ü ጽንፈኞች ነፍሰ ገዳዮች ናቸው፥ “የአብርሃም ዘር መሆናችሁንስ አውቃለሁ ነገር ግን ቃሌ በእናንተ አይኖርምና ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ” እንዲል የዮሐንስ ወንጌል 8: 37, (ማቴ 23: 31)
ü ጽንፈኞች ሐሰተኞ: ውሸተኞችም ናቸው፥ (2ኛ ቆሮ. 11: 13)
ü ጽንፈኞች ተመጻዳቂዎች: ግብዞችም ናቸው፥
ü ጽንፈኞች ከእውቀት ማነስ የተነሳ የሚፈጡሩ እውቀት አልባ ቀናኢያን ናቸው፥ (ማቴ. 22: 29)
ü ጽንፈኞች ማንም ይሁን ምን የሚገባንን ያክል ከሚገባው ማህበረሰብ ጋር እንደ ሰው ሊኖር ስለሚገባ ሰብአዊ ግኑኝነት የሚያሻክሩ: ጸረ ሰብዓዊ መብት አቋም የሚያራምዱ: ለሕዝብ ሰላም ለሀገር ደህንነት ጠንቅ ናቸው፥
ü ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት ጸረ- ዲሞክራሲዊ አስተሳሰብ የወለደው በየትኛውም መድረክ ተቀባይነት የሌለው ከይሳዊ አካሄድ ከመሆኑ በላይ የሰው ልጅ ነጻ ፈቃድ የሚገፋም ነው፥
ü በአጠቃላይ "ማህበረ ቅዱሳን" ማለት ሌላ ማንም ሳይሆን ዘርዘር ባለመልኩ የተመለከትናቸውን መጠነኛ የጽንፈኞች መገለጫዎች የሚታዩበትና የሚንጸባረቁበት ሁነኛ አገር አጥፊ ማህበር ከመሆኑ በተጨማሪ በግርግር የሚያምን ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያለው መንፈሳዊ ካባ የተላበሰም ነው:: ስለሆነም በእኔ ላይ ብትፈርዱ ትበተናላችሁ: መንግስታችሁ አይጸናም  እያለ በባዶ ሲያስፈራራና ሲያናፋ የነበረውን ለበርካታ ዓመታት ታይቶ ተሰምቶ በማይታወቅ አኳኃን "ክንፍ አለው ይበራል አይሞትም ያርጋል" እየተባለ ሳይገባው ሲፈራና ሲከበር ብዙዎችን ለከፋ ችግር የዳረገ፣ የብዙዎችን ትዳር አናግቶ ቤተ-ሰብን ያፈራረሰ፣ ባለ አውልያና ባለ ክራማቱ "አባባ" ታምራት ያገኘች እጅ ታገኘው ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው::

ጥብቅ ማሳሰቢያ:
ብዙ ጊዜ እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች (ማህበሩ በመንግስት ባለስልጣናት በተነቀፈ ቁጥር ማለት ነው) በውስጠ ታዋቂነት ጣቶቹን  የሚያወራጫቸው ወደ ተቃዋሚዎች ሰፈር ማለት መንግስትን ስለምቋወመው ነው የሚል መልዕክት ባዘለ መንገድ ነው:: እንዲህ ዓይነቱ የለበጣ ጨዋታ እየተጫወተም ዛሬ ላይ ደርሷል እውነቱ ግን "ማህበረ ቅዱሳን" በኢህአዴግ መንግስት ተነቀፈ ማለት ሌላ ምንም ማለት ሳይሆን የተገለጠው የተነገረውና የሰማነው ምስክርነት እውነት እንደመሆኑና ነገ ለሚመጣ መንግስትም ቢሆን ነቀርሳ እንደመሆኑ መጠን  ሀገር ወዳድ ዜጋ ሁሉ የማህበሩን እኩይ ድርጊት በመቃወም እድሜውንም ለማሳጠር የተቻለውን አስተዋጽዖ ያበረክት ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ:: ሌላው ይህን ለመጻፍ የተገደድኩበት ዋና ምክንያት ዜጎች ምንም እንኳን ሕገ መንግስትም ቢሆን የመቃወም መብት (እስካልጠቀማቸው ድረስ) እንዳላቸው የማምን ብሆንም በሃይማኖትና በመንግስት መካከል ሊኖር ሲለሚገባው ግንኙነትም ሆነ ልዩነት በተመለከተ ለጊዜው ሌላውን እንከን ትተን "ማህበረ ቅዱሳን" በተመለከተ ከመንግስት በኩል የተሰጠውን መግለጫ ጤናማ አእምሮ ያለው ዜጋ ይጋራዋል የሚል እምነት ስላለኝ ነው::

/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
April 2012

20 comments:

  1. እስከዛሬ የት አባህ ነበርክ? ቆራጣ አስመሳይ

    ReplyDelete
    Replies
    1. የትም ይሁን የት እወነት ጽፏል አልጻፈም ነው ነጥቡ። ጽሁፉን ውሻት ለማለት ሞራሉም ድፍረቱም የለህም። በርታ ሙሌ ክፍል ሁለት መጽሀፍህ የት ገባች። ቶሎ አሳትማት እንጂ

      Delete
    2. እውነት የት እንዳለች አይተህም ሰምተህም የምታውቅ አይመስለኝም ዳሩ ምን ያደርጋል ክርስትናን በወሬ እንጂ በተግባር ለመግለጽ አልታደላችሁም ለመሆኑ የትኛዋ እናት ቤተ/ክ ናት እናንተን እና መሰሎቻችሁን ያፈራች?? እኔ እስከማውቀው ቤተ/ክ የሚረግሟችሁን መርቁ እያለች ነው ያሳደገችን ታዲያ የናንተን ጽሁፍ ማንበብ እራሱ ሃጢያት ነው ዲ/ን እኔ ለማንበብ የዘገነነኝን የስድብ ውርጅብኝ አንተ ቃሉን የምታውቀው በመጸፍህ አዘንኩልህ እግዚአብሄር አይነ ልቡናህን ያብራልህ! እስኪ አስበው ይሄንን አጸያፊ ስድብ ለመጸፍ ያባከንከውን ጊዜ ለጸሎት አውለኅው ቢሆን ኖሮ.... ስንት በረከት ታፍስበት ነበር መሰለህ ማህበሩ በሚገባ ግዴታውን እየተወጣ ነው ወዮ ለንዳንተ አይነቱ!!!!

      Delete
  2. ወደድኩዋቸሁ።

    ReplyDelete
  3. እንዲህ በድምረትና በማስረጃ የሚቃወማቸው ነበር ያጡት። እንኳን ደህና መጣሽ አውደ ምህረት

    ReplyDelete
  4. Enanten yemettsfuten tshuf manbeb erasu betam yekefal yemegermew menem meseret yelelachu woregnoch nacheu selezih manaem ayamnachum ene bemesereti yemhbere kidusan abal aydelhum serachew gen lebetkrstian menor hon hluna selmitekem betam menor albachew enantem endezih yemthonut menem lehymanotua yematkorekoru thdso selhonachu new betkrstian atetadesem selale aydel yetemdachut lenegeru enante temedachu altmedachu meles awora alawora Egziabher hulunem neger selemiawk MK aytefam lemen ybtkrstian mert legoch slhonu enante gen betam worgnoch Egziabhern yematferu menem yehymanotegna serat yelelachu nachu Egziabher degmo besewor yemtseruten slemiawo yeserachun tagegnalachu lebona yestachu!!!!

    ReplyDelete
  5. There was no the slogan One country one religion in the Holiday of TEMQET,the so called pm Meles read the one baptism changed as one country for his political agenda to creat division between christians and moslems,we aware that tehadiso and weyane work together to destroy our religion but they never can destroy it since the shepherd is the Almighty Jesus Christ.

    ReplyDelete
  6. yehenenema derom belekew yele ende .....adis neger alametam wedaje ahun PM seletenageru sayehon medgemu degmo lela yemetelw kaleh..........

    ReplyDelete
  7. Endet des yilal:MK lekas sira eyesera new yalew. Ahunim negem and geta and haymanot and timiket. Beka. Yih malet gin leloch Ethiopian wogenochachin yemnor edil yinefegachew ayibalim, yihin sil MK altesemam. Ante deacon neh woys deagon, diabilos. "አባባ" ታምራት ያገኘች እጅ ታገኘው ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው:: Mech yetselot hiwot alehena, wodeman new yemititseleyew? Wode seytan new woyes.....? Egziabheren endew atawikewim. Tenekabih, begirgir sholkesh litigebi, aye merzua tenekabish!!! Ante betsafihew egnam mahibereun yemanawekewiena abal yalneberew abal enehonalen.

    ReplyDelete
  8. where are the evidences? No evidence at all...

    ReplyDelete
  9. please show us evidence to say MK is terrorist,so that any one can believe..but repeating what the PM says mean nothing .it shows your weakness"dn mulugeta" else you are tehadiso..white believer rather than believing in God

    ReplyDelete
  10. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንዱ አምላክ አሜን!
    በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ውስጥ የነበረው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዲያብሎስ በቤተ ክርስቲያን ላይ ያለውን ሁሉ ዝናር አራገፈ ቤተ ክርስቲያንን ግን አልጎዳትም የሚል አስተምህሮ ትቶልን አልፏል
    ይህች መሠረቷ ለሰው ልጆች ሁሉ ድኅነት ሲል በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቦዛ የሆነላት ቤተክርስቲያን ሰማያዊት ነችና አሁንም ድረስ አለች ወደፊትም ትኖራለች- ከምንም በላይ የሚያሳዝነው ግን ክርስቲያን ነን ብለው ራሳቸውን የሚያስቡ/የሚጠሩ ጡቷን ጠብተው አድገው የእናት ጡት ነካሽ የሆኑ/ አመለካከታቸው አማሌቃውያን ለክርስቲያኖች ካላቸው ጥላቻ በላይ የሆኑ ግለሰቦች ዓላማና ግባቸው ጥፋት ሆዳቸው አምላካቸው ሆኖ እያለ እንደ ግብር አባታቸው ዲያብሎስ የሐሰት ካባ ደርበው/የበግ ለምድ ለብሰው ቤተክርስቲያንን ተጠልለው እውነተኛ ልጆቿን ወደ እምነት ጥርጥር እንዲገቡ
    በክሕደት ትምህርት ለመውሰድ የሚያደርጉትን ሩጫ ባለመገንዘብ አሁንም ለጥፋት መሰለፋቸው ያሳዝናል-ማኅበረ ቅዱሳንን የምትከሱት እናንተ ሳትሆኑ በእናንተ ላይ ያደረው አባታችሁ ዲያብሎስ ነው- በመጨረሻው ሰዓት እናንተ ከአባታችሁ ናችሁና አላውቃችሁም ሳትባሉ ንስሐ ገብታችሁ ወደ እውነተኛዋ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተመለሱ! እግዚአብሔር አምላክ በተዋሕዶ እምነታችን ያፅናን! ሃይማኖታችንን እና አገራችንን ይጠብቅልን!

    ReplyDelete
  11. 'ለወንድሜ' ኤፍሬም:

    ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ!!!!!!!!!

    በመጀመሪያ ደረጃ ባሕር ማዶ በሞቀ ኑሮ ላይ ሁነህ እዚህ አገር ቤት ባለነው የሁሉም ችግር ገፈት ቀማሾች ብቻ ሳንሆን ጭልጥ አድርገን ጠጪዎች ላይ የስንፍና አንደበትህን ባትከፍት መልካም ይሆን ነበር:: የለም የመጻፍና የመናገር ሱስ አለብኝና ዝም ማለት ፈጽሞ አልችልም ያገሬና የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል ያንገበግበኛል ለማለት ከሆነ ግን 'ያልተነካ ግልግል ...ነውና' ዝም ብትልና የሚሆነውን ብትመለከት ወይም እንደገባው እውነተኛ የጌታ ተከታይ ብትጸልይ ይሻልህ ነበር:: ተርፈህ ታተርፋለህና::

    አዎ! በውጭ ሆነው ወይም በዳር ቆመው እርስበርሳችንን ሊያዋጉን የሚፈልጉ የአፍ ጀግኖች ሞልተውናል:: ታሪካችን ይህን በመሰሉ የድል አጥቢያ ባንዳ አርበኞች የተሞላ መሆኑን ያለፈው ተመክሯችን (በጣሊያን ጊዜ ሳይቀር) በሚገባ አስተምሮናልና ለአሁኑዎቹ አንተን መሰል ዳር ቋሚ እሳት ጫሪዎችና ለአንተ ለራስህ ግን ይህ ዓይነቱ አካሄድ አያዋጣችሁም ለአራችንና ለቤተ ክርስቲያናችንም አይጠቅምምና ዝም በሉ ወይም በል የሚል ምክሬን እለግስሃለሁ::

    ከዚህ በተረፈ ማን ምን እየሠራ ነው? ዓላማውስ ምንድነው? ወዘተ ለሚሉት በርካታ ጥያቄዎች መልስ ግን እንኳን አገርን እመራለሁ ለሚል መንግሥት ይቅርና ለእኛ በአገሪቱ ውስጥ የሚሆነውንና እየሆነብን ያለውን ለምናይ ኗሪ ምስክሮች ብቻ ሳይሆን ለእናንተም (በዓላማችሁ ታውራችሁ እንጂ) የተሰወረ አይደለም::

    ስለዚህ እባካህ 'ወንድሜ' ኤፍሬም ከመሰል የግብር ወንድሞችህ ጋር የሚያስተውል ልብ ይኑራችሁና ለአገርና ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም አስቡ ተነስታችሁም ፍሬ ያለውና የሚታይ ሥራ ለመሥራት ሞክሩ:: በተጋለጠ የማንነት ሥራችሁ ላይ እንደገና የማይመስልና የማይታመን ነገር በመጻፍ ደግማችሁ ደግማችሁ ሕዝብ ለማታለል አትሞክሩ ወይም ከተቻላችሁ ሌላ የማታለያ ስልት ቀይሱ:: ለእንደዚህ ያለ በሬ ወለድ ነገር ብርቱዎች ናችሁና::

    'እውነት ትመነምናለች እንጂ አትበጠስም' እንዲሉ ስለ ማህበረ ቅዱሳንና ስለተሃድሶ ማንነት ለማዎቅ የሁለታችሁም የሥራ ፍሬ እየገለጣችሁ ስለሆነ ሚዛኑን በዚች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመሆን ወደ ሰማይ ለምናነባ የቤተ ክርስቲያኒቷ ምእመን ተውት:: እንባን የሚያብስ የጌታ ቀን መገለጫው ቀርቧልና::

    'አመጸኛው ወደ ፊት ያምጽ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ
    ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ ቅዱሱም ወደ ፊት
    ይቀደስ አለ::' (የዮሐንስ ራእይ 22:11)

    የሞጣው ጊዮርጊስ የቆሎ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በመላው ያገራችን አድባራትና ገዳማት ውስጥ 'በማህበረ ቅዱሳን' (ዲያቆን ሙሉጌታ ግብራቸውን ተመርኩዞ ያወጣላቸውና ለመጽሐፉ የሰጠው ማሀበረ ሰይጣን የሚለው ስም ይስማማኛል) የፈሰሰውና እየፈሰሰ ያለው የንጹህ ወገኖቻችን ደም አሁንም ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው አምላካችን በመጮህ ይጣራልና ወዮ! ወዮ!! ወዮ!!! ለኤፍሬምና ለመሰሎቹ::

    እግዚአብሔር አገራችንና ቤተ ክርስቲያናችንን በመካከላችን ከሚገኙ ተናካሺ ውሾች ይጠብቅ!!!! አሜን::

    ሰላም ለሁላችን ይሁን!!

    በዚህ ጉዳይ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር የዘወትር ሙግት ያለኝ እና የሁሉንም ወገኖቼን እውነተኛ ሰማያዊ ፈውስ የምሻ እህታችሁ

    ReplyDelete
  12. ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የተናገሩት የማህበረ ቅዱሳንና የሰለፊዎችን አሸባሪነት ብቻ አይደለም::እነዚህን አሸባሪዎች የሚከተሉትን በትምህርት መመለስ ይቻላል በማለት የጠቀሱት ነገር መረሳት የለበትም እነዚህ አሳሳቾች ያሳሳቷቸውን በትምህርት የሚመለሱበት መድረክ ማመቻቸት መረሳት የሌለበት ነገር ነው::በተለይ የተከተሉ የዋሃን የሀገራችን ቅዱሳን አፍቃሪዎች መሳሳታቸውን ማሳየት አስፈላጊነው::ሌላውእኮ የሚል መፈከር ለጠፈው መሄድ ከጀመሩ ቆይቷል::እነዚህ የዋሃን ዓለም በሙሉ የእነርሱን የሐሰት ትምህርት ካልተከተለ አይድንም ብለው የሚያምኑ ጠባቦች ናቸው::መለስ ብለው በሌሎች ዓለማትሃይማኖት ተከታይ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል እየተከተሉ የሚኖሩ እንዳሉ ቢያውቁ እንዴት ያፍሩ?እንግዲህ ስለማቆች መነገር ከተጀመረ ቆይቷል::ለነገሩ አሁን በፓርላማው ውስጥ ስለተነገረ ነው እንጂ መንግሥታችን ይህችን ስቶ ሳያውቅ ቀርቶ ተሰውሮበት ነው ሳይናገር የቆየው ብዬ ማመን እቸገራለሁ::መንግሥት የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ በቤተክህነት ቅጽር ግቢ ውስጥ የተነሳው ረብሻ ዋና ምክንያት ማቆች መሆናቸውን የሳሰተ አይመስለኝም::የሃይማኖት ነገር በጣም በጥንቃቄ ካልተያዘ አደጋው ከፍተኛ ሆኖ ብዙ የዋሃንን ቅኖችን ሊያጠፋ ሊጨፈልቅ እንደሚችል በመገንዘብ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው::የሆኖ ሆኖ እግዚአብሔርና ጊዜ ተገናኙና በተለይ ላላወቁ ላልተረዱ ይህ የጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጨረፍታ እንዲነቁና እንዲመራመሩ ያደርጋቸዋል::መትረፍ ከፈለጉ ማለቴ ነው::እንደው መንግሥት በማያገባው ገብቶ ነው የሚሉ ሞኞች ካሉ ግን ሊያስቡበት ይገባል::ሀገሪቱ እግዚአብሔርንም የሚክዱ የእስላሞችም የክርስቲያኖችም የሃይማኖት የለሾችም ናትና በቅንነት እግዚአብሔርን መፍራት በሚገባን መንገድ እየፈራን እንኑርበት::
    ኒቆዲሞስ

    ReplyDelete
  13. "እድሜ ለማሳጠር" this is for your heretic (Nufake)teaching!!!

    ReplyDelete
  14. የጻፍህው አንተ ነህ ወይስ ሰይጣን?አሁን አንተ የወልደገብርኤ ልጅ ነህ ሊባል ነው አባትህ ፍርድ ቤት ሂደው ስማቸውን መውሰድ አላባቸው::

    ReplyDelete
  15. ዲ ሙሉጌታ ወልደ ገብሬል ስለ ጽሑፍህ ከልብ አመሰግናለሁ፤
    ምክንያቱም ሀቅና ትክክል ጥራትና እውነት አዘል በመሆኑ ነው፤
    ዳሩ ግን አስመሳዩና በሰው ዘንድ ተመጻዳቂው አካል በድሆች የምጽዋት ገንዘብ ሰ
    ሠክሮ ልቡ ስለ ደነዘዘ
    አይኑ ስለ ፈዘዘ ሊረዳው ቀርቶ ሊያነበው አይችልም፤ ይሁን እንጂ ውሀ የሚጠጣኝ የለም ብሎ መፍሰሱን
    ጸሓይ የሚሞቀኝ የለም ብሎ መውጣቱን እንደማይሰርዝ አንተም በዚሁ ትጋ ጻፍ

    ReplyDelete
  16. ዲያቆን ሙሉጌታን ልናመሰግን ይገባል፡፡ ‹‹ማህበረ ቅዱሳን›› የተባለው ክፉ ስብስብ በቤተክርስቲያናችን እና አገልጋይ ልጆችዋ ላይ መከራና ስቃይ ሲከምር እንደኖረ የታወቀው ከቶ ዛሬ አይደለም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉዳዩ ላይ የሰጡት ማብራሪያ የችግሩን ጥልቀት ያሳይ እንደሆን አንጂ አዲስ አይሆንም፡፡ በማህበሩ ጨንገር ሲገረፉና ሲለበለቡ፤ ከሚወዱአት እናት ቤተክርስቲያናቸው በግፍ እያለቀሱ ሲጋዙና ሲባረሩ፤ የነበሩና ያሉ ልጆችዋ፤ ላለፉት ሃያ አመታት (የማህበሩ እድሜ ሙሉ!) የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡፡ ‹‹የቅዱሳን ማህበር›› ተብዬው ቡድን፤ ሲያመቸው በእጅ ካልሆነም በማንኪያ ሲያገላብጠው የኖረውን ፖለቲካዊ አጀንዳ የምናውቅ እናውቃለን፡፡ ደርሶም ድንቅ ዜና አይሆንልንም፡፡

    ከጥንስሱ ጀምሮ በክፉ አጋንንታዊ ልማድ የተወጠነው የጥራዝ ነጠቆች ጉባኤ፣ እሰራላታለሁ እያለ የሠራላትን ቤተክርስቲያን ወደ አዘቅት ውስጥ ለመጨመር ሌት ተቀን በመትጋት የሚቻለውን ሁሉ ጥVል፡፡ ሞያ ብሎ በያዘው የጅል ዘፈኑ፤ ‹‹ተሃድሶ መጣባችሁ፤ ብትንተናችሁን ሊያወጣው ነው›› በማለት እንደ ልጆች ጨዋታ ታሪካዊቱን ቤተክርስቲያን በአንደ ጀምበር ተንዳ የምትጠፋ የጨረባ ተዝካር ሲያስመስላት ኖVል፡፡ ይኸው ጨዋታው ዋና ማስፈራሪያና ማደናገሪያ ጥበቡ ነው፡፡ በእውነተኛ ልቡ ግን የአገር እና የቤተክርስቲያን ጠላት የሆነ አጀንዳ አራማጅ ነው፡፡ አባቶችን መናቅ እና መዝለፍ፤ እርስ በእርስ እንዲናከሱና እንዲፈራሩ በአይነ ቁራኛ እንዲጠባበቁ ማድረግ፣ ሐሰተኛ ወሬ ፈጥሮ ማዛመት፤ አላማዬን ይደግፉልኛል የሚላቸውን ደግሞ በገንዘብ መደለል፤ አልፎም ተርፎም፣ በመንግሥታዊው መዋቅር ውስጥ (በተለይም በሰሜኑ የአገራችን ክልሎች) ለክፉ አላማው ደጋፊ የሚሆኑና ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት የዘነጉ ግለሰቦችን መልምሎ በማዘጋጀት ሲጠቀምባቸው ኖVል፡፡ እኛ አሁን ደርሶ ጉዳዩን መንግሥት አጋለጠ ብለን አሼሼ ገዳሜ የምንመታ የሚመስላቸው ካሉ እጅግ ተሣስተዋል፡፡ መች ከበአታችን ወጣንና? ስናለቅስ እኮ ሃያ አመት ሞላን ጃል!! በየገዳማቱና አደባራቱ፤ ከተሞቹና ገጠሮቹ፤ በዚህ ማህበር የሐሰት ውንጀላ ተነድፈው የሚያለቅሱ፤ የሚቆዝሙና የሚተክዙ ለቁጥር የሚያታክቱ የቤተክርስቲያን ልጆቸ አሉ እኮ ሰዎች?

    አሁንም ቢሆን፣ ሲቻል በምክርና በመፀፀት ቢመለሱ፤(በማህበሩ ውስጥ በቅንነት የሚሳተፉ እንዳሉ ስለሚታመን) ካልሆነም ደግሞ ግብርና አድማቸውን ከሥሩ ነቅሎ የሚጥል አምላካዊ ጣልቃ ገብነት እንዲሆን ጸሎታችንን እንቀጥላለን፡፡

    ReplyDelete