Thursday, April 19, 2012

ማህበረ ቅዱሳንና ሰለፊያ፤ ማን የማን ግልባጭ ነው?

Click here to Read in PDF

የማህበረ ቅዱሳን ሰለባ የሆኑ ብዙ የቤተክርስቲያን አባቶችና ልጆች ማቅን በአሸባሪነት ከፈረጁት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ ማቅ ግን እንዲህ የሚሉኝ ለቤተ ክርስቲያን ጥብቅና ስለቆምኩ ነው በሚል ራሱን ሲከላከል ቆይቷል። ማህበሩ አሸባሪ የመሆኑ ጉዳይም በአንዳንዶች ዘንድ እንደ ስድበ ሲቆጠር መቆየቱ ይታወሳል። ለማኅበሩ ይህ ስም የተሰጠው በከንቱ አልነበረም። ስራው በአክራሪ ሙስሊሞች ከሚካሄደው የበለጠ እንጂ ያላነሰ ሆኖ ስለተገኘ ነበር ይህ የግብር ስም የወጣለት።

 ዕድሜ የሰጠው ሰው ብዙ ያያልና ይኸው የማህበሩ የግብር ስም ከትናንት በስቲያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ጸድቋል። በማኅበሩ ሲገፉና ሲነቀፉ ለኖሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ይህ እንደ አንድ ትልቅ ድል የሚቆጠር ነው። እንኳንም በትክክል የወጣለት የግብር ስም በማኅበሩ ዘንድ እንደ ስድብ ከመቆጠር አልፎ ትክክለኛ የማህበረ ቅዱሳንን ማንነት የሚገልጥ ስም ሆኖ ተነገረ! ይህን የተናገሩት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትራችን መሆናቸው ትልቅ ግምት የሚሰጠው ብቻ ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን ከማሸበር አልፎ አገርንም ለማተራመስ ትልቅ አላማ እንዳለው በመንግስት በኩል የተደረሰበት መሆኑን ያመለክታል።   

በአሁኑ ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳን ማነው? ምንስ ነው የሚሰራው? አላማው ምንድነው ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ የሚፈልገው የህብረተሰብ ቁጥር እየበዛ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ሰለፊያን አስመለክተው ሲናገሩ ሰለፊያ የማኅበረ ቅዱሳን ግልባጭ መሆኑን በግልጽ ቋንቋ እንዲህ ሲሉ ነግረውናል። “አንዳንድ የሰለፊ እምነት ተከታዮች አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱትን ግልባጭ ሲያራምዱ ይታያሉ።” ማኅበረ ቅዱሳን ለክፋት መምህር እንጂ ደቀመዝሙር እንደማይሆን የተረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ማኅበረ ቅዱሳን ስልቶቹንና አካሄዱን ለሰለፊያ ማውረሱን በማያሻማ መንገድ ገልጸዋል፡፡
መቼም ማቅ የሚሰራውን ስራ አስተውሎ ያየ ሰው በማቅና በሰለፊያ(ወሀቢያ) መካካል ያለውን የመንፈስ አንድነት በቀላሉ ይረዳል። ለማስረጃ ያህል፡-

1.     ሰለፊያ(ወሀቢያ) ሃሳቡን ለማስፈጸም እስከ መጨረሻው ጥግ ድረስ ሄዶ ሰዎችን ሊገድል ይችላል። ማቅም ከአባቱ ከዘርኣ ያዕቆብ ተምሮ በመንፈሳዊነትና በሀይማኖት ፍቅር ስም ሰዎችን ማሰቃየት መደብደብና መግረፍ ተገቢ ነው ብሎ ያምናል። እያደረገ ያለውም ይሔንን ነው። ከመቀሌ እስከ ቦረና ከሐረር አስከ ጋምቤላ ከጎንደር እስከ ሐዋሳ እንዲሁም በክብረመንግስት፣ በሻኪሶ፣ በአለታወንዶ፣ በአላባ፣ በድሬዳዋ፣ በደሴ፣ በባኮ እና በአዲስ አበባ የፈጸማቸው ድርጊቶች ለዚህ ትክክለኛ ምሳሌ ናቸው፡፡
  
2.    ሰለፊያ ትምህርቱን ለማስተላለፍ የሚጠቀምበት መንገድ የሃይማኖቱን በጎ ጎን ማሳየት አይደለም፤ የእነርሱ የሀይማኖት ማስፋፋያ መንገድ አሉታዊ ነው። ማቅም ስለቤተክርስቲያን ትምህርቶች መጽሀፍ ቅዱስን ተመርኩዞ የሚያስተምረው መሰረታዊ ነገር የለውም። የማቅ ዶግማ “መናፍቃን ተሀድሶ” የሚሉትን የስድብ ስሞች እያነሳ የቤተክርስቲያንን ልጆች ማሳደድ ብቻ ነው። በየቀኑም እንዲህ አደረጉ ይህን ፈጸሙ እያለ ሽብር በመንዛት ለኦርቶዶክሳውያን “እኔ ባልኖር ኖሮ መንፈስ ቅዱስማ ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ አቁሟል፤ “የጊዜው መንፈስ ቅዱስ” እኔ ነኝ፤ ትክክለኛው የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ” በማለት በመንፈስ ቅዱስ ቦታ ራሱን አስቀምጦ እኔን ብቻ ስሙ እያለ ምእመኑ በእምነት ሳይሆን በስጋት እንዲመላለስ እያደረገ ይገኛል።

3.    ሰለፊያ የአጭር ጊዜ እቅዱ መጅሊሱን መቆጣጠር ሲሆን፣ የረጅም ጊዜ እቅዱ ደግሞ የመንግስትን ሥልጣን መያዝ ነው። ማቅ ልክ እንደ ወሀቢያ የአጭር ጊዜ እቅዱ ቤተክህነትን መቆጣጠር ሲሆን የረዥም ጊዜ እቅዱ ደግሞ የመንግስትን ስልጣን መያዝ ነው። ቤተክህነትን ለመቆጣጠር በሙሉ ሀይሉ እየሰራ ይገኛል። ጳጳሳትን በተለያዩ ስጋዊ  ጥቅሞች በመደለልና በማሳሳት፣ አልሆን ሲለው ደግሞ በነውራቸው በማስፈራራት የማህበሩ ፍላጎት አስፈጻሚ ለማድረግ እየተጋ ይገኛል። እስካሁንም በእግዚአብሔር እርዳታ የሚፈልገውን ነገር መስፈጸም አልቻለም እንጂ በተለይ በሲኖዶስ ስብሰባዎች ሁሉ ማቅ አጀንዳ በአንዳንድ የሲኖዶስ አባላት በኩል አስቅርቦ የሚፈልገውን ውሳኔ ለማስወሰን አመራሮቹ እንቅልፍ አጥተው እንደሚያድሩ ቤተ ክህነቱን በቅርብ የምናውቅ ሰዎች የምናስተውለው እውነት ነው። የመንግስትን ስልጣን በተመለከተ ያላቸው ሀሳብ ምን እንደሆነ እንኳን ማህበሩን ቀርበን አይደለም በሩቅም አይተነው የምንረዳው ሀቅ ነው። በተለያየ ጊዜ የግል ጋዜጣን ፈንድ አድርጎ ከማቋቋም ጀምሮ ክፍተት ባገኘ ቁጥር ጭንቅላቱን ለማስገባት የሚያደርገውን ጥረት ለተመለከተ ማህበሩ ፖለቲካዊ እንጂ መንፈሳዊ አቋም እንደሌለው በቀላሉ ሊረዳ ይችላል።

4.    ሰለፊያ ቀድሞ በመጮህ የሙስሊሙን ህብረተሰብ አመለካከት ለመሳብ በአህባሽ ላይ የተቀነባበረ ዘመቻ እንዳደረገ ሁሉ ማቅም እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆችን ያልሆኑትን ሆኑ ያላደረጉትን አደረጉ፣ ያልረገጡትን ወረሱ እያለ በሀሰት የስም ማጥፋት ዘመቻ በማድረግ የዋሁን ሕዝባችንን በማሳሳት ላይ ይገኛል።

5.    ሰለፊያ ፍላጎቱ እስካልተሳካ ድረስ በመስጊድ አካባቢ የፈለገው ነገር ቢፈጸም ግድ የለውም። ማቅም አላማው ይሳካ እንጂ ህዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል ቢማር ባይማር ወጣቱ ወደ ቤተክርስቲያን ቢመለስ ባይመለስ ምንም ግድ የለውም። ወጣቱ እግዚአብሔርን አውቆ የእነርሱ እጅ ያን ቤተ ክርስቲያን መቆጣጠር ከሚተው ይልቅ እነርሱ ያን ቤተ ክርስቲያን ተቆጣጥረው ወጣቱ ወደ ጫት ቤት ቢገሰግስ ይመርጣሉ። ካለፈው አንድና ሁለት ዓመት ወዲህ በስብከተ ወንጌልና በመንፈሳዊ ዝማሬዎች ወጣቱን ትውልድ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየመለሱ ያሉትን የቤተክርስቲያን ልጆች ስም በማጥፋት ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ በከፈተው ዘመቻ እየተገኘ ያለው ውጤትም የሚያሳየው ያንን ነው። ብዙዎች ከቤተክርስቲያን እየሸሹ ነው። ማኅበሩ ለመቆጣጠር እጁን ባስገባባቸው አንዳንድ አድባራት ውስጥ የሚታየው ነገርም እጅግ አሳሳቢ ነው። በወጣቱ ትውልድ ደምቀው ይታዩ የነበሩ የሰርክ መርሀግብሮች የመቃብር ቤት እንደሚመስሉ ዘወትር የምናየው እውነት ነው።

በአጠቃለይ ማቅንና ሰለፊያን የማያመሳስላቸው ነገር ቢኖር እቅዳቸውን የሚያስፈጽሙበት ቀዳሚው ቦታ ብቻ ነው፡፡ ሰለፊያ መጅሊሱን ሲፈልግ ማቅ ደግሞ ሲኖዶሱን መቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ሁለቱም ይህን እቅዳቸውን ቢያሳኩ(አያሳኩም እንጂ) ቀጣዩ ኢላማቸው ስልጣን በመሖኑ እኔ እሻል እኔ እሻል የሚለው አስተሳሰባቸው ወደ ለየለት ጦርነት ሊያመራቸው ይችላል፡፡ ሁለት የአሸባሪ ቡድኖች በአንድ ከተማ ላይ መኖር እንደማይችሉ እኔ እበልጥ በሚል ስሜት አገሪቱን ከማጥፋታቸው በፊት አንድ ሊባሉ ይገባል፡፡ 

29 comments:

  1. Replies
    1. ki ki ki ki ki ki lela yelehem stupid mk
      yilke tenektobehal ante afehen zega

      Delete
  2. lek new dink mabrariya new? bertulen abo yihen aremene mahebre agaletulen

    ReplyDelete
    Replies
    1. Aremene enante nachehu zem belachu yesew sem yemetatefu!

      Delete
  3. Menafikanen kegetsemider sayatefa ayetewachihum
    Tekulawoch

    ReplyDelete
    Replies
    1. anet awrewe nehe malte nwe xYedle? kentu mk.

      Delete
  4. endihe new mkn magalet angeten kebe atetachut

    ReplyDelete
  5. enante mehayeboci satemaru yetemare setsedebu atafrum eregetenga negn kenanete mekakle 4 kefel blaye yelem mjmerya bdenb temaru kzya lekommentu tdrsalchu

    ReplyDelete
    Replies
    1. ወርኛ ማህበር ዲግሪ ቁጠር ያለመማር እኮ አያሰድብም ብዙ ያልተማሩ ናቸው የኛ ቤተሰቦች ሀይማኖታቸውን አቻችለው የኖሩት አንተ ግን ባንድ በቤተክርሲቲያን ውስጥ ትከፋፍላለህ ምቀኛ በሰው ጸጋ የምትቀና ያንተ መማር ራስህን ብትመርምር ይሻልሀል እግዚያብሄር ልቦና ስጥህ፡፡

      Delete
  6. no comment but am redy to wrid

    ReplyDelete
  7. reaLy mahbere qdusan yesetan mahber . fooooooo mahbre qdusan .yebetekrstyan bishtya .

    ReplyDelete
  8. Ebakachehune kemenagere weyeme kemetsafachehu befite masetewale yasefelegale amelake hoye masetewalene setene

    ReplyDelete
    Replies
    1. አዎ ማስተዋል ያስፈልግል። ግን ይቺን ምክር ከ10 በላይ የውሸት ብሎግ ፈጥረው ሲሳደቡ ሲያታልሉ ለሚውሉት ለማቅ ሰዎች ብታደርሳት የበለጠ ጠቃሚ ነው።

      Delete
  9. Ebakachehu kemetsafachehu ena kemenagerachehu befite masetewale yasefelegale lehulume negere amelake masetewalune yesetene

    ReplyDelete
  10. Ewenetena Negate ............. Nawe Yemebalwe ''Lehulume Geze Alwe''

    ReplyDelete
  11. wow enante degmo mane nachehu teklaye mineseteru yalubet angel mjmerya ewku keziea tktelalachehu ..... werae bmawerate batekerseteyanene attebkuatem leke endeyhuda lmetawek ybatkerseteyanachehune seme asalefachu atesetu ....

    ReplyDelete
  12. des sillllllllllllllllllllllllll

    ReplyDelete
  13. የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ”ማኅበረ ቅዱሳን ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ግኑኝመት አለው” በማለት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ እና የዛኔው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር አቶ አባይ ፀሐዬ ማስጠንቀቂያ ሰጥተውት እንደነበረ ይታወሳል:: አቶ ስብሃት ነጋ(ኦቦይ ስብሃት) እለተ አርብ ሰኔ 30፣2003 ዓ/ም ለፍትሕ ጋዜጣ በሰጡት ቃል ”ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት እዳ ነው:: የቤተ ክህነት አስተዳደር ለማሻሻል መጠነኛ እንቅስቃሴ ሲጀመር ገንቢ ተራ ከመጫወት አፍራሽነት ይበዛበታል፣ ብልሽት እያየ ዝምታ ያበዛል፣ ማኅበረ ቅዱሳን የፖለቲካ መድረክ ይታይበታል፣ማኅበረ ቅዱሳን በሕገ መንግሥት ክህደት ወንጀል ይጠረጠራል” በማለት ተናግረው ነበረ::

    ማክሰኞ ሚያዝያ 9፣2004 ዓ/ም ክቡር ጠቅላይ ሚኒተር መለስ ዜናዊ በፓርላማ ንግግራቸው ላይ ማኅበረ ቅዱሳንን ከዓለም አቀፍ አሸባሪ ድርጅት ከአልቃይዳ ጋር አመሳስለውታል:: ክቡርነታቸው ከምን አይነት መረጃ እና ማስረጃ ተነስተው ማኅበረ ቅዱሳን ከአሸባሪ ድርጅት ጋር እንዳመሳሰሉት ሰፋ ያለ ገለጻ አልሰጡም:: በደፈናው ግን “አልቃይዳ/ሰለፊ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ያራምዳል” አሉ::

    አልቃይዳ/ሰለፊ ባሳለፍናቸው በሃያ ዓመታት ጊዜ በሀገራችን ውስጥ ብዙ ጥፋቶችን አድርሶዋል:: ለዚህም በቂ መረጃ እና ማስረጃዎች አሉ:: ክርስቲያኖች አርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት አቃጥለዋል እንዲሁም ኢትዮጵያ መተዳደር ያለባት በሸርያ ሕግ መሆን አለበት በማለት አስተምረዋል እያስተማሩም ናቸው:: ሰለፊዎች በቁጥር በዛ ብለው በሚኖሩበት ዞኖች እና ክልሎች ብቻ ገንጥለው የሸርያ ሕግ ተግባር ላይ ለማዋል እየሰሩ ናቸው:: ለምሳሌ የስልጢ ዞን እና የሐረሪ ክልል መጥቀስ ይቻላል:: ታድያ ማኅበረ ቅዱሳን የትኛው መስጅድ/መስጊድ አቃጠለ? የትኛው የፕሮቴስታን ማምለኪያ ቦታዎች አቃጠለ? ማኅበረ ቅዱሳን የትኛው ዞን ወይም ክልል በክርስትና ሕግ ይተዳደር ብሎ አስተማረ? አባላቱን ከፍለው ከአልቃይዳ ጋር እንዴት አመሳሰሏቸው? የአልቃይዳ ዓላማ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰተር ጠንቅቀው ያወቁት ይመስለናል:: ጠቅላይ ሚኒስተሩ የአልቃይዳ ዓላማ ጠንቅቀው ስላወቁ ይመስለናል ወታደራቸውን ወደ ሶማልያ የላኩት::


    የማኅበረ ቅዱሳን ዓላማ ሆነ ግብ ከአልቃይዳ ዓላማ እና ግብ ጋር ፈጽሞ አይገናኝም:: ሁለቱ ተቋማት ፍጹም ተቃራኒ ናቸው:: ምንም ሊያመሳስላቸው የሚችል ነገር የለም:: የእኔን ሃይማኖት ካልተቀበልክ ትታረዳለህ ብሎ የሚያስምረው አልቃይዳ እና የአባቶችን ሃይማኖት ተጠብቆ ለትውልድ ይተላለፍ ብሎ የሚስተምረው ማኅበረ ቅዱሳን ጋር እንዴት ሊመሳሰሉ ይችላሉ? ስለዚህ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ተሳስተዋል:: ክቡርነቶ በማኅበሩ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ወንጀል ነው የተናገሩት:: አንድ የአሸባሪ ድርጅት ለመምታት ግዴታ ሌላው አብሮ መመታት የለበትም:: በእስልምናው አልቃይዳ የአሸባሪ ድርጅት ነው ይህ ዓለም ያወቀው እውነት ነው:: የአንድ እምነት አክራሪ/አሸባሪን ለመቅጣት ግዴታ የሌላው እምነት ማኅበር መወንጀል ለምን አስፈለገ? ማስረጃ እና መረጃ ሳይኖር ዝም ብሎ በአንድ ድርጀት ወይም ግለሰብ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ ወንጀል መሆኑን ክቡርነቶ የሰሩልን ሕግጋት ይናገራሉ:: ስለስዚህ ክቡርነቶ “ሰለፊዎች(አልቃይዳዎች) አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ሲያራምዱ ታይተዋል” ብለው ማኅበረ ቅዱሳንን ከአልቃይዳ ጋር ያመሳሰሉበት ንግግር ፍጹም የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው:: ለዚህም ይቅርታ ሊጠይቁበት ይገባል::

    ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ያሉዋቸው እነማን ናቸው? አባ ሠረቀ ብርሃን 10% አሸባሪ ያላቸው የማኅበሩ የሥራ አመራር አባላት ይሆኑ? ወይስ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስውር የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ያላቸው? ማብራርያ የሚያስፈልገው ጥያቄ ነው:: የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ቅዱስ ሲኖዶስ ያጸደቀላቸው መተዳደርያ ደንብ ይዘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ እና ቀኖና ለትውልድ እዲተላለፍ የድርሻቸው እየተወጡ መሆኑን የአይን ምስክሮች ነን:: አባላቱ በሙሉ አንድ አይነት ዓላማ ይዘው እንደሚጓዙ እናውቃለን:: ነገር ግን አባ ሠረቀ እና መሰሎቻቸው አንዳንድ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰዎች “ማኅበረ ቅዱሳን ድብቅ ዓላማ አለው” በማለት በተደጋጋሚ ሲከሱት ሰምተናል:: መንግሥት ተጨባጭ መረጃ እና ማስረጃ ሳይዝ የእነዚህን ሰዎች ውንጀላ የሚቀበል ከሆነ ክሱ መሰረተ ቢስ ይሆናል:: ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ይህንን የተሳሳተ የአባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የተሳሳተ መረጃ ይዘው በአደባባይ ማኅበረ ቅዱሳን ከአልቃይዳ ጋር ማመሳሰሎ ከመስመረ የወጣ ክስ በእርሶ አገላለጽ ደግሞ የፈንጂ ወረዳ የረገጡ ይመስለናል::

    የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን አንዳንድ፣ 10%፣ ስውር አመራር እያሉ ቢከፋፍሉዋቸውም ከእውነታ የራቀ ውንጀላ በመሆኑ የማኅበሩ አባላት ግን ፈጽሞ ሊከፋፍሉ አልቻሉም፤ አይችሉምም ምክንያቱም የማኅበሩ አባላት ያሰባሰባቸው የቤተ ክርስቲያን ዓላማ እንጂ የዓለም መንግሥት የፖለቲከኞች ዓላማ እናዳልሆነ ምስክሮች ነን:: ዓላማቸው የተሰቀለውን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ መስበክ እንደሆነ እኛ እንመሰክርላቸዋለን:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓት፣ ታሪክ፣ቅርስ ሳይፋለሱ እና ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፍ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በአንድነት ሆነው እንደሚሰሩ እናውቃለን::

    ከተመሠረተ ሃያ ዓመታትን ያስቆጠረው ማኅበረ ቅዱሳን በጉዞው ብዙ ፈተናዎችን እንደገጠሙት የማኅበሩ አባላት በተለያየ ጊዜ ይናገራሉ:: ማኅበሩ በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱሳን አበው እና እመው ጸሎት እስከ ዛሬ ድረስ ቢቆይም አሁንም እየተፈተነ መሆኑን አባላቱ ሲናገሩ ሰምተናል:: ስለዚህ አሁንም ቢሆን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በዚህ ሳትደነግጡ እና የተሰባሰባችሁበትን ዓላማ ሳትስቱ ሰዎችን ለማስደሰት ሳይሆን ሰለ እውነት ብላችሁ እግዚአብሔርን ለማስደሰተ ሥራችሁን ከበፊቱ ይልቅ ተግታችሁ እንድትቀጥሉ በዚሁ አጋጣሚ አሐቲ ተዋሕዶ አደራዋን ታስተላልፋለች::
    እግዚአብሔር አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን!!!

    I hope you will post it.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Sorry, I forgot to write the source. I found it from 'Ahati tewahido' blog and I belive it reflect my idea. By the way, Thank you for posting it.

      Delete
  14. Yezih mahber mechereshaw alkaida catagori memedebu yasaznal .(yigermal Yet yidersal yetebale Tija lku.a nda bet tegeNge ) yibalal mk arfo bikemet eko ehe hulu wurgibigne aydersibetim .

    ReplyDelete
    Replies
    1. ይህ የሰነፍ መፍትሄ ነዉ
      "የሞተን ዉሻ ማንም የሚደበድብ የለም "እንደሚባለዉ ነዉ
      ይልቅስ ከዚህ የምንረዳዉ ይህ ማህበር ምን ያህል ትልቅ ሥራ እየሰራ መሆኑን ነዉ
      እግዚአብሔር ይጠብቃቸዉ!

      Delete
  15. I menafekan yetetsafwe tenebit yifetsme zened yenanet endihe mhon iydnekeme Mk benanete kenetu weree wedhola ayleme yaglegelo mhaber enji yewree adeleme

    ReplyDelete
  16. mutE selraSU MEMOT SAYIHONE YELELAWENE BEMEMOGNET YITINANAL
    EWNET, EMENT K MK ESKALTLEYU MANEME BENAGRWE RASU WASHOW YITEFAL ENJI...

    ReplyDelete
  17. what ur point bro.r u noremal kande ye hayemanote sew yemeyetebek neger new eyalik yalehew.weyes ye meles amaker neh.ahunis melesen meselekeng.

    ReplyDelete
  18. anite eraseh melesen meselekeng.ye meles amakar neh enda.menew be maheber kudesan ley yehen yahel mewered asefelegeh.seret masayet new.

    ReplyDelete
  19. Why you spend your time by talking & writing false . It is better to you to come to truth than running for business like "Begashaw" who used to take more than ten thousand birr in each church by his pereach , he is prostitant.

    ReplyDelete
  20. የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን አንዳንድ፣ 10%፣ ስውር አመራር እያሉ ቢከፋፍሉዋቸውም ከእውነታ የራቀ ውንጀላ በመሆኑ የማኅበሩ አባላት ግን ፈጽሞ ሊከፋፍሉ አልቻሉም፤ አይችሉምም ምክንያቱም የማኅበሩ አባላት ያሰባሰባቸው የቤተ ክርስቲያን ዓላማ እንጂ የዓለም መንግሥት የፖለቲከኞች ዓላማ እናዳልሆነ ምስክሮች ነን:: ዓላማቸው የተሰቀለውን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ መስበክ እንደሆነ እኛ እንመሰክርላቸዋለን:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓት፣ ታሪክ፣ቅርስ ሳይፋለሱ እና ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፍ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በአንድነት ሆነው እንደሚሰሩ እናውቃለን::

    ከተመሠረተ ሃያ ዓመታትን ያስቆጠረው ማኅበረ ቅዱሳን በጉዞው ብዙ ፈተናዎችን እንደገጠሙት የማኅበሩ አባላት በተለያየ ጊዜ ይናገራሉ:: ማኅበሩ በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱሳን አበው እና እመው ጸሎት እስከ ዛሬ ድረስ ቢቆይም አሁንም እየተፈተነ መሆኑን አባላቱ ሲናገሩ ሰምተናል:: ስለዚህ አሁንም ቢሆን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በዚህ ሳትደነግጡ እና የተሰባሰባችሁበትን ዓላማ ሳትስቱ ሰዎችን ለማስደሰት ሳይሆን ሰለ እውነት ብላችሁ እግዚአብሔርን ለማስደሰተ ሥራችሁን ከበፊቱ ይልቅ ተግታችሁ እንድትቀጥሉ በዚሁ አጋጣሚ አሐቲ ተዋሕዶ አደራዋን ታስተላልፋለች::
    እግዚአብሔር አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን!!!

    I hope you will post it.
    Reply

    ReplyDelete
    Replies
    1. አጨብጭቡ ማህበሩ ትልክክ ስራ እየስራ ነው ምን ማለት ነው ማፈሪያ ማፈሪያ ማፈሪያ ናችሁ ስራችሁ
      • ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን መሳደብና ማወረድ ፣
      • ሀሰትኛ በኮፒ ፔስት የተቀነባበረ ሲዲ በማባዛት እንዲታይ በነጻ መበተን ፣
      • ቤት ለቤት የናንተ ጉባዬ ካልሆነ እንዳይካፈሉ ቅስቀሳ ማድረግና ህዝቡ ከቤተ ክርስቲያን ና ከእግዘዚያብሄር እንዲርቅ ማድረግ ፣
      • ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መዘምራን ሲዘምሩ ጥሎ መውጣት አብሮ አለመዘመር ፣
      • በየዋሃን ተጠቅሞ አገልጋዮችን መደብደብ ማስደብደብ፡፡ ብዙብዙ….
      ይህ ነው እንግዲህ ታላቅ ስራችሁ አልተሳካም የተሳካ መስሎዋችሁ ነበር እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ነውና እግዚያብሄር ታላላቅ ስራዎችን በሚሰራባት አገር ላይነን ያለነው ፣ አልተሳካም ቆም ብላችሁ አስቡ ግን ምን ያድረጋል አውቆያጠፋ አደንቁዋሪ ነውና እግዚያብሄር ልቦና ይስጣችሁ

      እግዚያብሄር ኢትዮጰያንና ህዝቧን የባርክ!!!!!!!አሜን አሜን አሜን--------

      Delete