Monday, April 2, 2012

ከዋልድባው ጉዳይ በስተ ጀርባ የአቡነ ሳሙኤል እጅ እንዳለ እየተነገረ ነው


               Click here for PDF:Waldeba
           ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግስት ሊሰራ ያሰበውን የልማት ስራ መነሻ በማድረግና በሃይማኖታዊ ሽፋንነት በመጠቀም ማህበረ ቅዱሳን በውጪ ካሉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እያጋጋለ ካለው የፖለቲካ አጀንዳ ጀርባ አባ ሳሙኤል እንዳሉ እየተነገረ ነው። የቀድሞው የዋልድባ መነኩሴና የዛሬው የልማት ኮምሽን ጳጳስ አባ ሳሙኤል፣ በጉዳዩ ላይ የዋልድባን መነኮሳት በማነሳሳትና ከቪኦኤና ከሌሎችም አካላት ጋር የሚገናኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት፣ በሰልፍ መልክ ወደጠቅላይ ቤተክህነት እንዲመጡና ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ በማድረግ፣ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ለጳጳሱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ሲናገሩ ተሰምተዋል። ይህን እያደረጉ ያሉትም በአቡነ ጳውሎስ ላይ ተቃውሞ እንዲነሳ ለማድረግና ተቃውሞው ተጋግሎ ከቀጠለና እርሳቸውን በአመጽ ከመንበራቸው ማስነሳት ከተቻለ በእርሳቸው እግር እተካለሁ የሚል ቅዠት ስላላቸው ነው ይባላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ድጋፍ እየሰጣቸው ያለው ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ 

           ማህበረ ቅዱሳንንና አባ ሳሙኤልን ያገናኛቸው አጀንዳ ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን፣ የቤተመንግስቱንም የቤተክህነቱንም ስልጣን ጠቅልሎ መያዝ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። አባ ሳሙኤል ከልባቸው አልወጣ ያለውን ፓትርያርክ የመሆን ቅዠት ለማሳካት እየወደቁ እየተነሱ፣ የተለያዩ ክፍተቶችን እየተጠቀሙ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ላይ መፈንቅለ ፓትርያርክ ለማካሄድ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ የዋልድባን ጉዳይ ሽፋን በማድረግ እንደተለመደው አባ ጳውሎስን መታገላቸውን ቀጥለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ ከመንግስት ጋር ሳያጋጫቸው እንደማይቀር የአንዳንዶች ግምት ነው፡፡ 

        ማህበሩ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀስ መሆኑ ከእስከዛሬው እንቅስቃሴው በግልጽ የሚታወቅ ነው። አንጻራዊ ሰላም የሚመስል ሁኔታ በቤተክርስቲያኒቱ ሲፈጠር ትኩረቱ ሁሉ ተሀድሶ መናፍቃን የሚል ስም በሰጣቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ይሆናል። ምክንያቱም ቤተክርስቲያኒቱ በእነርሱ አገልግሎት እየተሸፈነች ከመጣች እኔ ከጨዋታ ውጪ እሆናለሁ ብሎ ስለሚሰጋ ነው፡፡ ለፖለቲካው ምቹ የሆነ ነፋስ ሲነፍስ ደግሞ የሃይማኖት ካባን የደረበ እስከማይመስል ድረስ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ ያርፈዋል፡፡ 

         ሰሞኑን እየሆነ ያለውም ይኸው ነው፡፡ ብላቴ ላይ ለወለዱት ፖለቲከኛ አባቶቹ ባመቻቸው በዚህ ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም፣ በውጪ የተቃውሞ ፖለቲካቸውን ለማራመድ ልዩ ልዩ ስልቶችን እየተጠቀሙ ሲሆን፣ በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ እንኳ በሃይማኖት ሸፍነው ያሰሙት ዋና ድምጽ በሌሎች ሃይማኖት ለበስ መፈክሮች የታጀበ ይሁን እንጂ አሁን ያለው መንግስት እኛን አይወክልምና ይውረድ የሚል እንደነበር ቪኦኤ ላይ ቀርበው ከተናገሩ የሰልፉ አስተባባሪዎች ለመታዘብ ተችሏል። ይህም እነርሱን ያሳሰባቸው የገዳሙ ጉዳይ ሳይሆን ፖለቲካዊ ስልጣኑ ነው የሚል አንድምታን አሳድሯል፡፡ ገዳሙ ሽፋን ሆኖ ነው እያገለገለ ያለው፡፡ የማህበሩ ድረገጾችም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ሃይማኖትን እየቀባቡ ፖለቲካቸውን ማራመዳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ እየወጡ ያሉት ጽሁፎች፣ በወጡት ጽሁፎች ላይ እየተሰጡ ያሉ አስተያየቶችም ሁሉ ሃይማኖት ለበስ የፖለቲካ ሀሳቦች ናቸው፡፡ የሁሉም ጥያቄ ግን ማህበሩ ለምን ሚናውን አይለይም? የሚል ነው።


15 comments:

  1. The writer of this article, I believe, is a dying heretic who could not implement his hidden heretic agendas in the Church. MK is not voicing or opposing the projects underway in and around 'Waldiba' Monastery as it should have been. Even if it did so in the strongest terms, one cannot take it as political opposition; because this issue/ project/ directly infringes up on the rights of the church with enormous repercussions regarding the existence of the Monastery in the future. Therefore, in my view, the piece in the blog seems a product of grievances against the good job MK has done over the years in exposing the hidden heretics in the Church who associates themselves to the ruling politics to get cover and cheap support.

    ReplyDelete
    Replies
    1. አረ ባክህ!! አልክ እንዴ!! እነ አንድ አርገን ይመስክሩብሀ፡፡ የነ መለኩ እዘዘው የነ ብርሀኑ አድማሴ ፌስ ቡክ ፔጆች ይመስክሩብሀ!! ይልቅ አይነህን ከፍተህ ማህበርዋ የምትሰራውን ጥፋት ብታይ ይሻልሀል፡፡

      Delete
    2. ይህ ብሎግ አውደ ምህረት ሳይሆን አውደ ሰይጣን ነው መባል ያለበት። አይ መናፍቃን የተለያየ ብሎግ ብትከፍቱም ትታወቃላችሁ "በምግባራቸው ታውቋቸዋላችሁ" እዳለው ጌታ።

      Delete
  2. This article should be written by Aba Sereke and/or his supporters. It is not trusted and meaning less.

    ReplyDelete
  3. God Bless you the writer of this article, That is exactly what is going on. God open thair eyes too. Keep up the good work, Awde Mihret.

    ReplyDelete
  4. yezih article alamaw alegebagnem wendeme yehen zefen betedegagamo yeminagerut ye eslemena hayemanote teketayoch zefen new i think you are one of them.

    ReplyDelete
  5. ማህበረ ቅዱሳንንና አባ ሳሙኤልን ያገናኛቸው አጀንዳ ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን፣ የቤተመንግስቱንም የቤተክህነቱንም ስልጣን ጠቅልሎ መያዝ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። አባ ሳሙኤል ከልባቸው አልወጣ ያለውን ፓትርያርክ የመሆን ቅዠት ለማሳካት እየወደቁ እየተነሱ፣ የተለያዩ ክፍተቶችን እየተጠቀሙ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ላይ መፈንቅለ ፓትርያርክ ለማካሄድ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

    ይህንን ሐቅ የሚክዱ ማህበረ ቅዱሳንና አባ ሳሙኤል ብቻ ናቸው!!!!!

    ReplyDelete
  6. ማቅ ተረታ ተረት በማቅረብ የሕዝብንና የቤተክርስቲያንን ሀብት የሚዝረፍ የለየለት ፓለቲከኛ ድርጅት ነው ማኅበረ ቅዱሳን" የቤተክርስቲያንን አስተዳደር ተክቶ ዘመቻ እንዲያስተባብር፣ እንዲሳደብ፣ እንዲወቅስ፣ እንዲከራከር፣ ዕርዳታና መባዕ እንዲያሰባስብ ማንም ውክልና አልሰጠውም፤ አይሰጠውምም፡፡ ማንኛውም እንቅስቃሴው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንንና 50 ሚሊዮን የሚሆኑ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናንን አይወክልም፡፡ የማ/ቅ/ ዋና መነኸሪያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን መ/ቤት ነው፡፡ መ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሹን፤ ልዩ ልዩ ቢሮዎችንና መንግስት ንብረቶችን ያለክፍያ ማ/ቅ እንዲገለገልበት ያደርጋል፡፡ እንዲያውም የማ/ቅ ህንጻ ሲሰራ ብዙ የግንባታ ቁሳቁሶች የወሰደው ከመ/ቤቱ መሆኑን አንዳንድ ሰራተኞች በግልጽ ይናገራሉ፡፡ መንግስት ይህንንና ሌሎችንም መስሪያ ቤቶች የማህበሩ ስውር መጠቀሚያ መሆናቸውን አጣርቶ አርምጃ መውሰድ አለበት፡፡

    ReplyDelete
  7. Aye!!! abatachen mene nekah, tehadiso yemitilut yetebela ekube honbachihna
    ahun dgmo eslam alach-hu kikikikiki.... Ayi, mk??????? endew gira gebachu
    haimanot slelelach-hu eko new. menm degmo slmatawqu dnqoro worobla hulu tesebesebo nach-hu:::::

    ReplyDelete
  8. Ene endemegebagn yehenen ayenet astesasebena mereja bemalet yemedenakor atsirarebetekristian enje yebetekristeyan yekurt geze lej lehon aychilem.

    So live our church with out any baises

    ReplyDelete
  9. I believe the writer must be anti-orthodx church or a political activist for the ruling party. You are lighting a match on your hair that can first destroy your top physical body and later your life too. The life, history and presence of WALDIBA is the life, history and nature of Ethiopia. If you are a man who feels patriotism and heroes of this nation, you should respect and accept the private property of the people even if your religion is not Christian or other religious organizations. You shouldn't go in one way, but you have to ask this:"Why did the Ethiopian People go to the Ethiopian Embassy through peaceful demonstration in Washington DC?" They are not running to power. Rather, they are opposing the government's rule regarding to its principle, "State and religion are separated". The government should wind up and cut down his hand from Waldiba and other monasteries of the Ethiopian Orthodox churches. A ruling party who doesn't give any kind of humanity to the dignity his people can be said either dictator-observable & democrat- theoretical or authoritarian. Therefore,if the government is against our church, every christian should oppose it.

    ReplyDelete
    Replies
    1. because you mks are are politicians and anti orthodox you felt that every one is just like you. it is better to watch your self first. you truly know who is the enemy. you guys are the one.

      Delete
  10. above anonymous Apr. 3, 2012 05:57 AM. Awqehe motehal maferiya asmesaye
    ye-mk, jele. . mk be-haymanot eyasabebe yerasun agenda enedenante yalu
    jilochin yajajilal. yale mk eko ye-ewnetegna krestiyan mehon ychalal. Lemn
    ye-sitan mesariya tehonalachu? Krestos yastmarn ametse newn? betekrstiyanachens yastemarechin yihen newne? yasaznal::

    ReplyDelete
  11. You are indulged in paradox. You said ማቅ ተረታ ተረት በማቅረብ የሕዝብንና የቤተክርስቲያንን ሀብት የሚዝረፍ የለየለት ፓለቲከኛ ድርጅት ነው ማኅበረ ቅዱሳን" የቤተክርስቲያንን አስተዳደር ተክቶ ዘመቻ እንዲያስተባብር፣ እንዲሳደብ፣ እንዲወቅስ፣ እንዲከራከር፣ ዕርዳታና መባዕ እንዲያሰባስብ ማንም ውክልና አልሰጠውም፤ አይሰጠውምም፡፡ MK is operating under the umbrella of the church. If MK is a political association then the church is and Aba Paulos is the leader of that association. what are you talking about? who you are and from where you are? your words have revealed who you are!

    ReplyDelete
  12. wey gud demo enante min yemiluachu yeseytan milas nachu ? wey gize ere endew fetarin firu

    ReplyDelete