Monday, June 11, 2012

“በረከታችሁም” ሆነ “ውግዘታችሁ” ማንንም አያድንም አይገድልምም!

Click here to read in PDF
በትናንቱ ዕለት በምዕራቡ ዓለም የሰዓት አቆጣጠር ከለሊቱ 12: 00 (pm) ይሆናል (በሀገር ቤት የሰዓት አቆጣጠር ማለዳ መሆኑ ነው) ወደ አገር ቤት ስልክ መትቼ ነበር። የረጅም ዘመን ትውውቅና ወዳጅነት አለን ከትውውቅም ያለፈ የአባትነትና የልጅነት ያክል የጠበቀ ግኑኝነት ካለን አንድ የዕድሜ ባለፀጋ፣ የመጻህፍት አዋቂ፣ የሲኖዶስ አባልም የሆኑት አባት (ሊቀ- ጳጳስ) በስልክ ተገናኝተን “አውግተን” ነበር። ስልክ የመደወሌ ምክንያት ለሰላምታ ነው። መንፈስን የሚያሳርፍ መንፈሳዊ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላም “ጨዋታ ጨዋታን ያመጣዋል” እንደሚባለው አገልግሎትን በተመለከተ አንዳንድ ነገሮች ስናነሳ ያመራነው ወደ ቤተ-ክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ነበር። አንስተን ከተነጋገርንባቸው ዓበይት ቁምነገሮች መካከል እጅግ የገረመኝና ያሳዘነኝ በመጨረሻው ዕለት በመጨረሻዋ ሰዓት በጥቂት የሲኖዶሱ አባላት ተከሰተ ሲሉ ዝቅ ባለ ድምጽና በስብራት ያወጉኝን በጥቂቱ ለንባብ በሚያመች መልኩ ላካፍላችሁ ወደድኩ።
በዋናነት እኚህ ሊቀ ጳጳስ “ተዉ! እንዲህ ያለ ስህተት መስራቱ አስፈላጊ አይደለም። እየሆነ ያለውም አግባብነት የለውም ደግሞም በታሪክ የሚያስጠይቅ ውርደት እየፈጸምን ነው ያለነው። … እዚህ የተሰባሰብን ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሁላችን ሴራው ሳይገባን ቀርቶም አይደለም ታድያ ግን ነገም በቀረን በእኛ ላይ መነሳታቸው የማይቀር ጥቂቶችን ለማሰደሰት ሲባል ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን ጥሰን የገዛ ልጆቻችንን እየገፋን ነው ያለነው … ።” በማለት ድምጻቸውን ካሰሙ ጥቂቶች መካከል አንዱ ናቸው። 

Sunday, June 10, 2012

የአዶላ ከተማ የማኅበረ ቅዱሳን ተጠሪ የተማሪዎችን ፈተናና የፈተና ጣቢያውን ኃላፊ አገቱ

Click here to Read in PDF
ማኅበረ ቅዱሳን በተለያየ የአገሪቱ ክፍሎች ሁከት ማነሳሳትን አላማው አድርጎ ተያይዞታል። ጭር ሲል አልወድም በሚል ባህሪው የሚታወቀው ይሄ አሸባሪ ማኅበር አባላቱ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ሁከት እያነሳሱ ይገኛሉ። የዋልድባን ጉዳይ እነደ መንግስትን ማዳከሚያ ስልት እየተጠቀመበት ያለው ማቅ ደመቅ ባለበት ቦታ በቤተክርስቲያን ውስጥ፤ ምዕመኑ አነስተኛ በሆነበት ቦታ ደግሞ ባሉ ክፍተቶች ተጠቅሞ አመጽ ማነሳሳቱን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል።

ሰሞኑን ይህን እውነት የሚያጎላ ክስተት በጉጂ ዞን በጨንቤ ወረዳ ተከስቷል። የአዶላ ወረዳ የማቅ ተጠሪ የሆነውና ባለፈው የካቲት 16 በነበረው ግርግር አመጽ በማነሳሳት ታስሮ በገደብ የተለቀቀው ስምንት ስልጣንን ደራርቦ በያዘው ቀሲስ መኮንን ጉተማ አስተባባሪነት ሌሎች የማኅበሩ አባላት በሆኑ መምህራን አጋዥነት ክፍያ አነሰን በሚል ሰበብ የተማሪዎቹን ፈተናና የፈተና ጣቢያውን ኃላፊ ለሁለት ቀናት አግተው ቆይተዋል። የክብረ መንግስት ከተማ የሀገር አቀፍ ፈተናዎች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ግለሰቦቹ የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስድባቸው ለጉጂ ዞን ት/ቢሮ ደብዳቤ የጻፉ ሲሆን ለኦሮሚያ መንግስትና ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በግልባጭ አሳውቀዋል።

Friday, June 8, 2012

‹‹የባርነት ልጆች››(ገላ. 4፥21-31)

click here to read in PDF
የገላትያ መልእክት ዐቢይ ዓላማ በክርስቶስ አምነው ከጸጋው ቃል ወደ ኋላ በመመለስ እውነትን ይቃወሙ ለነበሩ ምዕመናን የተጻፈ ነው፡፡ ሐዋርያው በዚህ መልእክት ላይ የተለያዩ ምሳሌዎችን በመጠቀም እንዲሁም በቀደመው ኪዳን ስለበነሩ ነገሮች በመጥቀስ የገላትያ ምዕመናን አስቀድሞ ከተሰበከላቸው የክርስቶስ ወንጌል የተለየ ወንጌልን የሚሰብክላቸው ሰውም ይሁን መልአክ የተረገመ ይሁን! በማለት በሐዋርያዊ ሥልጣኑ ይገዝታል›› (ገላ. 18)፡፡
በገበሬ እርሻ ላይ ምርጥ ዘር ከተዘራ በኋላ ዘሩ መብቀል ሲጀምር ቀደም ያልነበረ ነገር መታየቱ አይቀርም፡፡ ይህም የሚሆነው መልካም ነገር ሁሉ ተቃዋሚ ስላለበት ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ መልካም ነገር ኃላፊነት ነው፡፡ ጥበቃና እንክብካቤም ይፈልጋል፡፡ ያለበለዚያ ለፍሬ አይበቃም፡፡ ጌታም በእርሻው ላይ ስለተዘራው መልካም ዘር ከተናገረ በኋላ ሰዎቹ ሲተኙ ጠላት መጥቶ እንክርዳድ እንደዘራና እንደሄደ ለደቀ መዛሙርቱ ሲናገር እናያለን፡፡ (ማቴ. 1324-30)
በዚህ ዘመንም በእውነተኛው የወንጌል አገልግሎት ላይ እንክርዳድ ለመዝራት የተሠማሩ፣ ሕዝብ የክርስቶስን ወንጌል እንዳይሰማ በተረትና በወግ እንዲሁም የራሳቸውን የጥቅም ፍላጎት ለማሳካት በሚያመች ሁኔታ ተብትበው ሕዝብን ለባርነት የሚወልዱ ብዙ ናቸው፡፡

Thursday, June 7, 2012

ዘሪሁን ሙላቱና ግራ የገባው ትምህርቱ

Click here in PDF
በዲያቆን ፈታሂ በጽድቅ
ዘሪሁን ሁሉን አዋቂ ሆኖ መታየት የሚፈልግ ሰው እንደሆነ  ብዙዎች ይናገሩለታል፡፡ ከጓደኞቹ ጋር አብሮ ተቀምጦ ከሆነ ከእርሱ በላይ እንደማያውቁ በአንድም በሌላም መንገድ መልእክት ያስተላልፋል፡፡ ከሁሉ ይልቅ አዋቂ እንደሆነ ሊያሳይ የሚፈልገው ዘሪሁን የሥላሴ ኮሌጅ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ስብከት እንጀራው መሆኑን በመናገር በተደጋጋሚ በአምላክ ሕልውና እንደማያምን ሊያስረዳ ይሞክር ነበር፡፡ እንደዚህ በድፍረትና በግልጽ ክህደቱን እየተናገረ ማንም ምንም ለምን እንዳላለው ግልጽ ባይሆንም የሥላሴ ቆይታውን በሰላም ጨርሶ ለመመረቅ በቅቷል፡፡የእግዚአብሄርን እውነት ስለተናገሩ መናፍቅ የሚባሉ ተማሪዎች ባሉበት ግቢ እንዲህ ዓይነት የከፋ ክህደት የሚያስተላልፍ ሰው ግን ምንም አለመባሉ አስገራሚ ነው፡፡
ከሃዲው ዘሪሁን ግን አሁንም የክህደት ትምህርቱን ማስተላለፉን አላቆመም፤ እንዲያውም ባሰበት እንጂ፡፡ ከምህረተ አብ ጋር በመሆን እየዘሩት ያሉትን የስህተት ትምህርት ዘር ምን እንደሚመስል በተከታታይ ልናስነብብዎ ጀምረናል፡፡
ኦርቶዶክስ መልስ አላት በሚል በጀመሩት መርሃ ግብር ላይ ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ የተሰጠበት ነው በሚል የቀረበው ቪሲዲ ለሕዝብ መልቀቁ ይታወቃል በዚህ ቪሲዲ ላይ ያስተላለፋቸውን ኑፋቄዎችና የክህደት ትምህርቶች ለጊዜው እናቆያቸውና አሁንም በዛው መድረክ ላይ እያቀረባቸው ያሉትንና አባቶች አይተው ወደ ኦርቶዶክሳዊት ትምህርት እንዲመለስ ቢመክሩት በሚል ያሰብናቸውን በተከታታይ እናቀርብሎታለን፡፡

Wednesday, June 6, 2012

አሁንም ከግብጽ ነጻ አልወጣን ይሆን?

click here to read in PDF
ቤተ ክርቲያናችን ራሷን ችላ ከመውጣቷ በፊት በግብጽ ሳንባ የምትተነፍስ ኢትዮጵያ ጎርሳ ወደግብጽ የምትውጥ እንደነበረች የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ከዚህም በመነሳት ይመስላል አንድ ሰው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እኮ ገና 100 ዓመት እንኳ ያልሞላት ታዳጊ ናት ሲሉ የተናገሩት፡፡
በግብጽ ሳንባ ከመተንፈስና በግብጽ ጭንቅላት ከማሰብ ነጻ ወጥተናል አሁን በባዕድ ሳይሆን በአገር ልጅ የቤተ ክርስቲያናችን ነገር ግድ በሚላቸው በራሳችን ሰዎች ነው የምንተዳደረው ብለን ሐሴት ማድረግ ሳንጀምር የአገር ልጅ መሳይ ግብጻዊ ቤተ ክርስቲያናችንን እንደወረራት ዓይናችን አይቶ ልባችን አዘነ፡፡
ግብጻዊያኑ ሲመሩን (ሲገዙን ብለው ይሻል ይሆን?) ቋንቋቸው ከቋንቋችን ስለማይገጥም በመንፈሳዊው ረገድ ምንም የሰጡን አገልግሎት የለም ለማለት ያስደፍራል፡፡ ከዚህም በመነሳት ጥቅማቸው ለአገራችን ሳይሆን ለአገራቸው ብቻ ነበር ቢባል ስህተት አይሆንም፡፡ ማቅ ሳያውቃቸው አውቃቸዋለሁ እያለ የሚሟገትባቸው አቡነ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በተሰኘው መጽሐፋቸው ግብጻዊያን ‹‹ክርስቲያን›› ጳጳሳት ሰማያዊውን ገዢ እግዚአብሔርን ለማገልገል ሳይሆን ምድራዊውን ንጉሳቸውን ለማስደሰት መስጊድ ያሰሩ እንደነበረ ያሰፈሩትን መመልከቱ ወደ ኢትዮጵያ የመምጣታቸው ጥቅም ለማን ነበር? የሚለውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን እነዚህን ጳጳሳት ለማስመጣት በወቅቱ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ነገስታት ብዙና ብዙ እጅ መንሻ የሚሆን ሐብት ወደ ግብጽ ይልኩ እንደነበረም ብጹሕነታቸው አስፍረውልናል፡፡

Monday, June 4, 2012

መምህር ዘበነ ለማ መመሪያ አክብሮ እንዲሠራ ደብዳቤ ተጻፈለት

Click here to read in PDF

የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውንና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተሰጠውን መመሪያ ጥሰዋል ያለፈቃድም ሰብከዋል በሚል ለመምህር ዘበነ ለማ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጻፈ። ደብዳቤውን የጻፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣ ዘበነ መኖሪያውን በአሜሪካ ቢያደርግም በእናት ቤተክርስቲያን ውስጥ እያገለገለ ለመሆኑ የሚያስረዳ ደብዳቤ በአሜሪካ ከሚገኘው ሀገረ ስብከት ይዞ መምጣት ሲገባው እርሱ ግን ያለ ፈቃድ እየተዘዋወረ በመስበክ የስብከተ ወንጌል መምሪያ ውሳኔዎቹን ለማስፈጸም በሚያደርገው ጥረት ላይ አፍራሽ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ደብዳቤው ገልጾ፣ ከዚህ በኋላ ከሚኖርበት ሀገረ ስብከት በእናት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ካላመጣና እንደለመደው እሰብካለሁ ቢል ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማድረግ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾአል።

መምህር ዘበነ ነዋሪነቱን በአሜሪካ አድርጎ ከሁለቱም ሲኖዶሶች ውጪ ነኝ በሚል በገለልተኛነት የሚኖር ሲሆን፣ እንዲህ ያደረገውም ወደ አገር ቤት ብቅ እያለ በስብከተ ወንጌል ስም ቢዝነሱን የሚሰራበት በር እንዳይዘጋበት ሲሆን፣ በሌላም በኩል በውጪ ያለው ዳያስፖራ ማህበረሰብ ደግሞ ከአገር ቤቱ ሲኖዶስ ጋር ነው የሚሰራው እንዳይለው በማሰብ ነው።  

Sunday, June 3, 2012

የቀረባችሁ የእግር ጉዞ ብቻ ነውን?

በትናንትናው ዕለት ማኅበረ ቅዱሳን ላለፉት ሦስት ወራት የ20ኛ ዓመት መርሐ ግብር ዋና በዓል አድርጎ ሲቀሰቅስበት የነበረው የእግር ጉዞ ከማኅበሩ ነውጠኛ ባህሪ የተነሳ እንዲካሄድ እንዳልተፈቀለት ዘግበን ነበር። ትናንት ከሰዓቱን የማኅበሩ አመራሮች በሙሉ ኃይላቸው ሰልፉን ለማስፈቀድ ቢሯሯጡም የማንአለብኝ ባህሪያቸውን በሚያስተነፍስ መልኩ ፈቃዱን ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል። በተለይም አውደ ምሕረት ጉዳዩን ከዘገበች በኃላ አብዛኛው የማቅ አመራሮችና አቸፍቻፊዎች እኛን ውሸተኛ ለማድረግ ቢሯሯጡም ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
ነገሩ እንዳልተሳካላቸው  አርፍደውም ቢሆን የተረዱት የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች በዛሬው ዕለት በህጋዊ ዌብ ሳይታቸው ሰበር ዜና፡ የእግር ጉዞው መርሐ ግብር ተቀየረ፡፡ በማለት ሳያቅዱ እንደሚሰሩ ያረጋገጠ ዜና ጽፈዋል። በጻፉት ዜና ላይ የጉዞው መርሐ ግብር ለመቅረቱ ተጠያቂው ቤተክህነት መሆኑን “ጠቅላይ ቤተ ክህነት መጻፍ ያለበትን ደብደቤ ባለመጻፉ ” በማለት ገልጸዋል። ጉዞውን ለማድረግ ከስድስት ወር በፊት ያቀዱትና ለጉዞው ከሶስት ወር በፊት ጀምሮ ማስታወቂያ እያስነገሩ የነበሩት የማቅ አመራሮች ፈቃድ የጠየቁት ጉዞው ሶስት ቀን ሲቀረው መሆኑን ዘንግተው የወታደራዊ ጉዞ ናፍቆታችንን ያልተወጣነው የጠቅላይ ቤተክህነት ሰራተኞ ስላልተባበሩን ነው በማለት የለመዱትን ለጥፋታቸው ሌሎችን የመውቀስ አባዜያቸውን ተጠቅመዋል።
በየትኛውም አገር ቢሆን ማንኛውም ሰልፍ አዘጋጅ የሰልፉን ቀን የሚያስታውቀው ፈቃድ ካገኘ በኃላ ነው እነጂ ፈቃዱ ሳይጠይቅ በፊት ቀን ቆርጦ በዚህ ቀን የሚል ማስታወቂያ ማድረግና ትኬት መሸጥ አይጀምርም። ነጋዴው ማኅበር ግን ገንዘብ መሰብሰብ አላማው ስለሆነ አንዳች ፈቃድ ሳይጠይቅ ሰልፍ የሚያድርግበትን ቀን እየገለጸ ትኬት መሸጥ መጀመሩ አስተዋይ አዕምሮ ላለው ሰው የአመራሩን ብቃት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው።መልዕክቱ ብቻ ሳይሆን እቅዱም የተሰበረውን ዜና በዌብሳይት እንደለቀቁም ትኬቱን ለገዙ ሰዎችና ለማህበሩ የልብ ሰዎች በእንግሊዝ አፍ እንዲህ የሚል የጽሁፍ መልዕክት አስተላልፈዋል የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን፣ እናዝናለን በቤተክህነት ምክንያት ጉዟችን ወደ ቤተ ክህነት አዳራሽ  ጉባኤነት ተለውጧል።  የሚጀመረው ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን! ደውሉልን’’ ይልና ስልክ ቁጥር አስቀምጧል።  

Friday, June 1, 2012

ፈቃድ ሳይጠየቅበት ቅስቀሳ ይደረግበት የነበረው የማኅበረ ቅዱሳን ጉዞ ታገደ

Click here to read in PDF
ምስረታውን በብላቴን ማሰልጠኛ ጣቢያ በወታደራዊ ሰልፍ ያከናወነው ማቅ 20ኛ አመቱን ለማክበር አስቦት የነበረው አመሰራረቱን የሚያስታውስ ሰልፍ እንዳይካሄድ ተከለከለ። ከዚህ ቀደም ሚያዝያ 27/2004 በተሰላፊ እጦት ሳይደረግ የቀረውና ለግንቦት 26 ዳግም የተቀጠረው የማቅ ሰልፍ መከልከሉ ማቅ አክራሪ ጠባዩን በአደባባይ እንዳያሳይና የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት አደጋ ላይ እንዳይጥል የተወሰደ እርምጃ ተደርጎ በብዙ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ተወስዷል። አሁንም ቢሆን ቲኬት የሚገዛው ሰው ብዛት አናሳ መሆኑ እየተነገረ ሲሆን የማቅ የገንዘብ ትርፍ በዚህ ሰልፍ ስኬታማ እንደማይሆን ታውቋል። ቀድሞም ቢሆን ዋናው የማቅ አላማ የዋልድባውን ጉዳይ በአገር ውስጥ ይበልጥ ለማቀጣጠልና ከውጪው ፖለቲካዊ ትግል ጋር ለማዋሀድ በመሆኑ ቲኬት ገዝቶ የሚሰለፍ ቢታጣ እንኳ አባላቱን፣ አንዳንድ የሰንበት ተማሪዎችንና የኮሌጅ ተማሪዎችን ይዞ ሰልፉን ለማካሄድ ቆርጦ ነበር ተብሏል።
ከማንኛውም የመንግስት አካል ፈቃድ ጠይቆበት ያልነበረው እና እንደተፈቀደለት ሳያረጋግጥ ከፍተኛ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰራ የነበረው ማቅ በዚህ ሳምንት ሰልፉን ለማስፈቀድ ከረቡዕ ጀምሮ ሲሯሯጥ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ባለን መረጃ ፈቃድ ማግኘት እንዳልቻለና ፈቃድ አጠያየቁ በቂ ጊዜ ያልቀረበበትና የአካሄድ ችግር ያለበት በመሆኑ እንደተከለከለ ማረጋገጥ ችለናል።
በተመሳሳይም በአዋሳ ከተማ አስበውት የነበረው ሰልፍ በአቡነ ገብርኤል ይሁንታን አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ከተማዋ ካለባት የቤተክርስቲያን ሰዎች ክፍፍል እና አለመግባባት የተነሳ ፈቃድ የተጠየቀበት ጊዜ አጭር በመሆኑ ከመንግስት አካል ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል።