Sunday, June 3, 2012

የቀረባችሁ የእግር ጉዞ ብቻ ነውን?

በትናንትናው ዕለት ማኅበረ ቅዱሳን ላለፉት ሦስት ወራት የ20ኛ ዓመት መርሐ ግብር ዋና በዓል አድርጎ ሲቀሰቅስበት የነበረው የእግር ጉዞ ከማኅበሩ ነውጠኛ ባህሪ የተነሳ እንዲካሄድ እንዳልተፈቀለት ዘግበን ነበር። ትናንት ከሰዓቱን የማኅበሩ አመራሮች በሙሉ ኃይላቸው ሰልፉን ለማስፈቀድ ቢሯሯጡም የማንአለብኝ ባህሪያቸውን በሚያስተነፍስ መልኩ ፈቃዱን ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል። በተለይም አውደ ምሕረት ጉዳዩን ከዘገበች በኃላ አብዛኛው የማቅ አመራሮችና አቸፍቻፊዎች እኛን ውሸተኛ ለማድረግ ቢሯሯጡም ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
ነገሩ እንዳልተሳካላቸው  አርፍደውም ቢሆን የተረዱት የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች በዛሬው ዕለት በህጋዊ ዌብ ሳይታቸው ሰበር ዜና፡ የእግር ጉዞው መርሐ ግብር ተቀየረ፡፡ በማለት ሳያቅዱ እንደሚሰሩ ያረጋገጠ ዜና ጽፈዋል። በጻፉት ዜና ላይ የጉዞው መርሐ ግብር ለመቅረቱ ተጠያቂው ቤተክህነት መሆኑን “ጠቅላይ ቤተ ክህነት መጻፍ ያለበትን ደብደቤ ባለመጻፉ ” በማለት ገልጸዋል። ጉዞውን ለማድረግ ከስድስት ወር በፊት ያቀዱትና ለጉዞው ከሶስት ወር በፊት ጀምሮ ማስታወቂያ እያስነገሩ የነበሩት የማቅ አመራሮች ፈቃድ የጠየቁት ጉዞው ሶስት ቀን ሲቀረው መሆኑን ዘንግተው የወታደራዊ ጉዞ ናፍቆታችንን ያልተወጣነው የጠቅላይ ቤተክህነት ሰራተኞ ስላልተባበሩን ነው በማለት የለመዱትን ለጥፋታቸው ሌሎችን የመውቀስ አባዜያቸውን ተጠቅመዋል።
በየትኛውም አገር ቢሆን ማንኛውም ሰልፍ አዘጋጅ የሰልፉን ቀን የሚያስታውቀው ፈቃድ ካገኘ በኃላ ነው እነጂ ፈቃዱ ሳይጠይቅ በፊት ቀን ቆርጦ በዚህ ቀን የሚል ማስታወቂያ ማድረግና ትኬት መሸጥ አይጀምርም። ነጋዴው ማኅበር ግን ገንዘብ መሰብሰብ አላማው ስለሆነ አንዳች ፈቃድ ሳይጠይቅ ሰልፍ የሚያድርግበትን ቀን እየገለጸ ትኬት መሸጥ መጀመሩ አስተዋይ አዕምሮ ላለው ሰው የአመራሩን ብቃት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው።መልዕክቱ ብቻ ሳይሆን እቅዱም የተሰበረውን ዜና በዌብሳይት እንደለቀቁም ትኬቱን ለገዙ ሰዎችና ለማህበሩ የልብ ሰዎች በእንግሊዝ አፍ እንዲህ የሚል የጽሁፍ መልዕክት አስተላልፈዋል የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን፣ እናዝናለን በቤተክህነት ምክንያት ጉዟችን ወደ ቤተ ክህነት አዳራሽ  ጉባኤነት ተለውጧል።  የሚጀመረው ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን! ደውሉልን’’ ይልና ስልክ ቁጥር አስቀምጧል።  
ዜናውን የማኅበሩ አባላት በፌስ ቡክ የተቀባበሉት ሲሆን ደቂቀ ናቡቴ የሚባል የማቅ ፌስ ቡክ ገጽ “የማኅበረ ቅዱስንን ፳ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በማስመልከት ግንቦት 26 የተዘጋጀው የእግር ጉዞ ቤተ ክህነት አና ቤተ መንግስት በመተባበር አገዱት” በማለት ለምን ቤተክህነት ብቻ መንግስትም ከወቀሳው ይቅመስ እንጂ የሚል መልእክት አስተላልፏል። አንድአድርገንም እንዲህ ሲል አግዞታል። በመሰረቱ ከቤተክህነቱ ይህ ደብዳቤው ወደ አዲስ አበባ መስተዳር ቢሄድም ያለ ጥያቄ ጉዞ ይፈቀዳል የሚል እምነት የለንም”
በእኛ አስተያየት ጉዞውን ማንም ያግደው ማንም ጉዞው ከማኅበሩ ነውጠኛ ባህሪ አንጻር መታገዱ ተገቢ ነው እንላለን። በተለይም ጉዞው ሰሙ የማኅበሩ 20ኛ አመት ወርቁ ደግሞ ዋልድባን አስመልክቶ የሚደረግ የተቃውሞ ሰልፍ ስለነበር የማኅበሩ አመራሮች “ነገር ያደግንብሽ እንዴት አደርሽ?” ለማለት የነበራቸውን ናፍቆት ክልከላው አምክኖታል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የማኅበሩ ህጻናተ አዕምሮ አንድአድርገኖች “የቀረብን የእግር ጉዞ ብቻ ነው” በሚል ርዕስ አጭር ዜና የሰሩ ሲሆን በዚህም የተውተረተረ አጻጻፋቸው የብሎጉ ባለቤት ማን እንደሆነ አሳውቀውናል። “የቀረብን የእግር ጉዞ ብቻ ነው” በሚለው ርዕስና “እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ ” በሚለው ባለቤትን በሚያመለክት አንቀጽ አንድ አድርገን የማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን ነግረውናል። በዚህም በከፍተኛ ደረጃ መንግስትን ከተቃማዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች በላይ በመቃወምና ቤተክርስቲያንን ተጠልለው ፖለቲካዊ አላማቸውን ለማሳካት በመፍጨርጨር ላይ ያሉት ማቆች የበሬ ወለደ ዘገባዎቻቸውን በአንድ አድርገንና መሰል ብሎጎች የሚያቀርቡት በአላማ መሆኑን አረጋግጠውልናል።

ከአፈርኩ አይመልሰኝ በማለት የቀረብን የእግር ጉዞ ብቻ ነው በሚል ለጻፉት አንድ አድርገኖች በርግጥ የቀረባችሁ የእግር ጉዞ ብቻ ነውን? ስንል እንጠይቃቸዋለን። በእግር ጉዞው ሰበብ ልታደርጉት የነበረው አመጽ፣ ተጽእኖ ፈጠራ፣ የፖለቲካ ትርፍ እና ከሁሉ በላይ የነበራችሁ ከፍተኛ ትምክህት ውሃ በልቶታል።
ከፎቶግራፋቸው በቀር ትምህርታቸውንም አገልግሎታቸውንም የማያውቁትን የአቡነ ጎርጎሪዮስን  ፎቶ ፊት ለፊት ለጥፈው የሊቅ ወዳጅ ነን እወቁን በሚል መንፈስለሁለንተናዊ ቤተክርስቲያን እድገት አብረን እንሥራ ኑ ! ጉዞውን አብረን እንጓዘው” በማለት ባዘጋጁት ፖስተር ጉዞው ለማህበረ ቅዱሳን ምን ማለት እንደሆነ ሲቀሰቅሱበት እንዳልነበር አሁን ሳይሳካ ሲቀር ደግሞ ከእርምጃ ምን ይቀራል? ማለታቸው አስገርሞናል።
ማኅበረ ቅዱሳን ከመመስረቱ ከሁለት አመት በፊት የሞቱት አቡነ ጎርጎርዮስ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በትምህርትም በአቋምም እንደማይተዋወቁ መጽሐፍቶቻቸውን ያነበበ ሰው የሚያውቀው እውነት ነው። አባቶቻችን አባቶቻችን እያለ የአባቶቻችንን ትምህርት ትቶ የራሱን አዲስ ዶክትሪን የፈጠረው ማኅበረ ቅዱሳን እንዲያውም ብጹዕነታቸው ከሚያስተምሩት ትምህርት አንጻር በዚህ ጊዜ ቢኖሩ፣ ሚሥጢረ ስላሴም ክብረ መቋሚያም አንድ ናቸው ብሎ በሚያምነው የጨዋ ጸባዩ አማካኝነት ይወገዙልኝ ሲል መጠየቁና  ዶግማንና ሥርዓትን ተግሳጽና ሚሥጢራትን ለይተው በማያውቁ አንዳንድ የሊቃውንት ጉባዔ አባላት አማካኝነት ሊያስወግዛቸው የሚችሉ አባት መሆናቸው  ግልጽ ነው።
ልትሰሩት የፈለጋችሁት የተጋነነ ዜና ማንም አያቆመንም የሚል ትዕቢታችሁ ጉዞውን ታሪካዊ ብላችሁ ልትገልጹበት የነበረው መንገድና ከጉዞው ጋር ኣያይዛችሁ ልታጋብሱት የነበረው ገንዘብ ጭምርም ቀርቶባችኋል። በመሰረቱ የምስረታ በዓሉ ብላችሁት የነበረው ጉዞውን ራሱን ስለነበር የምስረታ በዓሉም ጭምር ቀርቶባችኋል።
የደረሰባችሁንስ የሞራል ስብራት ያልጠበቃችሁት ስለሆነ ያገኘነው ትርፍ ትሉት ይሆን? 

3 comments:

  1. Woregnoche lemen selesew taworalachu selerasachu asebu!!

    ReplyDelete
  2. this is not a news. It is a hate on Ethiopianism and Orthodox follower. Time will come. we will stand as strong and firm.

    ReplyDelete
  3. በልዎ ለአግዚአብሔር ግሩም ግብረከ

    ReplyDelete