Monday, June 4, 2012

መምህር ዘበነ ለማ መመሪያ አክብሮ እንዲሠራ ደብዳቤ ተጻፈለት

Click here to read in PDF

የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውንና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተሰጠውን መመሪያ ጥሰዋል ያለፈቃድም ሰብከዋል በሚል ለመምህር ዘበነ ለማ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጻፈ። ደብዳቤውን የጻፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣ ዘበነ መኖሪያውን በአሜሪካ ቢያደርግም በእናት ቤተክርስቲያን ውስጥ እያገለገለ ለመሆኑ የሚያስረዳ ደብዳቤ በአሜሪካ ከሚገኘው ሀገረ ስብከት ይዞ መምጣት ሲገባው እርሱ ግን ያለ ፈቃድ እየተዘዋወረ በመስበክ የስብከተ ወንጌል መምሪያ ውሳኔዎቹን ለማስፈጸም በሚያደርገው ጥረት ላይ አፍራሽ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ደብዳቤው ገልጾ፣ ከዚህ በኋላ ከሚኖርበት ሀገረ ስብከት በእናት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ካላመጣና እንደለመደው እሰብካለሁ ቢል ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማድረግ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾአል።

መምህር ዘበነ ነዋሪነቱን በአሜሪካ አድርጎ ከሁለቱም ሲኖዶሶች ውጪ ነኝ በሚል በገለልተኛነት የሚኖር ሲሆን፣ እንዲህ ያደረገውም ወደ አገር ቤት ብቅ እያለ በስብከተ ወንጌል ስም ቢዝነሱን የሚሰራበት በር እንዳይዘጋበት ሲሆን፣ በሌላም በኩል በውጪ ያለው ዳያስፖራ ማህበረሰብ ደግሞ ከአገር ቤቱ ሲኖዶስ ጋር ነው የሚሰራው እንዳይለው በማሰብ ነው።  

ዘበነ በአገር ውስጥና በውጭ አገር አክራሪነትን የሚሰብክና ክርስቲያኖች ተቻችለውና ተከባብረው እንዳይኖሩ የሚያደርጉ ርእሶችን በማንሳት፣ በስብከት ንግድ ለመክበር የሚሠራ ሰው እንደሆነ አሜሪካ ውስጥ በሬዲዮ ከሚያስተላልፋቸው ፕሮግራሞችና አልፎ አልፎ ከአሜሪካ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገባቸው ገበያ ተኮር ርእሶች፣ በአገር ውስጥም የሚያገኛቸው አንዳንድ በመለያየት ላይ የሚያጠነጥኑ ርእሶች ምስክር ናቸው። ዘበነ የወንጌልን ዓላማ ስላልተረዳና እንዲረዳም ስለማይፈልግ፣ ይሸጥልኛል ብሎም ስለማያስብ እስካሁን የወንጌልን እውነት የሚገልጥ የቪሲዲም ሆነ የካሴት ስብከት አላቀረበም።

 

 ድብዳቤውን ለማንበበብ ይሔንን ይጫኑ

 

ዘበነ በትምህርት ቤት ሳለ የስብከት ዘዴ የሚያስተምሩት የነበሩት የእህት አብያተ ክርስቲያን መምህር የትምህርቱ ይዘት ተማሪዎቻቸው ምን ያህል እንደገባቸው በሚገመግሙበት የሙከራ ስብከት ጊዜ ገና ስብከቱን ሲጀምር እየጮኸ ስለሚያስቸግራቸው ስብከት ጩኸት አይደለም እያሉ የሙከራውን ስብከት እያቋረጡ ያስቆሙት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። አዋቂ ነኝ ከሚል እሳቤ ውጭ መማር የሚፈልግ ማንነት ስለሌለው አሁንም ስብከት ካልጮኸ የማይደምቅ እንደሚመስለው የሚታይ እውነት ነው።

ዘበነ ከማን እንደተማረውና ከየት እንዳገኘው ባይታወቅም ክብርን ለራሱ በማከማቸት የሚታወቅ ሲሆን ከአሜሪካን ሲመጣ ለሚያውቃቸው ሰባኪያን እየደወለ ልመጣ ነውና ቀሚስ ለብሳችሁ ተቀበሉኝ በማለት እየደወለ በመጥራት የታወቀ ሰው ነው። ለስብከት ከቦታ ቦታ ሲዘዋወር ያለ አጃቢ የማይዘዋወር ሰው መሆኑ አላማው ምንድን ነው? የሚያሰኝ ነው። በአንድ ወቅት ከአሜሪካ ሲመጣ ከስብከት በኃላ እንደ ዘፋኝ እየፈረመ ረዥም ጊዜ ይወስድ እንደነበር የምናስታውሰው እውነት ነው።

አላማው ሕዝቡ እውነትን እንዲያውቅ ሳይሆን፣ እርሱ የሚያውቀውንና ሁሌ ከአፉ የማይለየውን “አውሬው” የሚለውን ስም ብቻ እንዲያጠናና በስጋት እንዲሞላ ለማድረግ ነው። ይህም ፍሬ አልባ ትምህርቶቹ የሚጠቀምበት እውነቱ ያልገባቸውና እንደዘበነ ያሉ ጆቢራዎች ያቀረቡላቸው ሁሉ እውነት የሚመስላቸው ወገኖች ገዝተው የእነዘበነን ኪስ እንዲሞሉና እነርሱ ግን የወንጌሉ ዓላማ ሳገባቸው እንዲሁ ስለ ልዩነት ብቻ በማሰብ በእነርሱ ጉንጭ አልፋ ክርክር ውስጥ ጠፍተው እንዲኖሩ ለማድረግ ነው።

የወንጌሉን ዓላማ ከተረዱ ግን የእነርሱን የተሳሳተ አስተምህሮ እንደማይቀበሏቸውና የስብከት ገበያቸው እንደሚቀዘቅዝ  ስለሚያውቁ፣ ሁሌ ስለመለያየት በሚሰብክ አመለካከት ስለተጠመዱ፣ የዕውር መሪዎች መሆንን መርጠዋል። በእውነትም ለሕዝቡ የወንጌል እውነት ማለትም «የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።» (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡4) ተብሎ እንደተጻፈው ሰይጣን ብቻ ሳይሆን ለሆዳቸው ያደሩ አንዳንድ ሰባኪዎችም ለጥቅማቸው ሲሉ ሕዝቡን ማሳታቸውን በመቀጠላቸው የስብከተ ወንጌሉ መመሪያ ተግባራዊ መሆኑ ጠቃሚ ነው።

19 comments:

  1. Wey Zebe we have told you that to be humble to serve the crowd of God but you put yourself on the roof and you wanna play the game here and there.
    Please Zebe the time is yet sit and evaluate your service for the past ten years what you preached.
    I hope you will wake up and serve humbly.

    Thanks

    Your batch

    ReplyDelete
  2. Mr Zebene Bichawn Yebela Bichawn Yimotal yibalal
    Mr Abunu-Mr Nehimiya-Kesis Sebisbe-D.Getahun-
    Abba Gebre wold -Abba Filipos Degimos shimagilew Astedadar Wedet Nachew ?Wonadimochin Mewdedi -melkam negeri new

    ReplyDelete
  3. zebe endet nehe, selam new? bel teregagethe asbe. ende fenta ezam ezam atzelele

    ReplyDelete
  4. ebakachu hul;achum este betkirystiananen ensasebat, hule kesena zelefa becha aykebdem ende.yehe manenem ayantem ,pls este enante men serachu ???? ken lebe yenuren,amlakachen hulachenemm yirdan,emamlake anche tawkiyalesh.
    kidest betikrtiyanchenen kefetena yetibkenenn,amen.

    melkam yetome wekete yehunlen,amen

    ReplyDelete
  5. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete
  6. what about dn andulem ?

    ReplyDelete
  7. it is a good decision.

    ReplyDelete
  8. ya,this is good thing. minawn meleyet alebet he is a good merchant he kill orthodox church....i know he is serving people not a God,usa different teacher in addis different......be hulet bila atebla"
    Memeher Abunu u try to acting like him pls.......rashen feleg

    ReplyDelete
  9. please please ers bersachin bantechachi tiru yimeslegnal enante
    yekinat menfes yitayibachihual. be midia kemetechet
    ye memihir zebenen yakil bitseru kinatachihu yiberdal

    ReplyDelete
  10. ይህ ደብዳቤ ስለምን ለፌደራል ፖሊስ በግልባጭ ሳይላክ? ረስተውት ስለሆነ እባካችሁ ንገሩልን። ለፌደራልፖሊስ፤ ለአዲስ አበባ መስተዳድር እና ለጠቅላይ ሚነስቴር ቢሮ ግልባጭ ቢደረግ ጥሩ ነው።

    ReplyDelete
  11. የነዘበነ ጊዜ እያከተመ ነው። የነ ፊደል ገደሉ ለብ-ለብ ሰባኪያን ጊዜ እያበቃ ነው። የዛሬ አያርገው እና በየስቴቱ እነሱ የሌሉበት ንግስ እማይታሰብ ነበር። ዛሬ ምእመኑ በካድሬዎችና በሊቃውንት መካከል ያለው ልዩነት እየገባው እሚጠሩበት ደብር በቁጥር ነው። አገር ቤት ሂዶ በእንተ ጳውሎስ እዚህ መጥቶ በእንተ ገለልተኛ እያሉ ለሁለት ጌታ ማደር ያሳፍራል። ክርስትና "ኦፕሽናል" የሚባል ነገር የለውም። "እመኒ እወ ወእመኒ አልቦ" ብቻ ነው። ሕርያቆስ

    ReplyDelete
  12. እንዴት አንድ ወንጌላዊ ለ10 ዓመት ሙሉ በአሜሪካ ምድር ላይ ስለ ጴንጤና ስለ "አውሬው" በMediaና በመድረክ ላይ ቆሞ ይናገራል? የቤተክርስቲያንስ ዋና ዓላማዋ ስለ መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መመስከርና መስበክ አይደለምን?

    ጌታችን "ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ" እንዳለ it is so apparent the moment you walk in his weekly Monday sermon, no kind of spirituality exists. One person told me all the people at Zebene's program sitting on the front rows are the same people at Babylon nightclub at the dance floor. This is because his teaching is solely based on slandering Protestants and he is famous for attacking a straw man. I have stopped my own sister from attending his sermon because I realized he is committed with passion to brainwash people and to lead people astray; and eventually have asinine thoughts.

    Also about the Mother of Our GOD, the Virgin Mary. Those who attend his congregation say some non biblical stuff to come to their skewed conclusion concerning the Virgin Mary. He says, well before the annunciation, the Virgin knew she was going to bore the son of GOD. That is the most unbiblical and baseless teaching. I have asked church fathers and none of our fathers taught such dogma. This is Minfikina!!

    Off all the people Mahibere kidusan labeled "tehadiso", I wonder why they are so reluctant to label him so. In my personal opinion, Mk and Zebene are two complete opposites; Zebe is just fame starved individual unlike anyone else in our church. At least MK has good intentions; but we all know where good intentions lead to. "ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው።" ምሳሌ 16:25 እንደተለዉ ሆኖባቸው ነው።

    Anyway, lehulachinim mastewalun Yadilen

    ReplyDelete
    Replies
    1. መ/ር ዘበነ ታገደ ወይስ ወንጌል ታገደ ለመሆኑ አሁን ዘበነን ያገዱ ሰዎች ዘበነ በሚያገለግልበት በዚያ ማንም ባልነበረበት ሰዓት የት ነበሩ ፀሐፊው ያሳዝናል ስለ ዘበነ መታገድ ያነሳቸው ሀሳቦች ሙሉ በሙሉ ስህተቶች ናቸው በእርግጠኝነት መጋቤ ሐዲስ አእመረም ደብዳቤውን የፃፈው ፊርማውን ለማስተዋወቅ አይደለም ተገዶ ነው እባካችሁ ለሕዝብ በሚደርስ መረጃ ላይ ይህን የሚያክል ስህተት አትስሩ ዘበነ ለመሆኑ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ለንግድ ነው ያ ዘመን ደረሰ ማለት ነው ሰዎች በዲቪ ወደ ኢትየጵያ የሚመጡበት ዘመን ፀሐፊው ዘበነ እዚህ ሀገር ደሞዝ እየከፈላቸው የአብነት ትምህርት የሚያስተምሩ ብዙ የአብነት መምህራን እንዳሉ ታዉቃለህ ዘበነ የሚረዳቸው ብዙ ችግረኞች እንዳሉስ ታውቃለህ መምህር ዘበነ የታገደበት ጉዳይ ሌላ ነው እጅግ ሌላ መምህር ዘበነ የለብለብ መምህር ነው ያልከው ዘበነ ከዚህ ሀገር ሲወጣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቃነ ጳጳሳቱን ሰብስበው የተማረ አትወዱም የተማረ የሚወድ ወሰደው ብለው መቆጨታቸውን ሰምተህ ይሆን ነው ይሄ ስህተት ብቻ ማነፍነፍ የለመደው ጆሮህ ዘበነ ሲጮህ ከለከሉት የሚለውን ብቻ ነው የሰማህው ሳዝናል መጋቤ ሐዲስስ ያላምንክበት እንድትፈርም ሲያደርጉህ የቤተ ክህነትን አሰራር በቃ ተላምደህ ለመኖር ወስነህ ነው ወይስ ብቻ ምዕመናን በዚያም ይሁን በዚህ ወንጌል እየታገደ ነው አቡነ . . . . አሁን እንቅልፍ ወሰደዎት ወይስ ገና ቪዛ ያስከለክሉት ይሆን ለዘበነ ምንም አይደል ወንጌሉ ፍሬ አፍርቶ ፀጠላት አስነሳበት እንጂ እንግዳ ነገር አይደለም ዘቤ በርታና ወንጌል ስበክ ወንጌል ስትሰብኩ ትከበራላችሁ ትመሰገናላችሁ የሚል ወንጌል አልያዝክም አይደል በርታ

      Delete
    2. ዘበነ ወንጌል እንደሚያስተምር አድርገህ ያሰፈርከውን ፈገግ ብዬ አነበብኩትና ወንጌል የሚባለው ምን እንደሆነ እንዳልገባህ ስለተረዳሁ ዳግመኛ እንደዚህ ዓይነት ሐሳብ እንዳታሰፍር ላስታውቅህ ይህን አጭር መልእክት ለአንተ አሰፈርኩ፡፡ እባክህ ወንድሜ ወንጌልና ተረትን ለይ፡፡ ዘበነ የተረት አባት ነው እንጂ የወንጌል አስተማሪ አይደለም እስከዛሬ በቪሲዲ ለገበያ ያቀረባቸውን ስብከቶች መመልከቱ ብቻ በቂ ምላሽ ለማግኘት ይረዳል፡፡
      ደቂቀ አቡየ ነኝ

      Delete
  13. በደብዳቤው የምትቆጡት በሙሉ ሕገ እንዳይከበር የምትፈልጉ ናችሁ፣ የሚገርመው እንዴት እንዴት እንደምታስቡ ለመረዳት አለመቻላችን ነው፡፡ ሕግ አክብሩ እምቢ፣ ሕገ ወጥ ናችሁ የሕግ ባለቤትና ምንጭ ከሆነችው ከቤተ ክርስቲያን ውጡና እዚያው በመለዳችሁበት ዝለሉ እምቢ እሽ ምን ትደረጉ፣ ወደ እስሳነት እንድትለወጡ መጸለይ አለበት እንደባሕርያችሁ፡፡ ጠቕላይ ቤተ ክህነቱ በርቱ ሕግ አስከብሩ

    ReplyDelete
  14. http://www.wust1120.com/Audio/Demtse%20Tewahedo.mp3
    Please listen to ዘበነ about Male circumcision at 49 minutes 51 seconds. He said it is our religion and we must perform Male circumcision at the 8th day. He quoted from the bible and said it is God's commandment and he gave good examples like (people who don't believe Jesus as the son of God) are doing Male circumcision at the 8th day. Based on his teachings and answers to listener's question, our Tewahdo Haimanot still believes Male circumcision at the 8th day as one of the requirement to be a good Tewahdo Christians. He is not only against the current Holy Synod Decision but also he is against the first Holy Synod decision (that was attened by st. Paul, St. Peter, St. James and all the deciples.

    The bible teaches us

    "Some men came down from Judea to Antioch and were teaching the brothers: "Unless you are circumcised, according to the custom taught by Moses, you cannot be saved." Acts 15:1

    (please note that in our generation those "Some men" are ዘበነ and his followers. If you forgot the first synod's decision here it is read it. Sometimes it is good to learn as well.

    "Then the apostles and elders, with the whole church, decided to choose some of their own men and send them to Antioch with Paul and Barnabas. They chose Judas (called Barsabbas) and Silas, men who were leaders among the believers. 23 With them they sent the following letter:

    The apostles and elders, your brothers,

    To the Gentile believers in Antioch, Syria and Cilicia:

    Greetings.

    24 We have heard that some went out from us without our authorization and disturbed you, troubling your minds by what they said. 25 So we all agreed to choose some men and send them to you with our dear friends Barnabas and Paul— 26 men who have risked their lives for the name of our Lord Jesus Christ. 27 Therefore we are sending Judas and Silas to confirm by word of mouth what we are writing. 28 It seemed good to the Holy Spirit and to us not to burden you with anything beyond the following requirements: 29 You are to abstain from food sacrificed to idols, from blood, from the meat of strangled animals and from sexual immorality. You will do well to avoid these things.

    Farewell"

    Acts 1:51-29

    ReplyDelete
  15. It is all about money for the orthodox clergy right?
    $$$$$$$$$$$$$$$$$$$$

    Yiblagn le abalochachu

    ReplyDelete