Friday, June 1, 2012

ፈቃድ ሳይጠየቅበት ቅስቀሳ ይደረግበት የነበረው የማኅበረ ቅዱሳን ጉዞ ታገደ

Click here to read in PDF
ምስረታውን በብላቴን ማሰልጠኛ ጣቢያ በወታደራዊ ሰልፍ ያከናወነው ማቅ 20ኛ አመቱን ለማክበር አስቦት የነበረው አመሰራረቱን የሚያስታውስ ሰልፍ እንዳይካሄድ ተከለከለ። ከዚህ ቀደም ሚያዝያ 27/2004 በተሰላፊ እጦት ሳይደረግ የቀረውና ለግንቦት 26 ዳግም የተቀጠረው የማቅ ሰልፍ መከልከሉ ማቅ አክራሪ ጠባዩን በአደባባይ እንዳያሳይና የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት አደጋ ላይ እንዳይጥል የተወሰደ እርምጃ ተደርጎ በብዙ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ተወስዷል። አሁንም ቢሆን ቲኬት የሚገዛው ሰው ብዛት አናሳ መሆኑ እየተነገረ ሲሆን የማቅ የገንዘብ ትርፍ በዚህ ሰልፍ ስኬታማ እንደማይሆን ታውቋል። ቀድሞም ቢሆን ዋናው የማቅ አላማ የዋልድባውን ጉዳይ በአገር ውስጥ ይበልጥ ለማቀጣጠልና ከውጪው ፖለቲካዊ ትግል ጋር ለማዋሀድ በመሆኑ ቲኬት ገዝቶ የሚሰለፍ ቢታጣ እንኳ አባላቱን፣ አንዳንድ የሰንበት ተማሪዎችንና የኮሌጅ ተማሪዎችን ይዞ ሰልፉን ለማካሄድ ቆርጦ ነበር ተብሏል።
ከማንኛውም የመንግስት አካል ፈቃድ ጠይቆበት ያልነበረው እና እንደተፈቀደለት ሳያረጋግጥ ከፍተኛ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰራ የነበረው ማቅ በዚህ ሳምንት ሰልፉን ለማስፈቀድ ከረቡዕ ጀምሮ ሲሯሯጥ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ባለን መረጃ ፈቃድ ማግኘት እንዳልቻለና ፈቃድ አጠያየቁ በቂ ጊዜ ያልቀረበበትና የአካሄድ ችግር ያለበት በመሆኑ እንደተከለከለ ማረጋገጥ ችለናል።
በተመሳሳይም በአዋሳ ከተማ አስበውት የነበረው ሰልፍ በአቡነ ገብርኤል ይሁንታን አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ከተማዋ ካለባት የቤተክርስቲያን ሰዎች ክፍፍል እና አለመግባባት የተነሳ ፈቃድ የተጠየቀበት ጊዜ አጭር በመሆኑ ከመንግስት አካል ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል።
ፈቃድ ሳይጠይቁ የሰልፉን ቀን የወሰኑበት ምክንያት ለሰሚው ግራ ነው። እንዲህ ያለ አሰራር የአመራሩን ዝርክርክነትና በተሳካ ሁኔታ ወደ “ኢንግሊዝኛ ተናጋሪ ቤተክህነትነት” መቀየሩን ያመለክታል ተብሏል። ማኅበሯ አስካሁን ድረስ ፈቃድ ሳትጠይቅ የማስታወቂያ ስራ ላይ ብቻ ለምን አተኮረች የሚለው ጥያቄ ከአመራሮችዋ ራሱን የቻለ ምላሽ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ በኛ ግምት ግን እኛ ከጠየቅን ማን ይከለክለናል? ከሚል ማን አለብኝነትና ከሰልፉ በላይ ትኩረት የሚሰጠው የትኬት ሽያጩ ስለሆነ ፈቃድ ጠይቆ ሰልፍ ከማድረግ ሳይጠይቁ ብሩን መሰብሰብ ይበልጥ አዋጭ ነው ከሚል ነጋዴያዊ እሳቤ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
ከሶስት ወር በፊት የማስታወቂያ ስራ ሲሰራበት የነበረውን የጉዞ ፈቃድ ለመጠየቅ ሶስት ቀን ብቻ ሲቀረው የጠየቀበት ምክንያት ሆን ተብሎ መንግስትን ለማሳጣትና በአጋጣሚው ግርግር ፈጥሮ ፖለቲካዊ አላማውን ለማሳከት የተደረገ እንደሆነ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይናገራሉ። ጉዞውን plan A እና plan B በማለት የማኅበሩ ስውር አመራሮች አቅድ እንዳወጡበት የሚነገር ሲሆን፣ የመጀመሪያው እቅድ ጉዞውን እነርሱ በፈለጉት መንገድ ጠይቀው ለመንግሥት ያላቸውን ንቀት በሙላት በሚያሳይ መልኩ ጉዞውን በወሬና በማስታወቂያ ጋጋታ ተጽዕኖ ፈጥሮ  ሶስት ቀን ሲቀረው ጠይቆ ሳይወድ በግዱ እንዲፈቅድ ማድረግ ሲሆን፣ ሁለተኛው እቅድ ደግሞ በጊዜው እጥረትና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች መንግስት ሳይፈቅድ ቢቀር መንግስትን ለማስወቀስና ኢሳትን ጨምሮ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎችና ብሎጎቻቸው ፓለቲካዊ ትርፍ የሚያስገኝ ቅስቀሳ ማድረግ ነው የሚል መሆኑ ታውቋል።
 ሰልፉ ቢሳካ ማኅበርዋ ዋልድባን በተመለከተ ከጠራችው አለምአቀፍ ሰልፍ ጋር በተከታታይ ለማድረግና የአዲስ አበባውን ጉዞ በኢሳት ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋልድባን አስመልክቶ በአዲስ አበባ የተደረገ ሰልፍ አድርጎ ለማስዘገብ የታቀደ ቢሆንም፣ ሰልፉ እንዳይካሄድ በመከልከሉ በዋልድባ ምክንያት የአረቦች መነሳሳት አይነት ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጠረ በማለት በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ስሜት ወደ ሌላ አቅጣጫ ወስዶ በመንግስት ላይ ለማነሳሳት ያለመው የኢሳትና የማቅ አመራሮች ውጥን ሳይሳካ ቀርቷል።
ልክ እንደ ዋልድባው ጥናት ሁሉ የኢሳት ቴሌቪዥን የአዲስ አበባውን ሰልፍ ከዋልድባ ጋር ኣያይዞ በሚያቀርበው ዘገባ ምክንያት ከመንግስት ሊደርስበት የሚችለውን ወቀሳ ለማስቀረት ታስቦ የኢሳትን ዘገባ የሚተች መግለጫ አስቀድሞ ያዘጋጀው የማቅ አመራር በሰልፉ ውስጥ የደበቀው ፓለቲካዊ ህልሙ ቅዠት ሆኖበታል።
አሁን የሚቀራቸው ሁለተኛው እቅድ ሲሆን፣ እርሱም መንግስት ሰልፉን ከለከለን በማለት የሚገኘውን ፖለቲካው ትርፍ ማጋበስ ነው ተብሏል። የሆነው ሆኖ አብዛኛው በውጭ ያለ ኢትዮጵያው የማቅን ሀሳብ በሚገባ በማወቁ በዋልድባ ጉዳይ ገለልተኛ መሆንን ከመረጠ ቆይቷል። በሀገር ውስጥ ያሉ ደጋፊዎቻቸው እንደተለመደው መንግሰትን ማማረራቸው የሚጠበቅ ቢሆንም ከመንግስት ይልቅ ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ የሚወጣውን አመራራቸውን እንዲወቅሱ እንመክራቸዋለን።
ይህ በእንዲህ እያለ አሁን በደረሰን ዜና መሰረት ከአባሉ ውስጥ ውስጡን እየሰሙት ያለው ተቃውሞ ከጠበቁት በላይ በመሆኑ ከእገዳውም በኋላ ዘና ብለው የነበሩት የማቅ አመራሮች እገዳውን ለማስቀልበስ እየተሯሯጡ መሆናቸው ታውቋል።

11 comments:

  1. ena min yitebes enanite sirafetoch

    ReplyDelete
  2. kkkkkkkkkkkkkkkkk kentu neger nachu

    ReplyDelete
  3. haymanot beselamawi self yisfafal?

    ReplyDelete
  4. ገድ ጉድ ነው። ምነው ማህበረ ቅዱሳን እንድህ እንዳበደች ዉሻ ይንቀጀቀጃል? የእረሱ ምስረታ እና የዋልድባ ሰልፍ ለምን ማገናኘት አስፈለግው? ምናልባት የውጭው ስኖደስ የዋልድባን ገዳይ ለተባበሩት መንግስታት ስላቀረበ ደብዳቤ Credit ለረሱ ለመዉሰድ በማሰብና ብዙ ደጋፍ አለኝ ለማለት ነው። ለዚህም ለማህበሩ ቅስቀሳ እንድሆነ ተብሎ ዳንኤል ክብረት በካሊፎንያ በBay area ባሉት ሶስት ቤተ ክርስትያናት ውስጥና በየ ሰው ቤት እየገሄደ ቅስቃሳ እያደረገ ነው።ይህ ጉባኤ ከMay 25, 2012 to June 17, 2012 ነው:: ለዳንኤል ክብረት ወደ $3000.00(3 ሽህ) ዶላሮች እያነዳንዱ ቤተ ክርስረቲያን (እንድ ቸሩት)ለመስጠት ተጠይቋል።በየ ቀኑ በምደረገው ጉባኤ ላይ እጅግ በቁጥር አነስተኛ ሰው ነው የሚገኘው።ይህ በራሱ ማቅ በህዝቡ ዘንድ ጥላቻን እንዳተረፈ ይገልጻል። ለመሆኑ ለዋልድባ ገዳም አንድ መቶ ዶላር ያላኩት የማቅ እና የዋልድባ ሰልፍ አዘጋጆች ምንው ይህን ያህል ገንዘብ ለአንድ ግለሰብ መስጠት አስፈለገ? ለዋልድባ ገዳም መነኮሳት መቶ ዶላር ብሰጡ የጽድቅ ይሆንላቸው ነበር።ዳሩ ግን በፖለትካና በስልጣን ጥማት አይኑ ስለ ታወረ የጽድቅ ሥራ መስራት አየፈልግም። የሐሰት አባት ስለ ሆነ ነው ።

    ReplyDelete
  5. Weregna bicha. Negeru min yidereg????

    ReplyDelete
  6. please don't worry so much! you think every thing negatively. it is known that your mind is fully occupied with evil spirit. sorry you are unable to think positively! but God make every thing for good. it has nothing harm to mk!

    ReplyDelete
  7. beahunu gize kutere and yebetekerestiyan telat mk new. mk yehager segatem eyehone new silezihe endi yalew yeamese masefafiya mengede litagedu yegebal.

    ReplyDelete
  8. ልጅህ
    እንደ ቃየል በቅናት ካደገ የገዛ ወንድሙን ይገድላል። /ዘፍ 4፤5/
    እንደ ካም ካደገ ያንተኑ ሃፍረት ይገልጥብሃል። /ዘፍ 9፤21-22/
    እንደ ዲና ካደገች ሂዳ ከጠላቶችህ ትወዳጃለች። /ዘፍ 34፤1/
    እንደ ዔሳው ካደገ ምቀኛ ይሆንብሃል። /ዘፍ 27፤41-45/
    እንደ ይሁዳ ልጆች ካደገ የከፋ ይሆንብሃል። /ዘፍ 38፤1-11/
    እንደ ሮቤል ካደገ ሚስትህን ይቀማሃል። /ኩፍ 28፤35-44/
    እንደ አፍኒንና ፊንሐስ ካደገ ታቦት ሻጭ ይሆንብሃል። /1ኛ ሳሙ 2፤12/
    እንደ አምኖን ከደገ የገዛ እህቱን ይደፍርብሃል። /2ኛ ሳሙ 13፤1-19/
    አንደ አቤሴሎም ካደገ አንተንም ያሳድድሃል። /2ኛ ሳሙ 17፤21-24/
    አንደ ሴምና ያፌት ከደገ ሃፍረትህን ይደብቅልሃል። /ዘፍ 9፤23/
    አንደ ዮሴፍ ካደገ በችግርህ ደራሽ ይሆንልሃል። /ዘፍ 39፤7-23/
    እንደ ይስሐቅ ካደገ ታማኝ ሆኖ ራሱን ይሰዋል። /ዘፍ 22፤9/
    እንደ ሳሙኤል ካደገ የእግዚአብሔር ሰው ይሆንልሃል። /1ኛ ሳሙ 3፤17-20/
    እንደ ዳዊት ካደገ የአገርህን ጠላት ያጠፋልሃል ፤ በሰው በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ ይሆንልሃል። /1ኛ ሳሙ 17፤34-54/

    ReplyDelete
  9. Seme joro kalehe sema

    ReplyDelete
  10. boo gize lekulu.............

    ReplyDelete