Wednesday, June 6, 2012

አሁንም ከግብጽ ነጻ አልወጣን ይሆን?

click here to read in PDF
ቤተ ክርቲያናችን ራሷን ችላ ከመውጣቷ በፊት በግብጽ ሳንባ የምትተነፍስ ኢትዮጵያ ጎርሳ ወደግብጽ የምትውጥ እንደነበረች የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ከዚህም በመነሳት ይመስላል አንድ ሰው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እኮ ገና 100 ዓመት እንኳ ያልሞላት ታዳጊ ናት ሲሉ የተናገሩት፡፡
በግብጽ ሳንባ ከመተንፈስና በግብጽ ጭንቅላት ከማሰብ ነጻ ወጥተናል አሁን በባዕድ ሳይሆን በአገር ልጅ የቤተ ክርስቲያናችን ነገር ግድ በሚላቸው በራሳችን ሰዎች ነው የምንተዳደረው ብለን ሐሴት ማድረግ ሳንጀምር የአገር ልጅ መሳይ ግብጻዊ ቤተ ክርስቲያናችንን እንደወረራት ዓይናችን አይቶ ልባችን አዘነ፡፡
ግብጻዊያኑ ሲመሩን (ሲገዙን ብለው ይሻል ይሆን?) ቋንቋቸው ከቋንቋችን ስለማይገጥም በመንፈሳዊው ረገድ ምንም የሰጡን አገልግሎት የለም ለማለት ያስደፍራል፡፡ ከዚህም በመነሳት ጥቅማቸው ለአገራችን ሳይሆን ለአገራቸው ብቻ ነበር ቢባል ስህተት አይሆንም፡፡ ማቅ ሳያውቃቸው አውቃቸዋለሁ እያለ የሚሟገትባቸው አቡነ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በተሰኘው መጽሐፋቸው ግብጻዊያን ‹‹ክርስቲያን›› ጳጳሳት ሰማያዊውን ገዢ እግዚአብሔርን ለማገልገል ሳይሆን ምድራዊውን ንጉሳቸውን ለማስደሰት መስጊድ ያሰሩ እንደነበረ ያሰፈሩትን መመልከቱ ወደ ኢትዮጵያ የመምጣታቸው ጥቅም ለማን ነበር? የሚለውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን እነዚህን ጳጳሳት ለማስመጣት በወቅቱ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ነገስታት ብዙና ብዙ እጅ መንሻ የሚሆን ሐብት ወደ ግብጽ ይልኩ እንደነበረም ብጹሕነታቸው አስፍረውልናል፡፡
 ምንም እንኳ ዘመን ቢያልፍም በስም ኢትዮጵያዊያን የሆኑ በግብራቸው ግን ከግብጻውያን ጋር የሚዛመዱት የዘመናችን ቀኝ ገዢዎች ለቤተ ክርስቲያኒቱ ጥቅም አንድ እንኳ ለመራመድ ጥረት ማድረግ ሳይሞክሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ማህበራቸውንና ኪሳቸውን በረብጣ ብር እያበለጸጉ አልያም ቀደም ሲል እንደተባለው ወደቤተ ክርስቲያን ጎርሰው ወደማህበራቸው የሚወጡ በመሆን ስመ ኦርቶዶክሳዊነታቸውን በተግባር አስመስክረዋል፡፡ አቡነ የሚለው ስም የተሸከሙትና ቤተ ክርስቲያንን ለማስተዳደር ከእግዚአብሔር አደራን የተቀበሉትም ቢሆኑ ለሾማቸውና አደራውን ለሚጠይቃቸው አምላክ ማገልገል አቅቷቸው ምድራዊ ሆዳቸውን ለሚሞላላቸው ባሪያ መሆናቸውን ያስመሰከሩ ናቸው፡፡
ግብጻዊያኑ ቅድሚያ ለግብጽ የሚል መርህን ይዘው ስለሚመጡ ኢትዮጵያዊያኑ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ገበሬ በነበረበት በዛን ዘመን ገበሬው በትጋት ቢሰራ የአባይ ተፋሰስ ወደግብጽ የመሄዱ መጠን ይቀንሳል በሚል ኢትዮጵያዊያንን በበዓላት ብዛት ስራ ፈት  አድርገው ይሄ እስከአሁን አስቀምጠውታል፡፡
የዘመናችን ግብጻዊያንም ወጣቱ በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተሞልቶ ወደ መንግስተ እግዚአብሔር የሚሄድበትን መንገድ ካወቀ ማህበሩ በሚፈልገው ሁኔታ አያገኘውምና መንፈሳዊ እውነት በሌላቸውና እዚህ ግባ በማይባሉ አቡነ እንትና ሰይጣንን አሸክመው ያመጡት ድንጋይ እያሉ ወንጌልን ሳይሆን ሀሳባቸውን በሚያገለግሉ  እንቶ ፈንቶዎች ሕዝቡ ወደ ሲዖል እያገፉት ይገኛል፡፡  
በግብጻዊያን እንተዳደር በነበረበት ጊዜ ተገዢነታችን ለግብጽ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለግብጽ ሱልጣናትም ጭምር ነበር፡፡ ማለት ወደኢትዮጵያ ይላኩ የነበሩት ጳጳሳት የሚሰሩት ለክርስቶስ ሳይሆን ለግብጽ እስላማዊ ገዢያቸውም ነበር፡፡ አሁንም በስልጣን ያሉት ስመ ጳጳስነት የተሸከሙት ለተሾሙበትና ሊያገለግሉት ለሚገባው ለእግዚአብሔር መንግስት ከመስራት ይልቅ ለአንድ ማህበር ተገዢ መሆናቸውን በአደባባይ እያሳዩ በመሆናቸው ከግብጽ ነጣ አልወጣንምን እንድንል ምክንያት ሆኖናል፡፡
ግብጻዊያኑ በኢትዮጵያ ምድር ጳጳሳት ሳይኖር ቀርቶ ወይንም ግብጻዊዉን ጳጳስ ኢትዮጵያዊያኑ የሆነ በደል ቢያደርጉበት እንደአጋጣሚ ሆኖ የሆነ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ችግር ሲከሰት መቅሰፍት እንደሆነ ሲነግሩን ስለነበረ ያለ ግብጻዊያን ምንም ማድረግ እንደማንችል አድርገን እንድናስብ ሆነን ነበር፡፡
አሁንም ማህበሩ ከሌለ ቤተ ክርስቲያን አበቃላት ማህበሩ ከፈረሰ ኢትዮጵያ የምትበላው ምድር ለምልክት እንኳ እስከማትገኝ ድረስ እንደምትጠፋ አድርገው ሊሰብኩን ሞክረዋል፡፡ ይህን ስብከታቸውንም እውነት አድርገን እንድንቀበል ብዙ ድንጋይ ፈንቅለዋል፡፡   
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የራሷ አስተዳደር ያላት በአንድ መንፈሳዊ ግንዛቤ በሌለው ማህበር የምትመራ ሳትሆን ምንም እንኳ አንዳንድ አሁንም ከግብጽ ባርነት ነጻ ያልወጡ ጳጳሳት ቢኖሩባትም መንፈሳዊ እውቀታቸው ጥሩ በሆኑ ጳጳሳት የምትተዳደር ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ የአገር ልጆች የሆኑት ግብጻዊያን ግን ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደቀደመው (ወደየባርነት) ታሪኳ እየመለሷት ይገኛሉ፡፡ ወደ ኋላ (ወደ ዳግም ባርነት) መመለስ የሚፈልግ ቢኖር ጎዳናውን ሊያሳዩት በደጅ እየጠበቁት ይገኛሉ፡፡ ወደተሻለው ነጻነት መጓዝ የሚፈልግ ካለ ግን ከእንግሊዘኛ ተናጋሪው ቤተ ክህነት ራሱን ይጠብቃል፡፡    

9 comments:

  1. አሁንም ማህበሩ ከሌለ ቤተ ክርስቲያን አበቃላት ማህበሩ ከፈረሰ ኢትዮጵያ የምትበላው ምድር ለምልክት እንኳ እስከማትገኝ ድረስ እንደምትጠፋ አድርገው ሊሰብኩን ሞክረዋል፡፡ ....It is only because of the Almighty this church survived various challenges.

    ReplyDelete
  2. leboch men yeshalachehuwal

    ReplyDelete
  3. ጥሩ እይታና ጥሩ ንጽጽር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ከዚህም በላይ እንዳታድግና ለአፍሪካ እንኳ የሚበቃ ስራ እንዳትሰራ የዳረጓት ግብጻዊያን እንደሆኑ ግልጽ ነው፡፡ አሁን የተማርን ነን በሚሉት በማህበር ቅዱሳን ባሉት አጥፍቶ ጠፊዎች እየተሰራ ያለው ስህተት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከድጡ ወደማጡ እንደሚባለው ወደታች እየጎተታት መሆኑን ስንቶቻችን አስተውለን ይሆን? የዓለምን አብያተ ክርስቲያናት ለመምራት አቅም ኖሮን ሳለ የራሳችን ለመምራት ግን እንዴት ተሳነን? መልሱ ግልጽ ነው በማህበሩ በኩል በእጅ አዙር እየተሰራ ያለው የአመጽ ስራ እንኳን የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር መንግስትንም የሚያሰጋ መሆኑን እያየን ነውና፡፡

    ReplyDelete
  4. etabatachihu...endet ererre endalachihu yasayal yihe tsihuf...gena trerralachihu....tesfa yemekuret tsihuf new. midre menafik tesfa kuret

    ReplyDelete
    Replies
    1. ነው እንዴ? አላወቅንም ነበር!! ጅል ማቅ

      Delete
  5. ለራሱ ደመወዝተኛ ለነ አቡነ እንትና ከየት የሚሰጥ ይመስልሀል

    ReplyDelete
  6. ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ያለምንም ማስረጃ ማህበረ ቅዱሳንን ከአሸባሪ ድርጅት ጋር በማነጻጸር አይናገርም፡፡ ስለዚህ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ቤተ መንግስትና ቤተ ክህነት ማህበረ ቅዱሳን አመጸኛ እና አሸባሪ ድርጅት ነው ብለው ከመሰከሩ ማህበረ ቅዱሳን ለምን አይታገድም/አይዘጋም ?????? ማህበሩ ለቤተክርስቲያን መጥፎ ስም እያሰጠ ያለ በመሆኑ እንዲታገድ ሁላችንም እንነሳ

    ReplyDelete