Thursday, June 7, 2012

ዘሪሁን ሙላቱና ግራ የገባው ትምህርቱ

Click here in PDF
በዲያቆን ፈታሂ በጽድቅ
ዘሪሁን ሁሉን አዋቂ ሆኖ መታየት የሚፈልግ ሰው እንደሆነ  ብዙዎች ይናገሩለታል፡፡ ከጓደኞቹ ጋር አብሮ ተቀምጦ ከሆነ ከእርሱ በላይ እንደማያውቁ በአንድም በሌላም መንገድ መልእክት ያስተላልፋል፡፡ ከሁሉ ይልቅ አዋቂ እንደሆነ ሊያሳይ የሚፈልገው ዘሪሁን የሥላሴ ኮሌጅ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ስብከት እንጀራው መሆኑን በመናገር በተደጋጋሚ በአምላክ ሕልውና እንደማያምን ሊያስረዳ ይሞክር ነበር፡፡ እንደዚህ በድፍረትና በግልጽ ክህደቱን እየተናገረ ማንም ምንም ለምን እንዳላለው ግልጽ ባይሆንም የሥላሴ ቆይታውን በሰላም ጨርሶ ለመመረቅ በቅቷል፡፡የእግዚአብሄርን እውነት ስለተናገሩ መናፍቅ የሚባሉ ተማሪዎች ባሉበት ግቢ እንዲህ ዓይነት የከፋ ክህደት የሚያስተላልፍ ሰው ግን ምንም አለመባሉ አስገራሚ ነው፡፡
ከሃዲው ዘሪሁን ግን አሁንም የክህደት ትምህርቱን ማስተላለፉን አላቆመም፤ እንዲያውም ባሰበት እንጂ፡፡ ከምህረተ አብ ጋር በመሆን እየዘሩት ያሉትን የስህተት ትምህርት ዘር ምን እንደሚመስል በተከታታይ ልናስነብብዎ ጀምረናል፡፡
ኦርቶዶክስ መልስ አላት በሚል በጀመሩት መርሃ ግብር ላይ ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ የተሰጠበት ነው በሚል የቀረበው ቪሲዲ ለሕዝብ መልቀቁ ይታወቃል በዚህ ቪሲዲ ላይ ያስተላለፋቸውን ኑፋቄዎችና የክህደት ትምህርቶች ለጊዜው እናቆያቸውና አሁንም በዛው መድረክ ላይ እያቀረባቸው ያሉትንና አባቶች አይተው ወደ ኦርቶዶክሳዊት ትምህርት እንዲመለስ ቢመክሩት በሚል ያሰብናቸውን በተከታታይ እናቀርብሎታለን፡፡

ዘሪሁን ትክክል ነው ብሎ እስካመነበት ድረስ ሳሩም ቅጠሉም እሱን የሚደግፍ የሚመስለው ሰው ነው፡፡ ስለዚህም ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች ደስ ካለው ግሪኩን ካልሆነም እንግሊዘኛውን እነሱን ካልፈለገም ግዕዙን ለምስክርነት ይጠራል፡፡ ሌላው ሰው ግን ከእንግሊዘኛው ሲጠቅስ ‹‹እንግሊዘኛው ችግር ስላለበት እሱን ተወው›› ይላል ወይም ግሪኩን የሚያነሳ ጠያቂ ከመጣ ‹‹ክላሲካል ግሪኩን ካልሆነ አልቀበለህም›› ሲል ይደመጣል፡፡
እንዲሁ ደግሞ ለእሱ ‹‹ከዚሁ ከጥያቄው ጥቅስ ተነስተህ መልስልኝ የሚል ጠያቂ ሲመጣ አንዱን ጥቅስ ለማብራራት ሌላኛው ጥቅስ ወሳኝ መሆኑን በመናገር ሌላ ቦታ ያለ ጥቅስ በመጥቀስ እንደሚመልስ አመቻችቶ ከሌላ ቦታ ባለ ጥቅስ ለማብራራት ይሞክራል፡፡ ነገር ግን ጠያቂው ጥያቄውን ለማስረዳትም ይሁን ጥያቄ ሲጠይቅ የጥያቄ ጥይቄ ተነስቶለት የተጠየቀውን ለመመለስ ሌላ ጥቅስ ቢጠቅስ ‹‹ማን ፈቀደልህ? በዚሁ በራሱ በጥቅሱ አስረዳ›› ይባላል፡፡ ለዛሬ ስለ ሴትነት የተናገረውን እናቀርባለን።
ሴትነትና ዘሪሁን
በግልጽ እንደሚታየው መድረኩ የተዘጋጀው መልስ ለመስጠት ሳይሆን ራስን ለማሳየት ወይም ለማስተዋወቅ ነው የሚመስለው፡፡ ዛሬ የምናየው ከእህቶች በወረቀት ተጽፎ ተልኮለት ከነበረው ጥያቄ ላይ መልስ ለመስጠት የሞከረውን ነው፡፡ ይህን የማደርገው ዘሪሁን መልካም ሰው አይደለም ለማለት ሳይሆን ዘሪሁን ራሱን ለማስተካከል ፍቃደኛ ከሆነ ምን እንዳደረገ እሱ ያላስተዋለውን እንዲያስተውልና ከእንደዚህ ዓይነት ድርጊት ራሱን እንዲያወጣ ለመጠቆም ነው፡፡
በወረቀት ተልከውለት ራሱ እያነበበ መልስ ከተጠባቸው የጥያቄዎች ውስጥ አንዱ እኛ ሴቶችን አትወደንም የሚል ነበር፡፡ እሱም ለዚሀ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ “እኛ ሴቶችን አትወደንም አለች ጥሩ ብላለች እኛ ማለቷ፡፡ እኔን ብትለኝ አዎ! ነበር የምላት ስሟን አልጠቀሰችም እንጂ፡፡ ስለዚህ ሴቶች ሲጠይቁ በአንድ ወቅት ምናልባት ጥያቄው ከበድ አላለም ብዬ ተናግሬአለሁ መሰለኝ፡፡ ይሄ ደግሞ በእኔ አልተጀመረም ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን 5000 ሰዎች መገበ ወንዶች ናቸው ሴቶች የተቆጠሩት ወንዶች፡፡ ሴቶቹ ለምን አልተቆጠሩም ንቋቸው ነው ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳይቆጠሩ ያዘዘው? አይደለም፡፡ በወቅቱ አባላላቸው እንደህጻናት ነው ደካማ ስለዚህ የበሉትን በደንብ የበሉት ወንዶች የዘንድሮ ሴቶች ቢሆኑ ይቆጠራሉ፡፡ እያየናቸው በየካፌው በርገሩን እንዴት እንደሚበሉት እኮ እኛ ነን የምናውቀው ሥጋችን አብሮ ውልቅ እስኪል፡፡ ትቆጥሩ ነበር እናንተ ብትሆኑ፡፡ ግን ያን ዘመን የነበሩት ሴቶች ሲበሉ ስነ ስርዓት አላቸው እየቆነጠሩ ነው እነዚህንስ በሉ ብለን ከምንቆጥራቸው ወንዶቹ ብቻ የበሉትን እንቁጠራቸው ተባለ፡፡ ይሄ የሴቶችን የበታችነት ለመናገር አይደለም፡፡ በወቅቱ የነበረውን ድርጊት ለማሳየት ነው ስለዚህ በአንድ ወቅት ለሴቶቹ ጥያቄ ተባለና ስትጠይቀኝ ባለፈው ሳምንት ይታጠባል እሁድ? አለችኝ፡፡ ቀጠለች ደግሞ በሳምንቱ አንዷ ይሰጣል ወይ? አለችኝ አንዷ ደግሞ ይደርቃል ወይ? ልትለኝ ነው እኔ እንግዲህ አንድ ልብስ ላይ አንድ ወር አልቆይም፡፡ ከዚህ አንጻር ይሄ መርሃ ግብር የተዘጋጀው በመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት እንድናድግ ስለሆነ ሰንበት ትምህርት ቤት ገብታችሁ መማር ያለባችሁን ዕውቀት ሁሉ እዚህ ቦታ ላይ እንዳታመጡ ስለተፈለገ እንጂ፡፡”
መልሱን ሲጀምር እኔን ብትለኝ አዎ! ነበር የምላት ስሟን አልጠቀሰችም እንጂ የሚለው ንግግሩ ለሴቶች ያለው ክብር ምን ድረስ እንደሆነ አመላካች ነው፡፡ ማንነቷን የማያወቃትን ሴት እንዲህ ለማለት ከደፈረ ከሚተዋወቃቸው ሴቶች ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል ለመገመት አያስቸግርም፡፡ ይህን የተናገረው እየቀለደ እንዳልሆነ የድምጽ አወጣጡ በሚገባ የሚያስረዳ በመሆኑ ይህን የተናገርኩትኮ ለፈገግታ ነው ለማለት አይችልም፡፡ ከሴት የተወለደና ለማርያም ልዩ ክብር አለኝ የሚል ሰው ለሴት እንዲህ ያለ ቃል ለመናገር መድፈሩ ከምን ተነስቶ እንደሆነ ቢያብራራው መልካም ነበር፡፡
ምናልባት . . . መሰለኝ የሚለውን ንግግሩን ሲያነቡ ተናግሮ ይሆን ወይ? ብለው ተጠራጥረው ከሆነ ከዚህ በፊት ወደ ወንዶቹ፤  ሴቶቹ ትንሽ አቅም የለውም ጥያቄአቸው ሲል የተናገረውን ዘንግቶት ሳይሆን ሆነ ብሎ እንደሆነ የሚያሳይ አንድ ድርጊት እናሳይዎ፡፡ አሁን የምናሰፍርልዎ ድርጊት የተከናወነው ለእህቶችና ለእናቶች እረ ሴቶች እወዳችኋለሁ የሚለው ከተናገረ በኋላ መሆኑን ሲያስተውሉ ዘሪሁን ሴቶችን በተመለከተ ምን ዓይነት አመለካከት እንዳለው ለመረዳት አያቅትዎም፡፡
በግንቦት 15 በነበረው መርሃ ግብር ላይ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ከወትሮው ቀደም ብሎ በስፍራው የተገኘው ዘሪሁን የጠያቂዎቹ ቁጥር እንደለመደው ሳይሆን በቁጥር 7 ሴቶች ብቻ መድረኩ ላይ ወጥተው የእሱን እሺ ወደጠያቂዎች የሚል ቃል በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን ከተመለከተ በኋላ ዛሬ ጠያቂዎቻችን የሉም እንዴ? ሴቶቹ አሉ ወጥተዋል ወንዶቹ ጠያቂዎች ተመናምነዋል፣ ሳስተዋል፣ ወይንም ደግሞ ጥያቄአቸው አልቋል፣ ወይንም ተመልሶላቸዋል፣ ወይንም ፈርተው ቀርተዋል የታል እየጠብቅን በወንዶች በኩል... ካለ በኋላ ሴቶቹን ቸል በማለት መዝሙር የዘመረ ሲሆን መዝሙሩን ከጨረሰም በኋላ 20 ደቂቃ በላይ አንድ በቪሲዲ የተለቀቀ እስላማዊ ስብከትን ተንተርሶ ራሱ ጥያቄ አንስቶ ራሱ መልስ ለመስጠት እዚህም እዛም ከረገጠ በኋላ የወንዶቹ ቁጥር እሱ እንደሚፈልገው ሆነለት መሰለኝ ለጠያቂዎች እድል እንስጥ በማለት ቀደም ብለው መጥተው የነበሩትን ሴቶቹን ትቶ ወደ ወንዶቹ ፊቱን በማዞር ወንዶቹን አስተናግዷል፡፡ ይህ ምን ያሳየናል? ከአንድም ሰባት እህቶች በመድረኩ ላይ (ታዳጊዎችም አብረው ተሰልፈው ነበር) እያሉ ወደ መድረክ ያልወጡትን መጠበቅ እንደገናም የቀደሙ ሴቶች እያሉ አሁን የመጡትን ወንዶች ቅድሚያ ሰጥቶ ማስተናገድ ከአክብሮትና ከፍቅር የሚመነጭ ድርጊት ይሆን ይሆን?
ወደ መነሻው ጥያቄ ስመለስ ዘሪሁን በልቡ ውስጥ ያለውን ተንኮል ያውቀዋልና ያደረኩት ትክክል ነው ለማለትም ሆነ ተሳስቻለሁ በሚል ይቅርታ ለመጠየቅ ስለተቸገረ በተለመደው ጥቅስ የማጣመም መንገዱ በመግባት ለጥፋቱ ማለሳለሻ የሚሆነውን ነገር ፍለጋ ወደመጽሐፍ ቅዱስ ጎራ በማለት በእኔ አልተጀመረም ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን 5000 ሰዎች መገበ ወንዶች ናቸው ሴቶች የተቆጠሩት? ወንዶች፡፡ ሴቶቹ ለምን አልተቆጠሩም? ንቋቸው ነው ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳይቆጠሩ ያዘዘው? አይደለም፡፡ በሚል ክፋቱን ለመሸፈን ጥረት ማድርግ ጀምሯል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ‹‹ወንዶቹም ተቀመጡ ቁጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያህል ነበር›› ተብሎ የተጻፈው ክርስቶስ እንዲቆጠሩ ስላዘዘ አይደለም፡፡ እሱ ያዘዘው ሕዝቡ በልቶ ከጠገበ በኋላ የተረፈውን ምግብ እንዲሰበስቡ ብቻ ነው - ዮሐ. 65-14፡፡ ሴቶቹንና ሕጻናቱን ከቆጠራ ያስወጣቸው የአይሁድ ልማድ (ባህል) ነው እንጂ የክርስቶስ ትህዛዝ አይደለም፡፡ አምታታው በከተማ የሆነው ዘሪሁን ግን ማለፊያ መንገድ ቢጠፋ መብረሪያ አየር ሞልቷል ለማለት እየዳዳው ነው፡፡
ሌላው ደግሞ ከቁጥር ውስጥ አለማስገባትና ሴቶቹን እንደሰዎች አለመቀበል በምንም መንገድ የሚገናኙ ነገሮች አይደሉምና በአንድ ላይ ሊወራላቸው አይችልም፡፡ ሙሉ በሙሉ ዘሪሁን ያደረገው የሴቶቹን ክብር ማናናቅ ነው በመጽሐፍ ቅዱሱ ላይ ከወንዶቹ እኩል በማእድ ተቀምጠው በአግባቡ ተስተናግደዋል፡፡ ዘሪሁን እያቀረበ ያለው ማእድ የእግዚአብሔር አይደለም እንጂ በአንድ ማእድ ያስለፋቸውን ሰዎች  አመጋገብ ላይ ይህ ለአንቺ አይገባም፣ አንቺ ይህን መመገብ አይኖርብሽም በሚል ለሴቶቹ ያለውን ግልጽ የሆነ ንቀት እያንጸባረቀ ነው፡፡  
እኔ ሴቶቹን አልናቅኩም ለማለት እየዳዳው ያለው ከሃዲው ዘሪሁን ንቀቱን ብቻ ሳይሆን ትችቱንም እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ የዘንድሮ ሴቶች ቢሆኑ ይቆጠራሉ፡፡ እያየናቸው በየካፌው በርገሩን እንዴት እንደሚበሉት እኮ እኛ ነን የምናውቀው ሥጋችን አብሮ ውልቅ እስኪል፡፡ ትቆጥሩ ነበር እናንተ ብትሆኑ፡፡ ግን ያን ዘመን የነበሩት ሴቶች ሲበሉ ስነ ስርዓት አላቸው እየቆነጠሩ ነው እነዚህንስ በሉ ብለን ከምንቆጥራቸው ወንዶቹ ብቻ የበሉትን እንቁጠራቸው ተባለ፡፡” 
በዚህ ንግግሩ ደግሞ የዘንድሮ ሴቶች ሆዳሞች መሆናቸውን ለዛውም ስራ በመፍታት ብዙ ሰዓት በየካፌው የሚያሳልፍ ሰው መሆኑን በሚያሳብቅበት ሁኔታ ሴቶቹ ሲበሉ የእነሱ (ከራሱ ጋር ማንን አብሮ እንዳሰለፍ ግልጽ ባይሆንም) ስጋቸው አብሮ ውልቅ አስከሚል ድረስ በሚያስደንግጥ ሁኔታ የሚበሉ እንደሆነ ከተናገረ በኋላ ያን ዘመን የነበሩት ሴቶች ሲበሉ ስነ ስርዓት አላቸው እየቆነጠሩ ነው በማለት የዚህ ዘመን ሴቶች እየገመጡ እንጂ እየቆነጠሩ ስለማይበሉ ስርዓት አልባ ናቸው የሚል መልእክቱን አስተላልፏል፡፡ አሁን ታዲያ ይህን ሰው ለሴቶች ክብር አለው ለማለት ይቻላል?   
“ይሄ የሴቶችን የበታችነት ለመናገር አይደለም፡፡ በወቅቱ የነበረውን ድርጊት ለማሳየት ነው ስለዚህ በአንድ ወቅት ለሴቶቹ ጥያቄ ተባለና ስትጠይቀኝ ባለፈው ሳምንት ይታጠባል እሁድ? አለችኝ፡፡ ቀጠለች ደግሞ በሳምንቱ አንዷ ይሰጣል ወይ? አለችኝ አንዷ ደግሞ ይደርቃል ወይ? ልትለኝ ነው እኔ እንግዲህ አንድ ልብስ ላይ አንድ ወር አልቆይም፡፡” ሲል ያቀረበውም ጥፋቱን ለመሸፈንና ይቅርታ ላለመጠየቅ የሸፋፈነበት መንገድ ነው፡፡ በቦታው ተገኝተን የሰማነው ሁላችን እንደምናስታውሰው የቀረበለት ጥያቄ አሁን እሱ እንዳወራው ከልብስ ማጠብና ማድረቅ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ እንደምክንያት አድርጎ የሚያቀርበውን ጥያቄ የጠየቀችው አንዲት ሴት ናት የእሷም ጥያቄ በማርያም፣ በገብርኤልና በሚካኤል በዓላት ለምንድን ነው ስራ የማይሰራው የሚል ነው እንጂ  ይታጠባል ይሰጣል ይደርቃል የሚል ነገር ፈጽሞ አልተነሳም፡፡ ይህም ንግግሩ ቢሆን ለሴቶች ያለው አመለካከት ምንድረስ እንደሆነ ጠቋሚ ነው፡፡ በእሱ እምነት ሴቶች ስፍራቸው ልብስ አጥቦ ማድረቅ ድረስ ብቻ ነው ማለት ነው፡፡
 ጥፋቱን ለመሸፋፈን ለደቂቃዎች ያለ የሌለውን ከለፈለፈ በኋላ ብዙ በመናገር ብቻ ሳይሆን በሽንገላም ማለፍ ስላለበት ኧረ ሴቶች እወዳችኋለሁ እውነቴን ነው እወዳችኋላሁ ይቅርታ አድርጉልኝ ካጠፋሁ፡፡ ቢልም ይቅርታውን እንደተቀበሉት ሊያሳይ የሚችል ፍንጭ በጉባኤው መካከል ስላልተየ እልል አትሉም እንዴ በማለት ምንም ያልተሰማቸውን ሰዎች ደስ ብሎት የሚያደርጉትን እልልታና ጭብጨባ እንዲለግሱት ማስገደድ ጀመረ፡፡ ለምን እሱ ሳይናገር እነሱ እልል ሳይሉ ቀሩ? ምክንያቱም የተናገረው ነገር ውሃ የሚቋጥር የሰውን ስሜት የሚያነቃቃ ስላልነበረ ነው፡፡
አዎ እላት ነበር ካለው ጀምሮ እልል አትሉም እንዴእስከሚለው ድረስ ሲናገር ያንጸባረቀው ለሴት እናቶቻችንና እህቶቻችን ያለውን ክብርና ፍቅር ሳይሆን ንቀቱንና ደካማ አመለካከቱን ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የማስተምር ሰው ነኝ ብሎ ካመነ በቅድሚያ ይህን አመለካከቱን ቢያስተካክል መልካም ነው፡፡
ባለፈው ቀን አዋሳ ሄዶ “እመቤታችን የጎርፍ ውሃ ነች” ብሎ የተናገረው ዘሪሁን ምን ለማለት እንደፈለገ ለማብራራት ቢሞክርም ፈጽሞ ሊሳካለት አልቻለም። የምሳሌው ግራ መሆን በቦታው የነበሩ ሰዎችን ግራ ያጋባ ሲሆን አላማው እንዲህ ያለ ንግግሩ ለሴቶች ካለው አመለካከት ጋር ይገናኝ ይሆን የሚል ጥያቄን አጭሮብናል። አላምንም ብሎ ደፍሮ ሲናገርበት በነበረው እውነትን እንደገና ንስሀ ሳይገባና ወደ እምነት ሳይመለስ ለመስበክ መሞከሩ እንዲህ ካለው የድፈረትና ግራ የመጋባት ንግግር አሳልፎ ስለሚጥል ልብ ያጣኸው ዘሪሁን እባክህን ቅድሚያ ንስሀ ገብተህ ወደ እምነት ተመለስ የሆነ ያልሆነውን ከመዘባረቅ የምትድንበት መንገድ ይኸው ነው እንላለን።

14 comments:

  1. ዘሪሁንን አውቀዋለሁ። ምንም መንፈሳዊነት የሌለው ሰው ነው። አደራረጉ ሁሉ ለጥቅም የቆመ ነው። ገንዘብ እስካገኘበት ድረስ ምንም ነገር ከማድረግ አይመለስም።

    ReplyDelete
  2. Zerihun is insane. Does it give any sense talking about him? Please let us discuss about our church other than mad people.

    ReplyDelete
  3. belabela yetelate kess ematrbu

    ReplyDelete
  4. ከአባ ሳሙኤል ተጠግቶ እንጀራ ሲበላ ከቆየ በኋላ መልሶ የተናከሰ ከሃዲ ወንጌል ይሰብካል ቢሉ ይገርመኛል! ጥቅሙን ብቻ የሚመለከተው ማቅ የአባ ሳሙኤል ወዳጅ መምሰሉን ወደጎን ትቶ አሁን ደግሞ ይህንን የሳሙኤልን ጠላት ሰውዬ በእነ በጋሻው ቦታ መድረኩን እንዲቆጣጠር ይሻል። ደጀ ሰላም ስለ ዘሪሁን አዋቂነትን ሁሉም መላሽነት እያስተጋባ መገኘቱ አንድ ማሳያ ነው። አይ ገንዘብ! ገንዘብ እንኳን ጊዜያዊ ወዳጆችን ቀርቶ መድኃኒት ክርስቶስንስ ለሽያጭ አቅርቦ የለ!! ማቅ ነጋዴው ሁሉን እያራገፈ ሁሉም ነገር ከገንዘብና ከራስ ጥቅም ጋር ወደፊት እያለ ነው!!!!!

    ReplyDelete
  5. ክርስቲያንን ማየት ቤቱ ነው ያለኝን አንድ ወዳጄን አስታወስኩ፡፡ ዘሪሁን መድረክ ላይ እንዲህ ካለ ቤቱ ምን ዓይነት ሰው ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አይከብድም፡፡ ይህን ማንነቱን ይዞ ግን የክርስቶስ ስም የሚጠራበት መድረክ ላይ ለመውጣት መድፈሩ የሚገርም ቢሆንም ከሁሉ በላይ የሚገርመው ደግሞ ምህረተአብ ተብዬው ሰውዬ ነው፡፡ ሃይማኖት የሌለውን ሰው መድረኩ ላይ የሚጋብዘው እሱም ሃይማኖት ስለሌለው ይሆንን? መጠርጠር ደጉ፡፡
    ደቂቀ አቡዬ ነኝ

    ReplyDelete
  6. ዘሪሁን ምላሽ ስላሳጣችሁ ነው እንዲህ ጥምድ ያደረጋችሁት

    ReplyDelete
  7. መልስ ሰጣችሁ ስትል ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ምንን በተመለከተ ነው መልስ የሰጠው? ስለማያምንበት መጽሐፍ ቅዱስ ያነበበውን ወይም የሰማውን እንደቁራ ስለጮኸ ነው መልስ ሰጣችሁ ያልከው? ከሆነ ተሳስተሃልና አንተም ራስህ ንስሐ ግባ
    ደቂቀ አቡዬ ነኝ

    ReplyDelete
    Replies
    1. ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ተገልጦ ሲያስተምር አምስት አይነት ዓመለካከት የነበራቸው ሰዎች ነበሩ አሁንም በመድረኩ ነግሶ የሚያስተምረው የሚመክረው የሚገስጸው እርሱ ነው ዛሬ ግን ሰሚው አምስት ዓይነት አመለካከት ብቻ ያለው አይደለም ብዙ ነው የዚህ ጸሐፊ ቁጥሩ ከምን ይሆን

      Delete
    2. የዚህ ጸሐፊ ቁጥሩ የእግዚአብሔርን ቃል ተርቦ ከሄዱት ውስጥ ነው፡፡ በዚህ ጉባኤ ክርክር ለመስማት የሚመጣ አለ እንዲሁም ሰው ጋብዞት የሚመጣ አለ እንዲሁም ለመወያየት የሚመጣ አለ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን መምጣት ስለሚያዘውትር የሚመጣ አለ እንዲሁም… እያልኩ ብዙ ለማለት እችላለሁ፡፡ ጸሐፊው ግን በእኔ ምልከታ የእግዚአብሔርን ቃል ለመማር የሄደ ሰው ይመስለኛል፡፡ እናም ዘሪሁን ከሚሰጣቸው መልሶች ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል የሆነ ነገር ስላጣ ይህን መልእክት ያስተላለፈ ይመስለኛል፡፡ በነገራችን ላይ እኔም በጉባኤው ላይ በቋሚነት ተከታታይ ነኝ፡፡ ጸሐፊው በጽሑፉ ያሰፈራቸውን ነገሮች በጆሮዬ የሰማሁ ሰው በመሆኔ እውነትነቱን በሙሉ ቃሌ በመመስከር ማረጋገጥ እችላለሁ፡፡ ዘሪሁን ማለት ዘር አልባ ዘሪ ነው፡፡ ዘር ስለሌለው አይበቅልለትም፡፡
      ደቂቀ አቡዬ ነኝ

      Delete
    3. ATo Abuye ...ዘሪሁን ከሚሰጣቸው መልሶች ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል የሆነ ነገር ስላጣ ይህን መልእክት ያስተላለፈ ይመስለኛል፡፡ yihen new yalkew ..ene aferkubih...ewnet Zerihun yemiastemirew ke metsaf kidus wuchi new ? Egziabher libona yistih...ye aganint wekil honeh atinager.....

      Delete
  8. ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ

    ReplyDelete
  9. ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ

    ReplyDelete
  10. እኔም በቪሲዲ የተቀረጸውን አይቻለሁ የእግዚአብሔር ቃል አይደለም የሚባል ነገር አላገኘሁም ምናልባት ዘሪሁነረ ሊያካትታቸው የሚገቡ ነገሮች ነበሩ ማለት ይቻል ይሆናል ያም ሆኖ የሀይማኖት ህጸጽ አለበት የሚያስብል አይደለም በተጨናሪም በዘመናችን የቤተ ክርስቲያኒቷ ሊቅ መጋቤ ሀዲስ እሸቱ ምስክነቱን ሰጥቷል ዳንኤል ክብረትም እንዲሁ ስለዚህ የዘሪሁን ትምህርት ምንፍቅናና ክህደት ካለበት መጋቤ ሀዲስም ሆነ ዳንኤል ክብረት ለዚህ ክህደት ተባባሪ ወይም አስተኳሽ ናቸው ማለት ነው?

    ReplyDelete