Click here to read in PDf: sinodos day 4
- · ተስፋዬ ከምክትል ስራ አስኪያጅነቱ እንዲነሳ ተወስኗል
- · ሰለሞን ቶልቻ ከገዳማት አስተዳደር ይነሳ ተብሏል
- · እስክንድር ከህዝብ ግንኙነት ይነሳል
- · ለግብጽ ቤተክርስቲያን የፓትርያርክ ምርጫ አምስት ጳጳሳት እንዲሄዱ ተወስኗል
- · አቡነ ሰላማ የአክሱም ህዝብን የደረሰባቸውን ተቃውሞ ለማስተባበል ጉዳዬ ይታልኝ ቢሉም ሰሚ አላገኙም
በዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ በርካታ ጉዳዮች የታዩ ሲሆን የጠቅላይ ቤተክህነቱ
ምክትል ስራ እስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ሁለት ስልጣን ደራርቦ መያዙ አግባብነት ስለሌለው በአንዱ ስልጣን በቤቶች አስተዳደር ብቻ ተወስኖ
እንዲቀመጥ እና ከጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅነቱ እንዲነሳ ተወስኗል፡፡
ተስፋዬ ከቦታው እንዲነሳ የተወሰነበት ተጨማሪ ምክንያት ደግሞ ጠቅላይ
ቤተክህነቱ በአቶ መመራት የለበትም የሚል ተጨማሪ ምክንያት በመቅረቡ ነው፡፡ አቶ ተስፋዬ የቤተክነቱ ትምህርት ስለሌለው እና የቤተክነትን
ቋንቋ በብቃት ስለማያውቅ አንዳንድ ጉዳዮችን በአቶ ደንብ ማስተናገዱ ቅር
እንዳሰኛቸው ያልደበቁ ጳጳሳት ነበሩ፡፡



