Click here to read in PDF
PDF: court decision
PDF: court decision
- አንድ የቤተክርስቲያንን ልጅ ለማባረር ሲል እራሱን ሕጋዊ ሰውነት የሌለው አድርጎ የሚያሳይ የክስ ወረቀት ለሰበር ሰሚ ችሎት አቀረበ
- ኮሌጁበሰበር ሰሚ ችሎት ከረታ ለተማሪዎቹ ከፍተኛ አደጋ አለው
የኢዮቤልዩ በዓሉን ለማክበር ጥቂት ዓመታት የቀሩትና ከተመሰረተ 69 ዓመት የሆነው የቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ከመምህር አሰግድ
ሣህሉ ጋር ባለው የሕግ ክርክር በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የገጠመውን ሽንፈት ሽሮ በድል
እንድወጣ ያስችለኛል ያለውን የይግባኝ አቤቱታ ለሰበር ሰሚ ሲያቀርብ ሕጋዊ ሰውነት የሌለኝና ከአንድ ግለሰብ እንኳ ያነስኩ ነኝ
ሲል ህልውናውን ካደ።
የኮሌጁ ጠበቃ እያለች የሕግ ክርክሩን በራሴ በኩል ልምራው የሚለው ማኅበረ ቅዱሳን አመራር በሆነው ደስታ በርሔ በተባለ
ጠበቃ በኩል የሕግ ክርክሩን ቢቀጥልም በስር ፍርድ ቤት የገጠመውን ሽንፈት ይሽርልኛል ብሎ ላለፉት አምስት ወራት ሲያስብ ቆይቶ
ባቀረበው አቤቱታ በተራ ቁጥር 2 ላይ ያለው የአቤቱታው ዝርዝር በሚለው አንቀጽ በግልጽ ህጋዊ ሰውነት የሌለው ኮሌጅ ነው ሲል የኮሌጁን
ህልውና ክዷል።
እኔ ያልኩት ብቻ ትክክል ነው የጠላሁትም መናፍቅ ነው የሚል መመሪያ ያለው ማቅ ፍላጎቱ እንዲሳካ የማያደርገው ነገር
እንደሌለው የሚያስረዳው አቤቱታ የ69 አመቱን አንጋፋ ኮሌጅ እዚህ ግባ የሚባል ካሪኩለም የሌለው እናደረጃውም የትምህርት ሚኒስቴርን
ተቀባይነት የማይመጥን በማለት የኮሌጁ ተማሪ የሆነው መምህር አሰግድ ይባረርልኝ የሚለው አቤቱታ ይህን ይመስላል።
የአቤቱታው ዝርዝር
በመሠረቱ አመልካች ኮሌጅ በራሱ ሕጋዊ ሰውነት የለውም፡፡ እንደ
ሌሎች የትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር ተመዝግቦና የንግድ ፈቃድ አውጥቶ የሚያስተምር ተቋም አይደለም፡፡ ቀደም ሲል በነበረው
መንግስት ተዘግቶ ከቆየ በኋላ በቀጥታ በመንግስት ፈቃድ ቤተክርስቲያኗ ከፍታ የሐይማኖቷን ተከታዮች ለማነጽ መምህራንን የምታፈራበት
ነው፡፡ የሚሰጠው የትምህርት ዓይነትም ሆነ ብዛት በትምህርት ሚኒስቴር ቁጥጥር የሚደረግበት አይደለም፡፡ በመሆኑም በስሙ ሊከሰሰም
ሆነ ሊፈረድበት አይችልም፡፡ በሕግ ‹‹ሰው›› የሚለውን መስፈረትም አያሟላምና፡፡ ስለዚህ የስር ፍ/ቤቶች ጉዳዩን ተቀብለው ማስተናገድም
ሆነ አስገዳጅ ውሳኔ መስጠታቸው መሠረታዊ የህግ ስህተት ነው፡፡
ይህ አቤቱታ ቀላል የማይባሉ ስህተቶች ያሉትና እራሱ ኮሌጁ ባለፉት አመታት ባስተማርኩዋቸው ተማሪዎቼ ደረስኩበት የሚለውን
ስኬት የሚንድና ተማሪዎቹ ወደ ሌላ የትምህርት ተቋማት ሄደው ለመማር ያላቸውን ፍላጎት ከንቱ የሚያደርግ ነው። አንድ የቤተክርስቲያን
ልጅን ካላባረርኩ በሚል ህልውና እስከመካድ ድረስ የደረሰ አቤቱታ ማቅረብ እጅግ በጣም አሳፋሪ የሆነ ተግባር ነው።

