Wednesday, May 16, 2012

ዜና ቤተክርስቲያን በ«ቀሲስ» ዶ/ር መስፍን ላይ «የጤና ዶ/ሩ ከክህነታቸው ተሻሩ» በሚል ርእስ ዘገባ አወጣ


ምንጭ፦ አባ ሰላማ
· «ዶ/ሩ የማኅበረ ቅዱሳን ቀንደኛ አባል፣ … በሥራ  ድክመትና ዛሬ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ግለሰቦች በድርጅቱ ውስጥ በመሰግሰጋቸው ተነቅቶባቸው የተባረሩ ናቸው» ብሏል
·    ማኅበረ ቅዱሳንን በሰይጣን መስሎታል
  • የዘገባው ሙሉ ቃል ከነትንታኔው ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል
«ዶ/ር መስፍን ተገኝ የተባሉት የማኅበረ ቅዱሳን ቀንደኛ አባል ያለ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ  ጳጳስ ፈቃድ በሰሜን አሜሪካ ባሉ ስቴቶች በመዘዋወር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ባደረጉት ኢ-ቀኖናዊ እንቅስቃሴና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ባልጠበቀ ሁኔታ አባቶችን እርስ በርስ የሚያጣላና የሚከፋፍል፤ በማለት የታገዱበትንና ከዚህ ቀደም ድረገጻችን አውጥቶት የነበረውን ደብዳቤ አትሞታል።«ዶ/ር መስፍን ተገኝ ቀደም ሲል በኃላፊነት ይሠሩበት ከነበረው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ በሥራ  ድክመትና ዛሬ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ግለሰቦች በድርጅቱ ውስጥ በመሰግሰጋቸው ተነቅቶባቸው የተባረሩ ናቸው፡፡

ምእመናንንም ለአድማ የሚያነሳሳ ትምህርት የሰጡ መሆናቸው በማስረጃ ስለተረጋገጠባቸው እንዲመከሩና በንስሐ እንዲመለሱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሰሜን አሜሪካና የካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያደርጉላቸው ጥሪውን በመናቃቸው በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 6 በቁጥር 224 ሦስተኛ ረስጠብ 22ኛው ድንጋጌ መሠረት ሊቀ ጳጳሱ ሥልጣነ ክህነታቸውን ሽረውታል፤ ከክህነታዊ አገልግሎትም አግደዋቸዋል፡፡»
«ዶ/ር መስፍን ከተጠቀሰው መሥሪያ ቤት ከተባበሩ በኋላም ለለጋሽ ድርጅቶች የተሳሳተ ኢንፎርሜሽን በመስጠት በብፁዕ ወቅድስ ፓትርያርኩ ጥረት ቤተ ክርስቲያናችን በሥራ ውጤት ከአሜሪካ መንግሥት ሽልማት ያገኘችበት የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ እንዲዘጋ በማስደረግ ሕሙማኑንም ሆነ የቢሮው ሠራተኞችን የበደሉ ከመሆናቸውም በላይ በሙያቸው የጀመሩት ሥራ አልሳካ ሲላቸው ‹‹ላም ካልዋለበት ኩበት ለቀማ›› እንዲሉ ፈተና የሌለበት መስሎአቸው የበለጠ ፈተና ወደአለበት ወደዚህ መንፈሳዊ ተግባር አምርተው በጅምራቸው ለዚህ ዓይነቱ መንፈሳዊ አደጋ የተጋለጡ ግለሰብ ናቸው፡፡» ብሏል። 

በዶ/ሩ ላይ የተወሰደውን ክህነትን የመሻር ተገቢ እርምጃ ከግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ቀደም ብሎ ከሳምንታት በፊት በተደረገ የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን፣ በጊዜውም ሆነ ከዚያ ቀደም ብሎ ዶ/ሩ ቅሬታውን አላቀረበም። ይሁን እንጂ ዜና ቤተክርስቲያን ሁኔታውን መዘገቧን ተከትሎ ቅሬታውን እንዳሰማ የማቅ ድረገጾች ጽፈዋል። በዚህም ግለሰቡም ሆነ ማኅበሩ ከመጀመሪያው ጀምሮ ጉዳዩን ከድረገጾቻቸው ባለፈ አለመቃወማቸውና ተቀብለውት ከሰነበቱ በኋላ አሁን ለአቅጣጫ ማስለወጫነት ለመጠቀም እንደ ፈለጉ አንዳንድ ተንታኞች እየተናገሩ ነው። ይሁን እንጂ በዜና ቤተክርስቲያን አማካይነት የነፈሰውን ሀይለኛ ነፋስ መቋቋም የተሳናቸው አንዳንድ ጳጳሳት እንኳን ሌላ ጉዳይ መጥቶ አቅጣጫ ሊለውጡ ከቆሙበት መንቀሳቀስ ተስኗቸው ተስለውሏል።  
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ፣ አቡነ አብርሃም አሜሪካ ተልከው ሳለ ባልተላኩበት ተልእኮ ተጠምደው የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪ በመሆን አፍራሽ ስራ ሲሰሩ መቆየታቸውንና ይኸው በመረጋገጡ አቡነ ፋኑኤል በምትካቸው መላካቸውን የሚገልጽ ዜና ያስነበበ ሲሆን፣ ከአዋሳ ጀምሮ አላሰራ ያላቸውንና እስከ አሜሪካ ተከታትሎ የተፈታተናቸውን በሰይጣን የመሰላቸውንና «የቤተክርስቲያናችን ፈታኞች» ሲል የጠራቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎችን ድል መንሳታቸውን እንዲህ ሲል አብራርቷል። «በእውነቱ ብፁእ አቡነ ፋኑኤል እንደሌሎቹ ያልተላኩበትን ስራ ሳይሰሩ ወይም እንደ አንዳንዶቹ የቁራ መልእክተኛ ሆነው ሳይቀሩ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚገኙትን የቤተክርስታናችን ፈታኞችን በትእግስትና በቆራጥነት ተቋቁመው «ካልጾማችሁና ካልጸለያችሁ ዘመዳችሁ ሰይጣን ከእናንተ ዘንድ ለቅቆ አይወጣም» የተባለውን አምላካዊ ቃል በተግባር በመተርጎም ከአዋሳ ጀምሮ ተከትሏቸው የሄደውን ሰይጣን በጾም በጸሎት ድል ነስተው በባዕድ አገር ለቤተክርስቲያናችን አንድ የታሪክ እመርታ በማሳየታቸው ምስጋና ሊቸራቸውና የሞራል ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል።»
በዚህ የተበሳጩ የመሰሉትና ከዚህ ቀደም፣ የ60 ዓመቱ ሽማግሌ በ10 አመቱ ሕጻን ተዘለፈ» በሚለው ጽሁፋቸው የማኅበረ ቅዱሳንን እኩይ ተግባር በተባ ብእራቸው በመተቸታቸው ከፍተኛ ዘለፋና ስድብ ያደረሱባቸውን፣ ባለፈው ለዘመን መለወጫ የተሀድሶ እንቅስቃሴን በቅኔ አጋለጡልን በሚል ደግሞ ሲያሞካሿቸው የነበሩትን መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒን፣ አሁን ፊታቸውን አዙረውና ጀርባቸውን ሰጥተው መኮነንና መውገዝ መጀመራቸውን ከድረገጾቻቸው መረዳት ተችሏል። በዚህ ጽሁፍ ማኅበሩን በትክክለኛ ዘገባዎቻቸው ያጠቁትን የጋዜጣውን አዘጋጆች፣ በተለይም ዋና አዘጋጁን ደጀሰላም የተባለው የማኅበሩ ድረገጽ ከፍተኛ ቅስቀሳ እያካሄደባቸው ይገኛል።
በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ አጀጋጆቹ ቀርበው ሳይጠየቁና ሳይመልሱ፣ ጥፋተኛ ሳይባሉም ማኅበሩ እንደለመደው በተጠናወተው በባዶ ሜዳ የማውገዝ አባዜው፣ ሲኖዶሱ ስለሚወደው እርምጃ ተወያይቶ የእርምጃ አማራጮችን አስቀምጧል ሲል መዘገቡ፣ የደጀሰላም አንባቢዎች ምን አይነት ይሆኑ? እንዴት? ለምን? ወዘተ ብለው የማይጠይቁና የተሰጣቸውን ብቻ የሚቀበሉ በድረገጹ አነጋገር «ዘገምተኞች» እና «ደመነፍሶች» ናቸው ወይ? አሰኝቷል። «ስለ ውሳኔው ምንነት በተደረገ ውይይትአስተዳደራዊ ይኹን” “የለም፣ በቀኖናዊ ቅጣት እንለፈውየሚሉ አማራጮች መነሣታቸው የተገለጸ ሲኾን በአመዛኙ የተያዘው ስምምነት ወደ አስተዳደራዊ ውሳኔ ያጋደለ መኾኑ ተጠቁሟል፡፡ አስተዳደራዊ ርምጃ ይወሰድ የሚለው አማራጭ ከታየ 1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ከጋዜጣው ሪፖርተርነት እስከ ዋና አዘጋጅነት ያገለገሉት መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ከሓላፊነታቸው የመሰናበት ዕጣ ፈንታ እንደሚገጥማቸው ተመልክቷል፤እስኪ እርሱም ይብቃውይላሉ ስለ ውሳኔው ከወዲሁ ሐሳብ የሚሰጡ የጉዳዩ ተከታታዮች፡፡» ሲል ማኅበሩ በዋና አዘጋጁ ላይ ከፍተኛ ዘመቻ መክፈቱን አውጇል።
አክሎም «ከጋዜጣው መውጣት በኋላ “ዜና ቤተ ክርስቲያን ስም ብቻ ይዞ ቢቀር በሚል ባለ ዘጠኝ ገጽ ጽሑፍ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ቅጽር እየተሠራጨባቸው የሚገኙት ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ 1967 . አንሥቶ በያዙት የዋና አዘጋጅነት ሓላፊነት የጋዜጣውን ዓላማ በመለወጥ የግል ሰዎች ስም ማወዳሻ፤ የስድብና የሐሜት መናኸርያ፤ የባለሥልጣናት ማጥመጃና መደለያ” የሚል ክስ እየቀረበባቸው ይገኛል፡፡» በማለት ዋና አዘጋጁን ማጥቃት መጀመሩን ጠቁሟል። ምንም መፈየድ ያልቻሉና በድረገጾቹ ላይ ከመነበብ ውጪ በጠቅላይ ነቤተክህነት አካባቢ ፈጽሞ ያልታዩ ጽሁፎችን እየጻፈ «ተበተነ» ማለትን ስራዬ ብሎ የያዘው ማቅ፣ በግንቦቱ ሲኖዶስ ራሱ እየበተነና በሌሎች እየላከከ «ተበተኑ» ያላቸው ጽሑፎች ሁለት መድረሳቸው ታውቋል። ከስም ማጥፋት የዘለለ ተጨባጭ ውጤት ግን እንዳልተገኘ እየታየ ነው።
የጋዜጣውን ሙሉ ቃል ከዚህ እንደ ሚከተለው አቅርበነዋል።
የጤና ዶክተሩ ከክህነታቸው ተሻሩ
ዶ/ር መስፍን ተገኝ የተባሉት የማኅበረ ቅዱሳን ቀንደኛ አባል ያለ ሀገረ ስብከቱ  ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ በሰሜን አሜሪካ ባሉ ስቴቶች በመዘዋወር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ባደረጉት ኢ-ቀኖናዊ እንቅስቃሴና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ባልጠበቀ ሁኔታ አባቶችን እርስ በርስ የሚያጣላና የሚከፋፍል ምእመናንንም ለአድማ የሚያነሳሳ ትምህርት የሰጡ መሆናቸው በማስረጃ ስለተረጋገጠባቸው እንዲመከሩና በንስሐ እንዲመለሱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሰሜን አሜሪካና የካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያደርጉላቸው ጥሪውን ባለመቀበላቸውና በመናቃቸው በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 6 በቁጥር 224 ሦስተኛ ረስጠብ በ22ኛው ድንጋኔ መሠረት ሊቀ ጳጳሱ ሥልጣነ ክህነታቸውን ሽረውታል፡፡ ከክህነታዊ አገልግሎትም አግደዋቸዋል፡፡
 የክሀነት ማገጃውን ደብዳቤ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ
ዶ/ር መስፍን ተገኝ ቀደም ሲል በኃላፊነት ይሠሩበት ከነበረው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ በሥራ ድክመትና ዛሬ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ግለሰቦች በድርጅቱ ውስጥ በመሰግሰጋቸው ተነቅቶባቸው የተባረሩ ናቸው፡፡
ዶ/ር መስፍን ከተጠቀሰው መሥሪያ ቤት ከተባረሩ በኋላም ለለጋሽ ድርጅቶች የተሳሳተ ኢንፎርሜሽን በመስጠት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጥረት ቤተ ክርስቲያናችን በሥራ ውጤት ከአሜሪካ መንግሥት ሽልማት ያገኘችበት የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ እንዲዘጋ በማድረግ ሕሙማኑንም ሆነ የቢሮው ሠራተኞችን እየበደሉ ከመሆናቸውም በላይ ከሙያቸው የጀመሩት ሥራ አልሳካ ሲላቸው “ላም ካልዋለበት ኩበት ለቀማ” እንዲሉ ፈተና የሌለበት መስሎአቸው የበለጠ ፈተና ወደአለበት ወደዚህ መንፈሳዊ ተግባር አምርተው በጅምራቸው ለዚህ ዓይነቱ መንፈሳዊ አደጋ የተጋለጡ ግለሰብ ናቸው፡፡

2 comments:

  1. Wademhret lemehonu yetochu nachew yeruk misrak
    Christianoch sileDr mesfin lekidus sinodos yestafut?tebilo bemahberu akenkagne blogs yewetut? Bemewakir tederagetew bête Christian tawkachewalech weyis yemahberekidusan akenkagne nachew? Endih simachew geno yetesemaw? Enes yemeselegne ye, arbaguba sewoCh mengistn astenekeku ,endemilew yimeslal.

    ReplyDelete
  2. እንኳን ማኅበረ ቅዱሳን ሃይማኖተ አበውም ታግዷል

    አንደኛ ማኅበረ ቅዱሳን ተቋቋመው ልክ እንደ ሃይማኖተ አበው የኢትጵያ ተማሪዎች ማኅበር ነው፡፡ በቀጥታ ትናንሽ ለውጦችና የስም መተካት ብቻ ነው የተደረገበት፡፡ ሃይማኖተ አበው ከዐርባ ሽህ በላይ አባላት ነበሩት፡፡ ግን ደርግ ወጣቱ ሃይማኖተኛ እንዲሆን ስለማይፈልግና አን ሀገራ የወጣቶች ማኅበር ስላቋቋመ በአንድ ደብዳቤ ማኅበሩ ታገደ አባቶችም ወጣቶች አባላት እንዳይበተኑ በማለት ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት እንዲታቀፉ አደረጉ፡፡ ማኅበሩም ለማደራጃ መምሪያውና ለሰንበት ትምህርት ቤት እድገት ከፍተኛ ስተዋጽኦ አደረገ፡፡

    ቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበረ ቅዱሳንን ያቋቋመችበት ሕግ ዶግማ አይደለም፡፡ እንደዚህ ዓይነት አመለካከት ያቸው አባቶች ካሉ እንኳን ካህናት ገና ክርስቲያን አይደሉም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ተባለው ማኅበር ከአእማደ ምስጢር ስድስተኛው የሃይማኖት መገለጫ ወይም ስምንተኛው የቤተ ክርስቲያን ምስጢር ነው ብለው ከሚያምኑ ሰዋች ይሠውረን፡፡ ለእኔ ማኅበረ ቅዱሳን ፕሮጀክት ነው እስከ አሁን በጣም የተወሰ ስኬታማ ውጤት አምጥቷል የጣሩትን አመስግኖና የምስክር ወረቀት ሰጥቶ ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ መሠራት አለበት፡፡ አሁነ ማኅበረ ቅዱሳን ወጥ ረግጧል፣ የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የመንደር፣ የኑፋቄ ማኅበር ሆኗል ማመን ካልፈለጋቸውሁ በብቁ ማስረጃ በሂደት ሁሉንም እናጋልጣለን እኛ የሰው ገመና ለምን ይጋለጥ ብለን ነው እንጅ፡፡

    አሁንም የምንጠብቀው ምንም እንኳ መደራጀት መብት በሕገ መንግሥት የተሰጠን ቢሆንም እንኳን ማኅበረ ቅዱሳንና ንጉሠ ነገሥቱ ሳይቀሩ የክብር አባል የነበሩበት፣ ፓትርያርኩ የሚመሩት፣ በሲኖዶስ ታወቀ፣ ከቤተ ክህነት በጀት የነበረው፣ ታላቁ ሃይማኖተ አበውም በዓለማዊውና ደርግ በሾመው ሥራ አስኪያጅ በአንድ ደብዳቤ ታግዷል፡፡

    ReplyDelete