Thursday, May 17, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ክፍል የዋልድባን ጉዳይ በተመለከተ የቤተ ክህነቱ አጣሪ ኮሚቴን ሪፖርት ያልዘገበበትን ምክንያት እንዲያብራራ ተጠየቀ

click here to read in PDF
ህዝብ ሆይ ስማ!! ተነስ! ታጠቅ! ዝመት! ዋልድባ ገዳም ተተረማመሰ። እያለ በድረ ገጾቹ ግልጽ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እያደረገ ያለው የመንፈሳዊነት ጭላጩ እንኳ የሌለው ማኅበረ ቅዱሳን በዋልድባ ጉዳይ ከቤተክህነት የተሰጠውን መግለጫ ላለመዘገብ መወሰኑ የቤተክህነቱን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ አስቆጣ።
የህዝብ ግንኙነት መምሪያው የሰንበት ማደራጃ መምሪያውን ማኅበረ ቅዱሳን ለምን ዜናውን እዘግባለሁ ካለ በኋላ ባሉት ህጋዊ ሚዲያዎቹ ሁሉ ላለመዘገብ መወሰኑን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጥበት በማዘዝ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው በደብዳቤ ጠይቋል። 
ለዚህ ጥያቄ የራሱን መልስ መስጠት የማይችለው ሰንበት ማደራጃ መምሪያው ጉዳዩ የማህበሩን የሚዲያ ክፍሎች በተመለከተ ይሆናል በሚል ርዕስ ባወጣው ደብዳቤ ለምን ዜናውን ሳትዘግቡ ቀራችሁ የሚል ጥያቄን ጠይቆ ለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡበት አዟል። የሁልጊዜውም አላማው የፖለቲካ አየሩ ላይ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አቧራ ማቡነን የሆነው ማቅ ዋልድባን በተመለከተ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ ሲሆን ባለፉት 2 ወራት እንኳ ከ20 በላይ የግልጽ ተቃውሞና ህዝብን የማነሳሳት ዘገባዎችን አንዳችም መንፈሳዊ ባህሪ በሌለው መልኩ ማቅረቡ የሚታወስ ነው። እንዲያውም የማህበሩ ብሎጎች በሚያደርጉት ቅስቀሳ ጠብቀውት የነበረውን የአረቦች መነሳሳት አይነት አመጽ ሊያገኙ ባለመቻላቸው ስሜታውያን ህጻናት እንደፈለጉ እንዲቧችሩበት ፈቅዶ ማቅ ባቋቋመው አንድ አድርገን በተሰኘ ብሎግ እኛስ ሞተናል በሚል ርዕስ ምሬቱን መግለጹ አይዘነጋም።

ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ በግልጽ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ በስውር ከፍተኛ የሆነና አልቃይዳ ተኮር ስልት ህዝብን በመንግስት ላይ ለማነሳሳት የሚያደርገው ቅስቀሳን ሽባ እንደሚያደርግበት ስለተረዳ በቤተ ክህነቱ የተሰጠውን መግለጫ የጋዜጠኛ ስነ ምግባርን በጣሰ መልኩ በህጋዊ የዜና ማሳረጫ መንገዶቹ  ላለመዘገብ ወስኗል።
ዳንኤል ክብረት እንደነገረን ከፍተኛ የአቅም ማነስ የሚታይባቸውና ሙያንና ስሜትን ለይተው የማያውቁት የማኅበሩ ጋዜጠኞች በይፋ የተዘገበን ዜና በይፋ እንዘግባለን ብለው ሄደው ውለው ሳያድሩ ግን በብሎጎቻቸው የቤተክህነቱን አጣሪ ኮሚቴ መግለጫ በከፍተኛ ሁኔታ እያጥላሉ ዘግበውታል።
ከኔ ወዲያ ላሳር የሚለው ማቅ የራሱን አጣሪ ኮሚቴ ወደ ዋልድባ ልኮ አጣርተው መመለሳቸው ይታወቃል። ልኡካኑ ደረሱበት የተባለውም ድምዳሜም ፕሮጀክቱ ችግር የለውም የሚል ነው። ማኅበረ ቅዱሳን የውጭ አገር ደጋፊዎቹን መንግስት አስገድዶኝ እንዲህ ብለህ መግለጫ ስጥ ብሎኝ ነው መግለጫውን የሰጠሁት ብሎ ማሳመን እንደሚችል ቢያውቅም፣ የአገር ውስጦቹን ግን በምን እንደሚያሳምናቸው ማጣፊያው አጥሮታል። የማኅበሩ አባላት በሞባይል የጽሁፍ መልዕከት ለአባለት ብቻ ጥብቅ ምሥጢር ተባብለው በሚላላኩበት የ “ተነስ ወደ ዋልድባ” ቅስቀሳ ደማቸው የሞቀውን አባላቱን ቁጣቸውን ወደ እኔ እንዳያዞሩ ሲል ልዑካን ልኬ አጣርቼ ደረስኩበት ያለውን የስኳር ፕሮጀክት ምንም ጉዳት የለውም የሚለውን መግለጫውን እስካሁን ለማቅረብ አልደፈረም። የ “ተነሱ” የጹሁፍ መልዕክት ከደረሳቸው አባላቱ አንዳንዶቹ ይሁን ሁሉ ቅስቀሳ አድርገው የእኛን ልብ ወደ ሌላ አቅጣጫ ከገፉ በኋላ አሁን ችግር የለውም ቢሉ በቀላሉ አንላቀቃትም። የእነርሱ የፖለቲካ ፍላጎት ማርኪያ ሆነን መቀጠልም አንችልም ሲሉ ተደምጠዋል።
በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ምጥን ዘገባ" ከሀይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለሀይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።" የገዳሙ አባቶች፣ የዋልድባ ጉዳይ በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ዘገባ (ክፍል ሁለት)የስብሰባ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ መጋቢት ቀን ፳፻፬ ..የዋልድባ ገዳም አበምኔት ቤት በፌዴራል ፖሊስ ፍተሻ ተካሄደበት‹‹ስለ ዋልድባ ለመሰዋት ተዘጋጅተናል›› የገዳሙ መነኮሳት VOA ‹‹ራሳችንን ለሰይፍ አዘጋጅተን የተቀመጥን ሰዎች ነን›› የዋልድባ መነኮሳት እና በሌሎችም ርዕሶች ከፍተኛ ቅስቀሳ ያደረገው ማቅ ለምን በህጋዊ ድረ ገጹና ባለው ጋዜጣና መጽሔት እንደ ጋዜጠኛ የቤተክህነቱ አጣሪ ኮሚቴ የደረሰበትን ውጤት ለማስተላለፍ ሳይፈቅድ ቀረ የሚለው ጥያቄ መልስ የማህበሩን ጭፍን ፖለቲካዊ አቋም የሚያረጋግጥ ነው።
በቅርቡ እንኳ ቤተክርስቲያኒቱ የራስዋን አጣሪ ኮሚቴ ልካ የደረሰችበትን ውጤት ማሳወቅዋ እየታወቀ በአንድ አድርገን ብሎግ “የዋልድባ ገዳም ጉዳይ እንደ አጀንዳ አለመያዙ እያነጋገረ ይገኛል” በሚል ርዕስ ባወጣው ጹሁፍ ቅዱስ ሲኖዶስን ክፉኛ ወርፏል። በጽሁፉ ውስጥ “… በተጨማሪም እስከ አሁን ዝም ያሉት አባቶች አቋማቸውን ያንጸባርቃሉ ተብሎም ይጠበቃል ፤ ይህን ጉዳይ በዋና አጀንዳነት ይዘው መነጋገር ካልቻሉ የእነርሱም ሰልፍ ከወዴት እንደሆነ ይታወቃል ፤ ይህ ደግሞ ምዕመኑ ከእዚህ በፊት  በቋፍ ላይ የነበረውን ለአባቶች ያለውን እይታ እስከ ወዲያኛው ገደል ሊከት ይችላል ፡፡ ብሎ  እኛ ያልነውን ካላላችሁ እንደ አርዮስ የተወገዛችሁ ናችሁ የሚል አንድምታ ያለው ሰለፊነቱን የሚያስመሰክር የፍረጃ ዘገባ አውጥቷል። 
የማቅ ብሎጎች እየተቀባበሉ ከፍተኛና ግልጽ በሆነ ሁኔታ የ “ተነሳና ተፋለም” ቅስቀሳ እያደረጉ ባለበት በዚህ ወቅት አስተዋይ ልቦና ያለው ሰው ሁሉ በማቅ ፕሮፓጋንዳ እንደ መናጆ ከመነዳት ነገሩ እውነት ይሆንን? ብሎ በማስተዋል እንዲመላለስ የዝግጅት ክፍላችን በአጽንኦት ያስረዳል። እኛ ባለን መረጃ መሰረት ፕሮጀክቱ ቀጥታ ዋልድባን እንደማይነካና ከሚታይ ግልጽ ችግር ይልቅ ገዳሙ የተያያዥ ችግሮች ሰለባ ሊሆን እንደሚችል ያደረግነው ጥናት ያመለክታል። ተያያዥ ችግሩም ቢሆን ሊከሰት የሚችልበትን እድል አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ መቀነስ እንደሚቻል እናምናለን። በእውነት ቤተክርስቲያናችን የምትጎዳበት ትልቅ ችግር ቢኖር ኖሮ የማቅን ሃሳብ በመደገፍ እንቆም እንደነበር እንገልጻለን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደጀ ሰላም ጉዳዩን በሚመለከት በጻፈው ጽሁፍ እንዲህ ሲል የተጻፈበትን ደብዳቤ ይዘት አጣጥሏል። “በእውነት በአገሩ ሕግ የለም ማለት ነው? በየትኛው አገር ነው አንድ ጋዜጠኛም ሆነ የሚዲያ ተቋም ስለዘገበው ሳይሆን ስላልዘገበው ነገር የሚጠየቀው? ስለጻፈው ሳይሆን ሳይጽፍ ስለቀረው የሚፈረድበት? ይህ በዓይነቱ በየትም ዓለም ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቀው ክስ መጨረሻው ምን እንደሚሆን ለማወቅ በጣም ያጓጓል። ደብዳቤውየጋዜጠኝነት ሥነ ምግባርን ማጉደልያለውን ይህንን ላልጻፉት ጽሑፍ የመወንጀልን ጉዳይ በዓለም የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ በብቸኝነቱ ሊያስመዘግብ የሚችለውን ጉዳይና ውጤቱን ወደፊት የምናየው ይሆናል።” እኛም ደጀ ሰላምን በየትኛው ሃገር ሕግ ነው የማኅበር አቋም ጋዜጠኝነት ላይ የሚንጸባረቀው? በየትኛው ሃገር ሕግ ነው ጋዜጠኛ የሚፈልገው ነገር ሲነገር ብቻ የሚዘግበው? በየትኛው ሀገር ህግ ነው ሚዲያን ለተንኮልና ሸፍጥ ተግባር የሚውለው? ብለን እንጠይቀዋለን። መግለጫው ላይ የተገኛችሁት እኮ እናንተ የምታምኑትበትን ልትዘግቡ ሳይሆን የቤተክህነትን አቋም ልትነግሩን ነው? ይሔ የእናንተ አቋም እስካልሆነ ድረስ ምን ያስፈራችኋል? ነገሩ ምን ያለበት ምን አይችልም ሆኖ ነው እንጂ በጉዳዩ ላይ የቤተክህነትን አቋም መግለጽ ምን አስፈርቷችሁ ነው ለመዘገብ ያልፈለጋችሁት? ሕዝቡ የቤተክርስቲያንን ድምጽ ከሰማ የአሰባችሁትን የአመጽ መንገድ አይሳካም ብላችሁ አይደለምን? ስለዚህ በጉዳዩ ላይ መልስ መስጠት አለባችሁ።
 ማቅ ጉዳዩን በትክክል ሳያጣራ ዳንኤል ክብረት እንደነገረን ወሬንና መረጃን ለይተው የማያውቁ የመረጃ ክፍል ሰራተኞቹ “ተባለን” “ሆነ” ብለው ቸኩለው ስላስወሩ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ስልት ተቃውሞውንና የ “ተነሱ” ቅስቀሳውን አጠናክሮ በመቀጠል ላይ ይገኛል። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ገንዘብ ላይ ዘሎ ፊጥ የሚለው ማቅ በውጭ አገር በሚኖሩ አባላቱ አማካኝነት ዋልድባን እናድን የሚል የገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገድ የቀየሰ ሲሆን፣ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ዋልድባን ለማዳን የገንዘብ መዋጮ ያስፈልጋል ወይ? ብሎ መጠየቁ አግባብ ነው። ይህ ጉዳይ ስህተት ነው ብሎ የሚያምን ክርስቲያን ከመንግስት ጋር በስነ ስርዓት ተነጋግሮ ፕሮጀክቱ የሚቀየርበትን መንገድ ከመቀየስ የተሻለ አማራጭ እንደሌለው ገልጽ ሲሆን ለዚህም ደግሞ የገንዘብ መዋጮ እንደማያስፈልገው የታወቀ ነው። አንዳንድ ወገኖች ማቅ ዋልድባን እናድን በሚል ሰበብ ገንዘብ እያሰባሰበ ያለው ምናልባትም በሰበሰበው ገንዘብ ዋልድባን ለማዳን ሲል መሳሪያ ለመግዛት አስቦ ነው በማለት እየተሳለቁ ይገኛሉ። ለነገሩ እንተዋወቅ የለ! መሳሪያውስ ቢኖር ልቡ ከየት ይመጣል? በተንኮል በመሰሪነትና ጉቦ በመስጠት ውጊያ እንደሁ የለ!!

4 comments:

  1. Awde Mihiret Daneil Kiberet Hulunim Neger Tenagirotal Ahun Sew Hulu Lebete Kirsitan Sayihon Le Mahibere Kidusan Endihon New yemfelgew Abba Sereke -D Begashaw Abune Pawlos Yetenekutina Menafik Nachew Yetebalut Bete Kiristiyann Sileneku Sayihon Mahibere Kidusann Neku tebilo new
    Awde Mihiret Enantem Menafik Timesilalachihu DEgimo zegebachihu melkam new Ahunim Mahibere Kidusan Wede Libu Temelso Lebete Kirsityan mekom Alebet
    Mahibere Kidusan Gonder & Tigiray Yetewelede Sew Metsifat Alebet Gojam & shewa Menor Alebet Yemil New Lemehonu Deje Selam -Ahat Tewahedo-And Adirgen-Gebir Her Yetebalutin Bilogoch Yemiyazegajew Sew Manew ?Amercia Yalutin Enawkalen Addis Abeba Yalut Eneman Nachew ?

    ReplyDelete
  2. Awde MIhiret MAhibere Kidusan Yemefires Adega Yagatsimewal Bemalet zegebachihu Ahat Tewahedo degimo sinodosu yetemeleketew yemahiberat guday Mahibere Kidusann Ayimeleketewm Ale Mann enmen ? Awde MIhiretn weis Ahat Tewahedon Awde Mihiret Yezegebew Min Ayito Min SEmto New ? weyis Ahat Tewahedo yeminagerew Belibu Yasebewn New ?Ahun sile Mahiberat yetewesenewn besefiw zegibu

    ReplyDelete
  3. Mechem Gojam Le Ashimur yetefetser yimesilal D Daneil Kibret Kahinate Aorit eyale Abatochchinn Yetenagerewn 05 17 2012 yezegebewn temelketu yigermal Huligize ashimur

    ReplyDelete
  4. This article itself is vicious propaganda. This can be seen from "MaQ". The organization calls iself "Mahbere Qdusan", not "MaQ". The aim of the article is to reinforce Melles' unnatural comparison of "some Salafists" with Mahbere Qdusan. Terrible.

    ReplyDelete