Friday, May 18, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ሰባተኛ ቀን ውሎ

Click here to read in PDF
  • አንዳንዶቹን ግረለሰቦች ሊቃውነት  ጉባኤ ጠርቶ ስላላነጋገራቸው ጠርቶ እንዲያነጋግር ታዘዘ
  • አቡነ ገብርኤል ከአዋሳ አይነሱም
  • የሰንበት ማደራጀውና የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ ታየ
  • ዲ/ን አሸነፊ መኮንን በፍጹም ይወገዝ ተብሎ አልቀረበም
በትናንትናው ዕለት በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ከተነጋገራባቸው ጉዳዮች አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን እንዲወገዙ ከቋመጠባቸው ግለሰቦች አንዳቸውም ሳይወገዙ እንደ ገና መታየት ያለባቸው ነገሮች እንዲታዩና ሲኖዶሱ ሊቃውነት ጉባኤው ሰዎቹን ጠርቶ በጥንቃቄ መርምሮ ይወሰወን የሚለውን ባለሟላቱ እንደገና ያላነጋገሩዋቸውን ሰዎች እንዲያነጋግሩ ታዘዘ። 

የአባ ሰረቀ እና የዲ/ን በጋሻው የውግዘት ሀሳብ እንደአልቀረበባቸውታውቋል። በጋሻው በትናንትናው ዕለት ሊቃውንት ጉባኤ ሊያነጋግረው ፈልጎ ተጠርቶ የነበረ ቢሆንም ሊቃውንት ጉባኤው ራሱ በሲኖዶሱ በመጠራቱ ሳያነጋግሩት ቀርተዋል። ደጀ ሰላም ዲ/ን በጋሻው ሊለማመጥ ሄደ ያለው ከሀቅ የራቀ ሲሆን ሊቃውንት ጉባኤው ስለጠራው መሄዱ ታውቋል።

“አቡነ አብርሃም ምንድንነው መልሶ መልሶ ነገር ማየት መናፍቁን ሁሉ ማውገዝ ነው። ለእነኚህ ደግሞ የማሕበረ ቅዱሳን ጥናት አነሳቸው?” ብለው የደነፉ ሲሆን በዛን ወቅትም ቅዱስ ፓትርያርኩ አቅማቸውን እንዲያውቁና ለማንበብ ለመጻፍ ዝግጁነት ሳይኖራቸው ይወገዙልኝ እያሉ ወመወራጨታቸውን እንዲያቆሙ አዝዘዋል። እኛ ለእውነት እንጂ ለማንም ማድላት የለብንም ድጋፍ ድምጽ ሰብስበን ሳይሆን የነገሩን እውነትነትና በጥንቃቄ መታየቱን መርምረን መፍረድ ነው የሚገባን አሊያ የሁሉ አባት መሆናችን በምን ይታወቃል? የተቀመጥንበት ወንበርም ይኼን ነው የሚያዘን በማለት ተናግረዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን የመጽሐፍ ገበያውን ለብቸኝነት ተቆጣጥሮት የኔ መጽሐፍ እንዳይሸጡ አድርጓል ያለውን ዲ/ን አሸናፊ መኮንንን እንዲወገዝለትና የመጽሐፍ ገበያውን በብቸኝነት ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረውም ሊቃውንት ጉባኤው ግን ውግዘት አይገባውም ምክር እንጂ ሲል ሪፖርት አቅርቧል ይህንን ገልብጦ ያነበበው ደጀ ሰላምም በትናንትናው ዕለት ይወገዛል ሲል የዘገበ ሲሆን ትንንትናም እንደሌላው ቀን ማንም ሳይወገዝ አልፋለች።

አባ አብርሃም ሊቃውንት ጉባኤው የውጭ ተጽዕኖ አለበት ሲሉ እንደተናገሩ ታውቋል። እኛም ይህ የሲኖዶስ ስብሰባ ከተጀመረ ከአባ አብርሀም የሰማነው አንድ ቁምነገር ይኼ ነው እንላለን። አባታችን ሊቃውንት ጉባኤው አዎን ተጽእኖ አለበት ተጽዕኖውም ከማኅበረ ቅዱሳን የመነጨ ነው እንልዎታለን። አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ እንደሚባለው ሊቃውንት ጉባኤው አባል በሆኑ የማኅበረ ቅዱሳን አባቶች እና የማኅበሩ ተጽዕኖ በከፍተኛ ደረጃ እንዳለበት የሚታወቅ ነው። 

የአዋሳው ጉዳይ የተነሳ ሲሆን በሁለት ወገን የተወጠሩት አቡነ ገብርኤል ከቦታቸው እንዳይነሱ ተወስኗል። ማኅበረ ቅዱሳን የምፈልገውን ሥራ አልሰሩልኝም በማለት በአባ አብርሃም ሊተካቸው ቢፈልግም ሳይሳከለት ቀርቷል።
የማኅበረ ቅዱሳንና የሰንበት ማደራጃ ጉዳይ የተነሳ ሲሆን ሁሉም ባለህበት እርጋ ተብሏል።

1 comment:

  1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
    ቅዱስ ሲኖዶስ ውይይት አጀንዳዎች ይዘት ከወቅታዊ ጉዳዮች አንጻር

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሃኛው ክፍለ ዘመን ከደረሰችባቸው አበይት ስኬቶች አንዱ በራስዋ መንበር በራሳዋ ፓትርያርክ በራስዋ ሊቃውንት ጳጳሳት መመሪት መጀመርዋ ነው፡፡ ይህም በሊቃውንቷ ብርታት በሦስት ነገሥታት ዘመን በዮሐንስ አራተኛ፣ በዘውዲቱ፣ እና በኃይለ ሥላሴ ዘመናት ነገሥታቱን መሣሪያ አድርገው የተቀዳጁት ድል ነበር፡፡ አሁን የሚያሰጋት የቀደሙት አባቶች የደረሱበትን ስኬት በየቦታው በሚሱልከለኩ የድሞው መንግሥት አስተሳሰብና አመራር ቅሬት አካሎችና የወቅታዊ አጥፊ ፖለቲካ አራማጆች፣ እንዲሁም የልዩ ጥቅም ተጋሪ ቡድኖች ጉዳይ አስፈጻሚ ባለአደራ ጳጳሳት እንዳይፈርስ ነው፡፡

    በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን በልዩ ልዩ ከፍተኛ ለውጥና ውጥረት ላይ ትገኛለች፡፡ ለውጦቹ ለምሳሌ ፈጣን ልማት፣ የድኅነት ቅነሳ፣ ለሞት የሚዳርጉ በሽታዎችን መቆጣጣር፣ የትምሀርትና የመረጃ ጥራት ማጠበቅ፣ የሰለጠነ የማኅበራዊ አደረጃጀት፣ የቱሪዝምና የባሕል ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ የሕጻትና የእናቶች ደህንነት፣ የፍትሕና የሰላም ትግበራ፣ የመሳሰሉት ሲሆኑ ውጥረቶቹ ከምራስቅ አፍሪካ መልከዓምድራዊ አቀማመጥ፣ በተያያዘ፣ የአክራሪዎች በሀገሮች ፖለቲካዊና ማኅበራ ደኅንነት ላይ የፈጠሩት ጫና፣ የተረጋጋ ሀገራዊ አደረጃጀት ከሌላቸው ሀገሮች የሚሰነዘሩ ጥፋቶች መከላከል፣ የተፈጥሮ ሀብት መራቆትና የኢነደስትሪ ጥሬ ዕቃ አቅርቦትን ማደራጀት፣ የመንግሥት ተቋማት ለሕዝቡ ብቁ አገልግሎት ስለሚሰጡበትና ሚዛናዊ የገበያ ሥርጭት ስለሚኖርበት ሁኔታ፣ በመሳሰሉት ከፍተኛ ተጠያቂነት ያለባቸው ጉዳዮች ላይ መንግሥት ሌሊት ከቀን እየሠራ ይገኛል፡፡ የዚህም ጥረት ዋና ምክንያት ምን ዓይነት ሀገርና አካባቢ ለተከታዩ ትውልድ ማስረከብ ይገባናል ከሚል ከፍተኛ የሀላፊነት ስሜት የመነጨ ልዩ የአስተሳሰብ ደረጃ ነው፡፡

    ከዚህ አንጻር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዓርባ ሚሊየን ሕዝብ የሀገሪቱን አጠቃላይ ሕዝብ ከ60 በመቶ በላይ የምትመራ መለኮታዊ (የመለኮት እገዛ የማይለያት) ተቋም ስትሆን አባቶች ደግሞ መለኮትን ፈቃድ የሚፈጽሙ ለከፍኛው መንፈሳዊ ተልዕኮ የተጠሩና የተሸሙ በዚሁ በተጠሩበትና በተሸሙበት የሥራ መስክ መክበርና መከበር የሚገባቸው ሊቃውንትና ቅዱሳን ናቸው፡፡ ይህ የሚሆነው ግን በዓመት አንድ ጊዜ ሲገኛኙ ሊያነሱ የሚገባቸው ጉዳዩች ቤተ ክርስያኒቱ ካላት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሕልውና፣ ሀገራዊና ሰብዓዊ ኃፊነት ጋር ሲገናኙና ሲታረቁ ነው፡፡

    ቅዱስ ሲኖዶስ ከፍተኛ ከበሬታና ኃፊነት በሚሰጣቸው አባቶች የተዋቀረ ከላይ በመንፈስ ቅዱስ ከታች በሕዝብ እምነትና ጸሎት፣ ከላይ በመለኮት ፈቃድ ከታች ከኛ ይሻላሉ ተብለው በተሸሙ ቅዱስ አባት እየተመራ አጀንዳዊቹ ምን መሆን አለባቸው ሚለው ነገር በቅጡ ካልተመለከትነው በርግጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ያለው የት ነው? የማንን ጉዳይ ነው የሚያፈጽመው? ለማን ሕልውና ነው የቆመው?የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡

    የሀገርን ጉዳይ ጉዳየ ማለት ይቅርና የቤተ ክርስያኒቱን ጉዳይ እንኳ እኮ በቅጡ እየተመለከቱ ነው ወይ፡፡ ዋናዎቹ የጳጳሳቱ መገኛ፣ የቅርስ ባለቤት፣ የታሪክ መዛግብት የሆኑት ገዳማት በከፍተኛ ደረጃ ተጉሳቁለው የተወሰኑ ቡድኖች በስማቸው አሮጌ ጨርቅ ሳይቀር እየለመኑባቸው፣ ኪስ መሙያ ሆነዋል፡፡ መነኰሳቱ የኮሙኒዝም ሥርዓት ካደረሰባቸው ግፍ በበለጠ ለልማትና ለእድገት እንቅፋት እንዲሆነ እስከመቀስቀስ በመድረስ የሁለት ዓለም ስደተኞች ሆነዋል፡፡ ጳጳሳቱ ከገዳማቱ ጋር ያላቸው ግንኙነት ላልቶ የከተማ ወጣቶች አለንላችሁ በማለት የሚነግዱባቸው፣ የዓለማውያን ጊዜ ማሳለፊያ ሆነዋል፡፡ ለመሆኑ ለገዳማቱ ጉዳይ ማነው ተጠያቂ፣ የከተማ ወጣቶች ወይስ የገዳማት መመሪያ፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር መገኛ የነበሩት የአብነት ትምህርት ቤቶች እንደገዳማት መነገጃ ሆነዋል ትምህርት መመሪያን በብቃት ማጠናከር ሳይቻል ቀርቶ ነው ወይስ አሁንም የጥቅም ጉዳይ አለበት

    የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ፣ የቅርስና ቱሪዝም ፣ የወጣቶች፣ የልማት ጉዳይ እኮ ለማንም ተላልፎ ሊሰጥ የማይችል የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ብቻ በዋናነት ሊሠራ ሚገባ ማንም ጣልቃ ሊገባበት የማይችል አስተዳደራዊ ተግባር ነው፡፡ ይህንን ከመለኮት ለቤተ ክርስቲያኒቱ የተሰጠ አደራ በቤተ ክርስያኒቱ ስም ለተዋቀሩ ቡድኖች አሳልፎ ከሰቱ በኋላ ይስተካከል ሲባል ቆቤን አወልቃለሁ ማለት ትርጉሙ ምንድን ነው፡፡

    ዛሬ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያሠጓት ዋና ዋና ጉዳዮች ስብከተ ወንጌል በተረት መዳከም፣ የቅርስ ዝርፊያና ውድመት፣ ወጣቶችን የሚመለከት ማዕከላዊ የሆነ አሠራር አለመኖር ወይም የማደራጃው ድክመት፣ በካህናት መካከል የሚፈጠሩ ጉዳዮችን የሚፈታ የፍትሕ መታጣት፣ ለቁጥር አዳጋች የሆኑ ደቃቅና የተደራጁ ማኅበራት ክፍፍልና የርስ በርስ ግጭት፣ የገዳማት አስተዳደር መዳከም፣ የገንዘብ ብክነትና ውደመት፣ ለራሳቸው ጥቅም ብቻ የሚተጉ ሀገረ ስብከት የለሽ የድርጅትና የቢሮ ሐዋርያት (ጳጳሳት)፣ ማዕከሉን ያልጠበቀ የውጭ ግንኙነት፣ ፍጹም ፖለቲከኞች ሆኑ ጳጳሳት፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተዳከሙ መምጣት፣ ወጣቶች ከሰንበት ትምህርት ቤት ውጭ፣ ከወጣትነት በኋ ያሉት ምእመናን ከሰበካ ጉባኤ ውጭ በመደራጀት መከፋፈል፣ የሌሎች ሃይማኖቶች እየበረቱ መምጣት፣ የመሳሰሉት ናቸው…

    ታዲያ አባቶች ጊዜያቸውን እያጠፉ ያሉት በምን ላይ ነው፡፡ እርስ በርስ በመወነጃጀል፣ በማደም፣ ከመዋቅራቸው ይልቅ ለቡድኖችና ዶግማና ቀኖና ላፈረሱ ሁሉም ማኅበራት ጠበቃ መቆም፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሥራ እንቅፋት በመሆን፣ እኔ እስከማምነው ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያዳከማት ሁሉም ራሱን ሥራ ባለመሥራቱ ነው፡፡ ተሐድሶ ለም ማለት አይደለም ግን ቤተ ክርስያኒቱ ከተደዳከመች ለምን አይገቡ ዓላማቸው እኮ ነው፡፡ መጡብን ብሎ በመረበሽ፣ ወይም የረብሻ ወሬ ላመጡት ከመሟገት መዋቅሩን አጠናክሮ ሥራ መሥራት፣ ማኅበራቸው ሥርዓትና መዋቅር እንዳይዝ ሚታገሉት ቡድነኞች ለምን መዋቅሩ ውስጥ ገብተው ሥራ አይሠሩም ተሀድሶን አይከላከሉም፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤት ገብተው እንዳይማሩ ማን ከለከላቸው፣ በሰበካ ጉባኤ ታቅፈው እንዳያገለግሉ ማን አገዳቸው ልማትን በልማት ኮሜቴ ገብተው እንዳያለሙ ማን አገደ በፖለቲካዊ ማኅበር ተገንጥለው ከመዋቅር ውጭ ሆነው ለመሥራት ለምን ፈለጉ፡፡

    ይህንን የመንግሥት አካላት ሳይቀሩ ሊታዘቡት የሚገባ ሐቅ ነው እንላለን፡፡

    ReplyDelete