Saturday, March 10, 2012

ሰበር ዜና - የዘመድኩን ባልንጀራ ጨዋው ደስታም ጥፋተኛ ተባለ


የመጋቤ ሀዲስ በጋሻውን ስም በማጥፋት ክስ የተመሰረተበት አቶ ደስታ የተባለ ግለሰብ ላይ የቦሌ ምድብ ችሎት ጥፋተኛ አለው፡፡ በከሳሽና ተከሳሽ የቀረቡትን ቅጣት ማከበጃና ማቅለያ ካዳመጠ በኋላም ብይን ለመስጠትም ለመጋቢት 5 2004 ቀጥሮ መስጠቱን ምንጮቻን ገለጹ፡፡

የፊትአውራሪያቸውን የዘመድኩንን ፈለግ ተከትለው ሳሩን እንጂ ገደሉን ሳያዩ ነበር ሳህሉና ደስታ ለደረሳቸው የማህበረ ቅዱሳን ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ የሠጡት፡፡ በንግድና በፖለቲካ እንጂ በመንፈሳዊ አገልግሎት ምእመናንን መማረክ ያልቻለውና ኪሳራ እየደረሰበት የነበረው ማህበረ ቅዱሳን በወንጌል አገልግሎትና በዝማሬዎቻቸው የብዙ ምእመናንን መንፈሳዊ ረሃብ ማስታገስ የመንፈስ ጥማቸውንም ማርካት የቻሉትንና እርሱን ከገበያ ውጪ ባደረጉት በእነመጋቤ ሐዲስ በጋሻውና በእነዲያቆን ትዝታው ላይ ‹‹ከህዝብ ልብ ማስወጣት›› በሚል የሰየሙትን የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈታቸውን ተከትሎ ማህበረ ቅዱሳን ለዘመቻው በመደበው ገንዘብ መጽሀፍ አዘጋጅተን በስማችን በማሳተም እነበጋሻው ከህዝብ ልብ እናስወጣለን ሲሉ <<ትግሉን>> ተቀላቀሉ፡፡ የመጋቤ ሀዲስ በጋሻውን ስም የሚያጠፉ መጽሀፍትን በስማቸው አሳተሙ፡፡ መጻህፍቶቹን እነርሱ መጻፋቸውን ብዙዎቹ ይጠራጠራሉ፡፡ በተለይም ከ3ኛ ክፍል ትምህርቱን አቋርጧል የተባለውና አንዳች የቤተክርስቲያን ትምህርት የሌለው ጨዋው ደስታ ሊጽፍ እንደማይችልና፣ ልቦለዱን ጽፎ የሰጣቸው የማህበረ ቅዱሳን የስም ማጥፋት ዘመቻ ክፍል መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ጨዋው ደስታ በስሙ ስላሳተመ ደህና ገንዘብ ተከፍሎታል የሚሉት ውስጥ አዋቂዎች፣ ማህበረ ቅዱሳን ካለ ማንም አይነካኝም የሚል ጽኑ እምነት ነበረው ሲሉ ያክላሉ፡፡

ስሙ የጠፋው መጋቤ ሀዲስ በጋሻው ክስ መመስረቱን ተከትሎ ሳሩን ብቻ ሳይሆን ገደሉን መመልከት የቻለው ሳህሉ የተመደበለትን ብር ከበላና ማህበሩ የሰጠውን ግዳጅ ከተወጣ በኋላ ከበጋሻው ጋር ጉዳዩን በእርቅ ለመጨረስ ሽማግሌ መላክ ጀመረ፡፡ መጋቢ ሀዲስ በጋሻውም እንደ በደሉ ሳያስከፍለው ማለትም ‹‹የበደለኝ በጽሁፍ ነውና ተመጣጣኝ ማስተባበያ በጽሁፍ ካልሰጠ አልታረቅም›› ሳይል፣ ከክርስቶስ እንደተማረው ይቅርታውን ተቀብሎ ክሱ ተቋረጠ፡፡ ይቅርታ መጠየቅን እንደ ሽንፈት የቆጠረውና ከመታረቅ ሲኦል መግባትን የመረጠው ዘመድኩን እንደምርጫው ወደማረሚያ ቤቱ ከገባ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደዘመድኩን ‹‹ይቅርታ አልጠይቅም፤ ካለ ማህበረ ቅዱሳን ማን ይነካኛል ያለው›› ደስታም ማህበሩ ሳያስጥለው ዘመድኩን ባለበት እርሱም ሊኖር ዛሬ መውጫ መቁረጡ ታውቋል፡፡ የፊታችን መጋቢት 5 ቀንም ዘመድኩንን ሊያጫውት ወደዚያው እንደሚያቀና ይጠበቃል፡፡

ዘመድኩንና ደስታ በማህበረ ቅዱሳን መደለያ ተደልለው በስም ማጥፋት ወንጀል ውስጥ መነከራቸውና ጥፋተኛ መባላቸው አሳዛኝ ሲሆን፣ ማህበሩ እንደእነዚህ ያሉትን ማገናዘብ የማይችሉና ወንጌልና ወንጀልን ለይተው የማያውቁ ሰዎችን በጊዜያዊ ጥቅም እየደለለ የፈለገውን በማድረግ ላይ መሆኑን ሁሉ ሊያውቀው ይገባል፡፡ ማህበሩ እሳትን በሰው እጅ የመያዝ ስልትን እየተከተለ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በየቦታው በገንዘቡ የቀጠራቸውን ወሮበሎች እያሰማራ የቤተክርስቲያንን እውነተኛ ልጆች ማሳደዱ ለዚህ ትልቅ ማስረጃ ነው፡፡ በወንጀል የተከሰሱትንና የተፈረደባቸውን ወንጀለኞች በወንጌል ምክንያት ነው በማለት የሰማዕትነት አክሊል ሊያቀዳጃቸው በመሞከሩ ደግሞ ማህበሩ ወንጌልና ወንጀልን ለይቶ የማያውቅ የፖለቲከኞች ስብስብ መሆኑን አስመስክሯል፡፡ ዘመድኩንን ሰማእት እንዳለው ሁሉ ደስታንም የዘመኑ ሰማዕት እንደሚለው ይጠበቃል፡፡

3 comments:

  1. kikikikiktaemere seretachehu motachehual...yetaweqale menafeqe eko hulea fukera newe....neche nafaqi hula...

    ReplyDelete
  2. yengigrachihu mastelate

    ReplyDelete