Friday, May 18, 2012

የአቡነ አብርሃም የጉድ ሙዳይ ሲከፈት

click here to read in PDF
አቡነ አብርሃምን የሚመለከት የጉድ ሙዳይ የሚል መጽሐፍ መጻፉን ባለፈው ጊዜ ገልጠን ነበር። የመጽሀፉ ሽፋንና ከፊል ታሪኩም እንደደረሰን እና በምቹ ጊዜ እንደምንለቀውም ተናግረናል። የመጽሐፉ ደራሲ ሲገለጽ በጊዜው ከልጅነት እስከ ዕውቀት ከእሳቸው ጋር ያደጉ ሰዎችን እንደሚያውቅ  እራሱም ስለእሳቸው በቂ እውቀት እንዳለው ያስረዳል። ያ ዳንኤል ክብረት የሚባል ሰው ልክ ያጣ ቅጥፈቱን በሀገር ልጅነትና በማኅበርተኛነት ስም ስለአስተጋባ እኛም የአገር ልጆቹ የምናውቀውን እውነት ለመናገራችን ማስረጃ እንዲሆነኝና ብዛታችንን እንዲያመለክትልን የጉድ ሙዳዩን አቡነ አብርሃምን እንደምናውቃቸው ብዬ በኔና በወዳጆቼ ስም ጽፌያለሁ ይለናል።
ዳንኤልንም "አንተም ታሪክህ የሚጻፍበት ቀን ስላለ ጠብቅ" የሚለው ሲገለጽ በጊዜው  ስለ አባ አብርሃም የሚያውቁትን ስጠይቅ እንቢኝ አልናገሩም ያሉ ወዳጆቼ የሚያውቁትን ሁሉ እንዲናገሩ ያደረጋቸው የአንተን ጽሁፍ ሳስነብባቸው ስለሆነ ለዚህ መጽሐፍ መጻፍ አንተም ቢሆን በዘባራቂነትህ ድርሻ አለህ። ይህን መጽሐፍ አንብበህም ምነው እጄ በተሰበረ ማለትህ አይቀርም ይለዋል። 
በትናንትናው ዕለት ቅዱስ ፓትርያርኩን ሃይማኖት እንዳለው ሰው "እርስዎንም በሃይማኖት ችግር እጠረጥርዎታለሁ" ብለው ሲናገሩ ትላልቆቹ ጳጳሳት እነ አቡነ ፊሊጶስ "እንዴት እንዲህ ይናገራሉ?" በማለት አባ አብርሃምን ገስጸው ተነስተው ጥለው በመውጣታቸው ክብራቸውን የማያውቁት ኣባ አብርሃም ተሸማቀው ቁጭ ማለታቸው ተሰምቷል።
 መቼም ጉድ ያለበት ሰው ንስሐ ገብቶ እስካልተመለሰ ድረስ ጉዱ እረፍት እየነሳ እወቁልኝ ንጹህ ነኝ ንጹህ ነኝ እያስባለ ያክለፈልፈዋልና? አባ አብርሃምን ሌላውን በመንቀፍ በመክሰስና ይወገዝልኝ በማለት ነውራቸውን ለመሸፈን ሌሎችንን ቆሻሻ በማለት የሚያደርጉት መሯሯጥ ስለበዛ አነሆ በሙላት ተዋወቋቸው ብለናል።
 መጽሀፉ
·        ስላለባቸው የሐይማኖት ሕጸጽ
·        ሰላሰሩት ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ
·        ስለአለባቸው የወገብ ችግር/በጣም በስፋትና በፎቶግራፍ የተደገፈ/
·        ራጉኤል ቤተክርስቲያንን እነዴት እንደዘረፉ
·        ከደብተሮችና መድሀኒት ቀማሚዎች ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት
·        ጎጃም ሳሉ ጉድ ስለሚያሰኙ ነውሮቻቸው
·        …… አስካሁን ድረስ የተላከልን ከፊል የመጽሀፉ ታሪክ ይዘረዝራል።
እኛም እንግዲህ ለዛሬ ስለ ሐይማኖት ሕጸጽና ስላሰሩት ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ከመጽሀፉ ወስደን እናቀርባለን።
“ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዓይናችን የምናየውን የቅዱስ ራጉኤልን ቤተ ክርስቲያን ለእንደዚህ አይነት ውበት ማብቃታቸው የልጅ አዋቂ አስብሏቸው ብዙ ውዳሴና ሙገሣ ተደርጎላቸው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ልጅ የያዘው ለራት አይበቃም እንደሚባለው በሕዝብና በካህናት ትብብር የተሠራውን ሁሉ ለራሳቸው ዝና ማትረፊያና ለጵጵስና ደጅ መጥኛ በማድረጋቸው የደብሩ ቀሳውስት ክፉኛ ተቀወሟቸው እንዲያውም ተመልሰው እንዳይገቡ ፖሊስ የማይበትነው ሰልፍ ከበሩ ላይ ጠበቃቸው በዚህም አፍረውና ተዋርደው ሊመለሱ የተገባቸው ሆነዋል፡፡ አቶ ምን ውየለት ለተባሉ አንድ የሰበካ ጉባዔ አባል በምሽት ሰዓት ስልክ ደውለው ‹‹የሸዋን ጋላ ተጫወትሁበት ከእንግዲህ ብሞትም አይቆጨኝ›› ማለታቸውና ከአንድ አባት ሊወጣ የማይገባው ጸያፍ ንግግር ከእርሳቸው መሰማቱ ይፋ ሆኗል፡፡ ዘመናዊ ትምህርታቸውን ከአራተኛ ክፍል ላይ ያቋረጡት አቡነ አብርሃም የ12ኛ ክፍል ማለትም የብሔራዊ ፈተና ፎርጅድ ማውጣታቸውም በዓይን ምሥክር ተረጋግጧል፡፡ በዚያን ዕለት መንግሥት ተከታትሎ ከእርሳቸው ጋር ያጭበረበሩትን በቴሌቭዥን ሲያጋልጥ እርሳቸውና የወገብ ችግር ፈቺያቸው የሆነች የአንድ ታዋቂ ጋዜጠኛ ልጅ(በመጽሐፉ ውስጥ የልጅቷ ስም የተገለጸ ቢሆንም እኛ ግን ለጊዜው ማለፉን መርጠናል) ከወንበር ሥር ተደፍተው እግዚኦ ማለታቸውም ተደርሶበታል፡፡ ይህንን ሙስና መንግሥት ጊዜው አልፎበታል ብሎ ይይዘው ይሆን ወይስ …..;”
ይልና ፎርጅዱን የትምህርት ማስረጃ እንዴት እንዳሰሩት ከማን ጋር እንደተዋዋሉና እነዴት እንደተደራደሩ ሰውየው ምን ያህል በአደባባይ ክብር በጓዳ ደግሞ ነውር ወዳድ እንደሆኑ በዝርዝር ያስረዳል። ይህ መጽሐፍ የወጣ ዕለት መንግስት ጉዳዩን በስፋት እንደሚይዘውና ምናልባትም ሰነድ በማጭበርበር ወንጀል የሚከሰሱና የሚታሰሩ የመጀመሪያው ጳጳስ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
ከዚህ ቀጥሎም ደግሞ መጽሐፉ አቡነ አብርሃም ስላለባቸው የሐይማኖት ሕጸጽ ሲያትት “ከደብረ ገነት እንነሳና እናውራ አባ ቃለ ጽድቅ /ብፁዕ አቡነ አብርሃም/ በምሥራቅ ጎጃም የቅባቶች አገር ከሆነው ጉንደ ወይን ማርያም ከሚባለው አካባቢ ተወልደው ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቅባቶች መፈጠሪያ ከሆነው ቆጋ ገዳም ገብተው ከፊደል እስከ ዳዊት ተምረው በዚያው መንኩሰው የቅባት እምነት አራማጅ ሆነው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ ቅዳሴ ለመማር ወደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሄደው ቅባትነታቸውን ደብቀው ሲማሩ ሳለ መምህራቸው አባ ገብረ ማርያም /የቦረዳ ዋሻ ታቦት ሲወጣ የተሸከሙት/ ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ገዳም ሲሄዱ አባ ቃለ ጽድቅም ተከትለው ሄደዋል፡፡ እስከዚህ ድረስ ማንነታቸው አልተገለጠም ነበር፡፡
በመሆኑም ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ገዳም ውስጥ ገብተው ሲቀድሱ ሲቆርቡና ሲያቆርቡ ቆይተው በቅርብ የሚያውቃቸው አንድ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ተማሪ በእርግጥ የቅባት እምነት ተከታይ እንደሆኑና የመነኮሱትና ያደጉትም በቅባት ገዳም እንደሆነ አስረግጦ ሲመሠክርባቸው አሁን ባሉበት ገዳም ጉባዔ ተሠርቶ ስለ ሃይማኖታቸው ሲጠየቁ ለጊዜው ቢክዱም ምርመራው ሲጠብቅባቸው አዎ የቅባት እምነት ተከታይ ነኝ የመነኮስሁትም በዚያው ገዳም ነው በማለታቸው ከነበሩበት ገዳም ለአንድ ዓመት ተባርረው ብዙ ካለቀሱ በኋላ ባይሆን ትምህርቴን ልጨርስ ብለው ስለተማጸኑ ተፈቅዶላቸው ትምህረታቸውን ጨርሰው ጎጃምን አያሳየኝ ብለው ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ተገደዋል፡፡” ይላል እነዲሁም የተባረሩበት ገዳም በደምበጫ ወረዳ የሚገኘው ደብረ ገነት መድኃኔአለም ገዳም እንደሆነ የተባረሩበት ዓመተ ምህረትም 1976 እንደሆነ መጽሐፉ በስፋት ያብራራል።
አባ አብርሃም የራሳቸውን የሃይማኖት ህጸጽ ሳያጠሩና ተወግዘውበት ከነበረው የቅባት ትምህርት ንስሀ ገብተው ሳይመለሱ አገር ይወገዝልኝ ካለው ማኅበረ ቅዱሳን ጋር አብረው ለውግዘት ወደፊት ማለታቸው አስገርሟል። ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ ሊቃውንት ጉባኤው የአባ አብርሃምን ሃይማኖት እንዲያጠራና ያወገዙዋቸውን አባት ፈልጎም ውግዘቱ እንዴት እነደተከናወነ ጠይቆ ንስሀ ከገቡ ንስሀ እንዲገቡ አሊያም እንዲወገዙ እንዲያደርግ እንጠቁማለን። መንግስትም የትምህርት ማስረጃቸውን አጣርቶ በአክሮባት ከ4 ወደ 12 የደረሱት በምን አይነት መለኪያ በጠጡት አብሾ እንደሆነ እንዲያጣራልን እንጠይቃለን።
ስለማኅበረ ቅዱሳንም መጽሀፉ
የቅባት ሃይማኖት አውጋዥ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳንም የቅባት እምነት ተከታይ የሆኑትን አባላቶቹን ጳጳሳቱን ቢያወግዝና ከእርሱ ፈቀቅ ቢያደርጋቸው ይበጀዋል ፡፡ የእርሱ አባላት ከሆኑ ሰይጣናትንም ሊቀበል ይችላል የተባለው ማኅበረ ቅዱሳን በብዙዎች ዘንድ እየተጠላ መምጣቱ ከዚህ የተነሣ ሳይሆን አይቀርም ፡፡ ይላል።
ይህ አባባል አውነትነት አለው እውነትን ሳይሆን ደጋፊነትን የሚያስቀድመው ማቅ በቅርቡ እንኳ እግዚአብሔር የለም ክርስትና እንጀራዬ ነው እንጂ ሌላ ምኔም አይደል እያለ የሚናገረውና እመቤታችን ስላሴን ወልዳለች ብሎ በአደባባይ መግለጫ የሰጠውን ዘሪሁን ሙላቱን በጋሻውን ስለሰደበ ብቻ እንደ እምነት አርበኛ ቆጥረውት እያንቆለጳጰሱት እንደሚገኝ ማንም አይክደው።  

6 comments:

  1. wow really amazing.....this reporter should be Addis Zemen Gazeta Reporter....because the news look like written by Beketu Semon

    ReplyDelete
  2. kkkkkkkkk you said approval ....Death for weyanes and Moron news reporter especially for this reporter and blog. You gus are really amazing please remove your hand from Religion ..shame on you!!

    ReplyDelete
  3. Manin Enimen AWde Mihiretin Or Deje Selamin
    1 Deje Selam -Ahat Tewahedo -Andi Adirgen -Gebir her Yetebalut bilodoch Andi Sew Silemiyazegajachew Mr Eniko bahiry Tenesu- Abba Hiruy Temelesu -Abba Sereke D Begashaw -Lelochim tewegezu Yilal
    2 Awde Mihiret -Abba Selama -Deje Birhan Yetebalut bilogoch Degimo Manim Altewegezem -Manim Altenesam Mr Enko bahiry Alu Abba Hiruy Tebareru Yilal
    Bemeseretu Abba Hiruy America Sandiyago St Gebreil Church Min Adirgew Endehedu -Debirun tseyiku Wendime Tamoal Motawl Bilew Atalewn Genzebachinin Yizew Hedu Alemaw Menkuse Neg Bay Addis Abeba yaskemetsuwat Wedagachew Yesebesebutinina besima Yegezutin Bet wesedechibachew Ahunim Zegibu

    ReplyDelete
  4. ለአባ አብርሃም
    ይህ የተጻፈብዎት እውነት ከሆነ ከሀረር በባዶ እግርዎ እንደምንሸንዎ ቃል እንገባልዎታለን።

    ReplyDelete
  5. Abatachen abune abreham edmewoten(yagelgelot zemenotnen) Egziabher yarzemelin. Amin

    ReplyDelete
  6. እኔ ማነኝ አምላክ ሲመርጠኝ ከከብትም የለየኝ ቀና ብዪ ላመሰግን ንስሐን እንዳስብ ነው ትንሳኤ ህይወት የሌለው ባለ አራት እንዳለው የዱር አራዊት ይመስል ያላወቅክውን መዘባረቅህ ያላወቅ ድፍን አላዋቂ ነህና እራስህን ጠብቅ ቤተክርስቲያን አንድ ነች አትገነጣጠልም ሲኖዶስ አይሰደድም ትዳሩን ያፈረሰ ካህን ወደ ልቡ ይመለስ በጥቅም የተሾሙ ቤተክርስቲያንን በአግባቡ ይጠብቁ
    ክኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ክህነት ያላቸውም ይሁን የሌላቸው በህገ ፈቃዳቸው ክሚኖሩ እግዚአብሔርን በመፍራት ብንኖር ሌላው ያንተም ታሪክ ይጻፋል ያልከው የኔንም እንዳትረሳ አደራ የኔ አውሪ

    ReplyDelete