Monday, November 12, 2012

የአክሱም ህዝብ እና ካህናት አጣሪ ኮሚቴውን አባረሩ

Read in PDF:Akesum
በጥቅምቱ የሲኖዶስ ስብሰባ አቡነ ሰላማ ለስራ ስለአልተመቹን ይነሱልን ሲሉ አቤቱታ ያቀረቡትን የአክሱም ምዕመናን እና ካህናትን አቤቱታ ቸል በማለት የአክሱምን ንቡረ ዕድ ከቦታቸው እንዲነሱ እና አጣሪ ኮሚቴ ወደ ስፍራው እንዲሄድ የተወሰነው ውሳኔ  ያሳዛናቸው የአክሱም ምዕመናን እና ካህናት በጉድ ሙዳዮቹ አለቃ በአቡነ አብርሃም የሚመራውን “አጣሪ ኮሚቴን” ምን ልታደርጉ መጣችሁ አባቶቻችን ስላልሆናችሁ አንፈልጋችሁም ሲሉ አባረሩ።
“ህዝብን ንቃችሁ የወሰናችሁት ውሳኔ አሳዝኖናል። አጣሪ ኮሚቴ ለመላክ መወሰናችሁ ስህተት ነው አንልም ነገር ግን ማጣራቱን ሳትጀምሩ ገና ኑብረዕዱን ከቦታቸው ማንሳታችሁ ግን ትልቅ ስህተት ነው። እንዲህ ያለውን ፍርደ ገምድል ውሳኔ ለመቀበል የሚፈቅድ ልብ የለንም።” በማለት አጣሪ ኮሚቴውን አቀርቅሮ እንዲመለስ አድርገውታል።


ህዘቡ እንቢ አላሰራ አለን በማለት ወደ ክልሉ መንግስት አቤት ያሉት እንደ ጉድ አያልቅበት አቡነ አብርሃም “ህዝብ ካልፈለጋችሁ እኛ ምንም ልናደርጋችሁ አንችልም” የሚል አንገት የሚያስደፋ ምላሽ አግኝተዋል።
መንፈስ ቅዱስን አማክሮ ውሳኔ ከመወሰን ይልቅ ወደ ማኅበረ ቅዱሳን ፊቱን አዙሮ መስገድ የጀመረው ሲኖዶስ እውነትን ሳይሆን የማኅበሩን ፍላጉት ብቻ ለማስፈጸም በሚተጉ ጳጳሳት አማካኝነት ማኅበረ ቅዱሳንን የማይቀሉ ሰዎችን ከቦታቸው እያነሳ ከትምህርቱም ከመንፈሳዊነቱም የሌሉበትን ጎጋዎች እየሾመ ቢሆንም የህዝቡን ልብ ግን ማሸነፍ አልቻለም። ስለዚህም ከቀውስ ለመውጫነት በማን አለብኝነት የሚወሰኑ ውሳኔዎች ሁሉ ቤተክርስታኒቱን ወደ በለጠ ቀውስ እየከተቱዋት ይገኛሉ። የአክሱሙ ኑብረዕድ ማኅበረ ቅዱሳን የተሰኘውን መፍቀሬ ሳጥናኤል አጥብቀው ከሚቃወሙ ወገኖች መካከል መሆናቸው ይታወቃል።

4 comments:

  1. we are so proud of you our fathers of Axum. we do know the Bishop of Axmum Aba Harigeweyn is a number one key suporter of MK the Enemy of Ethiopian Orthodox Tewahdo Church/ also he is not a spiritual father he is magician and he has the evil spirit like Aba Abrhan ze Gudmuday,

    ReplyDelete
  2. belivers of axum well done beacause Aba Abrham is the wiked man. I think is better to seprate from this mafyawoch

    ReplyDelete
  3. ወደ ማኅበረ ቅዱሳን ፊቱን አዙሮ መስገድ የጀመረው ሲኖዶስ እውነትን ሳይሆን የማኅበሩን ፍላጉት ብቻ ለማስፈጸም በሚተጉ ጳጳሳት አማካኝነት ማኅበረ ቅዱሳንን የማይቀሉ ሰዎችን ከቦታቸው እያነሳ ከትምህርቱም ከመንፈሳዊነቱም የሌሉበትን ጎጋዎች እየሾመ ቢሆንም የህዝቡን ልብ ግን ማሸነፍ አልቻለም

    ReplyDelete
  4. ይበላት እርሷም እንዲያው ናት!

    ReplyDelete