Sunday, November 18, 2012

አባ ሰረቀ ብርሃን እርቀ ሰላሙን አስመልከተው ለሲኖዶሱ ደብዳቤ ጻፉ

Read in PDF: Aba Serke
Read in PDF:Aba Sereke letter to sinodos


አባ ሰረቀ ብርሃን የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ይገባዋል ሲሉ ለሲኖዶሱ ደብዳቤ ጻፉ፡፡ አባ ሰረቀ ብርሃን በደብዳቤያቸው “ሁላችን እንደምንገነዘበው ዛሬ ቤተክርስቲያናችን በተለያዩ ኃይሎች በተከበበችበት ወቅት ከማንኛውም በፊት አንድነቷን በሚገባ ማጠናከርና ከሁሉ በፊትም በመካከልዋ የተከሰተውን መለያየት ማስወገድ ቅድሚያ ልትሰጠው ይገባታል።” በማለት በተለይ በዚህ ጊዜ እርቁ ከፍተኛ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
“በውስጥም ሆነ በውጭ ያለነው የቤተክርስቲያናቸን ባለድርሻ አካላት ሁላችን የየራሳችንን ክብርና ጥቅም በመተው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተክርስቲያን ለመጠበቅና የተሰጠንን አደራ እስከ መጨረሻ በብቃት ለመወጣት ከመቼም በበለጠ መልኩ በዚሁ ዙርያ ልዑል እግዚአብሐርን ደጅ በመጥናት ልንሠራ ይገባናል።” ሲሉ የገለጡት አባ ሰረቀ እርቁን ለማደናቀፍ እንደ እባብ ውስጥ ውስጡን እየተሸለኮለኩ ሴራ የሚሸርቡትን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እና መሰሎቻቸውን “ዕርቀ ሰላሙ እንዳይሳካ የሚጥሩና እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱንም ሊቃውንት በማሳደድ ላይ የሚገኙ አካላት ሁሉ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል፡፡” በማለት መክረዋል፡
ለበርካታ አመታት በሰንበት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ሆነው የሰሩት እና ቤተክርስቲናቸውንም አገራቸውንም በእጅጉ የሚወዱት አባ ሰረቀ ብርሃን የሰንበት ማደራጀውን እንቅስቃሴ በተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጎ የማይስማማው እና ሁሉን ንጄ እኔ እንደ አዲስ ልገንባው የሚለው ማኅበረ ቅዱሳን በመንገዳቸው ላይ እንደ ዐለት ተደንቅሮ የተለያየ ሰንካላ ምክንያት በመደርደር አላሰራ ይላቸው እንደ ነበር ይታወቃል፡፡ 


ይህ ማኅበር አባ ሰረቀን ይቃወም የነበረው በሰንበት ማደራጃ ባላቸው እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን የሁለቱ ሲኖዶሶችን እርቅ አስመልክቶ በነበራቸውም አቋምም ነው፡፡ አባ ሰረቀ ብርሃን ከሁለቱ ሲኖዶሶች መከፋፈል ጀምሮ እርቅ ለቤተክርስቲያኒቱ ህልውና አስፈላጊ መሆኑን አበክረው ያምኑ እንደነበር በ1992 ዓ.ም. ለቅዱስነታቸው የጻፉት ደብዳቤ ያስረዳል፡፡
ከሳሹ ማህበር ማኅበረ ቅዱሳን ግን እርቁን የማይፈልገው መሆኑን እና የአሜሪካውን ሲኖዶስ “…በውጭ ራሱን ሲኖዶስ ነኝ ብሎ የሚጠራውን ቡድን የቤተክርስቲያን ሕጓንና ሥርዓቷን ውሳኔውን በመተላለፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ማውገዙ ይታወቃል።…” ብሎ መስደቡ ይታወቃል፡፡ አሁን ታድያ የህዝቡ ሁሉ ልብ ወደ እርቁ መሆኑን የተረዱት የማቅ አመራሮች ልባቸው እርቁን ባይፈልገውም ከዲስፖራውየሚፈልጉት ጥቅም እንዳይቀርባቸው ሲሉ ግን በአደባባይ ስለእርቅ እያወሩ በድብቅ ግን እርቁን የሚያደናቅፍ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
አባ ሰረቀ ብርሃን ታሪክ አጣቅሰው እና መረጃ ጠቅሰው ይህንን ለሲኖዶሱ ያሳወቁ ሲሆን የሲኖዶሱ አባላት የሆኑት ሊቃነ ጳጳሳትም ይህንን የማኅበሩን ተንኮል ተረድተው ለእርቅ የሚደረገውን ጥረት በሙሉ ልባቸው ያግዛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአባ ሰረቀ ብርሃንን ደብዳቤን ሙሉ ቃል ከዚህ ቀጥሎ አቅርበነዋል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ጥቅምት 28 ቀን 2005 /

ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
ብፁዓን ገባርያነ ሰላም

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል አቃቤ መንበርና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
ከሁሉ አስቀድሜ ይህን አጭር ማስታወሻ እንድጽፍ ያነሳሳኝን ልዑል እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። በመቀጥልም ይሀ አጭር ማስታወሻ ሳቀርብ የተሰማኝንና የሚሰማኝን እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነቴ ለመግለጽ ብቻ እንጂ ከአባቶች የበለጠ ሐሳብና ዕውቀት ኑሮኝ እንዳይደለ ብፁዓን አባቶቼና ይህን የምታነቡ ሁሉ እንድትገነዘቡልኝ ከወዲሁ በትህትና ላሳስብ እወዳለሁ።
ብፁዕ አባታችን! ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
ምንም እንኳ በሕክምና ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ባልገኝም ባለሁበት ክፍለ ዓለም ሆኜ እንደተከታተልኩት በ2005 /31ኛ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባና በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተላለፈው ውሳኔ ለብዙ ዓመታት የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንትና ባለድርሻ አካላት ሲመኙት የነበረና በተለያየ ጊዜያት በጥናት መልኩ ለቅዱስ ሲኖዶስ ሲያቀርቡት የነበረ በመሆኑ በእጅጉ የሚያስመሰግንና ተፈጻሚነት ካገኘም ለቤተክርስቲያናችን ሁለንተናዊ እድገት የሚበጅ እንደሆነ አያጠራጥርም።  
ይሁን እንጂ እንደ እኔ እምነት ቅዱስ ሲኖዶሳችን ያስተላለፋቸው ውሳኔዎችና የተያዙት ዕቅዶች ሁሉ ስኬታማ ሊሆኑ የሚችሉት የቤተክርስቲያናችን አንድነትና ሰላም አስተማማኝ ሲሆን ብቻ ነው።
ሁላችን እንደምንገነዘበው ዛሬ ቤተክርስቲያናችን በተለያዩ ኃይሎች በተከበበችበት ወቅት ከማንኛውም በፊት አንድነቷን በሚገባ ማጠናከርና ከሁሉ በፊትም በመካከልዋ የተከሰተውን መለያየት ማስወገድ ቅድሚያ ልትሰጠው ይገባታል።
ብፁዕ አባታችን! ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
ቀድም ሲል በርካታ የቤተክርስቲያንዋ ልጆች በእናት ቤተክርስቲያናችን የተከሠተውን መለያየት በዕርቀ ሰላም መፈታት አለበት በማለት ከፍተኛ ጥረትእያደረጉ እንደቆዩ ቢታወቅም፡ በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣልእንደተባለው የቤተክርስቲያኒቱን መለያየት እንደታላቅ እድል በመቁጠር በቤተክርስቲያኒቱ ታዛ ሥር ተደብቀውና እንደመዥገር የቤተክርስቲያኒቱን ሃብት ያለ ገደብ ለግል ዓላማቸው እየተጠቀሙ የሚገኙ ኃይሎች የቤተክርስቲያናችን ሰላምና እንድነት መጠበቅ አለበት የሚሉትን የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ያለ ስማቸው ስምን በመለጠፍ እንደቆዩና አሁንም እንዳሉ የአደባባይ ምሥጢር ነው።
ለምሣሌ ያህል፤-24/6/ 92 /ም ለቅዱስ ሲኖዶስና ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ፡ በቤተክርስቲያናችን የተከሰተው የእርስ በእርስ መለያየት በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደፈጠረና ቅዱስ ሲኖዶስ በውጭ ከሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ገለልተኛ ነን ከሚሉት ጋር የሰላም ጉባኤ ማድርግ ያለበት ይመስልኛል በሚል ባቀረብኩት የማሳሰቢያ ጽሑፍ፡ 
የ1992 ዓ.ምቱን ደብዳቤ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ 
በተጨማሪም ቤተክርስቲያናችን የእስራ ምዕት በዓል ለማክበር በምትዘጋጅበት ወቅት ማለትም በ1999 /ም መለያየቱ እጅግ እየሰፋ ሲመጣና በውጭ የሚገኙት አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት፡ ኤጲስቆጶሳትን በመሾማቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ብፁዓን አባቶችን ለስብሰባ ሲጠራ፤-
ጥር 24 ቀን 1999 /ወይኩን ኩሉ ብእሲ ፍጡነ ለሰሚዕ ወጕንዱየ ለነቢብ፤ ወጕንዱየ ለመዓትበሚል ርእስ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያደርገው ስብሰባ ከሁሉ በፊት ለሰላም ቅድሚያ ቢሰጥ፡ መወጋገዝ ፈጽሞ መፍትሔ እንደማይሆን፡ መወጋገዝ በግራና በቀኝ ያለው ሕዝባችን አሳልፎ ለጠላት ስለሚሰጥ ቅድሚያ ለሰላም ቢሰጥ፤ ሰላም የማይመጣ ከሆነም ቅድሚያ የቤተክርስቲያኒቱ ባለድርሻ አካላት እንዲወያዩበት ቢደረግ መልካም ይመስለኛል በማለት እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነቴ ለቅዱስ ሲኖዶስና ለቅዱስ ፓትርያርኩ በማቅረቤ የማሕበረ ቅዱሳን የአመራር አካላት በሐሰት ለቅዱስ ሲኖዶስ ካቀረቡብኝ ወንጀሎች አንዱ እንደሆነ ብፁዓን አባቶች የምታስታውሱት ሐቅ ነው።
የዚህ አጠቃላይ መረጃም ቅዱስ ሊኖዶስ በጊዜው ለቋቋመው ኮሚቴ መቅረቡና ብሎም እውነትና ንጋትበተሰኘው መጽሐፌ ሙሉ መረጃው ማቅረቤ ይታወቃል። በመጽሐፉ በገጽ 83-87 በገጽ 192-193 በገጽ 210-211 እና በገጽ212-219 በከፊል የተጠቀሰው በግልጽ ያሳያል። በተለይ በማኀበሩ ጸሐፊዎች ሙሉጌታ ኃይለማርያም እና ዳንኤል ተስፋዬ ተፈርሞ ከቀረቡ የሐሰት ውንጀላዎች መካከል አባ ሠረቀ የማሕበሩን አገልግሎት በዓላማ ለማደናቀፍ መነሳታቸው ለዚህ ማኅበር ህልውና የሰጠውን ቅዱስ ሲኖዶስ መቃወማቸው መሆኑን ግልጽ ነው። በተለያዩ ጊዜያት ጥናታዊ ጽሑፍ ብለው በሚያቀርቧቸው ጽሑፎች ላይ ቤተክርስቲያኒቱን በበላይነት የሚመራውን ቅዱስ ሲኖዶስ ይነቅፋሉ።
ለምሳሌ፦ በውጭ ራሱን ሲኖዶስ ነኝ ብሎ የሚጠራውን ቡድን የቤተክርስቲያን ሕጓንና ሥርዓቷን ውሳኔውን በመተላለፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ማውገዙ ይታወቃል። ይህንን ውሴኔ በመተቸትይጽፋሉ። ይህ ደግሞ በቤተክርስቲያኒቷ አመራር ላይ ያላቸውን ንቀት ያሳያአል።በማለት በቊጥር ማቀሥአ13748/02/01 በቀን 15/10/01 /ም እርቀ ሰላም ያስፈልጋል ብየ ለቅዱስ ሲኖዶስ የጻፍሁትን ደብዳቤ ወንጅለው አቅርበውታል። 
 https://docs.google.com/open?id=0B7ITjesPu4tJaHJSY1RGWnpPNWM
ይሁን እና ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔርእንዳለው እኔና ሌሎች የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ሲመኙት የነበረውን የእርቀ ሰላም ጉዳይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ በሕይወተ ሥጋ እያሉ በቅዱስ ሲኖዶሳችን ተቀባይነት አግኝቶ በተደጋጋሚ በውጭ ከሚገኙ ቅዱስ ፓትርያርክና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሰላም ውይይት እያደረገ እንደቆየና አሁንም እንዳለ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ ይህ የሰላሙ ጉዳይ ትናንትና ሲያጨናግፉት የነበሩት ወገኖች በተለይ በዚህ ምክንያት ይከሱና ያሳጡ የነበሩት አካላት አሁን ደግሞ ስለ ዕርቀ ሰላም አስፈላጊነት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኀን ገለጻ እያደረጉ ይገኛሉ። ሐሳቡ እጅግ የሚያስደስት ቢሆንም እነዚህ አካላት ዕርቀ ሰላሙ እንዳይፈፀም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እያጨናገፉት እንደሚገኙ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። በተለይ የሰላም ወዳዱ ሕዝበ ክርስቲያን እዕምሮ ለመቀልበስ ዕርቀ ሰላሙ በመንግሥት በኩል ተቀባይነት የለውም በማለት ተጨባጭነት የሌለው ወሬ እያናፈሱ እንዲሚገኙ እማኞች ያስረዳሉ። ምክንያታቸው ደግሞ እንደለመዱት ሃይማኖትና ፓለቲካ እያጣቀሱ መኖር የሚፈልጉና በዘመኑ ቋንቋ ኪራይ ለመሰብሰብም እንዲመቻቸው ለማድረግ እንደ ሆነ አያጠራጥርም።  
በመሆኑ አሁንም እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነቴና አገልጋይነቴ በታላቅ ትህትና እማሳስበው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት የጀመራችሁትን የዕርቀሰላሙ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ቢሰጠውና ከማነኛውም ፊት ዕርቀ ሰላሙ ቢቀድም፡፡ የዕርቁ አፈጻጻምና ይዘት በተመለከተ ግን በብፁዓን አባቶች የሚታይ ሆኖ በሰላሙ ጉዳይ ግን የቤተክርስቲያኒቱ ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉበት ቢድረግ የተሻለ ይመስለኛል።
ይሀ ሳይሆን ቀርቶ መለያየቱ ከቀጠለ ግን ቤተክርስቲያናችንና ሕዝበ ክርስቲያኑ ለከፋ አደጋ ሊጋለጥ እንደሚችል መተንበይ የሚያሻው አይመስለኝም።
ስለዚህ በውስጥም ሆነ በውጭ ያለነው የቤተክርስቲያናቸን ባለድርሻ አካላት ሁላችን የየራሳችንን ክብርና ጥቅም በመተው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተክርስቲያን ለመጠበቅና የተሰጠንን አደራ እስከ መጨረሻ በብቃት ለመወጣት ከመቼም በበለጠ መልኩ በዚሁ ዙርያ ልዑል እግዚአብሐርን ደጅ በመጥናት ልንሠራ ይገባናል። ዕርቀ ሰላሙ እንዳይሳካ የሚጥሩና እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱንም ሊቃውንት በማሳደድ ላይ የሚገኙ አካላት ሁሉ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል እያልኩኝ ሐሳቤን ሳቀርብ በታላቅ መንፈሳዊ ትህትና ነው።
ቡራኬያችሁና ጸሎታችሁ አይለየኝ
ግልባጭ
v ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
v ለመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ቤተክህነት ጽ/ቤት
v ለሰሜን አሜሪካ አኅጉረ ስብከት ጽ/ቤት
v ለሚመለከታቸው የቤተክርስቲያናችን ባለድርሻ አካላት

4 comments:

  1. ...ዕርቀ ሰላሙ እንዳይሳካ የሚጥሩና እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱንም ሊቃውንት በማሳደድ ላይ የሚገኙ አካላት ሁሉ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል እያልኩኝ ሐሳቤን ሳቀርብ በታላቅ መንፈሳዊ ትህትና ነው።

    ReplyDelete
  2. መለያየት በዕርቀ ሰላም መፈታት አለበትNovember 18, 2012 at 4:21 PM

    የቤተክርስቲያናችን ባለድርሻ አካላት ቆራጥና ደፋር የውስጥ ትግል ያስፈልገዋል::

    ቀድም ሲል በርካታ የቤተክርስቲያንዋ ልጆች በእናት ቤተክርስቲያናችን የተከሠተውን መለያየት በዕርቀ ሰላም መፈታት አለበት በማለት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደቆዩ ቢታወቅም፡ “ በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል” እንደተባለው የቤተክርስቲያኒቱን መለያየት እንደታላቅ እድል በመቁጠር በቤተክርስቲያኒቱ ታዛ ሥር ተደብቀውና እንደመዥገር የቤተክርስቲያኒቱን ሃብት ያለ ገደብ ለግል ዓላማቸው እየተጠቀሙ የሚገኙ ኃይሎች የቤተክርስቲያናችን ሰላምና እንድነት መጠበቅ አለበት የሚሉትን የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ያለ ስማቸው ስምን በመለጠፍ እንደቆዩና አሁንም እንዳሉ የአደባባይ ምሥጢር ነው።

    ReplyDelete
  3. “ሁላችን እንደምንገነዘበው ዛሬ ቤተክርስቲያናችን በተለያዩ ኃይሎች በተከበበችበት ወቅት ከማንኛውም በፊት አንድነቷን በሚገባ ማጠናከርና ከሁሉ በፊትም በመካከልዋ የተከሰተውን መለያየት ማስወገድ ቅድሚያ ልትሰጠው ይገባታል።”

    ReplyDelete
  4. ስለ ስዎች ሳይሆን ስለ እግዚአብሔር ሰይጣንንና ሰራዊቱን ሐሳቡንና እቅዱን ለማፍረስ የድንግል ልጅ በቀራንዮ የከፈለው ዘግናኝ መከራ ህዝቡን ከሞት ለመታደግ « ገብረ ሠላመ በመስቀሉ » በሞቱ በስቃዩ ሠላም ን በምድር ተክሎልናል ። ስለተተከለውም ሠላም መላዕክት ከሰማይ ወርደው ከሰው ልጆች ጋር በቤተልሔም ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ብለው ደስታቸውን ገልጠዋል ። ለዚህ ሠላም መደፍረስ ምክንያቱ የክርስቶስ መስቀልና ወንጌል በእጃቸው የተሰጣቸ ዋኖች ሲሆኑ ሐዘኑ በሰማይ በመላእክቱ በምድርም በቤተ ክርስትያን ላይ ይሆናል ። ይህ ደግሞ የክርስቶስን ደም መርገጥ ነው ። ስለዚህ በጎቼን ጠብቁ ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስትያን ተጠንቀቁ የተባላችሁ አባቶች ዘርን ፤ ጎሳን ፤ የግለሰቦችን አስተሳሰብ ጥላችሁ ፡ ለሠላሙ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ ሳታቀርቡ ስለእግዚአብሔር ታረቁ እንላለን ። አለበለዚያ በየዘመኑ ታሪክ የሚሰራው የቤተ ክርስትያን አምላክ ህዝቡን እንደማይጥልና ስለ ታላቅ ስሙ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ተአምር ሰርቶ ለሕዝቡ የሚበጀውን እንደሚያመጣ አምናለሁ ። የዚያን ግዜ ይህ ቃል በሐይል ይሰማል ,....ቅድስና የሌላቸው ፍቅር የሌላቸው እርቅን የማይሰሙ ...ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ '' 1 ጢሞ 3፤3 ተብሎ በታሪካቸው ላይ ይቀመጣል መቅረዛቸውም ከፊታቸው ይወሰዳል ''''''ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላሶን /ብዋሽንግተን ዲሲ ከሚኖሩ ልቡ ያዘነበት አገልጋይ ነኝ /

    ReplyDelete