Wednesday, November 14, 2012

በአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት የ"ማኅበረ ቅዱሳን"ና የአባ ናትናኤል ፍጥጫበአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት የ"ማኅበረ ቅዱሳን"ና የአባ ናትናኤል ፍጥጫ



ምንጭ፡- http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com
·        ከአዲስ አበባ እስከ ሀዋሳ የተዘረጋው የሙስናና የአፈና መረብ ዓይነተኛ የ"ማቅ" አደገኛ ባህርይ ማሳያ ነው

·        ከ"ማኅበረ ቅዱሳን" ጋር የሚደረገውን ትግል የአየር ጤና ሕዝብ ተረክቦታል

በምደባም ይሁን በዝውውር ወደ አዲስ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለሚመጡ እንደ መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ናትናኤል መላኩ ላሉ አስተዳዳሪዎች የሚያጋጥማቸው አማራጭ ሁለት ነው፡፡ አንደኛው አማራጭ በሙስና በተጨማለቀ ብልሹ አስተዳደር ውስጥ ገብቶ በመጠቃቀም ፖሊሲ ከ"ማኅበረ ቅዱሳን" ጋር በሠላም መኖር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ቃለ ዐዋዲው በሚያዘው መሠረት ለእግዚአብሔርና ለቤተክርስቲያን በቅንነት አገልግሎ ከማቅ የሚመጣውን ጠብ በፀጋ መቀበል፡፡

አባ ናትናኤል ወደ አዲስ አበባ አየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተዛውረው ሲመጡም የተቀበሉት አማራጭ ሁለተኛውን ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ አባ ናትናኤል እግራቸው አየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢን ከረገጠበት ዕለትና ሰዓት አንስቶ "ማኅበረ ቅዱሳን" እርሳቸውን ለማስነሳት ያልበጠሰው ቅጠል፣ ያልማሰው ሥር፣ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም፡፡


አባ ናትናኤል ይህ ሙስና የሚባል ነገር ቆሻሻ ቆሻሻ ሥራን የሚጠየፉ በመሆናቸው በቃለ ዐዋዲው መሠረት አሠራሮችን አስተካክላለሁ ባሉ ቁጥር የ"ማቅ" መንጋ እየተነሳ ደብሩን ይንጥ ጀመር፡፡ አልፎ ተርፎም ያለ ስማቸው ስም፣ ያለ ግብራቸው ግብር እየሰጠ በየብሎጉ ይሰድባቸው ገባ፡፡ ጠብደል ጠብደል የሰንበት ት/ቤት አባላት ነን ባዮችን እያሰለፈባቸው ሁለት የማይተዋወቁ አባትና ልጆችን አናቆረ፡፡ በዚህ ውጊያ ማቅ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን በመቀሰቀስ ስለማንታቸው የማያውቋቸውን አባ ናትናኤልን አንፈልግዎትም እያሰኘባቸው ውጥረቱ ቢባባስ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት አጥኚ ቡድን ልኮ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ጳጉሜ 2 ቀን 2004 ዓ.ም በቁጥር 4801/265/04 በተጻፈ ደብዳቤ ባለ አራት ነጥብ ውሳኔዎችን አስተላለፈ እነዚህም:-

1.  ከ3 ዓመት በላይ የቆየውን ሰበካ ጉባዔ መስፈርቱን በሚያሟሉ አዲስ ምዕመናን እንዲተካ፣
2.  ዘመን ያስቆጠረው ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ግንባታውን እስከ ጥር 15 ቀን 2005 ዓ.ም ባለው ጊዜ አጠናቆ እንዲያስረክብ፣ ጨረታዎችንና ውሎችን ያለሰበካ ጉባዔው እና ያለ አስተዳዳሪው ዕውቅናና ያለ ሀገረ ስብከቱ ይሁንታ እንዳይፈጽም፣
3.  የደብሩ ሰንበት ት/ቤት መብትና ግዴታውን ለይቶ እንዲያውቅ፣ ተጠሪነቱ ለማን እንደሆነ ተረድቶ በሥርዓት እንዲሠራና እስከ ዕለቱም ድረስ ለፈጸመው ስህተት ምክርና ተግሳፅ እንዲሰጠው፣
4.  የደብሩ አስተዳዳሪ መ/ ገነት አባ ናትናኤል በአባትነት ሁሉን ችለው፣ ሕግና መመሪያው በሚፈቅደው መሠረት በሠላምና በፍቅር ደብሩን እንዲመሩ የሚሉ ናቸው፡፡  

ይሁን እንጂ ሕግና መመሪያን በመጣስ የሚታወቀው "ማቅ" ቋያውን በማቀጣጠል ቀጠለበት እንጂ ለአፍታም ቸል አላለም፡፡ ግን ለምን? "ማቅ" አባ ናትናኤልን ሆነ ብሎ የጠመዳቸው በምን ምክንያት ነው? መልሱን እነሆ:-


መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ናትናኤል መላኩ ወደ ደብሩ ሲመጡ ሁሉ ነገር ተዝረክርኳል፡፡ ሰበካ ጉባዔው ቃለ ዐዋዲው ከሚያዘው ሦስት ዓመት በላይ ዝጓል፡፡ አዲስ በመሠራት ላይ ያለው ሕንፃ ቤተክርስቲያን ድፍን አሥራ አራት ዓመታትን አስቆጥሮ ለመጠናቀቅ የቀረው ብዙ ነው፡፡ ምዕመናን ገንዘብ እያሰባሰቡ ቢሰጡም ብሩ ያልቃል እንጂ ግንባታው ፈቀቅ አላለም፡፡ በዚያ ላይ የሕንፃ አሠሪው ኮሚቴ ከዚሁ ግንባታ ጋር አርጅቶ በአዲስ ኮሚቴ እንተካህ ቢሉትም ወይ ፍንክች እያለ አስተዳዳሪዎችን በሆነ ባልሆነው እየወነጀሉ ከማባረር እና ልማቱ ባለበት ዳዴ ከማለት ውጪ ለውጥ አልታየም፡፡


አጥቢያ ቤተክርስቲያኗ ለክሊኒክ መሥሪያ ቦታ ቢሰጣትም፣ ግንባታው ከመሠረት ቁፋሮና ኮለም ማውጣት ሥራ ውጪ ካለመካሄዱም በላይ ሁሉ ነገር ቀዝቅዞ በቀሪው ይዞታ ላይ ማታ ማታ መኪናዎችን ለማሳደር የ3 ሺህ ብር ወርሃዊ ገቢ ብቻ እየተመዘገበ መኖር ግዴታ ሆኖ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አባ ናትናኤል ይህ ትክክል ሆኖ ስላላገኙት ቦታውን በግልፅ ጨረታ የተሻለ ዋጋ ላቀረበ የብሎኬት ማምረቻ ድርጅት እንዲከራይ በማድረጋቸው (አንድ አድርገን ብሎግ "ለክሊኒክ መገንቢያ በሊዝ የተገኘን  የደብሩን ይዞታ ለቱርኮች ያለሰበካ ጉባዔው ዕውቅና  የኪራይ ውሉ ምን እንደሚል እስካሁን ማወቅ አልተቻለም"፡፡ ብሎ እንዳወራው ሳይሆን፣ ቁልጭ ያለ ውል በሀገረ ስብከቱ፣ በወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤቱና በሰበካ ጉባዔው ጽ/ቤት ይገኛል) 29 ሺህ ብር ተጨማሪ ወርሃዊ ገቢ በማስገኘት የየወሩ ገቢ ወደ 32 ሺህ ብር ከፍ አለ፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" ያለጠያቂ የሚያዝበትን ይህንን ስፍራ በግልፅ ለቤተክርስቲያኗ በማዋላቸው ጥርስ ነከሰባቸው፡፡ በቤተክርስቲያኗ ዙሪያ ያሉትንም ወደ ሰባት ደጃፍ የሚጠጉ ሱቆችን የተሻለ ዋጋ ላቀረቡ ሰዎች በመከራየቱ በአንድ ሱቅ ከ300 ብር እስከ ስድስት መቶ ብር ብቻ ይገኝ የነበረውን ወርሃዊ ገቢ ከብር ስድስት መቶ እስከ ሁለት ሺህ ብር እንዲከራይ በማድረጋቸው አሁንም ይህ ድርጊት "ማቅ"ን ይበልጥ አስቆጣ፡፡


አባ ናትናኤል አዲስ በመገንባት ላይ ያለውን ሕንፃ ቤተክርስቲያንን ጎብኝተው ካበቁ በኋላ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴውን "ለመሆኑ አሁን ምንድነው የሚያስፈልጋችሁ"? ብለው ቢያነጋግሯቸው "ለኮርኒስ ሥራ ማሰጨረሻ 350 ሺህ ብር ያስፈልገናል" ብለው መለሱላቸው፡፡ እርሳቸውም ይህንኑ የቤት ሥራ በኃላፊነት ወስደው ባለፈው ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ለቅድስት ኪዳነ ምሕረት በዓለ ንግሥ ሕዝብን አስተባብረው 350 ሺውን በእጃቸው አደረጉላቸው፡፡


የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው አባላት በመቀጠል አባን ሳያማክሩ፣ ሰበካ ጉባዔ ሳያውቀው ከአንድ ሠዓሊ ጋር በመነጋገር ለውስጥ ሥዕል ማሠሪያ በ2 ሚሊዮን ብር ተስማምተው የ2.7 ሚሊዮን ብር ውል ስምምነት ይዘው በመቅረብ ይጽደቅልን የሚል ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አባ ናትናኤልም ጥያቄው ሥነ ሥርዓትን ያልተከተለ ከመሆኑም በላይ ከዋናው የማሠሪያ ዋጋ በተጨማሪ የቀረበችው ሰባት መቶ ሺህ ብር አድራሻዋ ምን ሊሆን እንደሚችል ቀድሞ መረጃ ደርሷቸው ስለነበረ ውሉን አገዱት፡፡


በዚህ ሁኔታ የተበሳጩት የ"ማቅ" ሠራዊት አባላት ሤራ ማውጠንጠን ይጀምራሉ፡፡ ያለፈ ታሪካቸውን ለምን ቆፍረን አናወጣም ብለው ቢፍጨረጨሩም ሊሳካላቸው አልቻለም፡፡ መጨረሻ ላይ ግን አንድ ዘዴ ተፈጠረና ይኸው አማራጭ የተሻለ ሆኖ ተገኘ፤ ሥራም ላይ ዋለ፡፡

አንድ ቡድን ወደ ሀዋሳ ተልኮ የምሽት ዳንስ ቤት ባለቤት የሚገኝበት ጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ ነጋዴዎችን ያገኝና ከማቅ የሀዋሳ ማዕከል አባላት ጋር በመቀናጀት በሀዋሳ ኃይሌ ሪዞርት በተካሄደው የጋራ ውይይት ስምምነት ይደረሳል፡፡ በስምምነቱም መሠረት የአየር ጤናው ቡድን ሙሉ የነዳጅና የአበል ወጪውን ሸፍኖ አባ ናትናኤልን ለአፈና እንደሚያመቻች፣ የሀዋሳዎቹም የሐሰት ክስ በመመሥረት አባ ናትናኤል በተገኙበት እጃቸው ተይዞ ወደ ሀዋሳ እንዲላኩና እሥር ቤት ተቆልፎባቸው እንዲረሱ የሚያደርግ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲዘጋጅ በወጠነው መሠረት ይኸው ሁሉ ተፈጸመ፡፡ የአፈናውን ሂደትና ፍጻሜ (Friday, October 26, 2012 አባ ናትናኤል በ“ማኅበረ ቅዱሳን”ና በጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ  ነጋዴዎች ቅንብር ታግተው ወደ ሀዋሳ ተወሰዱ) በሚል ርዕስ ያወጣነውን ዘገባ ይመልከቱ፡፡

ሆኖም፣ የሀዋሳውና የአዲስ አበባው የተንኮል መረብ የተፈለገውን ዓሣ መያዝ ሳይችል በሕዝብና በመንግሥት የተቀናጀ ጥረት ሊከሽፍ ችሏል፡፡ ይሁን እንጂ፣ የአፈና ቡድኑ በያዘው ድርጊት በመቀጠል ውስጥ ውስጡን በመዘጋጀት የራሱን ቀን መጠበቅ ያዘ፡፡ አባ ናትናኤል በግል ችግር ምክንያት አንድ ሁለት ቀን ቢሮ ሳይገኙ ይቀራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የአዲስ አበባው ቡድን የሀዋሳው ጉዶች እንደገና መጥተው የወሰዷቸው መስሎት አንድ አድርገን በተባለው የ"ማቅ" ብሎግ ( Wednesday, October 31, 2012 አባ ናትናኤል ዳግም በፖሊስ ተይዘው ዘብጥያ ወረዱ) በሚል ርዕስ ወሬውን ለቀቀው፡፡ እኛም (ይድረስ ለ"አንዳድርገን" ብሎግ ይህንን ውሸትህን ተወኝ ብዬሃለሁ) በሚል ርዕስ ዜናው ፍጹም ተጨባጭነት የሌለው ከንቱ ወሬ መሆኑን ለአንባብያን ማስረዳታችን አይዘነጋም፡፡


በወረዳ አምስት የአንድ ቀበሌ ሥራ አስፈጻሚ አባልና ቃለ ዐዋዲው የሰንበት ት/ቤት አባል ሆኖ ለመቆየት ከሚያዘው 30 ዓመት ዕድሜ በላይ ያስቆጠረው የአየር ጤና ሰንበት ት/ቤት ሰብሳቢ የሆነውና ኢዩኤል የተባለው የልጆች አባት ጎልማሳ ሰው በሥራው አጋጣሚ ተጠቅሞ አባ ናትናኤል ያልተገባ መብት የጠየቁ በማስመሰል "በቤተክርስቲያክኗ ስም የአዲስ አበባ መታወቂያ እንዲሰጣቸው የወረዳውን አስተዳደር መጠየቃቸው ምዕመኑን ግራ አጋብቷል" የሚል የተዛባ ዜና በአንድ አድርገን ብሎግ እንዲሠራጭ፣ የ"ሁለት በላ" ሚናውን ተጫውቷል፡፡ ይሁን እንጂ "ማኅበረ ቅዱሳን" አባላት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መዋቅር ውስጥም ተሰግስገው የሚገኙና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ማኅበራቸውን ከመጥቀም ወደ ኋላ እንደማይሉ የአቶ ኢዩኤል ድርጊት አንዱ ማሳያ ነው፡፡


ይህ በእንዲህ እንዳለ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ተላላኪ የሆነውና ራሱን ኢንጂነር እያለ የሚጠራው የቴክኒክና ሙያ ተመራቂው ግሩም ደብሩ የተባለው የሕንፃ አሠሪው ምክትል ሰብሳቢ አጋጣሚውን በመጠቀም ወ/ሮ ማርታ ከበደ ከሚባሉ አንዲት ግለሰብ ለኮርኒስ ማሠሪያ 100 ሺህ ብር እንዲያበድሩት ጥቅምት 21 ቀን 2005 ዓ.ም በቁጥር ህ.አ.ዐ.ኮ/008/05 በተጻፈ ደብዳቤ ይጠይቃል፡፡ በርግጥ ወ/ሮ ማርታ የሚባሉ ሰው በእውነት ስለመኖር አለመኖራቸው ማረጋገጥ አንደ ነገር ሆኖ፣ አንድ ተራ ኮሚቴ ቤተክርስቲያንን ወክሎ ከግለሰብ የሚበደርበት አንዳች ምክንያት የለም፡፡ በተጨማሪም አባ ናትናኤል እሥር ቤት ተጥለው የተረሱና ዳግም ወደ ሥራ ገበታቸው የማይመለሱ መስሎት አዲስ አስተዳዳሪ ተሳስቶ እንዲፈርምላቸው ለኮርኒስ ማሠሪያ ብር 498ሺህ487 ብር እንደሚያስፈልገው ጠቅሶ የብር 200 ሺህ ድጎማ እንዲሰጠው ጥቅምት 21 ቀን 2005 ዓ.ም በቁጥር ህ.አ.ዐ.ኮ/009/05 የተጻፈ ደብዳቤ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ መጠባበቅ ጀመረ፡፡


አባ ናትናኤልም የግል ጉዳያቸውን ፈጽመው ወደ ቢሯቸው ሲመለሱ ያልጠበቁትን ማመልከቻ ያገኙታል፡፡ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴውን ጠርተው በማነጋገር፣ "ከዚህ በፊት 350 ሺህ ብር ነው የቀረን ብላችሁ ከምዕመናን ለምኜ ሰጥቻችሁ አልነበረም እንዴ? ይኸ ደግሞ የምን ጥያቄ ነው? ደግሞስ ከግለሰብ 100 ሺህ ብር ብድር እንድትጠይቁ ሥልጣኑን የሰጣችሁ ማን ነው? ሰበካ ጉባዔ የማያውቀውን እንቅስቃሴስ ለምንድነው የምታደርጉት? የኮርኒስ ሥራ ጥያቄ እንደ አዲስ የምታቀርቡ ከሆነም ከዚህ በፊት የወሰዳችሁትን 350 ሺህ ብር አፈጻጸም ሪፖርት አቅርቡ ወይም ወደ ካዝና መልሱ በሕዝብና በቤተክርስቲያን ገንዘብ ለምን ትቀልዳላችሁ"? ብለው በምሬት ጠየቋቸው፡፡

የጉዳዩን ቁልፍልፍነት የሚያሳየው፣ ወ/ሮ ማርታ ከበደ ብድር የተጠየቁበት ቀን ጥቅምት 21/ 2005፣ አዲስ አስተዳዳሪ ይመጣል ብለው የገንዘብ ጥያቄ ያቀረቡበት ቀን ጥቅምት 21/ 2005፣ "አባ ናትናኤል ዳግም በፖሊስ ተይዘው ዘብጥያ ወረዱ" የሚል ዘገባ በአንድ አድርገን ብሎግ ያሠራጩበት ቀን ጥቅምት 21/ 2005 መሆኑ ነው፡፡

ትላንት አባ ናትናኤል ስለቤተክርስቲያኗ መብት ለብቻቸው ሲከራከሩ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ሕዝቡ ሁሉንም ለይቶ ስላወቀ በተለይም የእነ ግሩም ደብሩንና የአቶ ኢዩኤልን ሤራ ጠንቅቆ በመረዳቱ መብቱን ለማስከበር ጥቅምት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ባሳየው አቋም አሳይቷል፡፡ የአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ምዕመናን "ማኅበረ ቅዱሳን"ን ፊት ለፊት ተጋፍጠው የቤተክርስቲያናቸውን ኅልውና በመጠበቅ ላይ ናቸው፡፡

አባ ናትናኤልን አንዳንድ ጊዜ ስናስባቸው እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ዝርክርክ ሥራዎችን እንዲያስተካክሉ በየአጥቢያው የሚላኩ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ሳይሆኑ አይቀሩም እንላለን፡፡ ነገ ከአየር ጤና ሊነሱ ይችሉ ይሆናል፤ ግን አዲስ በሚላኩበት የሥራ ቦታም የሚጠብቃቸው የጎበጡ አሠራሮችን ማቅናት ነው - የአንዳንዱ ጥሪና አገልግሎት ይገርማል፡፡


አባ ናትናኤልን ያበረታ አምላክ እኛንም ያበርታን!!!
የቤተክርስቲያናችንን አንድነት ይጠብቅልን!!!
አሜን!!!


No comments:

Post a Comment