Saturday, November 17, 2012

የጉጂ ቦረና ሀገረ ሰብከት ጉዳይ መንግስትን አሳስቦታል፡፡

Read in Pdf:menegesete gugiborena Asasebotal
በማህበረ ቅዱሳን ምክንያት ችግር ውስጥ ከገባ ሁለት ዓመት የሞላው የጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት ችግሩ እየሰፋ እና እየከረረ በመሄዱ መንግስት ቤተ ክህነት አስቸኳይ መፍትሔ እንድትሰጥበት ቢወተውትም ቤተክህነቱ ግን ከአቡነ ጳውሎስ እረፍት በኋላ በጽንፈኛው ማኅበረ ቅዱሳን እጅ በመውደቁ በማኅበረ ቅዱሳን መንገድ ካልኆነ  በቀር ሌላ መንገድ የለም የሚል ልብ አይገቤ ምክንያት ላይ በመወጠሩም መንገስት ችግሩ ከፍቶ ሌላ ነገር ከመከሰቱ በፊት የሚያጣራ የራሱን አጣሪ ኮሚቴ ልኳል፡፡
ካለፈው እሮብ ጀምሮ የማጣራት ስራውን የጀመረው አጣሪ ኮሚቴ ስራውን በተገቢ ሁኔታ እያከናወነ ሲሆን አብሮ ይሄዳል ተብሎ ታስቦ የነበረው በተስፋዬ የሚመራው የቤተክህነቱ ቡድን ግን በተለያዩ ተልከሻ ምክንያቶች የማጣራት ሂደቱን በማዘግየቱ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተወከሉ አጣሪዎች ብቻቸውን የማጣራት ስራውን ቀጥለዋል፡፡

ይህ የማጣራት ሂደት አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ የተጀመረ ሲሆን ከቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጁ ተስፋዬ እስክንድር ፋንታሁን ሙጬ እና አለምእሸት ያሉበት እና ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ከአሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሰዎች ተወክለው አብረው ጀምረውት የነበረ ማጣራት አቡነ ጳውሎስ ሲያርፉ ግን አጣሪ ኮሚቴው ማጣራቱን አቋርጦ በቶሎ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ከዛ በኃላ ግን በተደጋጋሚ የነበሩ ጉዞዎችን እያሰናከሉ የነበሩት እነ ተስፋዬ በጥቅምቱ የሀገረ ስብከት ስብሰባ ላይ የጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት ችግር ተፈቷል ብለው ሪፖርት ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ሪፖርት የሀገረ ስብከቱን ህዝብ አስቆጥቶ ባደረጉት እንቅስቃሴ አጣሪ ኮሚቴው እንደገና ይሂድ ቢባልም እነ አቶ ተስፋዬ ግን እየተገለባበጡ ለመሸወድ እና የማጣራት ስራውን ለማደናቀፍ ሞክረዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳንን እንደ ገዢ መደብ የሚያየው የክልሉ ሕዝብ በቤተክህነቱ የተንሰራፋው የጭሰኛ ስርዓት ያብቃልን እያለ ለመንግስት የተለያየ ቢሮዎች እና ለጠቅላይ ቤተክህነት ደብዳቤ በማስገባቱ እና በክልሉ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከዕለት ወደ እለት እየከፋ በመሄዱ በማኅበረ ቅዱሳን በኩል እየተፈጸሙ ናቸው የተባሉትን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ ማጣራቱ አስፈላጊ ሆኗል፡፡
በማጣራቱ ሂደት ላይ የመንግስት አካላት የተለያዩ ወገኖችን እያነጋገሩ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳንን የሚቃወመው የኅብረተሰብ ብዛት እና አንድነቱ እንዳስገረማቸው ለመታዘብ ተችሏል፡፡ በተለይም በሻኪሶ ከተማ ላይ የነበሩ የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች የሀሳብ መከፋፈል እና በአጣሪው ኮሚቴ ፊት ወደ ጸብ ማምራታቸው ለታዘበ ሁሉ እነዚህ ሰዎች ከሁከት የሚወጡት መቼ ነው አስብሏል፡፡ ፡ አሸባሪው እና መፍቀሬ ስልጣን የሆነው ማኅበርን የተመለከቱ በርካታ ሰነዶች በሻኪሶ ከተማ ላይ ተገኝተዋል እየተባለ ሲሆን በተለይም ምርጫ 97ን አስመልክቶ ያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴን የሚያሳዩ በርካታ ማስረጃዎች መገኘታቸው ተገልጧል፡፡ አጣሪ ኮሚቴው ዛሬ በቦረና ከተማ ያለውን ሁኔታ ያጣራል ተብሏል፡፡

2 comments:

  1. Hahaha...maferiyawoch nachihu!eskemeche gin endih yeseyitanin sira tiseralachihu?yefugnit lijoch nachihu!Mk endenante kentu alama yalaw mahber ayidelem!dekamoch,hule endewusha ùechoh new sirachihu.

    ReplyDelete
  2. Good job Aba Serke with out fear to said those word to crazy Maheber Kidusan. They are leading our church leader wrong direction by control there mind with money.......... Please, would you tell them, do not proud with money. Money not greater than Lord God. I am proud you Aba Serek. We need kind of you strongest leader for our Orthodox Church. We will pray for our truth Spiritual father Aba Serek to be get well ............

    ReplyDelete