Friday, November 30, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ «ብላክ ማርኬት» እንዳለው ተሰማ


ምንጭ አባ ሰላማ

(ማሕበረ ቅዱሳን የተባለው የትናንሽ ጋኔኖች ስብስብ የሚሰራውን አሳጥቶ እያቅበዘበዘው ነው፡፡ ህልማቸው ሀሳባቸው እንቅስቃሴያቸው እና ግባቸው ሁሉ ገንዘብ ብቻ የሆነው እነዚህ ሰዎች እልል በቅምጤ ብለው ዶላር መመንዘር ያውም በቤተክህነት ግቢ ውስጥ መጀመራቸው ይደንቃል፡፡ ለምሩቃኑ ተስፋ ነው የተባለው የምሩቃኑ ስብሰብ እንደ ማንዘዋል ባለ የማቅ አለሌ ወታደር ከተያዘ ወዲሕ ተማሪዎቹን ረስቶ ማኅበረ ቅዱሳንን በጥፍሩም በጥርሱም ማገልገል ከጀመረ ሰነበተ፡፡ አቡነ ጢሞቴዎስ ከግቢው ውጡልኝ ብለው ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከተባረሩ ወዲህ በቤተክህነት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ባገኙት ቢሮ የማኅበረ ቅዱሳን ወግ የሚሰለቅበት እና የማኅበረ ቅዱሳን ስራ የሚሰራበት ሆኗል፡፡ አሁን ደግሞ ግቢው ባለቤት እንደሌለው መነግስትም እንደማቆጣጠረቅ አውቀው ብላክ ማርኬት መስራት ጀምረዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ለሚያቅደው መንገስት የመመስረት ህልሙ ብላክ ማርኬት ጥሩ የገቢ ማግኛ ስልት ነው፡፡ መንገስት አን ይሄን ደርሶበት እርምጃ ልውሰድ ቢል በለመደ አፋቸው በደጃ ሰላም ላይ መንገስትን በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገባ ሊባል ነው፡፡ መልካም ንባብ)

ድብቅ አላማ ይዞ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ በድብቅ መክፈቱን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ማኅበሩ ለዚህ ህገወጥ ተግባር የሚጠቀምበት ቢሮ በስም «የቲዎሎጂ ምሩቃን ማኅበር» እየተባለ የሚጠራውና የቲዎሎጂ ምሩቃን በአባልነት የሌሉበትና ማንያዘዋልን ጨምሮ ጥቂት የማቅ «የቲዎሎጂ ምሩቃን» አባላት የሚገናኙበት ቢሮ ነው ብለዋል፡፡ ቢሮው ቀድሞ ከነበረበት ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ቢሮ እንዲያገኝ አድርጓል፡፡ ይህን ያደረገውም የውጭ ምንዛሬውን ጨምሮ ሌሎች ድብቅ ስራዎችን ለመስራትና ለመጠቀም አስቦ እንደሆነ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ቢሮው የማቅ ሌላው ቢሮ ነው እያሉም ነው፡፡ ማኅበሩ የዶላር ዩሮና ፓውንድ ምንዛሬዎችን የሚያካሂደው በድብቅ ሲሆን ከውጪ አገር ዶላር ይዘው የሚመጡና ዶላር የተላከላቸው የማኅበሩ አባላትና አንዳንድ ጳጳሳትም ዶላር ዩሮና ፓውንድ በዚሁ ቢሮ እንዲመነዝሩ እንደሚደረግ የደረሰን መረጃ ያመለከታል፡፡ መንግስት የዶላር እጥረት አጋጥሞኛል በሚልበት በዚህ ወቅት ማቅ እንዲህ እያደረገ መሆኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡


ማኅበሩ ይህን ህገወጥ ስራ እንዲሰራ የመደበው ሃይለ ማርያም አያሌው ዘላሊበላ የተባለውና በአሁኑ ጊዜ የምሩቃን ማኅበር ተብዬው ምክትል ሊቀመንበር መሆኑም ታውቋል፡፡ ምክትል ሊቀመንበር የሆነው ለሽፋን እንደሆነና ዋና ስራው ግን የማቅን የምንዛሬና ሌሎች ህገወጥ ስራዎችን ማከናወን እንደሆነ የሚናገሩት ምንጮች ግለሰቡ ከእጁ ትልቅ ቦርሳ እንደማይለይና እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ለምንዛሬው ይዞ እንደሚንቀሳቀስ ተናግረዋል፡፡ ከአንዳንድ ከማህበሩ ጋር ንክኪ ካላቸው ኪራይ ሰብሳቢ የመንግስት ሰራተኞች ጋር በመመሳጠርም ኮንዶሚኒየም ቤት ላልተመዘገቡ የማህበሩ አባላት በህገወጥ መንገድ እንዲያገኙ ማድረግ የሃይለ ማርያም አያሌው ሌላው ስራ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮቻችን ኮንዶሚኒየም ያልተመዘገቡ አባላትን 20 ሺህ ብር በማስከፈል በፎርጅድ መረጃዎች ስማቸው ኮምፒውተር ላይ እንዲገባ የሚያደርግ ሲሆን ሲረከቡ ደግሞ 70 ሺህ ብር እንዲከፍሉ እንደሚያደርግ ምንጮቻችን ገልጸው እስካሁን ከ50 በላይ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለማኅበሩ አባላት ማሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ህገወጥ ስራ በሚሰበስበው ገንዘብ ለራሱ ጆሞ ሳይት ላይ በ200 ሺህ ብር ባለሱቅ ኮንዶሚኒየም ቤት እና በ30 ሺህ ብር 2 ጋሪ ከነፈረሶቹ ገዝቶ እያከራየ መሆኑንም ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን ቤቱን ከማህበሩ እውቅና ውጪ ገንዘብ ወጪ አድርጎ በመግዛቱ ከማቅ ጋር ጭቅጭቅ ውስጥ ገብቶ እንደነበረና ካለረፋችሁ እኔም ሌላውን ሚስጢር እንዳላወጣ በማለት ስላስፈራራ ጉዳዩ ተከድኖ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ሃይለ ማርያም የላሊበላ ሰው በመሆኑና ባለጊዜዎቹንና የወንዙን ሰዎች እነአባ ህዝቅኤልን ስለተማመነ ቤተክህነት ውስጥ እንደልቡ እየተንቀሳቀሰ ነው ይላሉ፡፡  

No comments:

Post a Comment