Sunday, November 25, 2012

ምነው? ኢሳትን ኸይ! የሚል ጠፋ?



 በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል
በተጠቃሹ "የዜና" ማሰራጫ ማዕከል ስራዎች ዙሪያ ስጽፍ ይህ የመጀመሪያዬ አይደለም። በተለያዩ ጊዜያት ማዕከሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በተመለከተ የሚያሰራጫቸው ሚዛናቸው የሳቱና ግልጽነት የሚጎድልባቸው ዘገባዎቹንና ሐተታዎቹን በማስመልከት ተደጋጋሚ ጽሑፎች ለንባብ መብቃታቸው የሚታወስ ሆኖ በርካታዎቹ ሃያ አራት ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ከስፍራቸው እየተነቀሉ ለአንባቢያን እንዳይደርሱ ተደርገዋል።
 ይህ በእንዲህ እንዳለ የዜና ማሰራጫ ማዕከሉ ግድፈቶቹን አምኖ ራሱን ከማስተካከልም ይልቅ  "ሰምቶ ማሳለፍ!” የሚልዋትን ፖለቲካ ተጋርቶ ባለበት ሲረግጥ እየተስተዋለ ነው። እውነት ነው የሕዝብ ጆሮና ዓይን መሆን ማለት "የሕዝብ ጆሮና ዓይን ነን!”  በማለት የመፎከር ያክል ቀላል ነገር እንዳይደለ አንድ የሰከነ ባለ አእምሮ ሰው የማይስተው መሬት የረገጠ እውነታ ለመሆኑ የሚያከራክረን አይመስለኝም።
አንድ መገናኛ ብዙሐን ራሱን በፈለገው መልክና ቅርፅ እየቃኘ ማስተዋወቁ አያጣላንም፤ የጽሑፉ ዓላማም አይደለም። በጥቅሉ ከስሙ ባሻገር በተገለጠው ፍሬው/በስራዎቹ አይጠየቅበትም ማለት ግን አይደለም።

በአጭሩ "የዜና" ማዕከሉ (ኢ.ሳ.ት) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በማስመልከት ለሚያስተላልፋቸውና ለሚያሰራጫቸው ዘገባዎች በተመለከተ ግን በምንጭ ደረጃም ሆነ የተፋለሱ መረጃዎችን በመቀባበል ረገድም ስውር ዓላማ ካለው ራሱን የቅዱሳን ማኅበር በማለት ከሚጠራ ትውልድ ገዳይ አገር አጥፊ ስመ መንፈሳዊ ድርጅት መተሻሸቱ እስላቆመቀናቀናውን ማሰብንና መስራትን ትቶ የቤተክርስቲያኒቱ ምእመናን በበሬ ወለደ ዜናና ሐተታ ለማተረማመስ፣ ሁከትንና ሽብርን ለመፍጠር አለሁ ማለቱ እስካልተወ ድረስ ጉዳዮ ተወዳጅነት የማትረፍና ቲፎዞ የመሰብሰብ ጉዳይ አይሆንምና "የዜና" ማዕከሉ ምእራብ ከምስራቅ ሰሜንም ከደቡብ እንደሚርቅ ጽንፍ የረገጠ መሰረት አልባ ዘገባዎችና ዜናዎች በማስመልከት በቃሉ እንደተፃፈ እንዲሁ እሬት እሬት ቢለንም እውነት እውነቱ መነገሩ የማይቀር ነው።
እንደማንኛውም መገናኛ ብዙሐን ቤተክርስቲያንን በተመለከተ አንዳች ነገር አይባል/አይዘገብ አይነት ጭፍን መልዕክት እያስተላለፍኩ አይደለም።
 በእርግጥ ለማለት የተፈለገው ምን እንደሆነ አንባቢም ሆነ ተደራሲው ያጣዋል የሚል እምነትም የለኝም።  ነገሩን ግልጽ ለማድረግ የተፈለገ እንደሆነ ግን ግመልን የሚያክል እውነት ወደጎን እየተተወ ትንሽዋን በማስፋት፣ በመለጠጥ፣  በመወጠርና ከዚህም አልፎ የሌለውን በመፍጠር የሚሰራ የግብር ይውጣ ስራ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይቁም! ነው። ሰው አይሳሳትም አይባልም።  ሰው ስራ እስከሰራ ድረስ ስህተት መስራቱ የማይቀር ነው።
 በተመሳሳይ ርእሰ ጉዳይ ከአንዴም ሁለቴ ሶስት አራት ጊዜ ተደራራቢ ጥፋት መፈጸም ግን ስህተት ሳይሆን ንቀት ነው የሚባለው።
ይኸውና November 11 2012 "የዜና" ማእከሉ ያሰራጨው "ዜና" እንደሚከተለው ይነበባል “እርቅን ለማውረድ በቀጠለበት በአሁን ወቅት የዓቃቤ መንበረ ፓትሪያርኩ ጥረት የሚያሰናክሉ ወገኖች መነሳታቸው ተገለጸ” ይላል። መቼም ኢሳት ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግን ወገን ብሎ እንደማይጠራ የታወቀ ነው።
 ታድያ ይህ ወገን የተባለ አካል ማን ነው? በማለት የጠየቅን እንደሆነ “...ከሲኖዶሱ እውቅና ውጭ በራሱ እየተንቀሳቀሱ ነው ከሚለው ወቀሳ ጀምሮ አቡነ መርቆሪዮስን አንፈልግም እስከሚለው ድረስ ከመንግስት ጋር ቅርበት ያላቸው ጳጳሳትና ሌሎች ወገኖች ችግር እየፈጠሩ መሆናቸው ተረጋግጧል::” ከንባቡ በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው ችግር ፈጣሪዎቹ ቀደም ብሎ "ወገኖች" ተብለው የተጠሩ ሊቃነ ጳጳሳት ጨምሮ ማንነታቸው በግልጽ ያልሰፈረ ግለሰቦች/ሃይሎች የሚያጠቃልል ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ "ማኅበረ ቅዱሳን"  ከመጋረጃ በስተጀርባ ተቀምጦ ከሚዘውራቸው የሁከትና የበሬ ወለደ ልሳኖቹ መካከል የሆነው “አንድ አድርገን”  በመባል የሚታወቀው መካነ ድር ጥቅምት 30 2005  ዓ.ም "በፓትርያርክ ምርጫ ላይ መንግስት ተጽህኖ ለማሳደር የራሱን ቡድን መሰረተ" ሲል በዘራው የፈጠራ ወሬ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ "የቀድሞ ፓትርያርክ ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ ብዙዎችን እያነጋገሩ ካሉት ነገሮች ውስጥ ስለ ቀጣይ ፓትርያርክ ምርጫ እና እርቀ ሰላም ይገኙበታል ፤ ከሁለት ሳምንት በፊት በፌደራል ጉዳዮች አማካኝነት የራሱን ተጽህኖ ማሳረፍ የሚልች 7 ሰዎችን የያዘ ቡድን በሚስጥር መመስረቱ ጉዳዩን በቅርበት ከሚያውቁ ሰዎች ተሰምቷል" በማለት የራሱን ሐጢአት በሌሎች ሲያሳብብና ሌላውን ሲወነጅል ከጥቂት ቆይታ በሃላ ደግሞ ኢሳት "የማህበረ ቅዱሳን"  ደጀን በመሆን ይህንን አሉባልታ በመጋራት መጠነኛ የቃል ማሻሻያም በማድረግ "በዜና"  መልክ ይዞ ለመቅረብ መድፈሩ በራሱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ያለውን ቁልጭ ያለ ንቀት የሚያሳይ ነው 
"ዜና" አንባቢው አክሎ “.. አቃቤ መንበር ብጹእ አቡነ ናትናኤልና በርካታ ጳጳሳት በብጹእ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱና የቤተክርስቲያኒቱ አንድነት እንዲመለስ የሚፈልጉ ቢሆኑም መንግስት አዲስ ፓትሪያሪክ አንዲመርጡ እየገፋ መሆኑን እየተሰማ ነው ሲል እንዳነበበው "የዜና"  ማእከሉ ምን ያህል ከእውነት እየራቀ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት መሪዎች አንድ አለመሆንና አለመግባባት የተነሳ በሚፈጠረው ሁከትና ግርግር የልዩ ጥቅም ተካፋይ/ተጋሪም አስመስሎታል። (ሙሉውን የዜናው ይዘት ለማድመጥ የሚከለተውን ሊንክ ይጫኑ (ESAT DC Daily News November 11 2012
በመሰረቱ የአገር ቤቱ ሲኖዶስ አዲስ ፓትሪያሪክ እንዲመርጥና እንዲሾም እየገፋፋና ቅጥረኞች አሰማርቶ ጠቅላይ ቤተክህነት እያተራማመሰ እንዲሁም ሌቃውንተ ቤተክርስቲያን እያመሰ ያለው ማን ነው?  ምን ነው ሕዝብ በተጨባጭ የሚያውቀውን እውነት በጠራራ ፀሐይ ለማድበስበስና የጥላሸት ለመቀባት የተነሳችሁ?  ለመሆኑ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው የቤተክርስቲያኒቱም ወደ ቀድሞ አንድነትዋ እንይመለሱ የማይፈልግ ማን ነው?  እውነት በእውነትነቱ መነገር መዘገብና ማቅረብ እየተቻለ እውነት ማንን ገደለ እና ነው መንግሥት ባልዋለበት የሚወነጀለው?  እውነት የማይጥማችሁ ከድርጅቱም አላማ ፈጽሞ የማይገጥም ከሆነም የሀገሬ ሰው "ዝም ያለ አፍ ዝንብ አይገባበትም"  እንዲል ሁሉንም ሳይሉና ሳይነካኩ አርፎ መቀመጥ ነው::   በተረፈ ግን በሀገር ቤቱ ሲኖዶስ በኩል እየተኬደ ያለውን ጸረ ሰላም አካሄድ ዋና አቀንቃኝና አራጋቢ በሁከቱ ቀዳሚ ተጠቃሚ የሆነው ራሱን "ማህበረ ቅዱሳን"  ብሎ የሚጠራ የጥቁር ራስ ስብስብ ሆኖ ሳለ በመንግስት ማላከኩ ዝናብ የሌለው ደመና ይፈጥር እንደሆነ እንጂ ዝናብ አያወርድም።
የመረጃ እጥረት ያለባችሁ/ ድርቀት የገጠማችሁ እንደሆነም ስለምትዘግቡት ዘገባም ሆነ ሰፊ ሽፋን ሰጥታችሁ ስለምታትቱት ሐተታ በመጠኑም ቢሆን ግንዛቤ ይኖራችሁ ዘንድ ይህን ላስታውሳችሁ።  ወቅታዊና ነባራዊው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የሃይማኖት መሪዎች ሁኔታ በተመለከተ በተለይ በአሁን ሰዓት እዩኝ እዩኝ ማለት ያበዙና ፎቶግራፋቸው በየጎዳናው እየበተኑ የሚገኙ መነኮሳት ("ሊቃነጳጳሳት")  ምንነት ሐቁ ቁም ነገር ኑሮባቸውና የሚረቡ ሆነው መንግሥትን የሚያክል ግዙፍ አካል የሚፈልጋቸው ዓይነት ሰዎች ሳይሆኑ በአንድም በሌላም መንገድ ሳይገባቸውና ሳይገባቸው የተቀራመቱትን ወንበር ለመጠበቅ ሲሉ ብቻ የመንግሥት ድጋፍና እርዳታ በብርቱ የሚሹ: ደጅም የሚጸኑ ለመሆናቸው ግልጽ ሳደርግላችሁ በአክብሮት ነውበተረፈ የሐሰት አባት ከሆነው የራሱ ነገር የሌለውና ራሱንም እንደ ባለ ጸጋ የሚጠራና የሚቆጥር ሌባ፣ አታላይ፣  ደም  አፍሳሽና ነፈሰ ገዳይ ከሆነው ከዲያብሎስ ጋርም በደም ቃል ኪዳን ተሳስረውና ተማምለው አብረው ለመስራት የማይመለሱ ከማንም በላይ የእግዚአብሔር ምሕረትና ቸርነት የሚያስፈልጋቸው ሕዝብን በሃጢአት፣  የጥፋት በሆነው መንገድ እየመሩ የሚገኙ ህይወት የሚያስፈልጋቸው የደረቁ አጥንቶች ናቸው።       

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል
United States of America

2 comments:

  1. እግዚአብሔር አምላክ ጥበቃው ከአንተ ከወንድማችን ጋር ይሁን። እውነት መናገር የአቃታቸው የጨለማ ክርስቲያኖች የሆኑትን ክፉ መንፈስ ዘወትር የሚዘሩትን ማህበር ቅዱሳን የደገፈው እሳት ግራ የገባው ስለሆነ አትፍረዱበት። የፖለትካው በኩል አልሳካ ስላሌው የቤተ ክርስቲያን ጠላት ከሆነው ከማቅ ጋር ወዳጅነት መፍጠሩ ለራሱ የሞተ ድርጀት ነው። ለምሳሌ ከዚህ በፊት በዉጪው ስኖዶስ በሚመሩት ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ለሁለት ስያሰነጥቅና ስያውክ የኖረ ማህበር ነው። እውነቱን በትክክል ለማወቅ ከፈለጋችሁ የስደተኛውን ስኖዶስ ቢሮ ጉራ ብላችሁ አነጋግሩአቸው። ብዙ አባቶች ሰለባ የሆኑት በማህበረ ቅዱሳን በእነ ዳንኤል ክብረት አይደለምን? ዛሬ ማህበረ ቅዱሳን ወደ ዉጪ ስኖዶስ ጠጋ ጠጋ ያለው ድጋፍ ለማግኝ እርቅ እያለ መጮህ ጀምሮዋል። ይገርማል። እሳቶች እውነት መናገርና በእውነት ቦታ መቆም ያስፈልጋችዋል። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብን ማታለል አትችሉም። በብዙ አታላይ መሪዎችና የፖለትካ ሰዎች ተፈትኖ ያለፈ እና ዛሬም እናንተን በመሰሉ አታላዮች እየተፈተነ ነው። በወጩ ሀገር በሚጠሩ የተቃዉሞ ስብሰባዎች ላይ ለምንድነው ብዙ የኢትዮጵያ ህዝብ የማሄደው ? መልሱ ብዙ ዉሸታም ፖለትከኞች ስለበዙ ነው። በማህበረ ቅዱሳን በተነሳ በዉጪ ያሉት አብያተ ከርስቲያናት አንድነት የላቸው። ሌላው ቀርቶ በአንድ ቤተ ከርስቲያን ያሉ ምእመናን አንኳን ፍቅርና ሰላም የላቸው። ካህናቱና ምዕመናኩ የጎርጥ ነው የምተያዩት። የንሰሐ አባትነት መሆን ቀርቶ ሌላ ወንጀል ነው የምስሩት። አሁን እግዚአብሔር ይመስገን ማህበረ ቅዱሳን ህዝቡ አንቅሮ ስለተፋው ሰላም እየ መጣ ነው። ግን አንዳንድ አባቶች የነዋይ ቅጥረኛ (ማህበረ ቅዱሳን) በመሆን ችግር እየፈጠሩ ነው። ቸሩ ፈጣን እርሱ ገና ይዋጋቸዋል። ለእረሱ መስጥት መልካም ነው። እሶቶች ከእሳት ውስጥ ዉጡ እሳት ለሰው አይበጅምና። ቸር ወሬ ያሰማን...............

    ReplyDelete
  2. እውነትን አፍረጥርጣችሁ የምትጽፉ እንዴት ተገኛችሁ? ፈጣሪ ያበርታችሁ!በዘመናችን ዕኮ ተመጻዳቂዎችና አስመሳይ
    መናፍስት የተሰራጩብትና ለቤተ ክርስቲያን ገዳይ መርዝ ሆነው ከተሜ ምላሳቸውን የሚያውለበልቡበት ዘመን ሆኗል።
    ባለቤቱ ከመርዛቸው ይሰውራችሁ!

    ReplyDelete