Monday, December 3, 2012

ይድረስ ለመንጋው እረኞች አባቶቼ



  ከደቡብ አፍሪካ      
ይድረስ...........ይድረስ........ይድረስ፦ከጥቅም ጋር ሳይሆን ስለእውነት ለምትሰሩ አባቶች፤ ለዘር ሳይሆን ለእምነታችሁ ለቆማችሁ አባቶች፤ ከሀሰተኞች ጋር ሳይሆን ከእውነት ፊት ለምትቆሙ አባቶች። >> መቼም (ጉድ ሳይሰማ መስከረም ኣይጠባም)>>  የተባለው በዚህ ባለንበት በደቡብ አፍሪካ በተግባር መተርጎም ከጀመረ ዘመናትን አስቆጥሮኣል። ይሁንና (የአሁኑ ይባስ) ብሎ በጣም የሚያስግርሙና አረ ወዴት እንሂድ?..... ወደ ማንስ አቤት እንበል?..... የሚያሰኙና፡ እንዲሁም ቤተክርስቲያኗ የማናት?......... ባለቤቷስ ማነው?......... መንፈስ  ቅዱስ ወይስ የአንድ ፓለቲካ ድርጅት? የቤተክርስቲያኗ ባለቤቶችስ በውስጧ የሚያገለግሉና የሚገለገሉ አማኞች ወይስ የገቢዋ ተጠቃሚ የሆኑ (የሆነ)ግለሰብ? መልሱን በጽሑፍ ሳይሆን በተግባር ለሚመልስ አውነተኛ እረኛ ስለ በጎቹ (ምእመናን)ለሚገደው ሁሉ ትቼዋለሁ።  
መቼም ከላይ ለተዘረዘሩት አጅግ ጥቂት፡ ነገር ግን መሰረታዊ ለሆኑ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ጊዜያችሁን እንደማትቆጥቡ በመተማመን ወደ ተነሳሁበትና፡ ለአንድ ሙሉ አመት የምእመናን ጭንቀትና መወያያ ሆኖ ከመቆየቱም ባሻገር አጅግ አስገራሚና ለሰሚ ጉድ ያሰኝውን በስላሴ ስም በተሰየመው ቤተክርስቲያን እየተከናወነ ስለ አለው እቃቃ_ እቃቃ ልበለው?........ ወይም አንቆቅልሽ?....... አሊያም . . . . . . . ብቻ ለኔ የሚመጥነው ቃላት ያላገኘሁለትንና፦ የብዙዎችን ልብ ክፉኛ ያሳዘነውን አስገራሚ ታሪክ ባጭሩ፡ በማስተዋል ለመጓዝና አውነቱ ምን አንደሆን አውቆ ለህሊና ዳኝነት ይረዳችሁ ዘንድ ብሎም ስለቤተክርስቲያኗ የሚገዳቸው አባቶች አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልጉልን ይረዳ ዘንድ ከዚህ አንደሚከተለው በዝርዝር የታዘብኩትንና በአማኝነቴ ውስጤን የጎዳውን ለማሳየት አሞክራለሁ።

Friday, November 30, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ «ብላክ ማርኬት» እንዳለው ተሰማ


ምንጭ አባ ሰላማ

(ማሕበረ ቅዱሳን የተባለው የትናንሽ ጋኔኖች ስብስብ የሚሰራውን አሳጥቶ እያቅበዘበዘው ነው፡፡ ህልማቸው ሀሳባቸው እንቅስቃሴያቸው እና ግባቸው ሁሉ ገንዘብ ብቻ የሆነው እነዚህ ሰዎች እልል በቅምጤ ብለው ዶላር መመንዘር ያውም በቤተክህነት ግቢ ውስጥ መጀመራቸው ይደንቃል፡፡ ለምሩቃኑ ተስፋ ነው የተባለው የምሩቃኑ ስብሰብ እንደ ማንዘዋል ባለ የማቅ አለሌ ወታደር ከተያዘ ወዲሕ ተማሪዎቹን ረስቶ ማኅበረ ቅዱሳንን በጥፍሩም በጥርሱም ማገልገል ከጀመረ ሰነበተ፡፡ አቡነ ጢሞቴዎስ ከግቢው ውጡልኝ ብለው ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከተባረሩ ወዲህ በቤተክህነት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ባገኙት ቢሮ የማኅበረ ቅዱሳን ወግ የሚሰለቅበት እና የማኅበረ ቅዱሳን ስራ የሚሰራበት ሆኗል፡፡ አሁን ደግሞ ግቢው ባለቤት እንደሌለው መነግስትም እንደማቆጣጠረቅ አውቀው ብላክ ማርኬት መስራት ጀምረዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ለሚያቅደው መንገስት የመመስረት ህልሙ ብላክ ማርኬት ጥሩ የገቢ ማግኛ ስልት ነው፡፡ መንገስት አን ይሄን ደርሶበት እርምጃ ልውሰድ ቢል በለመደ አፋቸው በደጃ ሰላም ላይ መንገስትን በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገባ ሊባል ነው፡፡ መልካም ንባብ)

ድብቅ አላማ ይዞ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ በድብቅ መክፈቱን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ማኅበሩ ለዚህ ህገወጥ ተግባር የሚጠቀምበት ቢሮ በስም «የቲዎሎጂ ምሩቃን ማኅበር» እየተባለ የሚጠራውና የቲዎሎጂ ምሩቃን በአባልነት የሌሉበትና ማንያዘዋልን ጨምሮ ጥቂት የማቅ «የቲዎሎጂ ምሩቃን» አባላት የሚገናኙበት ቢሮ ነው ብለዋል፡፡ ቢሮው ቀድሞ ከነበረበት ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ቢሮ እንዲያገኝ አድርጓል፡፡ ይህን ያደረገውም የውጭ ምንዛሬውን ጨምሮ ሌሎች ድብቅ ስራዎችን ለመስራትና ለመጠቀም አስቦ እንደሆነ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ቢሮው የማቅ ሌላው ቢሮ ነው እያሉም ነው፡፡ ማኅበሩ የዶላር ዩሮና ፓውንድ ምንዛሬዎችን የሚያካሂደው በድብቅ ሲሆን ከውጪ አገር ዶላር ይዘው የሚመጡና ዶላር የተላከላቸው የማኅበሩ አባላትና አንዳንድ ጳጳሳትም ዶላር ዩሮና ፓውንድ በዚሁ ቢሮ እንዲመነዝሩ እንደሚደረግ የደረሰን መረጃ ያመለከታል፡፡ መንግስት የዶላር እጥረት አጋጥሞኛል በሚልበት በዚህ ወቅት ማቅ እንዲህ እያደረገ መሆኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡

Wednesday, November 28, 2012

እናያለን ትላላችሁ እንጂ ዕውሮች ናችሁ!

Read in Pdf: Enayalen
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

ዕለታዊ፣ ሰሙናዊ: አልፎ አልፎም ወርሐዊና ዓመታዊ የዜጎች መውጫና መግቢያ የሚይዙ መነጋገሪያ አጀንዳዎችና ርእሰ ጉዳዮች ዛሬ ብቻ ሳይሆን በየትኛው ዘመን ያለ፣ የሚታይና የሚነሳ ነገር ነው። የዛሬ ሁለት ሺሕ ዓመት በእስራኤል ምድር ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ጥቂቶች የማይባሉ ጸጉር ያስነጨና ፊት ያስቧጨረ ወደ አንድ ጉዳይ ላምራችሁ።
"በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት ቀን በእርሻ መካከል አለፈ፤  ደቀ መዛሙርቱም ተራቡና እሸት ይቀጥፉ ይበሉም ጀመር ፈሪሳውያንም አይተው እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ አሉት። እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት በተራቡ ጊዜ፥ እርሱ ያደረገውን፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደገባ ካህናትም ብቻ እንጂ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሊበሉት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕቱን ኅብስት እንደ በላ አላነበባችሁምን? ካህናትም በሰንበት በመቅደስ ሰንበትን እንዲያረክሱ ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው በሕጉ አላነበባችሁምን? ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከመቅደስ የሚበልጥ ከዚህ አለምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ብታውቁስ ኃጢአት የሌለባቸውን ባልኰነናችሁም ነበር። የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።"

Monday, November 26, 2012

‘ማልደራደርበት ‘ማልቀብረው እውነት አንገት ‘ማያስደፋኝ የማላፍርበት ኢየሱስ የሚለው ስም እስትንፋሴ ነው እውነቱ ይሄው ነው


 Read in PDF: Malederaderebt
እነዚህ ስንኞች የተወሰዱት ከአንድ የግጥም መድበል ውስጥ እንዳይመስላችሁ፤ ዲ/ን ትዝታው ሳሙኤል ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን እና ዘማሪት ዘርፌ ከበደ በጋራ ከሳተሙትና «አለው ነገር» የሚል ርእስ ከተሰጠው የዝማሬ ሲዲ ላይ የተወሰደ ነው፡፡ እውነት ነው ኢየሱስ የሚለው ስም ለእውነተኛ ክርስቲያን እስትንፋስ ነው፡፡ አንገት የማያስደፋና የማያሳፍር የማይቀበርና ለድርድር የማይቀርብ ስም ነው፡፡ እውነትም ኢየሱስ በሚለው ስም ላይ ድርድር የለም!!!


ይህ የዝማሬ ሲዲ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ጀምሮ ለምእመናን ቀርቧል። በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አድባራትና ገዳማት በየበአላቱ ቀን ሞንታርቦ በያዙ ሚኒባሶችና በየመዝሙር ቤቱ ሁሉ እየተሸጠ መሆኑንና ታክሲ ውስጥ፣ በተለያዩ ንግድ መደብሮችና በየካፌውና ሬስቶራንቱ ሁሉ እጅግ እየተደመጠ ይገኛል፡፡ 12 ዝማሬዎች የተካተቱበት ይህ የዝማሬ ሲዲ በውስጡ አስሩ ጌታን የሚያከብሩ፣ ፍቅሩን የሚሰብኩ፣ አዳኝነቱን የሚያውጁና የሚማጸኑ፣ ፈራጅነቱን የሚያዘክሩ፣ ወደንስሀ የሚመሩና መሰል መልእክቶችን ያካተተ ሲሆን ለእመቤታችን ለማርያም የቀረቡ ሁለት ዝማሬዎችም አሉበት። የዝማሬዎቹን ግጥምና ዜማ የደረሱት ደግሞ አብላጫውን መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ ሲሆን በመቀጠል ዲ/ን ትዝታው ሳሙኤል እንዲሁም ዘማሪ ሀብታሙ ሽብሩ አንድ ዜማ መድረሱን ስቲከሩ ያስረዳል። 
  

የደሴ ተክለ ሃይማኖት ምዕመናን "ተስፋዬ ሞሲሳን ያያችሁ ወዲህ በሉን" እያሉ ናቸው

Read in PDF:Yedese Tekelehaymanote
ምንጭ ፡-http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com
  • የማኅበሩ አባላት ሌሎችን በሚኮንኑበት የንቅዘት ችግር መጠለፋቸው ዝንጀሮ የራሷን መቀመጫ ካለመመልከቷ ጋር የሚነፃፀር ነው
  • ንቅዘት የዘመኑ የቤተክርስቲያናችን ዋነኛ ችግር ሆኗል
  • ከዚህ በታች የቀረበውን ዘገባ የምትጠራጠሩ ካላችሁ ራሱን ተስፋዬንና በዚህ ዘገባ ስማቸው የተጠቀሱትን በተለይ የደሴ የገዳማት አለቆችንና የቤተክህነት ባለሥልጣናትን ጠይቁ፡፡
 የዛሬ ስድስት ወራት ገደማ ግንቦት 12/2004 . ዝቅተኛ ገቢ ባላት የደሴ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን የገቢ ማሰባሰቢያ መንፈሳዊ ጉባዔ ለማካሄድ ከሳምንታት ቀደም ብሎ ዝግጅቱ ቀጥሏል፡፡ አንድ የቤተክርስቲያን ልጅ፣ የተክልዬ ወዳጅ  የጉባዔውን ሙሉ ወጪ ለመሸፈን ቃል ገባ፡፡ ቃል መግባትም ብቻ ሳይሆን ከአዲስ አበባ ሰባክያንንና ዘማርያንን ጋብዙበት ብሎ 20 ሺህ ብር ለገሠ፡፡ የደብሩ የስብከተ ወንጌል ክፍል ሠራተኞችም ብሩ በእጃቸው ይግባ እንጂ የትኛውን ሰባኪ፣ የትኛውን ዘማሪ እንደሚጋብዙ አልተዘጋጁበትም፡፡ የጥቂቶቹን አገልጋዮች ስም የሚያውቁ ቢሆንም እንኳን የስልክና የመኖሪያ አድራሻቸውን አያውቁትም፡፡ ስለዚህ በአዲስ አበባ የሚኖረውን የሀገራቸውን የወንዛቸውን የደሴውን ልጅ በላይ ወርቁን ያገኙትና ለግንቦት 12 መንፈሳዊ ጉባዔ እያዘጋጀን ነው፤ ግን አገልጋዮችን ስለማናውቃቸው በአንተ በኩል ብታፈላልግልን ይሉታል፡፡
በላይ ወርቁም ሰባኪ ሲባል በዓይነ ኅሊናው የመጣለትን የጥቅም ተጋሪው ተስፋዬ ሞሲሳን አስቦ እሺ ችግር የለውም አገናችኋለሁ ይልና ተስፋዬን ያገናኛቸዋል፡፡ ሰዎቹ መቼም በበላይ በኩል የመጣ ያውም በቤተክርስቲያን ጉዳይ ችግር የለውም በማለት ሙሉ እምነት ጥለውበት ተስፋዬ ራሱንና ሌሎቹንም አገልጋዮች ይዞ እንዲመጣ ይነግሩትና ለትራንስፖርትና ልዩ ልዩ ወጪ መሸፈኛ የሚሆን 20 ሺህ ብሩን አስይዘውት ወደ ደሴ ተመለሱ፡፡
ከቀናት በኋላ በደሴ ተክለ ሃይማኖት ደብር የሚካሄደው ዝግጅት ተጠናቆ ጉባዔው የሚጀምርበት ሰዓት ላይ ተደረሰ፡፡ ይሁን እንጂ፣ በዕለቱ ተስፋዬና ሌሎች አገልጋዮች ይመጣሉ ተብሎ ቢጠበቁ፣ ቢጠበቁ ሳይመጡ ቀሩ፡፡  ተስፋዬን የበላው ጅብ አልጮኽ አለ፡፡ ራሱንም ስልኩንም ሸሽጎ እስከናካቴው ጠፋ፡፡ ወይ እርሱ አልመጣ ካልተመቸው ደግሞ ብሩን አልመለሰ፣ ተስፋዬ አዲስ አበባ ላይ ቁጭ ብሎ ብሩን ይቆረጥመዋል ተብሎ ሳይገመት እንደዋዛ፣ እንደ በረሃ አሸዋ ብሩን አሰረገው፡፡

Sunday, November 25, 2012

ምነው? ኢሳትን ኸይ! የሚል ጠፋ?



 በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል
በተጠቃሹ "የዜና" ማሰራጫ ማዕከል ስራዎች ዙሪያ ስጽፍ ይህ የመጀመሪያዬ አይደለም። በተለያዩ ጊዜያት ማዕከሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በተመለከተ የሚያሰራጫቸው ሚዛናቸው የሳቱና ግልጽነት የሚጎድልባቸው ዘገባዎቹንና ሐተታዎቹን በማስመልከት ተደጋጋሚ ጽሑፎች ለንባብ መብቃታቸው የሚታወስ ሆኖ በርካታዎቹ ሃያ አራት ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ከስፍራቸው እየተነቀሉ ለአንባቢያን እንዳይደርሱ ተደርገዋል።
 ይህ በእንዲህ እንዳለ የዜና ማሰራጫ ማዕከሉ ግድፈቶቹን አምኖ ራሱን ከማስተካከልም ይልቅ  "ሰምቶ ማሳለፍ!” የሚልዋትን ፖለቲካ ተጋርቶ ባለበት ሲረግጥ እየተስተዋለ ነው። እውነት ነው የሕዝብ ጆሮና ዓይን መሆን ማለት "የሕዝብ ጆሮና ዓይን ነን!”  በማለት የመፎከር ያክል ቀላል ነገር እንዳይደለ አንድ የሰከነ ባለ አእምሮ ሰው የማይስተው መሬት የረገጠ እውነታ ለመሆኑ የሚያከራክረን አይመስለኝም።
አንድ መገናኛ ብዙሐን ራሱን በፈለገው መልክና ቅርፅ እየቃኘ ማስተዋወቁ አያጣላንም፤ የጽሑፉ ዓላማም አይደለም። በጥቅሉ ከስሙ ባሻገር በተገለጠው ፍሬው/በስራዎቹ አይጠየቅበትም ማለት ግን አይደለም።

Sunday, November 18, 2012

አባ ሰረቀ ብርሃን እርቀ ሰላሙን አስመልከተው ለሲኖዶሱ ደብዳቤ ጻፉ

Read in PDF: Aba Serke
Read in PDF:Aba Sereke letter to sinodos


አባ ሰረቀ ብርሃን የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ይገባዋል ሲሉ ለሲኖዶሱ ደብዳቤ ጻፉ፡፡ አባ ሰረቀ ብርሃን በደብዳቤያቸው “ሁላችን እንደምንገነዘበው ዛሬ ቤተክርስቲያናችን በተለያዩ ኃይሎች በተከበበችበት ወቅት ከማንኛውም በፊት አንድነቷን በሚገባ ማጠናከርና ከሁሉ በፊትም በመካከልዋ የተከሰተውን መለያየት ማስወገድ ቅድሚያ ልትሰጠው ይገባታል።” በማለት በተለይ በዚህ ጊዜ እርቁ ከፍተኛ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
“በውስጥም ሆነ በውጭ ያለነው የቤተክርስቲያናቸን ባለድርሻ አካላት ሁላችን የየራሳችንን ክብርና ጥቅም በመተው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተክርስቲያን ለመጠበቅና የተሰጠንን አደራ እስከ መጨረሻ በብቃት ለመወጣት ከመቼም በበለጠ መልኩ በዚሁ ዙርያ ልዑል እግዚአብሐርን ደጅ በመጥናት ልንሠራ ይገባናል።” ሲሉ የገለጡት አባ ሰረቀ እርቁን ለማደናቀፍ እንደ እባብ ውስጥ ውስጡን እየተሸለኮለኩ ሴራ የሚሸርቡትን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እና መሰሎቻቸውን “ዕርቀ ሰላሙ እንዳይሳካ የሚጥሩና እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱንም ሊቃውንት በማሳደድ ላይ የሚገኙ አካላት ሁሉ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል፡፡” በማለት መክረዋል፡
ለበርካታ አመታት በሰንበት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ሆነው የሰሩት እና ቤተክርስቲናቸውንም አገራቸውንም በእጅጉ የሚወዱት አባ ሰረቀ ብርሃን የሰንበት ማደራጀውን እንቅስቃሴ በተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጎ የማይስማማው እና ሁሉን ንጄ እኔ እንደ አዲስ ልገንባው የሚለው ማኅበረ ቅዱሳን በመንገዳቸው ላይ እንደ ዐለት ተደንቅሮ የተለያየ ሰንካላ ምክንያት በመደርደር አላሰራ ይላቸው እንደ ነበር ይታወቃል፡፡ 

Saturday, November 17, 2012

የጉጂ ቦረና ሀገረ ሰብከት ጉዳይ መንግስትን አሳስቦታል፡፡

Read in Pdf:menegesete gugiborena Asasebotal
በማህበረ ቅዱሳን ምክንያት ችግር ውስጥ ከገባ ሁለት ዓመት የሞላው የጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት ችግሩ እየሰፋ እና እየከረረ በመሄዱ መንግስት ቤተ ክህነት አስቸኳይ መፍትሔ እንድትሰጥበት ቢወተውትም ቤተክህነቱ ግን ከአቡነ ጳውሎስ እረፍት በኋላ በጽንፈኛው ማኅበረ ቅዱሳን እጅ በመውደቁ በማኅበረ ቅዱሳን መንገድ ካልኆነ  በቀር ሌላ መንገድ የለም የሚል ልብ አይገቤ ምክንያት ላይ በመወጠሩም መንገስት ችግሩ ከፍቶ ሌላ ነገር ከመከሰቱ በፊት የሚያጣራ የራሱን አጣሪ ኮሚቴ ልኳል፡፡
ካለፈው እሮብ ጀምሮ የማጣራት ስራውን የጀመረው አጣሪ ኮሚቴ ስራውን በተገቢ ሁኔታ እያከናወነ ሲሆን አብሮ ይሄዳል ተብሎ ታስቦ የነበረው በተስፋዬ የሚመራው የቤተክህነቱ ቡድን ግን በተለያዩ ተልከሻ ምክንያቶች የማጣራት ሂደቱን በማዘግየቱ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተወከሉ አጣሪዎች ብቻቸውን የማጣራት ስራውን ቀጥለዋል፡፡