Wednesday, April 25, 2012

ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ - ጠ/ሚኒስትሩ ፣ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት ትስማማለህ አትስማማም?

Click here to read in PDF
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቻናል 3 ላይ የሚተላለፍና “እስማማለሁ፣ አልስማማም” የተሰኘ አንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አለ። በዚህ ፕሮግራም ለእድለኛ ከ1 ሳንቲም ጀምሮ እስከ 15 ሺህ ብር ድረስ ሽልማት አለ። በጨዋታው ህግ መሰረት ተጋባዡ እንግዳ ሽልማቶቹ ከተቀመጡባቸው ሳጥኖች መካከል አንዱን በመጀመሪያ ይመርጥና ይቀመጣል። ከዚያ ሌሎቹን ሳጥኖች በየተራ እየጠራ በውስጣቸው ያለው የገንዘብ መጠን ተከፍቶ ይታያል። በየጣልቃው ባንከሩ (the banker) እንዲስማማ የሆነ ብር ያቅርብለታል። እንግዳው አልስማማም ካለ ጨዋታው ይቀጥላል፤ እስማማለሁ ካለ ግን ጨዋታው እዚያ ላይ ያቆምና ባንከሩ የሰጠውን ብር ይወስዳል። ኤፍሬም እሸቴ /ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማምሲል በድረ ገጹ ላይ ከሰሞኑ ፖስት ያደረገው ጽሑፍ ርእስ ይህን የመዝናኛ ፕሮግራም አስታወሰኛና ነው በዚህ የጀመርሁት እንጂ የዚህ ጽሁፍ አላማ ስለእስማማለሁ አልስማማም ለመናገር አይደለም። 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት ተከትሎ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት መልስ ውስጥ ስለማህበረ ቅዱሳን በተናገሩት ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ይገኛል፡፡ የማህበረ ቅዱሳን አክራሪ አካሄድ ሰለባ የሆኑ ብዙዎች የማህበሩ ማንነት ይፋ እየወጣ መሆኑ ደስ ያሰኛቸው ሲሆን፣ በማህበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊዎች ዘንድ ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ብዙም አልተወደደም። ተቃውሟቸውን በየድረገጹ መግለጽ ቀጥለዋል። ለምሳሌ አንድ አድርገን ድረገጽ ሚያዝያ 10 ቀን “ይህ የግሌ አስተያየት ነው ፤ የማንም አቋም አይደለም” በሚል ርእስ ፖስት ያደረገውን፣ እንዲሁም በዚህ ጽሁፍ የምንመለከተውን የኤፍሬም እሸቴን ጽሁፎች መጥቀስ ይቻላል።

የማኅበሩ አባል የሆነው ኤፍሬም እሸቴ በጽሁፉ ማህበረ ቅዱሳንን ለመከላከል ሞክሯል። ኤፍሬም በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነጋገር አለመስማማቱን ከንግግራቸው የሚከተለውን ጠቅሷል “‘ጥምቀት ላይ ከነበሩት መፈክሮች አንዱ ‘አንድ  አገር - አንድ ሃይማኖት’ የሚል ነው። …. ‘አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት’ የሚል ሕገ መንግሥት የለንም። (መፈክሩ) … የክርስቲያን መንግሥት እንዲኖር የሚፈልጉ … እንዳሉ ያሳየናል’ ብለዋል - ጠ/ሚኒስትሩ ‘የዚህም መነሻው የግንዛቤ ማነሥ በመሆኑ በማስተማር የሚመለሱ ናቸው”ሲሉ አክለዋል።” ከዚህ ውስጥ “አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት” የሚለውን በመምዘዝ አሜሪካ የሚኖረው ኤፍሬም እሸቴ ግን ይህን የጠቅላይ ሚኒስትሩን አነጋገር ውድቅ በማድረግና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በማስደገፍ፣ “ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን እና የጥምቀት አክባሪ ክርስቲያኖች በቲ-ሸርቶቻቸው ላይ አትመውት በፎቶግራፍ የተመለከትኩት ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ኤፌሶን መልእክ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ የጻፈው “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የሚለው ሐዋርያዊ ቃል ነው። ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል እንጂ የጥምቀት አክባሪዎቹ የፈለሰፉት አይደለም። በዚህ የሐዋርያው ቃል ውስጥ ያለው “አንድ ሃይማኖት” የሚለው አገላለጽ የሚናገረው ስለ ክርስትና ሃይማኖት ነው። ሌሎች እምነቶች የሉም፣ መኖርም የለባቸው የሚል የጨፍላቂነት ትምህርት አለመሆኑን ሊቃውንቱ አምልተው አስፍተው ሲያስተምሩ ኖረዋል፤ እያስተማሩም ነው።አሁን ደርሶ የሚለወጥ ነገር የለም።” ብሏል።

በእርግጥ ኤፍሬም ነገሩን አቅልሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሊሸፋፍነው ሞከረ እንጂ በጥቅሱ ሽፋንነት ሲራገብ የኖረው ከእኛ በቀር እዚች አገር ላይ ሌላ ሃይማኖት ለምን ይኖራል? የሚል ጠባብና ኢክርስቲያናዊ አስተሳሰብ ነው። በዚህ አመለካከት በተቃኙ አንዳንድ አክራሪዎች የተደበደቡ፣ የተገደሉ፣ ቤታቸው የተቃጠለ፣ የቀብር ቦታ የተነፈጉ፣ ከተቀበሩበት አስከሬናቸው እየወጣ የተጣለባቸውና የመሳሰለው ጥቃት የተፈጸመባቸውን ቤቱ ይቁጠረው። እንደዚህ አይነት ኢሰብአዊና ኢሃይማኖታዊ ተግባርን አንዳንድ ሙስሊም አክራሪዎችም በኦርቶዶክሶችና በፕሮቴስታንቶች ላይ ሲፈጽሙ ተስተውሏል።

በአንዳንድ አክራሪ ቡድኖች በኦርቶዶክሶች መካከል እየደረሰ ያለውን ብዙውን ጥቃት እያደረሱ ያሉት የማህበረ ቅዱሳን አባላትና የማኅበሩ ጠባብና አክራሪ አመለካከት ሰለባ የሆኑ አንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች፣ ለምሳሌ መንግስትንና ሃይማኖትን መለየት የተሳናቸው አንዳንድ የማህበሩ አባላት የሆኑ የፖሊስ አባላት፣ አቃቤ ሕጎች፣ አመራሮችና የመሳሰሉት ጭምር ተባባሪ እንደሆኑ ብዙዎች ይናገራሉ። ተሀድሶ ወይም መናፍቅ ነው ብሎ ማህበሩ የፈረጃቸውን የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ አንዳንድ ቦታዎች ላይ አሁንም አልቆመም። በተለይ ጥቃቱ ተባብሶ ያለው ከአዲስ አበባ ርቀው በሚገኙ የክፍለ ሀገር ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች ነው። በእነዚህ አካባቢዎች በእምነት ምክንያት የብዙ ሰዎች ሰብአዊ መብት እየተጣሰ፣ ብዙዎች በግፍ እየታሰሩ ድብደባ እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ ይታወቃል። ይህን እያደረጉ ያሉት መንግስት የጣለባቸውን ሀላፊነት ወደ ጎን ጥለው የማህበረ ቅዱሳንን አጀንዳ እያስፈጸሙ ያሉ እነዚሁ ግለሰቦች ናቸው። ይህ በኦርቶዶክስ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሙስሊም አክራሪዎች ዘንድም የታየ ነው። ከጅማው ጭፍጨፋ በስተጀርባ የአክራሪዎች አመለካከት ሰለባ የሆኑ የመንግስት ሹመኞች የሆኑ ግለሰቦች እንደነበሩ በጊዜው ከመገናኛ ብዙሃን አድምጠናል።
   
ስለዚህ ሊቃውንቱ ስለ አንድ ሃይማኖት ሲያስተምሩ “ሌሎች እምነቶች የሉም፣ መኖርም የለባቸው የሚል የጨፍላቂነት ትምህርት እንዳልሆነ የገለጸው እውነት ቢሆንም፣ በማህበረ ቅዱሳን አክራሪ አመለካከት ስር የወደቁት ግን የሚያስቡትና የሚኖሩት ተቃራኒውን ነው። ለምሳሌ በአንዳንድ አክራሪ ሙስሊሞች የተካሄደውን የጅማውን ጭፍጨፋ ተከትሎ “ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት” የሚል መፈክር ተስተጋብቶ እንደነበር ይታወሳል። ይህ አባባል የኖረና የቀደመችውን ኢትዮጵያ የሚገልጽ ነው። አሁን ላለችው ኢትዮጵያ ግን የሚያስኬድ ሆኖ አይታይም። በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆኑ ሙስሊሞችና ሌሎች ሃይማኖቶችም የሚኖሩባት ስለሆነች በእኔ ግምት ጊዜውን ያገናዘበ አባባል መስሎ አይታየኝም። ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ሊያስከፋና ወዳልተፈለገ ውዝግብ ውስጥ ሊጨምር የሚችል ነውና ሁሉም በነጻነትና የሌላውን መብት በማክበር ሃይማኖቱን ሊያስፋፋ መብት እንዳለው ሊታወቅ ይገባል።

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮት የእግዚአብሔር ሀሳብ ሃይማኖቶች ሁሉ በአንድ ሃይማኖት ስር እንዲጠቃለሉ አይደለም። በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት የሚያምኑት ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኙ ነው። የወደፊት እቅዱም ሃይማኖቶችን ሁሉ በአንድ ሃይማኖት ስር ለመጠቅለል እንዳልሆነ ቅዱሱ መጽሐፍ ይመሰክራል በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።” (ኤፌ. 1፡10)።
ከኢየሱስ ክርስቶስ የተማርነው የክርስትናን ሃይማኖት ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ሌሎችን ማሳደድ፣ መከራቸውን ማብዛትና በሀይል ማስገደድ፣ በሌሎች ላይም የበላይነትን እንድናሳይ አይደለም። ሰዎች በክርስቶስ ወንጌል አምነው ወደ ክርስትና እንዲጨመሩ በክርስቶስ የመስቀል ላይ ፍቅርና በበጎ ምግባራችን እንድንማርክ ነው። የማህበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቂያ ስልቱ ክርስቶስ ካስተማረውና ሀዋርያት ካሳዩት ፈጽሞ የተለየ ወይም ተቃራኒ ነው። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት ጥቅስ ቃል በቃል ያሰፈረ ቲሸርት ኤፍሬም እሸቴ በሰበሰባቸው ፎቶዎች ውስጥ ሊያገኝ አለመቻሉ ከላይ የተገለጸው ኢክርስቲያናዊ አክራሪ አመለካከት የለም ሊያሰኝ አይችልም። ስለዚህ ጉዳይ አሜሪካ የሚኖረው ኤፍሬም እሸቴ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉና ለነገሩ ቅርብ የሆኑ ቢናገሩ የተሻለ ነው። 
-----------
ኤፍሬም እሸቴ ይቀጥልና “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እግረ መንገዳቸውን ያነሱትን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ‘አክራሪነት’ በክርስቲያኑ በኩል ‘ይወክልልናል’ ብለው የጠቀሱትን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ እኔም እንደ አንድ አባል የማምንበት አቀርባለኹ። ማኅበሩ በኃላፊዎቹ በኩል የሚሰጠው መልስ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሁለት አሥር ዓመታት አባል የሆንኩበት እና መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት በሁሉም ዘንድ የተመሰከረለት ማኅበር “አክራሪ” አለመሆኑን በግሌ ለመመስከር እገደዳለኹ።” ብሏል። አሁንም ኤፍሬም ስለ ማህበርህ አንተ ሳትሆን ሌላው ቢመሰክር የተሻለ ነው። ትልቁ ስህተትህ “በሁሉም  ዘንድ የተመሰከረለት” ብለህ ማህበርህን ፍጹምና እንከን የለሽ ማድረግህ ነው። ለአንተ የሚታዩህ አንተ “መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶች” ያልካቸው በሌሎች ዘንድ የሚታዩት በሌላ መልክ ነው። ይህም እንዲሁ ከጭፍን ጥላቻ የመነጨ ሳይሆን በማስረጃዎች የተረጋገጠ ነው። ለምሳሌ አንተ መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎት ይሰጣል የምትለው ማቅ ከማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ውጪ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀው አትራፊ ነጋዴ ሆኖ ነው። በቤተክርስቲያን ስም ይነግዳል፤ ለቤተክርስቲያን የሚያደርገው ፈሰስ የለም። ቤተክርስቲያን ሀብትህንና ምንጩን ልወቅ ስትለው እንኳ ለማሳየት ፈቃደኛ አይደለም። የመንፈሳዊነት አንዱ መገለጫ ጥብቅና ቆሞላታል ላልካት ቤተክርስቲያን መታዘዝ አይደለምን? ማቅ ግን እስከዛሬ የሚታወቀው ለቤተክርስቲያን ባለመታዘዝ ነው። ይህን ለመሸፈን ግን ብዙ ጊዜ የቤተክርስቲያኗን አባቶች ስም በማጉደፍ ስራ ይጠመዳል።
-----------
ማኅበሩ አገርንም ሆነ ፖለቲካን፣ ሌሎች እምነቶችንም ሆነ ተቻችሎ መኖርን በተመለከተ ከማንም በላይ በሰፊው በሰለ እና ጤናማ ሆነ መንገድ ሐሳቡን አስተጋብቷል። ስለዚህም የማኅበረ ቅዱሳን አቋም ጥምቀት ላይ የወጡ ጥቂት ሰዎች ይዘዋቸው ነበር በተባሉ መፈክሮች የሚገለጽ አይደለም።” ላልከው

ማቅ እንዲህ ያለ ማንነት ያለው ማህበር አይደለም። ደግሜ እላለሁ፣ ማቅ እንዲህ ያለ ማንነት ያለው ማህበር አይደለም። አንተ ነው ካልክ ግን የማህበሩ ጭፍን አፍቃሪ ነህ። ተቻችሎ መኖር ማለት ፈጽሞ ያልገባህ አክራሪ ነህ ማለት ነው። የማቅ እጅ ከፖለቲካ የጸዳ አለመሆኑ በተለያዩ ጊዜያት የተረጋገጠ እውነት ነው። አባ ሠረቀ በማህበሩ ላይ ካቀረቡት አንዱ ክስ ማህበሩ በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ ይገባል የሚል ነው። መንግስትም በማኅበሩ ላይ እንዲህ ሊናገር የቻለው በዚህ ምክንያት እንደሆነ ይገመታል። ከሌሎች እምነቶች ጋር ተቻችሎ ስለመኖር በበሰለና ጤናማ በሆነ መንገድ ሐሳቡን አስተጋብቷል ያልከው ግን ማንንም የማያሳምን ውሸት ነው። እንዲያውም ማቅ የሚታወቀው እኔ ብቻ ፍጹም ነኝ በማለትና ሌላውን በመኮነን ነው። ቤተክርስቲያን ውክልና ሳትሰጠው ቤተክርስቲያንን በመጠበቅ ስም በቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ሌት ተቀን እያደረሰ ያለው ወከባና ስደት እንኳን ከሌሎች ጋር ከቤተክርስቲያን ልጆች ጋርም ተቻችሎ መኖር እንዳልቻለና “ተቻችሎ መኖር” የሚለው መርህ በእርሱ መንደር እንዳላላፈ የሚያስረዳ ነው። 

በየጋዜጣውና በየመጽሔቱ ሲያወጣ የኖረው ተቻችሎ ስለመኖር ሳይሆን የራስን የበላይነት የሌላውን የበታችነት የሚያንጸባርቁ ሀሳቦችን ናቸው። የቤተክርስቲያንን መዋቅር ባልተከተለ መንገድ የሰዎችን ስም አለአግባብ እያነሳ ሲሳደብና በዚህ ምክንያት የጋዜጣ/የመጽሔቱ አዘጋጆች ተከሰው ሲፈረድባቸው ተመልክተናል። ለምሳሌ ከዚህ ቀደም በስምአ ጽድቅ ጋዜጣ የወጣውና “የገሃነም ደጆች” የተሰኘው ጥናት ተብዬ ጽሁፍ ስለመቻቻል የሚያወራ ነው? የክርስትና ክፍሎች የሆኑትን የካቶሊክና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትን እንያንኳሰሰ ኦርቶዶክስን እየኮፈሰ የሚናገርና ዳንኤል ክብረትን ለእስር በመዳረግ የዘራውን ያህል ባይሆንም በጥቂቱ ያሳጨደ ጽንፈኛ ጽሁፍ አይደለምን? ነው ወይስ አሜሪካ እየኖርክ መቻቻል የሚለው ቃል ገና አልገባህም። ኤፍሬም እስኪ በእውነት ህሊናዊ መልስ ስጥ የገሃነም ደጆች መቻቻል ሳይሆን ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚል አክራሪ ጽሁፍ አይደለምን?
--------------
ሌላው ኤፍሬም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር አልስማማም ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ከአክራሪነት ጋር የተገናኘበትን አስተሳሰብ ምንጭ መንግስት መረዳት አለበት በሚል ነው። እንደእርሱ አመለካከት ማህበረ ቅዱሳን አክራሪ ነው ለሚለው አስተሳሰብ ምንጩ “ቤተ ክርስቲያናችንን የእርሷ ባልሆነ ትምህርት እና እምነት ለመለወጥ የሚሞክሩ ነገር ግን ይህንን እንዳናደርግ ማኅበረ ቅዱሳን እንቅፋት ሆኖብናል የሚሉ አካላት (ተሐድሶዎች) ለረዥም ዘመን ሲያሰሙት የቆዩት ክስ ነው።እንግዲህ በኦርቶዶክሳውያን እና በተሐድሶዎቹ መካከል ሲደረግ የቆየ ትግል አዲስ ምዕራፍ የሚያገኘው እነዚህ ኦርቶዶክስን ለመከለስ (ለማደስ) የሚፈልጉ ሰዎች “በፖለቲካው ጉያ ምቹ ቦታ ባገኘን” የሚለው ሙከራቸው ተሳክቶ በራሱ በመንግሥት ስም ዓላማቸውን ማራመድ ከጀመሩ ነው።” 

እርግጥ ነው ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ መሆኑን ከሁሉ ቀድመው ያወቁት የቤተክርስቲያን ልጆች ናቸው። ይህን ስም የሰጡት ኤፍሬም እንዳለው ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ጥብቅና ስለ ቆመ ጠልተውት አይደለም። የቤተክርስቲያንን እውነተኛ ትምህርት ከተሳሳተ ትምህርት ሳይለይ ወንጌልና ተአምረ ማርያም እኩል ናቸው የሚል አይነት አመለካከት ስለሚያራምድና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በልማድና በወግ ደረጃ የሚመለከቱትን ትውፊት ሁሉ ወደመንግስተ ሰማያት መግቢያ ነው ብሎ ስለሚያምንና ስለሚያስተምር ነው። በተጨማሪም እምነቱን በስብከት ሳይሆን በሀይል፣ በማስፈራራትና በማሸማቀቅ ስለሚያስፋፋ ነው። ለዚህ እኩይ ግብሩ እንደ ኤፍሬም ባሉ የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎች የሚሰጠው ስም ግን ቅዱስ ነው። ሌሎችም አክራሪ ያሰኙት ብዙ ማንነቶች አሉት። ጠቅላይ ሚንስትር ማህበረ ቅዱሳንን አክራሪ ያሉት ግን ከእነዚህ ከብዙዎቹ ነጥቦች አንጻር እንዳይደለ ኤፍሬምም የሚጠፋው አይመስለኝም። ከፖለቲካና በሃይማኖት መካከል መቻቻል እንዳይኖር እየሰራ ካለው አደገኛ ሥራ አንጻር ነው። ይሁን እንጂ ይህን እውነት ክዶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ “አክራሪ” የሚለውን ስም ተሀድሶዎች ናቸው የነገሯቸው ማለት ግን የማይመስል ነገር ነው። ስለዚህ ተሀድሶዎች ያሉትን ሰምተው ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅን አክራሪ ያሉት የሚለው መከራከሪያ ከገለባ የቀለለ ነው።   

ኤፍሬም ይቀጥልና “ከነዚህም አብዛኞቹ የኢሕአዴግ የፖለቲካ መስመር ደጋፊዎች በመምሰል(በተለይም ከ1997 ዓመተ ምሕረቱ ምርጫ - ምርጫ ’97) እና ውዝግቡ ጀምሮ ማኅበረ ቅዱሳን ለቅንጅት ማሸነፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል በማለት በመንግሥት ልምጭ የራሳቸውን ዱላ ለማሳረፍ በብዙ ሲጥሩ እንደነበር ይታወቃል። በይፋም ጽፈዋል። የጠ/ሚኒስትሩ አጭርና ብዙ መልእክት የተሸከመች ዐረፍተ ነገር እነዚያ መንግሥትን ተገን አድርገው ቤተ ክርስቲያኒቱን ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች/ ተሐድሶዎች መንግሥትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተሳካላቸው ማለት ነው? የሚል ስሜት ያጭራል።’” ይላል።

በምርጫ 97 ወቅት ኤፍሬም የት ነበረ? ማህበሩ በምርጫው ወቅት የነበረውን ሚና  በተመለከተ መንግስት በራሱ የደህንነት አባላት የደረሰበትና ያረጋገጠው እውነታ እንጂ ተሀድሶዎች መንግስትን አሳስተው “በመንግስት ልምጭ የራሳቸውን ዱላ ለማሳረፍ” ባደረጉት ጥረት የተገኘ ድል አይደለም። ማህበሩ ጊዜና አጋጣሚዎችን እየጠበቀ ፖለቲካዊ አቋሙን እንደሚያራምድ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው። ከሰሞኑ በዋልድባ ገዳም ዙሪያ እንኳ እየሆነ ያለውን መመልከት ይቻላል። ጥያቄውና ተቃውሞው ለገዳሙ ከመቆርቆር ብቻ የመነጨ እንዳይደለና አጋጣሚውን ፖለቲካዊ ድል ለማግኘት የማህበሩ ስውር አመራሮች አየተጠቀሙበት እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው።

እርግጥ ተሀድሶ የምትላቸው ወገኖች አንተ በምትለው መልኩ የሉም። ቤተክርስቲያኗን ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ የያዙት አጀንዳም የለም። ይህ አንተና መሰሎችህ እድሜያችሁን ለማራዘም የምትጠቀሙበት ስልት ነው። ስለዚህ ጉዳይ ካልተናገራችሁ ተቀባይ የምታገኙ አይመስላችሁም። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አነጋገር ተሀድሶ የምትላቸው ወገኖች መንግስትን መጠቀሚያ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተሳካላቸው ማለት ነው የሚለው ስጋትህ ግን አስገራሚ ነው። በአንድ በኩል ቤተ ክርስቲያኗ ያለማኅበረ ቅዱሳን ፕሮቴስታንት ትሆናለች ማለት ነው። ይህ ጥንታዊቷን ቤተክርስቲያን እዚህ ያደረሳት ከዛሬ 20 አመት በፊት የተመሰረተው ማኅበረ ቅዱሳን ነው የሚል ትእቢት ያዘለ አነጋገር ነው። ቤተክርስቲያኗ ያለ ማኅበረ ቅዱሳን ነበረች፤ ወደፊትም ያለማኅበረ ቅዱሳን ትኖራለች። ስለዚህ ኤፍሬም ሆይ አንተና ማኅበርህ ስጋት አይግባችሁ። እንዳልኩህ ማህበረ ቅዱሳን ከመንገድ ሊቀር ይችላል። በቤተክርስቲያን ስም የሚያካሂደው ንግድና ፖለቲካ ይቆም ይሆናል። ቤተክርስቲያን ግን ምንም አትሆንም።
--------------
በመቀጠልም “ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ የወጣ እምነት ይዘው ቤተ ክርስቲያኒቱን እና ትምህርቷን በመለወጥ የራሳቸው ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች፣ ቡድኖች እና ድርጅቶች መኖራቸው እየታወቀ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እና በዕውቀቱ ለቤተ ክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን ለአገሩም በቅንነት የሚያገለግለውን አንድ ትውልድ ጨፍልቆ በአክራሪነት ስም መፈረጅ በቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውና ላይ ትልቅ የሚዛን መናጋት ያስከትላል ብዬ በድፍረት መናገር እችላለኹ። ተሐድሶዎቹም ሆኑ ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቀቃኞች ዓላማችንን ሊያውቅብን ይችላል የሚሉትን ማኅበር ሕጋዊ አገልግሎት ያለ አግባብ ሌላ ስም መስጠት ይህንን ቃል እንደ መመሪያ ወስደው የግል ፍላጎታቸውን ለመፈጸም ለሚቋምጡ ወገኖች ትልቅ ደስታ ነው።” ላልከው
በመሰረቱ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ እንጂ የማንም አይደለችም። አንተና መሰሎችህ የማቅ አባላት ግን የእኛ ናት ብላችሁ ታስባላችሁ። ለዚህም ነው የክርስቶስ የሆነችውን ቤተክርስቲያን የራሳቸው ለማድረግ የሚያስቡ ቡድኖችና ድርጅቶች አሉ ያልከው። እናንተ ለርእዮተ አለማችሁ ተገዢ ያልሆነውን ሁሉ ስም እየሰጣችሁ ከቤተክርስቲያን ማሳደዳችሁ በአንድ በኩል ቤተክርስቲያኗ የእኛ እንጂ የሌላ አይደለችም ከሚል ስጋዊ አስተሳሰብ የመነጨ እንደሆነም ይታወቃል። ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ናት። አንተ በሄድክበት ስሌት መሰረት እንሂድ ከተባለም ቤተክርስቲያኗ የእናንተ ብቻ ሳትሆን የእኛም ናት።
ማቅን በሁለት ከፍሎ ማየት ተገቢ ነው። ለቤተክርስቲያናቸው በቅንነት እያሰቡ በእውቀታቸውና በገንዘባቸው የሚያገለግሉ አባላት አሉ። እነዚህ አባላት ማቅን ላይ ላዩን እንጂ በስውር እያደረገ ያለውን ንግድና ፖለቲካ ልብ አይሉትም። ኤፍሬም በዚህ ጽሁፍ ለማድረግ የሞከረው በአንድ በኩል የእነዚህ የማቅ ተከታዮች ልብ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከማኅበረ ቅዱሳን ላይ እንዳይነሳና ከማኅበሩ እንዳይለዩ ለማድረግ ነው። እነዚህ የዋሃን አባላት እያደረጉ ያለውን መልካም ነገር የሚያደርጉት ለማኅበሩ ሳይሆን ለቤተክርስቲያን እስከ ሆነ ድረስ ወደፊትም አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል። የሚያደርጉትን ሁሉ የሚያደርጉት ለማኅበረ ቅዱሳን ብለው ከሆነ ግን ያ ሌላ ጉዳይ ነው። ታዲያ በየት በኩል ነው ማቅን እንደ ማቅ አክራሪ ነው ማለት በቤተ ክርስቲያ ህልውና ላይ ትልቅ የሚዛን መናጋት ሊያስከትል ይችላል ብለህ ደፍረህ የተናገርከው? እንደ እውነቱ ከሆነ በቤተክርስቲያኗ ላይ ሳይሆን በራሱ በማቅ ላይ ነው መናጋት ሊደርስ የሚችለው። ምክንያቱም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር አስተውለኸው ከሆነ፣ ይህን ስራ እየሰሩ ያሉት ጥቂቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል። አብዛኞቹ በማቅ ተሰብከው የአክራሪ አስተሳሰብ ሰለባ የሆኑት  የማቅ አባላትና ደጋፊዎች በትምህርት ሊቃኑ የሚችሉ ናቸው ብለዋል። ስለዚህ ከላይ ሆናችሁ በቤተክርስቲያኗ ስም ልዩ ልዩ ነገሮችን በመዘወር እኛ ከሌለን ቤተክርስቲያኗ ፕሮቴስታንት ትሆናለች ለሚለው የሞኝ ዘፈናችሁ የሚያጨበጭብ የለም። 
   
በመጨረሻም እንዲህ ብለሃል “የአክራሪነትን ምንነት ለመረዳት ሰፕቴምበር 11ን፣ የሎንዶኑን የባቡር ጣቢያ ፍንዳታ፣ የጅማውን ጭፍጨፋ፣ የኒው ዴልሒን የሽብር አደጋ፣ አል-ሸባብ በየጊዜው በሶማሊያ የሚፈጽመውን መመልከት ያስፈልጋል። ትርጉሙና ምንነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ያለቦታው ይህንን ቃል መጠቀም ሕዝቡ ቃሉ ያዘለውን ቁም ነገር እንዳይረዳ ከሚያደርገው በስተቀር ውጪ ሌላ ምንም ጥቅም የለውም።”

መቼም አሜሪካ ተቀምጠህ እንዲህ ብትል አይፈረድብህም። ማቅ ቦንብ ታጥቆ አጥፍቶ ወደ መጥፋት አልተሸጋገረም እንጂ በሃይማኖት ለበስ ውንጀላው ስንቱን የቤተክርስቲያን ልጅ እያሸበረና ተሀድሶ የሚል ስም እየሰጠ ከቤተክርስቲያን እንዳስባረረ የደረሰበት ብቻ ነው የሚያውቀው። ለምሳሌ በ1997 ዓ.ም  ሞጣ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነበሩ 21 የሚሆኑ የቆሎ ተማሪዎችን ተሀድሶ ሆናችኋል በሚል ከቤተክርስቲያን እንዲባረሩ ያደረገው የማቅ ወኪል የሆነው ሻውል የሚባልና ሌሎች ግብረአበሮቹ ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች ከሚኖሩበት ጎጆ እንዲለቁ የተደረገው በሀይል ሲሆን በሕይወታቸው ላይም ትልቅ ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል። እስከ መታሰርም የደረሱ ነበሩ። ከዚያም በከተማው ውስጥ ማንም እንዳያስጠጋቸው፣ ሙስሊሞች ጭምር ቤታቸውን እንዳያከራዩአቸው፣ ቤተሰቦቻቸውም እንዳይቀበሏቸውና ቢቀበሏቸው ግን ከማኅበረሰቡ እንደሚገለሉ በማስፈራራት ጭምር ብዙ መከራ አድርሰውባቸዋል። ይህ ምስክርነት እውነተኛ ነው። ለኤፍሬምና ለመሰሎቹ ግን ቤተክርስቲያንን መጠበቅ ተደርጎ እንደሚወሰድ አያጠራጥርም። በማንም አይን ግን ትልቅ አክራሪነትና አሸባሪነት ነው። በዚህ አይነት ብዙ መከራና ችግር የደረሰባቸውን በተለይም በሰሜኑ የአገራችን ክፍል እየሆነ ያለውን ቤቱ ይቁጠረው።

ይህን ወደጎን ብለህ “በርግጥ ገዳማትንና አብነት ት/ቤቶችን ከጥፋት መታደግ አክራሪነት ነውን?... በጭራሽ!!! ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ማኅበሩ ባሉት ሐሳብ አልስማማም።” ብለሃል። እናንተ ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤትን መታደግ የምትሉት ለጥቅማችሁ ነው እንጂ ለቤተክርስቲያን በመቆርቆር እንዳልሆነ ከላይ የቀረበው ምስክርነት በቂ ማስረጃ ነው። ስለዚህ ማኅበሩ አክራሪና አሸባሪ መሆኑን ከማንም በላይ እኛ እናውቀዋለን። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስክርነትም አያሻንም። ስለዚህ ኤፍሬም “ባንከሩ” በሰጠህ አክራሪ የሚል ስምና /ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት ትስማማለህ አትስማማም?

መሪጌታ ደመላሽ ዘሞጣ
ምንጭ፡- አባ ሰላማ

7 comments:

  1. betam yemetgerm neh (yasafhew sew) le mehonu ante orthodox neh? ena gin atmeselegnem. lemen meseleh yesafkew hulu selematakew neger new. le menkef ke metechekul lemen mahberun kerbeh mejemeria atakewem selematakew neger antem tesasteh lelochin lemasasat atchekul. degmos yetgnaw ye mesehaf kidus kefele negroh new ante endih new endae new eyalk ye metsefew please ye hone gropu degafi athun... ye kirstos teketaye hun enji... egziabher lib yestachihu..

    ReplyDelete
  2. መሪጌታ ደመላሽ ዘሞጣ ሳትሆን ዘጣሞ ብዬሃለሁ። ወይ ተሃዶሶ ወይ ቅባት መሆንህን እርግጠኛ ነኝ። ዘጣሞ ያልክሁም ለዚህ ነው። እኔ የማ/ቅ አባል አይደለሁም። ነገር ግን ጠ/ሚ ያሉት አባባል በፍጹም የተሳሳተ መሆኑን ምንም መላ ምት አያሻውም። ጠ/ሚ ማ/ቅ አክራሪ እንዳልሆነ አፋቸው ሳይሆን ልባቸው ጠንቅቆ ያውቀዋል። ጠ/ሚሩ "አክራሪ" የሚለውን ቃል "አንዳ አንድ የማ/ቅ አባላት" በሚለው ሃረጋቸው ከማ/ቅ ጋር ለማዘመድ የተጠቀሙበት በራሳቸው እሳቤ በቂ የሆኑ ፖለቲካዊና ጥቅማዊ ምክንያቶች ሰለአሏቸው ነው። ምክንያቶች በትንሹ አምስት ናቸው።
    ፩ በዋልድባ ጉዳይ የማ/ቅ አጣሪ ቡድን ዕውነትን ይዞ ብቅ እንዳይል ማስፈራራት፤
    ፪ ደጋፊዬ ናቸው የሚሏቸውን የእስላምና ክፍሎችና አብላት ለላማስከፋት - ከእነሱ እምነት ተከታዮች ብቻ አክራሪ እንዳልተባሉና በማ/ቅ ስም ክርስቲየኖችንም በማካተት በተነፃፃሪነት ማሳየት፤
    ፫ ማ/ቅ በሰፊው ምዕመን ዘንድ ያለውን ቀና እሳቤ ማዛባትና ጥላሸት በመቀባት ከኢሕአዲግ ውጭ ማንኛውም አካል የገዘፈ ስምና ዝና እንዳይኖረው፤
    ፬ ማ/ቅ ለቤ/ያን አስተምሮ ሳይሆን ለመንግስትና ለአባ ጳውሎስ ተገዢ እንዲሆን ያለዚያ በአክራሪነት ስም ያሻቸውን ለማድረግ መንገድ ሲያመቻቹና፤ ወያኔ/ኢሕአዲግ በቤ/ያን ላይ ያለውን ድብቅ ዓላማ በመፈፀም ላይ ማ/ቅ ይህን ድብቅ አላማ አውቆትም ሆነ ሳያውቀው ማህበሩ ከተመሠረተለት ዓላማ አንፃር የወያኔው ድብቅ ዓላማ ተፈፃሚነት ላይ በተጠናከረ መልኩ ማህበሩ አስጊ ሆኖ ከቀጠለ ማህበሩን ለማፈን ወይም ለማደከም ያለዚያም ማስወገድ እንዲቻል ከአሁኑ ምክንያት ለማበጀትና ለበኋላ ዜና ፍጆታ ስንቅ ለመሰነቅና
    ፭ በቤተ ክህነትና በመንግስት ውስጥ ያሉ ከኑፋቄ እስከ ንዋይ፣ ከዝና እስከ ስልጣን የመሳሰሉትን ዓለማዊ ፍላጎቶችን ያአነገቡ ቡድኖችንና ግለሰቦችን ነገር ግን "አፍቃሬ ወያኔ/ኢሕአዲግ" በመምሰል ያን ፍላጉታቸው ለማሳካት ሌት ተቀን የሚባዝኑ "አፍቃሬዎቻቸውን" ፍላጉት ባለማጎደል እነዚህ ቡድኖችና ግለሰቦች በአፍቃሬ ወያኔ/ኢሕአዲግነታቸው እንዲበረቱና ሲጠሯቸው አቤት ሲልኳቸው ወዴት በሚለው ታዛዠነታቸው እንዲቀጥሉ ጉልበት ለመሰጠት ነው።
    ይህን እርካሽ የጠ/ሚሩን ንግግር በመጠቀም ማ/ቅንን ማጥቃትህ በወኑ አንተ የቤ/ያን ሰው ነህን? በወኑ አንተ የቤ/ያን ሰው ነኝ ለማለትስ ምን አይነት የህሊና ብቃት አገኘህ? ለነገሩ የህሊና ብቃት ቢኖርህ ኑሮ ይህን የመሰለ ርካሽና የጥላቻ ሃሳብና ባላንጻባረቅህ ለጠ/ሚሩም ንግግር የገደል ማሚቶ ባልሆነህ ነበር። ምን እላለሁ? ህሊናህን የሚፈርድ ህሊና የቤ/ያን አምላክ ይስጥህ!

    ReplyDelete
  3. Comment yemiset tefa aydel? Lol

    ReplyDelete
  4. Comment yemiset tefa aydel? Lol

    ReplyDelete
  5. Betam yemtgerm achiberbari menafkneh yastawukebhal kemengist lemeletef timokiralh neger aketatay leba neh stop ur critics towards mahber kidusan ! Come learn from m.k eotc.

    ReplyDelete
  6. The article does not worth comment, there is nothing in it to comment for use or improvement. It is simply collection or words and sentences. Minew merigeta kene betim yewalu ayidelumin? Tadya endih yale lifisfis anegager keyet temarut; Abatewo Kidus Yared endih alneberem! Ereyitewu endiaw beziyaw bekine maheletu bizemu yishalal; yihegnaw lerersewo tesmami ayidelemena yitewet! Meregeyta menkefena kelijoch gar menekakes ayamirebetim!!!

    ReplyDelete
  7. Ereyitewu meregeta! ስለዚህ ማኅበሩ አክራሪና አሸባሪ መሆኑን ከማንም በላይ እኛ እናውቀዋለን። Enante eneman nachihu antuye? Ere kitifet, ersewom endih yale kit yata neger yinageralu ende? Ere ere ere... truely, ayimetinewotim!11

    ReplyDelete