Monday, April 23, 2012

ገደል አፋፍ ላይ የቆመ ጎረምሳ ማኀበርን ለማዳን

          Click here to read in PDF                                                          በበከመምህረትከ
       በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማህበራት መካከል አንዱ ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ማህበሩ ከተመሰረተ ሁለት አስርተ አመታትን ጨርሶ እነሆ ጉርምስናውን ተያይዞታል፡፡ ይሁንና ማህበሩ በተለይ ባለፉት ጥቂት አመታት ባልሆነ መስመር ሄዶ ሄዶ ከገደል አፋፍ ላይ ተንገራግጮ ቆሟል፡፡ ወደኋላ ተመልሶ ያለበትን ችግር በጥልቀት መርምሮ የሚሄድበት መስመር ካላስተካከለና በጀመረው መንገድ ከቀጠል ባጭር ጊዜ ውስጥ ወደገደል መግባቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡ እንደውጭ ተመልካች ገደል ሲገባ ዝም ብሎ ከማየት እንደ አንድ የቤተክርስቲያን አባል (እና የቀድሞ የማህበሩ አባል) እንዲሁም በፊት በፊት በሰራቸው መልካም ስራዎች አንጻር ችግሮቹን ፈቶ ወደ ቀደመ ክብሩ ይመለስ ዘንድ የመፍትሄ ሃሳቤን ለማቅረብ ወደድኩ፡፡ ማህበሩ 20 አመት ልደቱን ሲያከብር አገር ሰላም ነው ብሎ ሻማ ለኩሶ ኬኩን በመቁረስ ብቻ ሳይሆን ያለበትን አደጋ አስተውሎ ራሱን ይመረምርና መስመሩን ያስተካክል ዘንድ ይጠቅመዋል፡፡ ያን ካደረገ ደሞ ገደል ከመግባት ይተርፍና ካለበት የጉርምስና ጠባይና እድሜ ተሻግሮ ወደ ጉልምስናና እር እንዲደርስ ይረዳዋል፡፡
  
       አንዳንዶች ማህበሩ በስራው የቅዱሳን ስም አርክሷል፤ ለቤተክርሰቲያኒቱ እዳ ሆኗል፤ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ በዝቷልና መዘጋት አለበት የሚል አቋም ሲያራምዱ ይስተዋላል፡፡ እኔ ግን ምንም እንኳን በጥፋት ጎዳና ቢሄድም ተስተካክሎ ለቤተክርስቲያን እንዲያገልግል መደረግ አለበት እንጂ ፈጽሞ ሊዘጋ አይገባውም የሚል አቋም አለኝ፡፡ የማህበሩ አመራር አባላትም መንግሰትና ፓትሪያርኩ ሊዘጉን ነው ሊያጠፉን ነው የሚል ፍራቻ እንዳላቸው በውስጥ አዋቂዎች ተነግሯል፡፡ ይሁንና እንዲቀጥልም ሆነ እንዲዘጋም የሚያደርገው ራሱ ማህበሩ ነው እንጂ ፓትሪያርኩ ወይም መንግሰት አይደለም፡፡ የመቀጠል ዋስትናው ደሞ ያለበትን ችግር በመፍታት የተበላሸ አካሄዱን ማስተካከል ብቻ ነው፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ከቆመበት የገደል አፋፍ ሊመልሱት የሚችሉ ዋና ዋና የመፍትሄ ሃሳቦች ናቸው፡፡

 1ኛ፡ ራሱን ከስውር አመራር ነጻ ማድረግ፡- ከውስጥ አዋቂዎችና የቀድሞ አመራሮች እንደተገለጸው ማህበሩ ስውር አመራር አለው፡፡ ይህ ባስቸኳይ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡ አንድን መንፈሳዊ ማሀበር በእግዚአብሄር መንፈስ፤ በቤተክርስቲያን ሰርአትና በአባላቱ ፍላጎት እንጂ በሌላ በስውር እጅ ሊመራ አይገባውም፡፡ ማስፈጸም ያለበትም የእግዚአብሄርን፤ የቤተክርሰቲያንና የአባላቱን አላማ እንጂ የስውር አካልን ፈጽሞ ሊሆን አይገባውም፡፡ በመሆኑም በእግዚያብሄር መንፈስ ማገልገል የሚችል ጠንካራ አመራር ባስቸኳይ በመምረጥ ራሱን ማስተዳደር መጀመር ይኖርበታል፡፡

2ኛ፡እጁን በየትኛውም ፖለቲካ ውስጥ አለማስገባት፡- በተደጋጋሚ ማህበሩ ከሚቀርብበት ክስ መሃል ከህገ ደንቡ ውጪ እጁን በፖለቲካ ማስገባቱ ነው፡፡ መንግሰት ሳይቀር ይህን በማያሻማ ሁኔታ አስቀምጦታል፡፡ አብዛኛው የማህበሩ አባላት የኢህአዴግ አባላት ናቸው የሚለው የማህበሩ አመራር መግለጫም ቢሆን ከዚህ ክስ ነጻ የሚያወጣ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የተቃዋሚምም ሆነ የገዢ ፓርቲ አባል መሆን ያው ከፖለቲካነት የሚዘል ትርጉም የለውም፡፡  አመራሮቹም የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያለመሆናቸውን የሚያስረዳ ሰነድ ማቅረብ አለመቻላቸው አመራሩም ፖለቲካ ውስጥ እጁ የለም ለማለት የማያስደፍር ነው፡፡ በመሆኑም መንፈሳዊ ማህበር እንደመሆኑ ፈጽሞ በየትኛውም ፖለቲካ ያለመግባት የጸና አቋም ይዞ ሊተገብረው ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እንደፖለቲካ ተቋም የስለላ ድርጅት አቋቁሞ ሰዎችን ሊሰልልም አይገባም፡፡ ብዙዎች በፖለቲካ ውስጥ ገብቷል ብለው እንዲያምኑ ያደረጋቸው ደጀ ሰላም፤አንድ አድርገን እና ገብርሄር የተባሉት ብሎጎች የሚያስተላልፉት በሃይማኖት የተሸፈነ ፖለቲካና ሃይማኖታዊ አክራሪነት ነው፡፡ እነዚህ ብሎጎች ደሞ የማህበሩ ለመሆናቸው ብዙዎች እርግጠኞች ናቸው፡፤ ማህበሩም እስካሁን የራሱ ልሳን አለመሆናቸውን በማያሻማ ሁኔታ አልገለጸም፡፡ በመሆኑም የራሱ ብሎጎች ከሆኑ ባስቸኳይ የዚህ አይነት አካሄዱን መተው፤ የራሱ ካልሆኑ ደሞ ይህን በግልጽ በማስረጃ ማሰረዳት ብሎጎቹ የሚሄዱበትን ፖለቲካና ሃይማኖት ያጣቀሰ የተበላሸ አካሄድ መኮነን ይኖርበታል፡፡

3ኛ፡ ከራሱ ይልቅ ለቤተክርሰቲያን ቅድሚያ መስጠት፡ ማህበሩ የተቋቋመት ዋና አላማ ቤተ ክርስቲያንን ለማገለገል ነው እንጂ ራሱን ለማገልገል አይደለም፡፡ በመሆኑም ዝም ብሎ እንደስለላ ድርጅት በየቦታው መዋቅሩን ከማስፋት ይልቅ ቤተክርሰቲያንን ባሏት መዋቅር በስፋት ማገለገል አለበት፡፡ ራሱን እንደተለየ አካል ቆጥሮ ከቤተክርሰቲያን ለመጠቀም ከመሯሯጥ ይልቅ ቤተክርሰቲያኒቱን ማገልገል፤ ራሱን ከማዳን ይልቅ ቤተክርስቲያኒቱን ማዳን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነገር ሊሆን ይገባል፡፡

 4ኛ፡ የቤተክርሰቲያኒቱን አባቶች፤ ህግ፤ መዋቅርና አሰራር ማክበር፡ ማህበሩ ሌላ የሚከከስበት ትልቅ ቸግር የቤተክርሰትያን አባቶችን አለማክበር፤ መከፋፈልና ማጋጨት ነው፡፡ ይህ ፈጽሞ -ክርሰቲያናዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን ሰርአት አለበኝነትም ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለቤተክርሰቲያኒቱ ህግና መዋቅር አለመታዘዝ ሌላው የማህበሩ መገለጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለዚህም ራሱን ከሁሉም በላይ በማድረግ በቤተክርሰቲያኒቱ አመራር ራሱን በማስቀመጥ የፈለገውን ፍርድ ሲሰጥና የፈለገውን ሲሰራ መክረሙ ማሳያ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ይህን ሰርአተ አልበኝነት በመተው አባቶቹንእኔ ከናንተ አልበልጥምናብሎ ሊያከብራቸውና ሊታዘዛቸው እንዲሁም የቤተክርስቲያቱን ህግ፤ ሰርአትና መዋቅር ያለ አንዳች ማወላወል ሊያከብር ይገባል፡፡
  
5ኛ፡ ራሱን የቅዱሳንን ስም ከሚያሰድብ ነገር ማራቅ፡ማህበሩ ስማቸውን ለማስከበር ብሎ በቅዱሳን ስም ራሱን ሰይሞ የነበረ ቢሆንም ባሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እያሰደባቸው ይገኛል፡፡ የሚሰሩ አንዳንድ የክፋት ስራዎች ፈጽሞ በቅዱሳን ማህበር የሚሰሩ አይደለምና፡፡ ዘረኝነት፤ ቡድንተኝነት፤ አድመኝነት፤ ሰላይነት፤ ፖለቲከኝነት፤ስም ማጥፋት፤ ሰዎችን ከቤተክርስቲያን መግፋት፤ እንደፖለቲካኞች የውስጥ ቸግር ሲፈጠር ከውጭ የማምለጫ ፍየል መፈለግ፤ አባቶችን አለማክበር ወዘተ በየትኛውም መለኪያ መንፈሳዊ ሊሆንና የቅዱሳን ባህሪ መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ ቅዱሳን እንዲከበሩበትና እንዲዘከሩበት የተቋቋመ ማህበር ተሰድቦ ቅዱሳንንም ለሰዳቢዎች አሳልፎ የሚሰጥ ሊሆን አይገባውም፡፡ በመሆኑም እንደ ቅዱሳን መንፈሳዊነቱን ጠብቆ መንቀሳቀስ ያለበለዚያም ስሙን መቀየር ግድ ይሆንበታል፡፡

 6ኛ፡ ማህበሩ ስትራተጂክ እቅድ ኖሮት ለቤተክርሰቲያን ሊሰራ ይገባል፡ አንድ ማህበር የራሱን የረዥም ግዜ ራእይ፤ ተልእኮና ግብ ተልሞ ሊንቀሳቀስ ግድ ይላል፡፡ ያለበለዚያ በአውር ድንበር ከመጓዝ ባለፈ እንድም ተጨባጭ ነገር መስራት አይቻልም፡፡ በመሆኑም ማህበሩ ለቤተክርስትያን የሚያደርገውን አሰተዋጽኦ በስትራተጂክ እቅድ ሊያስቀምጥና በዛም ራሱን ሊገመግም ይገባዋል፡፡ ይሁንና በውስጥ አዋቂዎች እንደተቀመጠው ማህበሩ ራሱ እሳት ሆኖ ተራ በሆኑ የእሳት ማጥፋት አይነት አካሄድ ላይ ራሱን ጠምዶ ነው እድሜውን ያሳለፈው፡፡

 7ኛ፡ የኔ ካልሆናችሁ ጠላቶቼ/ምንትስ ናችሁ የኔ ከሆናችሁ ግን ወዳጆቼ/ቅዱሳን ናችሁ ከሚለው የተሳሳተ አስተሳብ ነጻ መውጣት፡ ማህበሩ ብዙ ጊዜ ራሱን ብቻ እንደቤተክርሰቲያን ጠበቃ የሱ አባል ያልሆኑትን (አባቶችን ጨምሮ) በጥርጣሬ የማየት ችግር አለበት፡፡ በተለይ ሁሉም ሰዎች የኔ አባል ካልሆኑ ምንትስ ናቸው እያሉ የተለያዩ ስሞ ሰጥቶ ጠላት ከማድረግ ከተቻለ አሳምኖ አባል ማድረግ ካልሆነ ግን በጋር የሚሰሩበትን ዘዴ መቀየስ ያስፈልጋል፡፡ ወይ የኔ ሁኑ ያለበለዚያ ጠላቶቼ ናችሁ የሚለው አካሄድ ማህበሩ በራሱ ጊዜ ብዙ ጠላቶችን እንዲያፈራ አድርጎታል፡፡ ከዚህም በላይ ብዙ ምንትሶች በማህበሩ ተጠልለው ክፍ ስራ ለመስራት ዋስትና ሆኗቸዋል፡፡
8ኛ፡ በማህበሩ ያለው ግኖስቲካዊ አመለካከት መሰበር አለበት፡ ባሁኑ ወቅት ማህበሩ አገልግሎት በእውቀት ነው የሚለው አመለካከት ተንሳርፍቶበት ይገኛል፡፡ የዚህም መነሻው አባላቱ በአለማዊ ድግሪ የተንበሸበሹ በመሆናቸው ነው፡፡ በመሆኑም የሆነ አለማዊ ድግሪ ያለውና በወራት በጊቢ ጉባኤ መንፈሳዊ ኮርስ የወሰደ የማህበሩ አባል እንደሱ በአለማዊ ትምህርት ያልገፉትን አገልጋዮች በመናቅ ራሱን ሰማይ ላይ ሰቅሎ ቁጭ ይላል፡፡ ዲፕሎማና ዲግሪ የሌለው አገልጋይ ደሞ ማለት ይጀምራል፡፡ ግኖስቲክነቱ ገኖ መድረክ ላይ ይወጣል፡፡ እግዚአብሄር ጸጋ አልሰጠውምና ሰው ጀሮ ይነፍገዋል፡፡ እነዛን አልተማሩም የሚባሉትን ግን በእልልታ ይሰማል፡፡ ይሄኔ በቅናት ተነስቶ ሌላ ጦርነት ያውጃል፡፡ ከዚህ ይልቅ አገልግሎት በድግሪና በዲፕሎም ሳይሆን በእግዚአብሄር ጸጋ ነው….የቢታንያ ድንጋዮችን ያናገረ ጌታ ለሰው ልጅማ የተሻለ ሊሰጥ የታመነ ጌታ ነው፡፡

9ኛ፡ በስጋ ሳይሆን በመንፈስ ማገልገል፡ የማህበሩ ቁልፍ ችግር በመንፈስ ሳይሆን በስጋ ማገልገሉ ነው፡፡ ምናልባትም አለማዊ ድግሪ ያላቸው አባላትና አመራሮች ስላሉት ይሆናል፡፡ ባሁን ወቅት ማህበሩ ላለበት አደገኛ ሁኔታ መሰረቱም ይሄ ነው፡፡ በጸሎት፤ በትህትና፤ በፍቅር፤ በመተሳሰብ በመሳሰሉት የመንፈስ ፍሬዎች ተደግፎ ከማገልገል ይልቅ    በስለላ፤በጥላቻ፤ በትእቢት፤ ጠልፎ በመጣል በመሳሰሉት የስጋ ፍሬዎች በመነዳቱ አሁን አለበት አዘቅት ላይ ደርሶአል፡፡ በመሆኑም ባስቸኳይ ያለው በመንፈሳዊ አገልግሎት እንጂ በስጋ ስራ ላይ አለመሆኑን ተረድቶ በመንፈስ ማገልገል መጀመር የማህበሩን ህልውና የማዳን ጉዳይ ይሆናል፡፡

ምንጭ፡- ፌስ ቡክ፡- በበከምህረትከ የተጻፈ በከመምህረትከ

5 comments:

  1. God bless the writer.

    I think this is a balanced view. Some ppl simply hate the MK but this author rather than simply expanding hates has come up with solutions. I also believe that the MK should solve its problems ASAP and serve the church with love and respect.

    ReplyDelete
  2. Melkam Ababal new Mahibere Kidusan Endinor efelgalehu Beteley legetser Abite KIrsityanat neger gin Bizu Mestekakel yalebet negr ale Bensha Mamen -SEwn Kemegifat Yilk Degifo Mansat-Yesewn Sim kematsifat yilk gebenawn Meshefen-Anid sebaki Or zemar masadedi bizu Teketayochin mawek newna Ahun Hizibu Papas -Kahin -Sebaki Zemar endayamin Hulunim Zerafi- Bedelega Adirgo Yaleyayachew Mahibere kidusan yesetsachew Kifu sim new Ahun BEhulum Bota metemamen yelem Tesebisibo Menegager yelem BEmekakelachin Mahibere KIdusan yinoral yemil firacha Masder tejemiroal

    ReplyDelete
  3. mahiberun lemekefafel yemititiru yezemenu hasawi mesih malet enanite nachihu mahibere kidusan beegiziabiher fekad yetemeserete mahibere mehonuni atizenigute.

    ReplyDelete
  4. 'ለወንድሜ' ኤፍሬም:

    ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ!!!!!!!!!

    በመጀመሪያ ደረጃ ባሕር ማዶ በሞቀ ኑሮ ላይ ሁነህ እዚህ አገር ቤት ባለነው የሁሉም ችግር ገፈት ቀማሾች ብቻ ሳንሆን ጭልጥ አድርገን ጠጪዎች ላይ የስንፍና አንደበትህን ባትከፍት መልካም ይሆን ነበር:: የለም የመጻፍና የመናገር ሱስ አለብኝና ዝም ማለት ፈጽሞ አልችልም ያገሬና የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል ያንገበግበኛል ለማለት ከሆነ ግን 'ያልተነካ ግልግል ...ነውና' ዝም ብትልና የሚሆነውን ብትመለከት ወይም እንደገባው እውነተኛ የጌታ ተከታይ ብትጸልይ ይሻልህ ነበር:: ተርፈህ ታተርፋለህና::

    አዎ! በውጭ ሆነው ወይም በዳር ቆመው እርስበርሳችንን ሊያዋጉን የሚፈልጉ የአፍ ጀግኖች ሞልተውናል:: ታሪካችን ይህን በመሰሉ የድል አጥቢያ ባንዳ አርበኞች የተሞላ መሆኑን ያለፈው ተመክሯችን (በጣሊያን ጊዜ ሳይቀር) በሚገባ አስተምሮናልና ለአሁኑዎቹ አንተን መሰል ዳር ቋሚ እሳት ጫሪዎችና ለአንተ ለራስህ ግን ይህ ዓይነቱ አካሄድ አያዋጣችሁም ለአራችንና ለቤተ ክርስቲያናችንም አይጠቅምምና ዝም በሉ ወይም በል የሚል ምክሬን እለግስሃለሁ::

    ከዚህ በተረፈ ማን ምን እየሠራ ነው? ዓላማውስ ምንድነው? ወዘተ ለሚሉት በርካታ ጥያቄዎች መልስ ግን እንኳን አገርን እመራለሁ ለሚል መንግሥት ይቅርና ለእኛ በአገሪቱ ውስጥ የሚሆነውንና እየሆነብን ያለውን ለምናይ ኗሪ ምስክሮች ብቻ ሳይሆን ለእናንተም (በዓላማችሁ ታውራችሁ እንጂ) የተሰወረ አይደለም::

    ስለዚህ እባካህ 'ወንድሜ' ኤፍሬም ከመሰል የግብር ወንድሞችህ ጋር የሚያስተውል ልብ ይኑራችሁና ለአገርና ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም አስቡ ተነስታችሁም ፍሬ ያለውና የሚታይ ሥራ ለመሥራት ሞክሩ:: በተጋለጠ የማንነት ሥራችሁ ላይ እንደገና የማይመስልና የማይታመን ነገር በመጻፍ ደግማችሁ ደግማችሁ ሕዝብ ለማታለል አትሞክሩ ወይም ከተቻላችሁ ሌላ የማታለያ ስልት ቀይሱ:: ለእንደዚህ ያለ በሬ ወለድ ነገር ብርቱዎች ናችሁና::

    'እውነት ትመነምናለች እንጂ አትበጠስም' እንዲሉ ስለ ማህበረ ቅዱሳንና ስለተሃድሶ ማንነት ለማዎቅ የሁለታችሁም የሥራ ፍሬ እየገለጣችሁ ስለሆነ ሚዛኑን በዚች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመሆን ወደ ሰማይ ለምናነባ የቤተ ክርስቲያኒቷ ምእመን ተውት:: እንባን የሚያብስ የጌታ ቀን መገለጫው ቀርቧልና::

    'አመጸኛው ወደ ፊት ያምጽ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ
    ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ ቅዱሱም ወደ ፊት
    ይቀደስ አለ::' (የዮሐንስ ራእይ 22:11)

    የሞጣው ጊዮርጊስ የቆሎ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በመላው ያገራችን አድባራትና ገዳማት ውስጥ 'በማህበረ ቅዱሳን' (ዲያቆን ሙሉጌታ ግብራቸውን ተመርኩዞ ያወጣላቸውና ለመጽሐፉ የሰጠው ማሀበረ ሰይጣን የሚለው ስም ይስማማኛል) የፈሰሰውና እየፈሰሰ ያለው የንጹህ ወገኖቻችን ደም አሁንም ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው አምላካችን በመጮህ ይጣራልና ወዮ! ወዮ!! ወዮ!!! ለኤፍሬምና ለመሰሎቹ::

    እግዚአብሔር አገራችንና ቤተ ክርስቲያናችንን በመካከላችን ከሚገኙ ተናካሺ ውሾች ይጠብቅ!!!! አሜን::

    ሰላም ለሁላችን ይሁን!!

    በዚህ ጉዳይ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር የዘወትር ሙግት ያለኝ እና የሁሉንም ወገኖቼን እውነተኛ ሰማያዊ ፈውስ የምሻ እህታችሁ

    ReplyDelete
    Replies
    1. “ማን አለብኝነት ነው ዋናው መነሻ ችግሩን የፈጠረው ” የምን መሸፋፈን ነው የተባለው ሌላ ምታወራው ሌላ የምን ሰው ላይ መንጠልጠል ነው አካፋን አካፋ ማለት ያስፈልጋል ምነው የእስከ ዛሬ አፍህ የት ሄደ ጸልይ የምትለው ሁለት ሁዳዴ አለፈ ስታተራምሱ በሶስተኛው ሁዳዴ ሲያልቅ መልስ ለናንተ መጣ አንተ ምን ስትሰራ ነበር ያን ጊዜ አትጸልይም ነበር ለምን የሽምግልና ስራ አልሰራህም ለጠብ፣ለክርክር ፣ለአድመንነት ፣ድብድብ እግርህን ስታፋጥን አልነበር ያን ጊዜ ይሄ ያሁኑ ቃላት የት ነበር ባለቤት አልነበራችሁም እንዴ የድብድቡ አስተባባሪ የሰንበት ተማሪዎችን ልጆቻችንን ችግር ላይ ልትጥሉ የነበረው ማን ይረሳል ምንም በማያውቁበት ከቤታቸው ወጥተው የማያውቁ ከፊት እናንተ ከኋላ ለድብድቡ ደግሞ ከመሓል ብቅ እያላችሁ አይደል እንዴ ባደባባይ ላቤቱታ የሄዱትን አገልጋዮች የደበደባችሁት አይታወቅም ባልተጠራችሁበት ላድማ የተነሳችሁት ለምን በጠጴዛ ዙሪያ እንፍታ ስተባሉ ታፔላ በመለጠፍ ሲኦል ያሻለናል አላላችሁም እናንተ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን ያልተገባ ነገር ውስጥ ገባችሁ የእናንተንማ አምላክ የስራችሁን ይስጣችሁ የማዝነው የዚች ቤተክርስቲያን ፈተና መብዛቱ ቀናተኝነታችሁ ባልከፋ ግን ቅናታችሁ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን በአገልጋዮች ጸጋ ላይ መሆኑ ነው አሁንም አልረፈድም በድብቅ አመራር መምራታችሁን ትታችሁ በግልጽና በፍቅር ይህችን ቤተክርስቲያን ፈተናዋን አታብዙት ህዝቡን መሄጃ አታሳጡት ሰው መሆናችሁን አትርሱት ዲግሪያችን ለሆዳችን መሙያ ፣ህሊናችን ለአምላካችን እናስገዛው----
      ድንግል ከልጂዋ ታማልደን እኛንም ልብ ስጠን ይቅር ይበለን!!!!

      Delete