Wednesday, April 25, 2012

የ“ማህበረ ቅዱሳን” ዲግሪና የካንጋሮ እጅ አንድ ነው!

Click here to read in PDF
/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
Email: yetdgnayalehe@gmail.com
ጥብቅ ማሳሰቢያ:
በቅድሚያ ጽሑፉን ለምታነቡ ወንዶችንም ሴቶችም የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ሰላም ይሁን! እያልኩ በጽሑፉ ከተካተቱ እውነታዎችና ከጽሑፉ ከፊል ይዘት የተነሳ ጽሑፉ ከጸሐፊው መልእክት ዓላማና ከመልእክቱም ግብ ውጭ ሌላ አንድምታ እንዳይዝና እንዳይሰጠው ይህን ጥብቅ የሆነ ወንድማዊ ማስጠንቀቂያ ለመጻፍ ግድ ብለዋል:: ጸሐፊው በስራ ክቡርነት ያምናሉ: በየትኛውም የስራ መስክ ተሰማርተው ከራሳቸው አልፈው ለቤተሰብና ለሀገር የሚተርፉት ዜጎችንም የላቀ ክብር አላቸው:: ክብር ስለማያውቅ: ሰላሙን አጥቶ በሰላማዊያን ዜጎች የህይወት ጎዳና ላይ እየቆመ እሾክና አሜከላ ስለሚዘራ: እርግማን ቀለብ ስለሆነለት: የራሱ ያለሆነውን በማጭበርበርና በማደናገር የራሱ በማድረግ የሚታወቀው እልል ያለ ህጋዊ ሽፍታ ማህበርና አባላቶቹ ብቻ ላይ ያነጣጠረ እውነታ መሆኑን ተገንዝባችሁ ጽሑፍን በቅንነት ታነቡት ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ::

 ምንም ዛሬ ደግሞ እንደገና ትኩስ ሆኖ ማወያያ ቢሆንም "ማህበረ ቅዱሳን" ከተመታ: ቅስሙ ከተሰበረና ተናዳፊ አንደበቱ ከተመነገለ ከራርመዋል:: ቢሆንም ግን የተመታ: ሞትን የማይቀርለት እባብ በቀላሉ አይገላገልምና ዛሬም ወዲያ ወዲህ በማለት መወራጨቱ አልቀረም:: ይህ በዚህ ሲባል በዚያ: ወድያ ሲባል ወዲህ: ከዚያ ሲታይ ከዚህ እየሆነና እያለ አልያዝ አልጨበጥ በማለት በመሸበት ቁጥር መልኩንና አድራሻውን እየለዋወጠ በሚፈበርካቸውና በሚለቃቸው የማደናገሪያ ወሬዎች በጥቂቶች ዘንድ ብዥታ እየፈጠረ በመምጣቱ ስለራሱ በራሱ ሰዎችና ዓላማውን በሚጋሩ አጨብጫቢዎች በኩል በእጅ አዙር ስለ ማህበሩና የማህበሩ አባላት መልካምነትና ብቃት ነጠላ ዜማ ለቆ ስሙልኝ! አልሰማችሁም ወይ! እያለ ይገኛል:: ከእነዚህ መካከልም የማህበሩ አባላት የትምህርት ደረጃና ብቃት የሚገልጽ መፈክር ማለት “የተማሩ ናቸው!” እየተባለ ማስተጋባት ይገኝበታል::

በመጀመሪያ ደረጃ የጽሐፉ መልእክት ለአንባቢያን ግልጽ ይሆን ዘንድ ማህበሩ አይደለም ከተራ ምእመን ቤተ-ክርስቲያን መንጋዬን ይጠብቁልኛል: በፈረሰ በኩል ይቆሙልኛል ብላ ከፍተኛ ወጪ አውጥታ ካስተማራቻቸውና ከምታስተምራቸው መምህራን ደቀመዛሙርት በአጠቃላይ ከካህናቶችዋ በመላ ሳይቀር የተሻልኩ ነኝ በማለት የሚመጻደቅባቸው ሦስት ዓበይት ነጥቦችን ላስቀምጥ

ይኸውም÷
አንደኛ: አስኳላ (በዘመናዊ ትምህርት) ከእኛ በላይ ላሳር የተማርን የተመራመርን አዋቂዎች ነን! ባዮች ናቸው::
ሁለተኛ: ማህበሩ (አባላቱ) በቅድስና ህይወት/በስነ ምግባር “እኛን ያላየ በአብርሃም ይደነቃል” ባዮችም ናቸው::
ሦስተኛ: “በማህበሩ ውስጥ ካህናት ዲያቆናት ሰባኪያን አሉ” በማለት በውስጠ ታዋቂነት መልእክቱ እኛም ካህናት ነን ባዮች ናቸው::

በአንድ ወቅት ትዕቢታቸው አድጎባቸው በጠቅላይ ቤተ ክህነት ቅጽር ግቢ በጠሩት ጉባኤ ላይ አፋቸው ሞልተው “ጋዜጣችን ስምዓ ጽድቅ የተሻለ ስርጭትና ይዘትም ስላለው የዜና ቤተ-ክርስቲያን ቦታ ተክቶ ይሰራ ዘንድ ይፈቀድልን” ሲሉ መናገራቸውን አስታውሳለሁ:: ታድያ ይህ የሚያመላክተው ማህበሩ እንደ ሌሎች የጥልቁ መልእክተኞች የእኩይ ምግባር ደቂቆች(አልቃይዳና አልሽባብ)  በኢ/ት/ኦ/ተ/ቤ/ያን የቀበረው ፈንጅ እግዚአብሔር ለክፉ ቀን ቅባቱን በላያቸው ባፈሰሰባቸው ዓመጻንና ክፋትን ለባህሪያቸው በማስማማቸው የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች የሚይዘው የሚጨብጠው እስኪያጣ ድረስ ነገሩ ሁሉ ነፋስን የመከተል እስኪሆንበትም ድረስ አከሸፉበት እንጂ ለማን ራርቶ? ቢሆንለት ኖሮማ እንጀራው ነው!! የሆኖ ሆኖ ማህበሩ እንደ እስትራቴጂ በእጅ አዙር ስለ ራሱና ስለ አባላቱ እያስተጋባው የሚገኘው ጭንቀት የወለደው መፈክር ስንመለስ እንዲህ ይመስላል::

በቅድሚያ ግን እውቀትና መሃይምነት በአሜሪካን አገር ምን መልክ እንዳለውና ምን እንደሚመስልም ጥቂት ልበላችሁ:: በአሜሪካን ሀገር "መሃይም" በሁለት ነው የሚከፈለው አንደኛው ሌጣ ዜጋ (የማይጽፍና የማያነብ) እንደማለት ሲሆን ሁለተኛው የመሃይም ዓይነት ደግሞ ዓይን እያለው የማያይ: ጀሮ እያለው የማይሰማ የአብርሃም በግ ዓይነት ይሉታል:: እንግዲህ ይህ ማለት ምንም እንኳን ከመጣበት ሀገር "የተማረ" ተብሎ የሚፈረጅ ባለ ዲግሪ ቢሆንም በሀገሪትዋ ሲስተም የማይበላ የማይጠጣ: ተግባራዊ የሆነ ትምህርት የሌለው በወረቀት ተንጠልጥሎ የቀረው እንደማለት ነው:: በዚህ ጎራ ብዙሐኑ እኛን (ኢትዮጵያዊያን) ጨምሮ የሦስተኛው ዓለም ዜጎች ናቸው:: ልብ ይበሉ! ከ85 ከመቶ በላይ ያልተማረ ዜጋ በያዘች ምድር ላይ “የተማርኩ ነኝ!” ሲል ደረቱን እየደቃ መለከት እየነፋ የሚፏንን መውጫ መግቢያ ያሳጣን የማህበረ ቅዱሳን አባላት ክፍላቸው ከዚህ ምድብ መሆኑ ነው::

በአሁን ሰዓት "የተማሩ የተመራመሩ የማህበረ ቅዱሳን" አባላት በታላቅዋ ሀገረ አሜሪካ ምን ይመስላሉ ያልን እንደሆነ ሐቁ እንደሚከተለው ነው:: ምድሪትዋ ማንም ሰው ከየትም ይምጣ ከየት ምንም ይሁን ምን ለሰው ልጆች በሙሉ የስራ ዕድል የምትሰጥ የላብክን ዋጋ የምታገኝባት የለውጥና የዕድገት ሀገር ለመሆንዋ አያጠያይቅም:: ታድያ እንዲህ ሲባል ዘሎ የሚገባበት ምንም ዓይነት የስራ መስክ አለመኖሩንም ሳይዘነጋ ነው:: ለእያንዳንዱ የስራ መስክ በሀገሪትዋ ተዘጋጅቶ የሚሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ማለፍ ይጠበቅበታል:: እንግዲህ ማነቆው ያለው እዚህ ላይ ነው ሁለት እግር አለኝ ብለው ሁለት ዛፍ ሲንጠላጠሉ ከሁሉ ያልሆኑ የማህበሩ አባላት የሀገር ቤቱ “ዳኛ” “ኢንጅነር” “የሂሳብ ባለሞያ” “ዶክተር” እዚህ የምርመራ ኬላ ላይ መታወቂያቸው በድንገት ይቀየርና በለስ የቀናው ቢጢዎቻቸውን እየደለሉ በጸሐፊነት በቀዳሽነት እየተባለ ቤተ-ክርስቲያን ላይ ተሰግስጎ ለእግዚአብሔር ቤት የሚገባውን ገንዘብ እየመዘበረ ቤተ-ክርስቲያንን ሲያውክ የምእመናን ሰላም ሲነሳና ሲያበጣብጥ ይኖራል በተረፈ ደግሞ በታክሲ ስራ ላይ ተጠምዶ የሰው ሰው ሲያመላልስ: በታላላቅ መጋዘኖች ክርታስን ሲወስድና ሲመልስ: በየመናፈሻውና መዝናኛው ስፍራ የወደቀውን ሲልቅም: የአሳማ ሲጋ ሲቆርጥ: በየነዳጅ ማድያውና የመኪና ማቆሚያ ስፍራ የተበተነው ባለ ዲግሪ ማን ሆኖ?

ለምሳሌ ያክል በኔቫዳ ግዛት ላስቬግስ ከተማ ያየሁትንና የታዘብኩትን ላካፍላችሁ (ይህ ምስክርነት እውነተኛ ነው):: በከተማው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የማህበሩ አባላት የሚገኙባት ቤተ-ክርስቲያን ስርዓተ ቅዳሴውን የሚከናወነው በዕለተ ሰንበት መሆኑ ቀርቶ በዕለተ ሐሙስ ነው:: ምን ነው ቢሉ በዕለተ ሰንበት ሰው ሁሉ (የማህበሩ አባላት) ስራ ስለሚገቡና በአንጻሩ ደግሞ በዕለተ ሐሙስ በብዛት የታክሲ ሰራተኛ: የሆቴል ሰራተኛ: የነዳጅ ማድያ ሰራተኛ: የካዚኖ (ቁማር) ቤት ሰራተኛ: የመኪና ማቆሚያ/"ፓርኪንግ" ሰራተኛ ዕረፍት ስለሚሆን ነጩን ነጠላ ለብሶ ለነገርና ለክፋት የሚሰባሰበው በዕለተ ሐሙስ ነው:: ጸሐፊው የካንጋሮ እጅና የማህበረ ቅዱሳን ዲግሪ አንድ ነው ያሉበት ምክንያትም ይህ ነው:: ምን ነው ካንጋሮማ ቢያጥርም ነፋሱን ትቀስፍበት የለም ወይ ቢሉ ማህበሩና አባላቱ እንደሆነም አለን የሚሉት ዲግሪ 85 በመቶ ያልተማረውን ማህበረሰብ ለማጭበርበር ጠቅሞታል ተጠቅሞበታልም ይሆናል መልሴ::
ፊተኞችን ኋለኞች ኋለኞችን ፊተኞች ማድረግ የሚችልበት:
የሌለውን እንዳለው የሚጠራ:
የተናቀውን የሰው ዓይን እያየ ጆሮውም እየሰማ ነፍሱን በከበረ ሰረገላ ላይ የሚያኖር:
የጠራውን ባሪያ የማይረሳ የአብርሃም የያዕቆብ የይስሃቅ አምላክ ይባረክ!!

ዛሬም እጄ በጠላቶቼ ደንደስ ላይ ነች!

27 comments:

  1. mehayib sewu dirom sile timihirt min yawukal ke senef sewu tibebin atebik yetebale iko le ante newu ina keantem kenante blog minim tibeb indemayiweta setanim yawukal

    ReplyDelete
  2. why u bother this much about MK? as far as i know many objectives of MK are anti-orthodoxs ,protestant,thehadeso,yegel tikem felagiwoch... because it always stands for z benfit of z church.

    ReplyDelete
  3. ere ewnethen new buken of buken zem belh awra dedeb!!!

    ReplyDelete
  4. ሌላ እንኩዋን አልልህም:: አባትህ እራሱ ሰይጣን ይገስጽህ!!! ማፈሪያ:: አለመማር ነውር አደለም ዛሬም መማር ትችላለህ ልቡና ቅንነቱ ካለህ::

    ReplyDelete
  5. ፊተኞችን ኋለኞች ኋለኞችን ፊተኞች ማድረግ የሚችልበት:
    የሌለውን እንዳለው የሚጠራ:
    የተናቀውን የሰው ዓይን እያየ ጆሮውም እየሰማ ነፍሱን በከበረ ሰረገላ ላይ የሚያኖር:
    የጠራውን ባሪያ የማይረሳ የአብርሃም የያዕቆብ የይስሃቅ አምላክ ይባረክ!!
    Amen brother. Thank you for sharing!

    ReplyDelete
  6. I love this article. So wonderful, God Bless you Dn. Mulugeta for ever. Ayzoh bereta giorgis
    tsena.... tsena.....tsena.... mk with his serawit go to hell.

    ReplyDelete
  7. Wushetam selaletesakaleh new.

    ReplyDelete
  8. አንተ ቂመኛ ደንደስ;የፈለከዉን ብታወራ ማንም ሊሰማህ አይችልም::እንዸት ከበተ ክርስቲያን እና ከሀገር እንደተባረርክ ሰው ሁሉ አዉቆታልና::ፖሊስ እየፈለገህ በኬንያ አድርገህ አሜሪካ ወጣህ::ጥላቻህን ይዘህ እስከ መቃብር ትኖራልህ እንጂ ያንትን የፈጠራና የጥላቻ ጽሑፍ የሚያምን የለማ

    ReplyDelete
    Replies
    1. zembele tera. ewnete lenante ewnete telacas new kentu

      Delete
    2. ያሳደዳችሁት እናንተ እንጂ ፓሊስ አይደለም፡፡ በናንተ ላ መጽሀፍ ስለጻፈ ባደራጃችሁዋቸው ማፊያዎች ተጠቅማችሁ አይደል እነዴ አገር የለቀቀው!! ነፍሰ ገዳይ ማህበር ለመሆኑ እሱ ቋሚ ምስክር ነው፡፡

      Delete
  9. የ“ማህበረ ቅዱሳን” ዲግሪና የካንጋሮ እጅ አንድ ነው! ብለህ ለዘባረቅኸው የጥፋት ልጅ አቶ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል


    ድሮም ከሰይጣንና እንዳንተ ካሉ የግብር ልጆቹ ከዚህ የተለየ ነገር ስለማይጠበቅ ባለተገራ ባለጌ አንደበትህ አፍህን ብታላቅቅ ብዙ የሚገርም አይደለም፡፡ ምን ጊዜም አውሬው ለትንሽ ጊዜ በተሰጠው የስድብ አፍ አፉን መክፈቱን አይተውም፤ እኛም ስልጣኑ ጊዜያዊ በመሆኑ የህንን ቢያደርግ አንደነቅም ይህ ሊሆን አስቀድሞ የተነገረ አውነት ነውና፡፡ ስለዚህ አንተ የሰይጣን የግብር ልጁ ስለሆነክ የድርሻህን እየተወጣህ ነው፡፡ በቼም በቅድስት ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ መንፈሳዊና መልካም ሥራ ሠርቶ ተሸመ ተሸለመ የሚል ታሪክ አለ ብለህ አንድም ምንጭ መጥቀስ እንደማትችል ኅሊናህ ያውቀዋል፤ ከኅሊና ፍርድ መሸሽ አይቻልምና፡፡ አሁንም አንተ ሁሉን ትቶ እግዚአብሔርን እያገለገለ ያለውን መንፈሳዊ ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳንን እየከሰስክ ያለኸው ከግብር አባትህ ከዲያብሎስ የተሰጠህን የጥፋት ተልዕኮ ለመወጣት ነውና በርታ፡፡ መቼም እንዳንተ ካለ መናፍቅ ሃይማኖትና ምግባር መጠበቅ ከዝንብ ማር እንደመናፈቅ ነው የሚቆጠረው፡፡

    እውነት ግን እውነትነቷ በጊዜው ይገለጥ ዘንድ ብትዘገይ እንጂ ተለውጣ አንተ እንደምትመኘው ሐሰት ልትሆን ከቶ አትችልም፡፡ ከእገዚአብሔር ጋር የሚጣሉ መድቀቃቸው አይቀርምና ይህ ዕጣ ፋንታ ደግሞ ለአንተና በግብር ለሚመስሉህ ለጥፋት ለሚፋጠኑ ወገኖችህ ሁሉ የሥራችሁ ዋጋ ነው፡፡

    እግዚአብሔር ልብ ይስጥህ፤ ለንስሐ ሞትም ያብቃህ፡፡

    “እኛስ ማኅበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን፤ የተጎዱ ቤተክርስቲያናትን ሲያስጠግን፣ ገዳማትን ሲረዳ፣ የተዘጉ አብያተክርስቲያናትን ሲያስከፍት፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ተማሪዎችን በብዙ ነገር ሲያግዝ፣ በገጠር ላሉ ምእመናን ወንጌልን በነፃ ሲያስተምር፣ ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረኮችን ሲያዘጋጅ፣ የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪዎችን ከመናፍቃን ይጠበቁ ዘንድ ሰብስቦ ሲያስተምር፣ በግእዝ ብቻ ተጽፈው የነበሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም ለኅብረተሰቡ ሲያቀርብ፣ መንፈሳዊ መጽሔቶችንና ጋዜጦችን በየጊዜው ለአንባቢያን ሲያደርስ፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ይከበር ሲል፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቁ መዝሙራትን ሲያወጣ፣ ቤተክርስቲያንን ለመውረር የሚተጉ መናፍቃንን የከፋ ግብራቸውን በማስረጃ እያጋለጠ ቤተክርስቲያንን ከተኩላዎች ሲጠብቅና ሲታደግ፣ እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን - - - ይህን ሁሉ ስለመሥራቱ በተለይም መናፍቃን እንዳሻቸው በቤተክርስቲያን ላይ እንዳይቦርቁ ዘብ ሆኖ በንቃት ተዋሕዶን በመጠበቁ መናፍቃንና መሰሎቻቸው ይህን ማኅበር ለማጥቃት ቢነሡ የሚደንቅ አይደለም፡፡ እኛስ ማኅበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን መናፍቃንንም አናጣቸውም፡፡”

    ReplyDelete
    Replies
    1. እኔው ነኝ ከደብረ ብርሀን(የማን ያዘዋል አብሮ አደግ)April 26, 2012 at 5:25 PM

      ዲያቆን ሙሉጌታ በትክክል ልንመለከተው የሚገባውን አውነት አሳይቶናል፡፡ ማቅ ሲዘባርቅ የነበረውን ነገር ሁሉ ምን ያህል ተራ ነግር እንደነበር በትክክል አሳይቶናል፡፡ ሲለዚህ ዘባራቂው አንተ እንጂ እርሱ አይደለም፡፡ መቼም መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ቀን አንብቦ የሚያውቅ ሰው የሰይጣን ደቀ መዝሙር ማን እንደሖነ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ሰይፍ ስላችሁ ሠይፍ ታጥቃችሁ ማቅ ያለሆነውን ሰው ሁሉ እንዴት እንደምታሰቃዩ አገር ያወቀው እውነት ነው፡፡ ያልተገራ ማንነት የት እንዳለ ንገሩን ከሆነ እንነግራችሁዋለን፡፡ ባያብልን ካወከው የማቅ ስብሰባ እንዴት ነው የሚከናወነው በለው እስቲ? ዳንኤል ክስረትንስ ታውቀዋለህ ስለአልተገራ አንደበት በአልተገራ አንደበት በደንብ ያሰረዳሃል፡፡ አንድ አድርገን ብሎጋችሁስ? ምን አይነት የባለጌና የስድ አደግ ጥርቅም መሆኑን በደንብ ያሳየ ብሎግ ነው፡፡ በደንብ አንብብው እስኪ አጉራ ዘለል መሆናችሁን በደንብ ታውቅበታለህ፡፡
      አውነት ነው ጊዜው የሰይጣን ነው፡፡ ፈረሱም ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ሰይጣን እሱን እየጋለበ ዐይደል እንዴ ቤተክርስቲያንን የሚበጠብጠው አይንህን ገልጠህ ለማየት ሞክር፡፡ “በቅድስት ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ መንፈሳዊና መልካም ሥራ ሠርቶ ተሸመ ተሸለመ የሚል ታሪክ…” ግብቶሃል ግን? ምን እንደጻፍክ ስቶህ ነው እንጂ ይህን ለማቅ አትጠቅስም ነበር፡፡ አሳዳጁ ገዳዩ ከሳሹ እና ከሰይጣን ጠገቢውን ሽልማት ወሳጁ ማው ነው፡፡እውነተኞቹ የቤተክርስቲያን ልጆችማ በአሳዳጁ ማቅ እየተገፉና እየተረገጡ መሆኑን አንተም ታውቀዋለህ፡፡ ስለዚህ ጥቅስ ተገላብጦሀልና ወደቦታው መለስ፡፡
      ለእናንተ ዛሬ ቤተክርስቲያን ማህበራችሁ ነው፡፡ ለናንተ መናፍቅ የማህበሩ አባል ያልሆነ ሰው ነው፡፡ እውነት የላችሁም፡፡ አታላይነትና ሸፍጥ መገለጫችሁ ነው፡፡ ማህበርህ ሁሉን ትቶ የሚያገለግለው ሰይጣንን መሆኑን የታወረ መንፈስህ አላሳየህ እንደሆን እወቀው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያገለግሉማ ስሰደዱ ሲገፉ እንጂ አራጅ ሆነው ሰው ሲያንገላቱ አናውቅም፡፡ እውነት ተሰውራ እንደማትቀር ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ አሳዳጆቹ እናንተ ውሸታሞቹ እናንተ አታላቹ እናንተ በጌታ ሐይል ትውድቃላችሁ፡፡

      እግዚአብሔር ልብ ይስጥህ፤ ለንስሐ ሞትም ያብቃህ፡፡

      Delete
    2. kentu nehe kemeteqena gebetehe sera egiziabeheare libe yestehe

      Delete
    3. እኔው ነኝ ከደብረ ብርሀን(የማን ያዘዋል አብሮ አደግ)ብለህ ራስህን ለደበቅኸው መናፍቅ

      ሰው ውሎውን ይመስላል፤ ስለዚህ አንተም ከግብር ጓደኛህ ከሙሉጌታ ወ/ገብርኤል የተለየ ሃይማኖት ይኖርሃል ብዬ አልጠብቅም፣ አልገምትምም፡፡

      የተናገርከው ሁሌ የምታልመውንና ከእውነት የራቀውን ቅዠትክን ነው፡፡ አይዞህ አጉራ ዘለሎችና ሕገወጥ ወሮበሎች ጓደኞችህ ከቅድስት ቤተክርስቲያን አውደ ምሕረት በቤተክርስቲያን ከዋክብት በምእመናን በመባረራቸው የተሰማህ ኃዘን ልብ የሚሰብር መሆኑ ይገባኛል፡፡

      ግን ምእመናን እንደ አንተ ጥሬ አስተሳሰብ ስለሌላቸው ማስቀደም ያለባቸውን የቤተክርስቲያን ጉዳይ አስቀድመው በቤተክርስቲያን ስም የሚነግዱትን ከነሸቀጣቸው ገርፈው የሸቀጥ ዕቃቸውንም ገልብጠው አባረዋቸዋል፡፡ ስለዚህ ሕገወጦቹ የተባረሩት በሰይጣናዊ ሥራቸው እንጂ ለአንተ እንደሚመስልህ መልካም በመሥራታቸው አይደለም፡፡ በመንፈሳዊነት ስም መነገድ ስለማይቻል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ (በንስሐ ካልተመለሱ በስተቀር) አረም ስለሆኑ ዳግም ላይመለሱ ተነቅለዋል፡፡

      ስለስድብክ አመሰግንሃለሁ በርታ፤ ድሮስ ልጅ ያባቱን አይደል የሚያነሳው፡፡ የግብር አባትህ ዲያብሎስ ተናንት፣ ዛሬም፣ ነገም ይሳደባል፤ አንተም እንዲሁ ታደርጋለህ፡፡
      እግዚአብሔር ፈቅዶ ያስነሣው ማኅበር ማኅበረ-ቅዱሳን ላይ የለጠፍከው የሀሰት ታርጋ ለአንተና ለግብረ አበሮችህ ለአነ ሙሉጌታ ወ/ገብርኤል ቢስማማ እንጂ ሁሉንም ነገሩን ለእግዚአብሔር ሰጥቶ በትጋት ያለመታከት ለሚያገለግለው ማኅበር-ቅዱሳን አይመጥንም፤ ይህን ደግሞ አንደበትህ ቢክድም ኅሊናህ የዋቀስሃል፡፡ እግዚአብሔር ከኅሊና ወቀሳና ስለ ሥጋዊ ጥቅም ስትል ከራስህ ጋር ከመጋጨት ይሰውርህ፤ ልብህንም ያቅናልህ፤ በጎውን ሁሉ የምታስተውልበትን በጎ ኅሊና ያድልህ፡፡
      ሌላ ምን እላለሁ . . . ጨርሻለሁ

      Delete
  10. bravo mule endihe erakotachewn askerelege

    ReplyDelete
  11. Yemaneme Chewa werega hulu man endehone selegelesegelene enamesegenalen. Bertalen endi adergehe misterun awtam. Kisarachewne negerene. Mule enamesegenalene. Awdemihret berche.

    ReplyDelete
  12. You! Guy the so called D/n Mulugeta W/Gebriel do you think I'm a christian? (of course you think since you do it being a horse of your senses only) What does it mean citing "ዛሬም እጄ በጠላቶቼ ደንደስ ላይ ነች!"?
    I raised the first question because if you think I'm a christian our common enemy is devil and its messengers. Having this, what is the value of writing as such shameful hop chop (here and there nonsense) thing?
    There is a saying that "when the mouth opens the brain could be measured.
    Mane! Tekele! Fares!

    ReplyDelete
    Replies
    1. mk is devils messenger. they work 4 him. they live 4 his government. you say so the enemy is devil and his messengers. so according to your argument the quotation is write.

      Delete
  13. ይህ ጽሁፍ ትልቅ ቁም ነገር ነው፡፡ እንዲህ ያለው እይታ ያስመሰግናል፡፡ ሰው ሁሉ ሊያየነውና ሊረዳው የሚገባ ቁም ነገር ነው፡፡ ወዳጄ በርታ፡፡ የምታውቀውን ሚስጢር ቶሎ ቶሎ ግለጥልን፡፡ ውሸታሙን ማህበር በእውነት ቃል ተናገረው፡፡

    ReplyDelete
  14. እኔ እምለው እናንተ ማቆች የሚቃወማቹ ሁሉ መናፍቅ ነው ከሚል አባዜ መቼ ነው የምትወጡት፡፡ ይህን የጡጦ ቀማሽ አስተሳሰብ ብትተዉት ይበጃችሁዋል፡፡ ሰው የታወቀ ስህተት ከሌለበት በቀር መናፍቅ አይሰኝም፡፡ ለናንተ ግን ማህበራቹን መቃመም ምንፍቅና ነው፡፡ለምን ሐይማኖታቹ ማህበራቹ ስለሆነ ነው፡፡ እግዚአብሄርንማ የት አውቃቹሁት አረ ባካችሁ ተሻሻሉ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. tikekel mk yemiqaweme hulu menafeqe newe!!!lebetekirstiyan sileqome!!!lebetekirstiyan yeqomene yemiqawem esu seyetane newe...menafeqe demo seyetane newe malete newe!!!!! gebahe/she?

      Delete
    2. thank you mawek yemenefelegew yehen neber. silaregeagetacehulen enamesegenalen. b20 ametachu betekerestiyan malet ega nen egan yemedede ortodox egan yetekamweme menafeque yemil astesaseb yeyazachu yeaddis astesaseb balebetoche nachu. selezhe menafeqanu enanete mkoche nachu. yebetekerestiyan telatoche yemengawe betagoche enante nachu.

      Delete
    3. @AnonymousApr 26, 2012 07:48 AM Min Ewunet GEletelih ?

      Delete
  15. mule you are the man. we love you so much.

    ReplyDelete
  16. mule bechahene anketeketekachew eko!!!

    ReplyDelete
  17. Eretew kibur deacon በቅድሚያ ግን እውቀትና መሃይምነት በአሜሪካን አገር ምን መልክ እንዳለውና ምን እንደሚመስልም ጥቂት ልበላችሁ:: yalihew enante bezeybeachihu mehayim malet bliever amagn new bilachihu tastemiru yele? Tadia minew mayim kemilew gis gar debalikew tetekemubet! Minale sile Mk melefilefewotin titew lemiemenan nefis yemitekim timihirt bitsefu. ERe yitewe yih akahedewo yemianits ayimeselegnim. Koy ersewo US lemin hedu? Sirawo mindin new? Degemos Nassa yalu, be universities yemiastemiru, Microsoft yemiseru, World Bank yalue... abalatin awekalehu.... Endyaw beterguamachihu bebezaw menager new bemitilut antsar menager feligew kehonem ayaskedim. Forget about MK and its members, preach the Word.

    ReplyDelete