Wednesday, May 30, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ጉዞና የዋልድባ ሰልፍ ግጥምጥሞሽ

Click here to read in PDF
ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል ሰሙ መንፈሳዊነት ወርቁ ደግሞ ፓለቲካ የሆነ ድርጅት ፖለቲካዊ ትርፍ ያስገኝልኛል ብሎ የሚያምናቸውን መንፈሳዊ መሰል ጉዳዮችን እንዴት አድርጎ እንደሚጠቀምባቸው ሴራ ሲሸርብ ውሎ እንደሚያድር ይታወቃል። መንግስት የጀመረውን የዋልድባ አካባቢ የስኳር ፕሮጀክትን እንደ ጥሩ ፖለቲካዊ ትርፍ ማግኛ ለመጠቀም በትጋት እየጣረ ያለው ድርጅት በተለያየ ብሎጎቹ ላለፉት አራት ወራት ሳይታክት ከፍተኛ የሆነ ቅስቀሳ አደርጓል። በዚህም በተለይም ሁሌ ቀድሞ የጮኸን እውነተኛ ብሎ የሚያምነውን የሕብረተሰብ ክፍል ልብና ቀልብ ለመግዛት ችሏል። የዋልድባ አካባቢ የስኳር ድርጅት ከገዳሙ ክልል የራቀ እና ገዳሙን በቀጥታ የጎዳበት ምንም አይነት ጉዳት የለም ብሎ ያረጋገጠውን የኅብረተሰብ ክፍል በአዲሱ የዜና ማሰራጫዋ ኢሳትና በብሎጎችዋ ማኅበርዋ አጥብቃ እየተቃወመች ነው ያለችው።
በተለይም ከመሰላቸው የሁለት ሰዎችን ቆሞ ማውራት እንኳ ተአምር ለማለት የማይመለሱት የአንድአድርገን ብሎግ አዘጋጆች ጉድ ጉድ እያሉ ተአምር ተአምር አረ ስሙ ተአምር በማለት የህብረተሰቡን ልብ ለማሸፈት ሮጠዋል። ነገሩ የፈለጉትን ያህል አልደምቅ ሲል ደግሞ ህዝብ ወደ ዋልድባ እየተመመ ነው የሚል ቅስቀሳ ወደ ዋልድባ እንደ ሁልጊዜው ለንግስ የሚሄደውን የኅብረተሰብ ክፍል ለሌላ አላማ የሄደ በማስመሰል ሌላው የኅብረተሰብ ክፍል እኔስ ለምን ይቅርብኝ ብሎ ለመስዋዕትነት እንዲወጣና ደም መፋሰስ እንዲከሰት ከፍተኛ ቅስቀሳ አድርጎ የነበረ መሆኑ አይዘነጋም። ወዲያውም ክተት ወደ ዋልድባ የሚል ፖስተር አዘጋጅቶ በማኅበሩ አመራሮችና አባለት ማለትም ብርሃን አድማሴ ህብረት የሺጥላ እና ሌሎችም ፌስ ቡክ ገጽ ላይ በመለጠፍ ግልጽ የሆነ የጦርነት አዋጅ አውጇል።
የጦርነት አዋጁም የሚፈለገውን ውጤት ስለአላስገኘለት አሁን ደግሞ በውጭ ስለዋልድባ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በሀገር ውስጥ ደግሞ ጸሎት በሚል ህብረተሰቡን በተመሳሳይ ቀን ለተቃውሞ በማነሳሳት ላይ ይገኛሉ። ይህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ የሚደረገው ግንቦት 27 ቀን ሲሆን ማኅበርዋ የአመጽ የማሳደድና ከአባትዋ ከዲያቢሎስ የተማረቻቸውን ድርጊቶች ሁሉ “በብቃት” ያከናወነችበትን 20ኛ አመት  በእግር ጉዞ አከብራለሁ ብላ ባሰበችበት ቀን ማግስት መሆኑ ግጥምጥሞሹ ለምን? ያሰኛል።
እንደሚታወቀው ጉዞው የታሰበው ለሚያዚያ 27 ቢሆንም በፈለጉት መንገድ ሰው ትኬት ስላልገዛቸው እና ተያያዥ አጀንዳ ለማስፈጸም ስላላመቻቸው በዋልድባ ጉዳይ በመላው አለም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለተቃውሞ እንዲሰለፉ በማኅበሩ ቴሌ ኮንፍረንስ በኩል ከፍተኛ ቅስቀሳ ከተደረገ በኃላ ሆን ተብሎ ጉዞው ወደ ግንቦት 26 እንዲዞር ተደረጓል። ሆኖም የግንቦት 26 ቀኑ ጉዞም እንደ ሚያዚያ 27ቱ የትኬቱ ሽያጭ ከሚጠበቀው በታች በመሆኑ ትኬት ባይገዙም ለሰልፍ መውጣታቸው ግዴታ እንደሆነ መመሪያ የተላለፈላቸውን የዩንቨርስቲ ተማሪዎችና ሰንበት ተማሪዎችን ውስጥ ውስጡን በሚገባ ለመቀስቀስና በግንቦት 27 የዋልድባ አካባቢ ስኳር ፕሮጀክት በሚካሄደው ተቃውሞ ላይ እጁን እንዲያስገባ እዛው ጥዶ እዛው አብስሎ ሳይበርድ በትኩሱ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ለማመቻቸት ሲባል ቀኖቹ ሆነ ተብሎ እንዲከታተሉ ተደርጎል።
በአሜሪካ በየሳምንቱ ሀሙስ ሀሙስ በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር 9-11pm በስልክ ቁጥር 599-726-1200 በaccess code 157715  የሚካሄደውን ቴሌ ኮንፈረንስ የተከታተለ ሰው የዋልድባን እንቅስቃሴ እየመራ ያለውና በዚህም ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት እየተፍጨረጨረ ያለው ማቅ ለመሆኑ ከቶውንም ሊስተው አይችልም። በአዲስ አበባ ከተማ ሊያደርጉት ያሰቡትን የተቃውሞ “ጸሎት” ሆን ተብሎ በብሎጎቹ ቦሌ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ከ10 ሰዓት ተገኙ እያለ ያለው ማቅ በዕለቱ ምን ለማድረግ እያሰቡ እንደሆነ ለማወቅና ለመከታተል የሚፈልገውን የመንግስት አካል በማሳሳት ወደ ቦሌ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ልከው እነርሱ ግን በማርቆስ ቤተክርስቲያን ያሰቡትን የተቃውሞ “ጸሎት” ለማድረግ ውስጥ ውስጡን ትዕዛዝ መውጣቱ ታውቋል። የክልሎቹን ተቃውሞ ከሰዓቱ ውጭ ቦታውን ያልገለጹ ሲሆን የታሰበውም በመድሃኒዓለም በዓል ስም ዝክር ነገር አዘጋጅቶ ተቃውሞውን ለመግለጽ ነው። እንቃወም ብሎ “ጸሎት” ከመነሻው መንፈሳዊ አላማውን የሳተ ሲሆን ክርስቲያን ከአምላኩ መፍትሔ የሚፈልግበትን ጉዳይ ይዞ በፊቱ ለጸሎት ይቆማል እንጂ ጠላሁ ተጸየፍኩ ብሎ ለተቃውሞ “ጸሎት” እንደማይነሳሳ እንኳን የተገለጠውን የተከደነውንም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያውቁ ሁሉ የሚገነዘቡት ሀቅ ነው።
የዋልድባን ጉዳይ አጠናሁ አልተቃመምኩትምም በማለት ከአጠቃላይ ዳሰሳ እና ተያያዥ ጉዳዮች ውጭ ግማሽ ገጽ ብቻ የሆነ ፍሬ ሀሳብ ያቀረበው ማቅ የጥናቱ ሪፖርት አጥኚ የተባሉት የማህበሩ አባለት ከአዲስ አበባ ሳይነሱ ተጽፎ መጠናቀቁን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ሪፖርቱም በውስጠ ወይራ ፕሮጀክቱን የሚቃወም መሆኑ ግልጽ ነው። ሪፖርቱ ከልብ ማኅበሩ ያመነበት ሪፖርት አለመሆኑንም መንግስት ሊጎዳን ፈልጎ የጠየቀን ሪፖርት ስለሆነ ከዚህ በላይ አትጠብቁብን ስትል ደጀ ሰላም ነግራናለች።
የሆነው ሆነ የግንቦት 26ቱ ጉዞና የግንቦት 27ቱ የዋልድባ ጉዳይ ተቃውሞ እንዲያው የመጣ ግጥምጥሞሽ ሳይሆን ታስቦበት የተደረገና የግንቦት 26ቱ ጉዞ ለግንቦት 27ቱ ተቃውሞ ግብዓት መሰብሰቢያ መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን።

14 comments:

  1. የፕሮግራም ማስታወቂያው በአፍሪካም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚናገር ይገልጻል። በአፍሪካ ደግሞ የት፤ የት ቦታ ነው?

    ReplyDelete
  2. mengist hulunm tenkiko yawkal atidkemu midre menafkan. Benantebet mkn maswegatachihu new miskinoch.

    ReplyDelete
  3. gerum eywta new. down with mk

    ReplyDelete
  4. እግዚአብሔር ይስጣችሁ ወውደ ምህረቶች ይህን የመሰለ እውነት በማውጣታችሁ። ይህ በአሜሪካ ከላስ ቬጋስ የሚተላለፈው የቴሌ ኮንፈረንስ የምያካሄዱት የቅንጅት የፖለትካ አባላት የነበሩ ናቸው።እነዝህ የማቅ ፖለትካ አባላት በሐይማኖት ስም የሚያካሄዱት ጦርነት ነው። የፖለትካ ይዘት ያለው ለመሆነ እስት ትንሽ ፍንጭ እንስጣችሁ። በዚህ ቴሌ ኮንፈረንስ ላይ የማቅ መሪዎች ያቀረቡ ሀሳብ እንድህ የምል ነበረ ።"በዚህ ሰልፍ ላይ ከእስላምናና ከፕሮተስታቱም ድጋፍ እንድሰጡአቸው ጥሪ እያቀረቡናቸው" (በካናዳ ሰልፍ ላይ አንድ የሙስል ሰው ተገኝተው ንግግር አደረጉ በለው የካናዳ የማቅ ተወካይ ተናግሮ ነበር። ይህ የፖለትካ ስራ አይደለምን? ለመሆኑ ትላንት የእስላሙን ህዝብ ስቃወም የነበረው ድርጅ ማቅ ዛሬ እንደት ትዝ አለው? ለዚህም ነው አብዛኛው በአሜሪካ የሚገኙት የኦርቶዶክስ ተካታይ ቤተ ክርስቲያን የዋልድባን ጉዳይ ያለተቀበሉትና በየቤተ ክርስቲያኑም በዐውደ ምህረቱ እንዳይነገር የተደረገው። እወነት ስላልሆነና እውነትም ብሆን መልሱን ከእግዚአብሔር ብቻ ነው የሚገኘው።

    ReplyDelete
  5. Teleba Binchaca . . . huleme chuhet becha . atesere wy ataseru mider menafik

    ReplyDelete
  6. የአሜሪካው ቴሌ ኮንፈረንስ የማቅ ማንነት ፍንትው አድረጎ የሚያስ ነው። ማህበሩ አላማው ሁከት ብትብጥና ማሰሳደድ ብቻ መሆኑን ቴሌ ኮንፍረንሱ ላይ በሚነሱ ሀሳቦች ማወቅ ይቻላል። ማህበሩ ክፉ መንፈስ ያደረበት የዲያቢሎስ አገልግ መሆኑን የሚያሳውቅበት ስለሆነ መከታተሉ ራስን ከማህበሩ አስተሳሰብ ነጻ ለማውጣት ይጠቅማል።

    ReplyDelete
    Replies
    1. u don,t know what MK means? so pls shut ur mouse all of u and wait what God says.

      Delete
  7. eski benatachehu endezihe neger kmetaragebu menalebet yegziabhyren kal betasetemerubet??? Hezebu ywory temat sayhon yegziabhyr kal temat selhon yalebet gizy wsedachehu betasebubet melkam nwe elalhu.

    ReplyDelete
    Replies
    1. poleteka eyalachh sewun kemekefafe selesew kemawurat aned yegeziyaabeharn qale betasetemerobet yeshalale

      Delete
  8. mk Ymibale awere ale alu yeegzizbehere lejocheneasado asdo yemibela. geta yigesesewe

    ReplyDelete
  9. Yegeata qale endaysebek eyekelekelachu endet adregen? Maqoch masmesel techlubetalachu. Be-ewnet le egziabeher qal meneger yemetelefubet weqt dero dero qere. Ahunema teru poletikegnoch honachu ayedel ende?

    ReplyDelete
  10. Wregnoche, achiberbariwoceh nachiu, yekifate sira bicha yalachcihu nachchiu MK endhone betesakana bmiyamere huneta aderegotale MK FOREVER TELATU YEFERE, EGNAME ABALE BANIHONME ENAWEKEWALENE!!!

    ReplyDelete