Saturday, May 19, 2012

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ 10 ጳጳሳትን ይዘው ወደ አክሱም ሄዱ

click here to read in PDF
  • መምህርን ዕንቆባሕርይ ከሰንበት ማደራጃ አይነሳም
  • የሚወገዝ ሰውም የለም
  • የደ/ር መስፍን ክህነት መሻር ይነሳልን ብለው ነበር  አልተሳከላቸውም
  • አባ አብርሃም የአሜሪካውን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ታዘዋል
  • የማኅበረ ቅዱሳን ድረገጾች ውሸት እየፈበረኩ መዘገባቸውን ቀጥለዋልና የዘገቡትን ገልብጦ መረዳት ያስፈልጋል
ከሲኖዶስ ስብሰባ በስተጀርባ ሆኖ እንዳሻው ከሚጋልብባቸው ጳጳሳቱ ጋር የመከረውን ሁሉ ከስብሰባው መካሄድ ቀደም ብሎ የሲኖዶስ ውሳኔ አስመስሎ በማቅረብ ሕዝብን በተሳሳተ መረጃ ማደናገርና የተናገረው ሳይሆን ሲቀር ሊያፍር ሲገባው፣ ነገር ግን «ማፈር ደህና ሰንብት» ያለው ማኅበረ ቅዱሳን በድረገጾቹ ውሸት እየፈበረከና ምኞቱን የሲኖዶስ ውሳኔ አስመስሎ ማቅረቡን ቀጥሏል። ከሰሞኑ እንኳ እነእገሌ ዛሬ ይወገዛሉ አለ። ነገር ግን እንኳን ውግዘት እዚያ በሚያደርስ ሁኔታ የተደረገ ማጣራት አልተካሄደም። ማህበሩ በተሀድሶነት የከሰሳቸው ግለሰቦች ጉዳይ በተገቢው መንገድ ተጠንቶ ስላልቀረበና ግለሰቦቹም ተጠርተው ስላልተጠየቁና ምላሻቸው ስላልተሰማ፣ ጉዳዩ በዚህ የህግ አግባብ ተሰርቶ ወደፊት እንዲታይ የተባለውን፣ «ከዛሬ ጀምሮ በእያንዳንዱ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በጥንቃቄ እየተወያየ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።» ሲሉ ድረገጾቹ እንደተለመደው የልባቸውን ተምኔት ጽፈዋል። ይህ እንደማይሆን፣ ቅዱስነታቸው 10 ጳጳሳትን ይዘው ለቅዱስ ያሬድ በዓል ወደአክሱም ተጉዘዋልና፣ ዛሬ፣ እንኳን ይህ ፈጽሞ ያልተጣራና በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በተወሰነበት ደረጃ የሚገኘው ጉዳይ ውሳኔ ሊያገኝ ቀርቶ የሲኖዶስ ስብሰባም እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል።
ሌላው የማኅበሩ ምኞትና የሲኖዶስ ውሳኔ ተደርጎ የተዘገበው መምህር ዕንቆባሕርይ ከማደራጃ መምሪያ ሀላፊነታቸው እንዲነሱ ተወሰነ፤ አባ ህሩይም ወደሃላፊነታቸው እንዲመለሱ ሲኖዶሱ አዘዘ የሚለው ዘገባ ነው። ይህ ፈጽሞ ሊሆን የማይችል የማህበሪቱ ምኞት ነው። ማኅበሯ ቆሽቷ እርር ስላለ መምህር ዕንቆባሕርይን ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሃላፊነት ለማስነሳት በጳጳሳቶቿ በኩል ጥያቄ ብታነሣም፣ ኪራይ ሰብሳቢው አባ ኅሩይ ተመልሰው የሰንብት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀላፊ እንደማይሆኑ፣ ማኅበሯ ተዋጠላትም አልተዋጠላትም መምህር ዕንቆባሕርይም እንደማይነሱና በመምሪያ ሀላፊነታቸው እንደሚቀጥሉ ተረጋግጧል።  
በማኅበራት ጉዳይ ላይ አጀንዳው እንደቀረበ ጳጳሳቱ ሁሉ መስማማታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ «ጉዳዩ እኔን ለማፍረስ የተደረገ ነውና እንዴት እንዲህ ያለ ስምምነት አድርጋችሁ ትወጣላችሁ?» በማለት ጳጳሳቶቿን ከመጋረጃ በስተጀርባ ሰብስባ ጉዳዩን እንደገና እንዲያንገራግሩበት ለማድረግ ባደረገችው ጥረት ጳጳሳቶቿ በጉዳዩ ላይ አቧራ ለማስነሳት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን በሁሉ ጥርስ ውስጥ የገባችውን ማኅበሯን ከመፍረስ ይታደጓታል ተብሎ አይታሰብም።
ማኅበሩ ከሲኖዶስ ስበሰባ በፊት በየድረገጾቹ አቡነ ጳውሎስን በግንቦቱ ሲኖዶስ ማውረድ አለብን የሚል ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ሲታወስ፣ ይህን ለማሳከትም በጥንተአብሶ ሰበብ ጳጳሳቶቿ ሙከራ እንዲያደርጉ ተልእኮ ሰጥታቸዋለች። ሌሎቹ ይህን ለማለት ባይደፍሩም፣ መቼም ያልተማረ ደፋር ነውና፣ ጨዋው (በትምህርት) አባ አብርሃም ቅባትነታቸውን፣ ኪራይ ሰብሳቢነታቸውን ሸፍነው ቅዱስነታቸውን «መናፍቅ» ለማለት መዳዳታቸው ብዙዎችን አስገርሟል። እርሳቸው ምን ያድርጉ አእምሮውአቸውን የተቆጣጠረችው ማኅበሯ በግንቦቱ ስብሰባ ላይ ከሌሎቹ በተለየ ሁኔታ የእርሷቸውን ተልእኮ እንደምትፈልገው አድርገው ለመፈጸም በመፋጠናቸው በትምህርት ሳይሆን፣ ፓትርያርክን በማንጓጠትና የማኅበሯን ተልእኮ ለመወጣት ከሌሎቹ ጳጳሳቶቿ ይልቅ አንደኛ ስለወጡ «ነደ ተሐድሶ» የሚል እንግዳ ማዕረግ ሰጥታዋለችና ለዚህ ይሆናል፤ ሽቅብ የተንጠራራው።
ሌላው ቄስ ነኝ ብሎ ሲዘላብድ የነበረው  መስፍን የተባለ ግለሰብ ክህነት ይመለስልኝ አቡነ ፋኑኤል ይገሰጹልኝ ብላ ማኅበርዋ ብትንደፋደፍም የአቡነ ፋኑኤል ስልጣንንና ክብር የሚጋፋ ምንም ነገር አልተፈጸመም። የመስፍን የክብር ቅስናም ሳይመለስለት ቀርቷል።
የአሜሪካ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትን በተመለመተ ሲኖዶሱ የተነጋገረ መሆኑ ሲታወቅ አባ አብርሃም ከአንዲት ሴት ወ/ሮ ጋር የገዛሁት ቤት ነው? ምኑን ነው የምመልሰው ብለው ለመከራከርና በዚህም አቡነ ፋኑኤልን ለመስደብ ቢሞክሩም አቡነ ፋኑኤል ግን ለስድቡ መልስ ሳይሰጡ በሰከነ መንገድ ነገሩን ለማብራራት በመቻላቸው ሲኖዶሱ አባ አብርሃም ቤቱን እንዲመልሱ አዟል።

3 comments:

  1. For safety reason, do not give aba abrham a chance to approach our favorite Patriarc in Eotc history called Aba PAULOS. He will plan to assicinate him, believe me he is not father of EOTC, simply he is mafya and killer. You can immagine he tried to evaluated his Deseretion that recognized by one of famous University in our planet, some group equalized as heaven called USA. In the first place Aba Paulos is holder of PHD here in USA, so he should not be as primary student of him. In simple laguage called DEFARRRRRRRRRR AND HATERRRRRRRRRRRRRR OF TIGREE THAT HE SAID HERE IN USA.Aba ABRHAM he failed to join Grade one student English Lnguage school when he was in VA. Long live for aba paulos and this web editor including to Abune fanuel and all victom of Mad dog mk. Death to mad dog MK THAT POISENES ALL TRUE FATHERS OF EOTC. Aba abrham he did not spelt his owen name, that is key problem of him to jump in lake and asked for $64,000 dollar question bc he is block head of Gojam Debtera. All south we got freedom through current gov. of Ethiopia. Aba Paulos is a father of all.

    ReplyDelete
  2. ahati tewahido mk called an other waldeba protest in DC JUNE 4,2012

    ReplyDelete
  3. I like it very much of the first Anonymous comment. He/She is teling the truth. yes.... go for the truth and God bless you more.

    ReplyDelete