Sunday, August 5, 2012

ማሕበረ ቅዱሳን( ማኅበረ ሰይጣን) ጉባኤ አርድዕት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከማንም በላይ ስጋት ላይ ጥሎኛል በማለት ለጳጳሳቱ 2.5 ሚሊዮን ብር በመበጀት የእግድ ደብዳቤ እንዲዘጋጅ አስደርጓል ተባለ።

Gubae ardiet: Click here to read in PDF
                                                   ከይሄ ነው እውነቱ
(ሐምሌ 30 2004 .. ዐውደ ምሕረት/ www.awdemihret.blogspot.com / www.awdemihret.wordpress.com) የቅርብ ምንጮቻችን እንደገለጡት “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የተሰኘው በአገር ውስጥና በውጭ አገር ባጭር ጊዜ በርካታ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን እየማረከና እያስከተለ የመጣውን ጉባኤ ለማሳገድ ማኅበረ ቅዱሳን ለጳጳሳቱ ጉርሻ የሚሆን የ2.5 ሚሊየን ብር በጀት መደበ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የገንዘብ ምንጩ ከምን እንደሆነ እንዳይታወቅ እና ኦዲት እንዳይደረግ የሚታገለው ገንዘቡን እንዲህ ላለው ሕገ ወጥ ተግባር በስፋት ስለሚጠቀምበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአመራር አካላትና ከፍተኛ ሊቃውንትን ማዕከል ያደረገው ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ በከፍተኛ ደረጃ እያካሄደው ባለው ቅዱስ ተግባር ምክንያት የማሕበሩ ደጋፊ የሆኑት ጳጳሳት ካህናት ሰባክያንና ምእመናንን ቀልብ እየሳበ በመምጣቱ ማኅበረ ቅዱሳንን የተለመደውን ድጋፍ እንዳያገኝ  እያደረገው መምጣቱ ታውቋል።
ከዚህ በፊት ሁሉንም የቤተክርስቲያኒቱ አካላት በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ቤተክርስቲያኒቱን ለውድቀት እያፋጠነ የቆየውና ያለው ማሕበረ ቅዱሳን በተለይ በአሁኑ ሰዓት ከአክራሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ግንባር በመፍጠር እያካሄደ ያለውን እኩይ ተግባር እየተጋለጠበት በመምጣቱና በአገር ውስጥና በውጭ አገርም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት በመምጣቱ ከዚህ ያድኑኛል ያላቸውን አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስንና አቶ ተስፋዬ ውብሸትን(የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ) በመደበው በጅት በመደለል  በዋና ሥራ አስኪያጁ በአቡነ ፊልጶስ እና በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ ሕዝቅኤል አማካኝነት “ጉባኤ አርድእትን “ አናውቀውም ይታገድልን የሚል ደብዳቤ እንደሚያጽፉ የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸዋል። 

 ከዚህ በፊት እንደገለጽነው አቶ እስክንድር  ከመንግሥት ሥራ ከተባረረ በኋላ ሙሰኞች ወደ የማይባረሩባት ቤተክህነት በመግባት ከግብረ አበሩ ጋር በመሆን ከፍተኛ ምዝበራ እየፈጸመ ያለ ግለሰብ ሲሆን በተለያየ ጊዜ ከማሕበረ ቅዱሳን የአመራር አካላት ጋር ባደረገው ስብሰባ ጳጳሳቱ የግል ቤት በመገንባትና በተለያየ ሥራ የተጠመዱ በመሆናቸው ገንዘብ ስለሚያስፈልጋቸው ለሁሉም የሚከፋፈል 2.5. ሚሊዮን  ብር ከመደባችሁ የእግድ ደብዳቤ ማጻፍ ይቻላል በማለት የማኅበረ ቅዱሳንን ሰዎች  ያሳመነ ሲሆን ጉባኤ አርድእትንም የሚመለከተውን የእግድ ደብዳቤ ለማጻፍ ቅድመ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ታውቋል። ገንዘቡን ለማግኘት  እነ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስና አቶ ተስፋዪ ውብሸት  የተጠቀሙበት ዘዴ አሁን ማሕበሩ  ይህንን ካላደረገ  ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ጉባኤው የጉባኤ አርድእትን መተዳደሪያ ደንብ ያጸድቅለታል። የሚል ሲሆን ይህም ከጉባኤ አርድእት ዓላማ ውጭ እንደሆነ ታውቋል። ምክንያቱም በጉባኤ አርድእት መመስረቻ ጽሑፍ እንደተገለጸው ጉባኤ አርድእት ጉባኤና የቤተክርስቲያኒቱ አካል በመሆኑ በአሏት ሕገ ደንቦች የሚመራ እንጂ  ማሕበር ስለአይደለ የሚጸድቅም ሆነ የሚታገድ መተዳደሪያ ደንብ ስለሌለው ነው፡፡
በመሆኑም  ሐሳብንም ሆነ መንፈስን ሊያግድ የሚችል አካል ስለሌለ ጉባኤው ሊታገድ የሚችል ነገር የለውም። የጉባኤ አርድእትን ራእይ ተልእኮና ዓላማ አግዳለሁ የሚል ካለ በአጠቃላይ የቤተክርስቲያኒቱን ሊቃውንትን ካህናትን ሰባክያንንና ዲያቆናትንን ከቤተክርስቲያኒቱ አስወግዳለሁ ብሎ እንደ መነሳት ነው።
ስለዚህ እነ እስክንድር ባወጡት ዕቅድ አማካኝነት ይህ የተባለው ደብዳቤ ቢወጣ “ጉባኤ አርድእትን በበለጠ ያጠናክረዋል፤ ያስተዋውቀዋል እየተባለ ሲሆን  በአንጻሩም የማሕበሩን እኩይ ተግባርና የእነዚህን አባቶች ነን ባዮች ጥቅማዊ ተልእኮ አግዝፎ እንደሚያሳይ ብዙዎች ይስማማሉ። የእግዱን ደብዳቤ በቶሎ እንዲጽፉ አቡነ ፊሊጶስና አቡነ ሕዝቅኤል እየተወተወቱ ሲሆን ደጀ ሰላምም ዜናውን ሰርታ ጨርሳ ለመልቀቅ ደብዳቤው እየጠበቀች መሆኑን ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ያሉን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ ከተወሰነ ጳጰሳት በቀር ለአብዛኛዎቹ ጳጳሳት በነብስ ወከፍ 50000 ሺህ ብር ይደርሳቸዋል የተባለለት የእጅ መንሻ ብር ጳጳሳቱን አየር ዳባሽ ውሳኔ ያስወስናቸው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  
ሌላው አቶ ተስፋዬ ውብሸና አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ  የመንግሥት ታማኞች ነን፤ ማሕበረ ቅዱሳንን በጥብብ ለመጣል ልዩ ስተራቴጂ ከሚመለከተው አካል ጋር ቀርጸናል፡፡ ጳጳሳቱንም በየክፍሉ ለያይተናቸዋል፤ ዕርቅ ብለን በማስገባት እንዘጋቸዋለን። በማለት ቅዱስ ፓትርያሪኩን እያወናበዱ የፓትርያርኩን ውድቀት እያመቻቹ እንደ ሆነ ተነግሯል። ለዚህም ምንጮች እንደመረጃ አድርገው የሚያቀርቡት፤
1 የቤተክርስቲያኒቱ የ53ኛ ነጻነት መታሰቢያ በዐልና የቅዱስ ፓትርያርኩ የ20ኛ በዐለ ሢመት አከባበር የደመቀ እንዲሆን የሁሉም አህጉረ ስብከት ሥራአስኪያጆች እንዲገኙ እንዲወሰን የቀረበውን ሐሳብ ዋና ሥራአስኪያጁ ሲቃመሙት እሳቸውን በማሳመን እንዲመጡ ከተወሰነ በኋላ የሊቀጳጳሱን ሀሳብ በመጠምዘዝ እንዳይመጡ ማስደረጋቸው፡
2 በ1991 የወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን  እንዲሻሻል የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት  ጥረት ሲያደርጉ እነአቶ እስክንድር ግን ጉዳዩን ለማጓተት በአስተዳደር ጉባኤ ወስነናል በማለት ሲያጨበረብሩ ቆይተው በመጨረሻ ሐሰት ሆኖ መገኘቱ፤
3 በትንሣኤ ዘጉባኤ ሊሠራ የታቀደውን ሕንጻ ከዋና ሥራአስኪያጁ ጋር በመሆን ክፉኛ መቃወማቸው፡
4 ጌታችን በቅዱስ ወንጌል፡ እነዚህ ሕጻናት ዝም ቢሉም ድንጋዮች ያመሰግናሉ እንዳለው፡ በቅዱስ ፓትርያርኩ ጉያ ሥር የተደበቁት እነእስክንድርና መሰሎቻቸው ሁሉ በቅዱስ ፓትርያርኩ የ20ኛ በዓለ ሢመት አከባበር ላይ የተቃውሞ ደምጽ ሲያሰሙ ራእይ ለትውልድ በተባለው ድርጅት በቀረበው እጅግ የተዋጣለት ፕሮግራም ተቃውሞ ማሰማታቸው፤
5ኛ በተመሳሳይ መልኩ በክራውን ሆቴል በተደረገ ግሩምና ድንቅ በዐል ተመሳሳይ አቋም መያዛቸው ሁለቱ ግለሰቦች ሌላ ተልዕኮ ያላቸው መሆኑን በግለጽ ያሳያል ይላሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ተስፋዩ ውብሸት የአቶ ገዛኸኝ ወንድም ሲሆን አቶ ገዛኸን ከዚህ ቀደም ማለትም በ1986 ዓ/ም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ጸሐፊ በመሆን በቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ትርምስ የፈጠረና ማሕበረቅዱሳንን በበለጥ እንዲጠናከረ ያደረገ ሰው ሲሆን ከቤተክህነት ከተባረረ ጊዜ ጀምሮም የዚህ ክፋት የተሞላበት ማሕበር ዋና ደጋፊና አቶ ተስፋዬንም ወደ ክፋት ጎዳና እየነዳ ያለ ሰው ነው፡፡ አሁንም ወንድሙ አቶ ተስፋዩ ውብሸት አንድም የቤተክርስቲያኒቱ ዕውቀት ሳይኖረውና በዘመናዊም  ይህ ነው የሚባል እውቀት  ሳይኖረው የቤቶችና ሕንጻዎች ድርጅት ዋና ሥራአስኪያጅና የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራአስኪያጅ በመሆን ቤተክርስቲያኒቱን እያመሳት ይገኛል፡
ስለዚህ ማሕበረ ቅዱሳን የተባለው ቀንደኛ ጥቅመኛና የፓለቲካ ደርጀት እነዚህን አካላት መሠረት አድርጎ ቤተክርስቲያናችን ለመታደግ ቆርጠው የተነሱትን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በመቃዎም ሌት ተቀን እየጣረ ይገኛል። አሁንም ድረስ ለብዙዎች እንቆቅልሽ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን የጉባኤ አርድእትን ጥላ እያየ እንዲህ የመርበድበደዱ ሚሥጢር ነው፡፡ አንዳንዶች ይህን የማኅበሩን ሁኔታ በጋዜጣ ላይ የሽጉጥ ስእል አይቶ በድንጋጤ ፖሊስ ከሚጠራ ንክ ሰው ጋር ያመሳስሉታል፡፡     

                                                 

7 comments:

  1. አቶ እስክንድር ከመንግሥት ሥራ ከተባረረ በኋላ ሙሰኞች ወደ የማይባረሩባት ቤተክህነት በመግባት ከግብረ አበሩ ጋር በመሆን ከፍተኛ ምዝበራ እየፈጸመ ያለ ግለሰብ

    ReplyDelete
  2. EXCELLENT IDEA: ሐሳብንም ሆነ መንፈስን ሊያግድ የሚችል አካል ስለሌለ ጉባኤው ሊታገድ የሚችል ነገር የለውም። የጉባኤ አርድእትን ራእይ ተልእኮና ዓላማ አግዳለሁ የሚል ካለ በአጠቃላይ የቤተክርስቲያኒቱን ሊቃውንትን ካህናትን ሰባክያንንና ዲያቆናትንን ከቤተክርስቲያኒቱ አስወግዳለሁ ብሎ እንደ መነሳት ነው።

    ReplyDelete
  3. በጉባኤ አርድእት መመስረቻ ጽሑፍ እንደተገለጸው ጉባኤ አርድእት ጉባኤና የቤተክርስቲያኒቱ አካል በመሆኑ በአሏት ሕገ ደንቦች የሚመራ እንጂ ማሕበር ስለአይደለ የሚጸድቅም ሆነ የሚታገድ መተዳደሪያ ደንብ ስለሌለው ነው፡፡ Oh My God!! I really appreciate the idea of Gubae Ardiet. I hope all the laties and clergies of the church will join Gubae Ardiet except MK. Yes indeed, oue association is our church not MK. Brothers in christ who brought this noble idea and strategy will be appreciated by all members even by MK members for the future.

    ANID MAHIBER - EOTC, ANID GETA, ENA ANID TIMIKET>>>>>>>>

    ReplyDelete
  4. አሁንም ድረስ ለብዙዎች እንቆቅልሽ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን የጉባኤ አርድእትን ጥላ እያየ እንዲህ የመርበድበደዱ ሚሥጢር ነው፡፡ አንዳንዶች ይህን የማኅበሩን ሁኔታ በጋዜጣ ላይ የሽጉጥ ስእል አይቶ በድንጋጤ ፖሊስ ከሚጠራ ንክ ሰው ጋር ያመሳስሉታል፡፡

    ReplyDelete
  5. Abba Gebire Kidan Yetebale Menekuse neg bay Las Vegasin Betsebetse
    Kesis Samueil Kemeseretut Bete Kirisityan Endibareru Eyastebabere new
    Abba Gebire Kidan Mahibere Kidusan Eyale Man Yinekagal Malet Gemroal
    Abba Gebire Kidan Maref Kalchale Awash -Shewa Robit -wolo -Yinager

    ReplyDelete
  6. then...KKKKKKKKKKKKKKK

    ReplyDelete
  7. May the Almighty God bless you all . please keep going with that goald plan. i

    ReplyDelete