Thursday, August 16, 2012

ሰበር ዜና፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አረፉ

Click here to read in PDF: Abun Pawlos is passed
      (ነሐሴ፣ 10 2004 ዓ.ም. ዐውደ ምሕረት/www.awdemihret.blogspot.com// www.awdemihret.wordpress.com)አምስተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዛሬ ንጋት ላይ አረፉ። ቅዱስነታቸው በድንገተኛ ሕመም ባልቻ ሆስፒታል ከገቡ ከሁለት ቀን በኃላ በዛሬው ዕለት በተወለዱ በ76 ዓመታቸው አርፈዋል። ላለፉት 20 ዓመታት ቤተክርስቲያንዋን ሲመሩ የነበሩት አቡነ ጳውሎስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሕመም እየተደራረበባቸው ቢመጣም እስካለፈው ሁለት ቀን ደረስ ስራ ከመስራት አላገዳቸውም ነበር። ላለፉት ሶስት ቀናት በጠና የታመሙት አቡነ ፓውሎስ እኩለ ሌሊት ላይ ማረፋቸው ታውቋል። የቅዱስነታቸው ዕረፍት ለቤተክረስቲያኒቱ ታላቅ ሀዘን ነው። አውደ ምህረት በቅዱስነታቸው እረፍት የተሰማትን ትልቅ ሀዘን ትገልጻለች።


ዜናውን እየተከታተልን እናቀርባለን

አሁን በደረሰን ዜና መሰረት የጠቅላይ ቤተክህነቱ ስራአስኪያጅ አቡነ ፊሊጶስ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ንግግራቸውን የጀመሩት ቤተክርስቲያኒቱ ታላቅ ሀዘን እንደወደቀባት በመግለጽ ነው። ብጹዕነታቸው ንግግራቸውን በመቀጠል “…ኃዘኑ የቤተክርስቲያን ኃዘን ነው። የሀገር ሀዘን ነው። ቅዱስነታቸው ትልቅ አባት ናቸው። የስራ ሰው ናቸው።ቀን ይሰራሉ ማታ ይሰራሉ። ሰኞ እና ማክሰኞ እንኳ ቅዳሴ ገብተው ነበር።  በሕይወቴ እንደዚህ አይነት የስራ ሰው አይቼ አላውቅም። ለኛ ሰርተው ለኛ ደክመው ያለፉ አባት ናቸው። ሞቱ ለእሳቸው ዕረፍት ነው ጉዳቱ ለእኛ ነው።…” ሲሉ ተናግረዋል።
ብጹዕነታቸው ንግግራቸውን በመቀጠል “እኒህን ታላቅ አባት እንዲሁ ዝም ብለን አንሸኛቸውም ለአለም አብያተ ክርስቲያናት አሳውቀን በተገቢው መንገድ እንሸኛቸዋለን።” ሲሉ ተናግረዋል። መግለጫውን በሰጡበት ወቅት የስብከተ ወንጌሉ አዳራሽ ሙሉ የነበረ ሲሆን ግቢው አሁንም በበርካታ ሰዎች እንደተሞላ ነው። በተለይም እሳቸው ይረዱዋቸው የነበሩት አቅመ ደካሞች ለቅሶ አብዛኛውን ሰው ያስለቀሰ ነበር።
ሲኖዶሱ አሁንም በስብሰባ ላይ ሲሆን ጳጳሳቱ ከየሀገረ ስብከቱ እየተሰባሰቡ መሆኑ ታውቋል።

4 comments:

  1. RIP Abune Paulos!

    ReplyDelete
  2. ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ፓትሪያሊክ ከዚህ አለም በሞት በስጋ በመለየታቸው እጅግ በጣም አዝነናል። ሆኖም ግን እውነተኛ
    የጌታ ሐዋርያ ፣ የሐይማኖታችን አርበኛ፣ በትእግስት የሚገባውን ሩጫ ፈፅሞ ወደ ጌታው በመሄዱ ደግሞ ፍፁም ክርስቲያናዊ ደስታና ሃሴት
    ተሰምቶናል። ሰው የማያውቀውን የድል አክሊል የሚያውቀው አምላኩ እግዚአብሔር እንደሚያቀዳጀውም በምሥሉ ልብ እናምናለን።

    እኛም ክርስቲያኖች ከብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፤ ፈተናንና መከራን በትእግስት ማሳለፍን ተምረናል። እግዚአብሔር አምላካችን ከቅዱስነታቸው ረድኤትና በረከት ያካፍለን እንላለን፣ አሜን፣ አሜን፣ አሜን።

    ReplyDelete
  3. By the well of the Almighty God our beloved Patriarch had done his plan according to the word of GOD. And he accomplished his mission by the power of GOD. He is now with the righteous people in the heavenly place. I am so proud of what he done for our Church. This is really good for him to depart from this sinful world but for this generation it is to bad. but
    we followers and leaders of the church will foffow his footstep. May the Lord Jesus Christ give rests to his soul.

    ReplyDelete
  4. የብጹነታቸው መሞት እጅግ ያሳዝናል። ለእርሳቸው ሰላም ነው። ብዙ ስቃይ ሳያገኛቸው የሚያመልኩት ሕያው እግዚአብሔር ጠራቸው። የእግዚአብሄር ስራ ድንቅ ነው። በዚህ በተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት በነዋይ የሰከሩበት ዓለም ርህራሄ በሌላቸው አባቶች መካከል እዳይኖሩ በክብር በሰላም ማረፋቸው ለእርሳቸው ታላቅ የሰላም እረፍት ነው። ለእኛ ለአማኞች ግን የመከራ ዘመን እየመጣ ነው። የማቅ ጳጳሳት ደስ ብላቸውም እርሱም አማማታቸውን እንኳን አያውቁትም። ሰው ሰለ እራሱ ሳያው በሌላው ላይ መፈረድ ነግ የእረሱ ተራ ይጠብቀዋል። ታላቅ አባት ቤተ ክርስቲያናች በእውነት አጥታለች። ጥቅምና ጉዳቱ ወደፊት ሁላችንም እግዚአብሔር እድሜ ይስጠንና እናየዋልን።

    ReplyDelete