Wednesday, August 15, 2012

ኢሳትና ማቅ : ግማታም ግማታምን ቢስመው አቤት ሽቶክ አቤት ሽቶክ ይባባላሉ!

Click here to read in PDF; Esat and MK
በሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል
ከኢትዮጵያን ሪቪው ድረ- ገጽ የተገኘ
http://www.ethiopianreview.com/amharic/?p=62765
ምስጋና - በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ሁለት የተለያዩ ፅንፍ የያዙ አመለካከቶችንና አስተሳሰቦችን እኩል ዕድል በመስጠትና በማስተናገድ ረገድ አንድ ተብሎ እስከ አምስት በማይዘልቁ የድረ ገጽ ባለቤቶች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያን ሪቪው ባለቤት ኤልያስ ክፍሌን (ሳይውል ሳያድር ጽሑፉን ከስፍራው ለማንሳት ቢገደድም) ጭብጥ ላይ የተመሰረተ ግላዊ አስተሳሰቦቼንና አመለካከቴን መግለጽ ይቻለኝ ዘንድ እስከ ዛሬው ዕለት በሰጠኝ ዕድል ከልብ ምስጋናዬ ለማቅረብ እወዳለሁ።

መንደርደሪያ

በሀገር ቤትኛው አማርኛ አንድ የሚድያ ሠራተኛ እንዲሁ በቀድሞ አጠራር በደፈናው ጋዜጠኛ መባሉ እየቀረ ኪራይ ሰብሳቢው ካልሆነ ደግሞ ልማተኛው በማለት በጎራ ተለይቶ መጠራት መጀመሩን ስሰማ እጅግ ደንቆኝ ነበር። ታድያ ሰው ከልምዱና ከተመክሮው ነው አዲስ ነገር የሚያስተዋውቅና እኔም እንግዲህ በተራዬ ኩታራም አለ ስል ሦስተኛና ተጨማሪ ስያሜ ላስተዋውቅ ነው። ወደ ሰፊው ሐተታዬ ከመዝለቄ በፊት ግን ስለ ስያሜው ትርጓሜ ጥቂት ልበል። ኩታራ ማለት ራዕይ/ግብ/ዓላማ የለሽ ፍርፋሪ ለቃሚ፣ ንዝህላል፣ በራሱ በዕድሜውና እንዲሁም በባልንጀሮቹ የሚቀልድና የሚያፌዝ - ዋዘኛ፣ በተለይ የቋንቋው መገኛ ከወደ ቤተ ክህነት አከባቢ እንደመሆኑ መጠን አንድ ተማሪ ስሙ በተጠራ ቁጥር በአስተማሪው ዘንድም ሆነ በጓደኞቹ "ኩታራው" የሚል ተቀጽላ የሚታወቅ እንደሆነ/የተሰጠው እንደሆነ ተማሪው ምን ዓይነት ሰብእና እንዳለው ለመገመት አያዳግትም።
ኩታራ የተማሪ መልክና ምስል ቢኖረውም ከአንድ ተማሪ የሚጠበቅ ሥነ ምግባር የማይታይበት፣ ግብረ ገብነት የሚጎድለው-ወፈፌ ማለት ሲሆን ይህ ማለት ለተማሪዎች በተዘጋጀ ማደሪያ ቢያድርም ስለ እመ ብርሃን ተብሎ በልመና የተገኘ ከጓደኞቹ እየተቆራመተ ቢመገብም ዳሩ ግን ከትምህርት ገበታ የሌለ፣ ምክንያተኛ፣ መዋያው የማይታወቅ - አውደልዳይ፣ በአጠቃላይ ኩታራ ማለት ፍሬ አልባ በለስ እንደ ማለት ነው። በጋዜጠኝነትና በሚድያ ተቋም ስም የሚፈጸሙ ዓይን ያወጡ ውንብድናም በተመሳሳይ የድርጊቱ ዋና ተዋናይ ግለሰብ ኩታራ ተብሎ ቢጠራ ያንስበታል እንጂ አይበዛበትም።

የጽሑፉ መነሻ ሐሳብ
ኢሳት"ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነት መፈረጅ ቤተ ክርስቲያንን እንደ መፈረጅ ነው ተባለ" ሲል ነሀሴ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ /ም ርዕስ አስጩሆ በተንቀሳቃሽ ምስልም የማህበሩ አርማ ደቅኖ ያስተላለፈውን "ዜና" ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው። ለበለጠ መረጃ ዝቅ ሲል የተቀመጠውን ሊንክ ተከትለው ለማንበብ ይችላሉ።
http://www.ethsat.com/2012/08/09/%E1%88%9B%E1%8A%85%E1%89%A0%E1%88%A8%E1%89%85%E1%8 %B1%E1%88%B3%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8A%AD%E1%88%AB%E1%88%AA%E1%8A%90%E1%89%B5-E1%88%98%E1%8D%88%E1%88%A8%E1%8C
%85-%E1%89%A4%E1%89%B0/
ሐተታ
የሀገሬ ሰው ሲተርት የአይጥ ምስክርዋ ድንቢጥ እንዲል ሆነና ነገሩ መቀመጫው አምስተርዳም ያደረገ .. በመባል የሚታወቀው የግል "የዜና" ማሰራጫ ማዕከል ሀገርና ትውልድ ቁልቁል እየደፋና እየገደለ የሚገኘው፣ በብዙዎች የቅድስት ቤተ- ክርስቲያን ልጆች ደም የተጨማለቀ፣ ተጠያቂም ሆነ፣ በኢ/////ያን የረጅም ዘመን ታሪክና ህልውና ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ችግሮችንና ዕንቅፋቶችን በማስተዋወቅ እንዲሁም የጥፋት መሰርተ ድንጋይ በማኖርም ራሱን የቅዱሳን ማህበር ሲል ያስተዋወቀ፣ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ- ክርስቲያን ነዋያተ ቅድሳትና የተለያዩ ጥንታውያን ቅርሳ ቅርሶች በመዝረፍና ለምዕራቡ ዓለምም በመሸጥ ኪሱን ያሳበጠ፣ አድባራትና ገዳማትን በማራቆት አገልጋዮችንም በማሳደድ ስም ያተረፈ፣ አረጋውያን አበውን በማታለልና በማጭበርበር ይዞታው የኢ////ያን የሆነው መሬት ሰነዶችን በማጨናበር እንዴት? በማንና ለማን? የሚሉት ጥያቄዎች የማይመልስ ሕንጻ ያቆመ የአሶር ምላጭ መሆኑን እየታወቀ ይህን ሁሉ ለሰሚ ጆሮ የሚሰቀጥጥ አተላ ታሪኩ ለማዳፈንና ለማድበስበስ ከፈተኛ ገንዘብ አፍስሶ ተናግሮ የሚያስነግራቸው ሰርቶ የሚያሰራቸው የፈጠራ ወሬዎችና ዜናዎችን ኢሳት በኩራዝ እየፈለገ እየለቀመና እያነፈነፈ የሚያነበንብበት፣ ሰሚ ጆሮ የሚያደነቁርበት ምክንያቱ ምንድን ነው?
ምን እያልኩ እንደሆነ ስለምን እየፃፍኩ እንደሆነም የጽሑፉ አንኳር መልዕክት/ጭብጥ በሚገባ ያገኙት ዘንድ ትንሽ ወጣ አድርጌ ልመልስዎት ዘንድ ይፈቀድልኝ። ባለፈው ሳምንት ኢሳት "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞተዋል" ሲል የቂል ከበሮ ሲደልቅ ሰንብቷል ከወደ ኢትዮጵያ ደግሞ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህመማቸው አገግመው ሀኪም ባዘዘላቸው መሰረት በዕረፍት ላይ ይገኛሉ" ሲሉ መግለጫ መስጠቱ የሚታወቅ ነው። ይህ ተከትሎም ኢሳት መልሶ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካልሞቱ በህይወት ለመኖራቸው መንግሥት የምስል ወይንም ደግሞ የድምጽ ማስረጃ ያቀርብ ዘንድ ኢሳት ጥሪውን ያቀርባል" ሲል መግለጫ ቢጤ መናገሩን የምንዘነጋው አይመስለኝም። እዚህ ላይ ግልጽ ማድረግ የምፈልገው ነጥብ አለኝ ይኸውም ጠቅላይ ሚንስትሩ ሞተዋል አልሞቱም በሚለው ሙግት ላይ "ሞተዋል!” "የለም አልሞቱም!" የማለት አቅሙም እውቀቱም የለኝም። ለነገሩ እኔም ብቻ ሳልሆን ኢሳት እንደ ድርጅትም ሆነ ሰራተኞቹ እንደ ግልሰብ እንደማንኛው ተራ ዜጋ ከጨዋታው ሕግ ውጭ እንደመሆናቸው መጠን ሟች ምስክር ወረቀት ይዘው እስካልቀረቡ ድረስ "ሞተዋል" የማለት መብት ብቻ ሳይሆን ከላይ ከፍ ስል ለማስታወስ እንደሞከርኩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህይወት ለመኖራቸው ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው ማንንም የመጠየቅ ስልጣኑም መብቱም የላቸው።
ማረጋገጫ ያቀርብ ዘንድ የሚጠየቀው አካልም እንደሆነ የማቅረብ ግዴታ የለበትም!! ሞተዋል ከተባለ በቃ ሞተዋል! ኢሳት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት የታየው በህልም አልያም ምዋርት ካልሆነ በስተቀር የሌላውን አካል ምስክርነት ምን አስፈለገው? የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያየውና እንዲሰማው የሚፈለገው እኮ ሲታከሙበት ከቆዩበት ሆስፒታል ትክክልኛ ተአማኒነት ያለው የምስክር ወረቀት (የሞት ሰርትፍኬት) ይዘህ ስትቀርብ ነው። ኢሳት ይህን ይዞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞተዋል ካለ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ ቃል ለመስማት የሚጠብቅበት ምክንያት አይኖርም። መዘንጋት የሌለበት ቁምነገር ግን "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞተዋል" ወደ ማለት ይፋዊ/ሕጋዊ ድምዳሜ ያልደረሰ ሕዝብ ግን የሚመለከተውን አካል በመጠየቅ የመሪውን ሁኔታ የማወቅ መብት አለበት።  ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከሞቱም አሁን ባለበት ሁኔታ ቀጥሎ ከሳምንታት ሆነ ከወራት በሃላ መንግሥት እንግዲህ "ጠቅላይ ሚኒስትራችን የስራ መደራረብ ከፈጠረባቸው ሕምም የተነሳ በውጪ ሲታከሙ ከቆዩ በሃላ በዛሬው ዕለት --- ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል" መስጠቱ አይቀርም፡፡
እንደው ነገሩ ቀለል እናድርገውና ለምሳሌ ያህል እርስዎን (ውድ አንባቢ ማለቴ ነው) አንድ ሰው ብድግ ብሎ "ኪስ አውላቂ ሌባ ኖት!" ያገቡትም እንደሆነ "ቃል ኪዳን አፍራሽ አመንዝራ" ቄስ/ዲያቆን እንደሆኑ "መናፍቅ" ሰራተኛ እንደሆኑም "ሙሰኛ" በማለት አንድ ሰው በቃልም ሆነ በጽሑፍ ከመሬት ተነስቶ የለጠፈቦት፣ የወረፍዎት የሰደብዎትና ያዋረድዎት እንደሆነ ወይንም ቢልዎት ምን ይሰማዎታል? እንደ እኔ ከሆኑ ይቅለልም ይክበድም ስድብ የጠገብኩ  ነኝና ሁኜ እስካልተገኘሁ በማለት ስድብን ንቀውና አቅልለው በማየት ሰምተው እንዳልሰሙ አይተው እንዳላዩ ማለፍ አንድ ነገር ነው ሆነም ግን የሚነገርው ቃል በትዳርዎ፣ በማህበራዊ ሕይወትዎና በስራዎ የሚያመጣው አሉታዊ ተጽእኖ ያለ እንደሆነ ግን ቀዳሚ እርምጃዎ ምን ይሆን ነበር? ንጽሕናዎትን ለማረጋገጥ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሰሜኑ ደቡቡ ያካልሉት ይሆን ወይስ ተናጋሪው ግለሰብም ሆነ ድርጅት መስመሩን ጠብቀው ለቃሉ ሃላፊነት ይወስድ ዘንድ ወደ ሚመለከተው አካል አቤት ይላሉ? በእርግጥ አቤት የማለት ዕድል የሌሎትም እንደሆነ ውሽት ሁል ጊዜ ውሸት ነውና መስቀለኛ ጥያቄዎች እያነሱ ወሬው ምን ያክል የፈጠራና በሬ ወለደ አሉባልታ ለመሆኑ በቃልም ሆነ በጽሑፍ መግለጽ ደግሞ ሌላ ተገቢ መንገድ ነው።
ማስረጃ የማቅረቡ ጉዳይ ሲሰርቁ፣ ሲቀጥፉም ሆነ ሲያፋልሱ በዓይኔ አይቻለሁ ማስረጃ አለኝ ለሚለው አካል የሚተው ይሆናል። አለበለዚያ ግን "ሌባ፣ አመንዝራ፣ መናፍቅ፣ ሙሰኛ ኖት" ብዬ መልካም ስሞትን አጥፍቼ ሳበቃ ተመልሼ ሌባ ላለመሆንዎ ማስረጃ ያቅርቡ ማለት በራሱ ቅሌት ይባላል። እርስዎም እንደሆኑ ሌባ፣ አመንዝራ፣ መናፍቅ፣ ሙሰኛ ላለመሆንዎ ባዩ አካልም ሌባ፣ አመንዝራ፣ መናፍቅ፣ ሙሰኛ ለመሆንዎ ደረቅ ማስረጃ ይዞ እስካልቀረበ ድረስ ንጽሕናዎ የማረጋገጥና አሉባልታውን የማስተባበል ግዴታ የለቦትም ብዬ አምናለሁ። ልብ ይበሉ! ለጊዜውም ቢሆን ማስረጃ ያልቀረበበት ሁሉ ንጹሕ ነው እያልኩ አይደለም። በግላጭ በሚነገሩ ነገሮች ግን በህግ ያስጠይቃል በወንጀልም ያስቀጣል ነው ነጥቤ። ባለፈው ወር የኢሳት ባልደረቦች ስማችን ጠፍተዋል ሲሉ በተናጠል "ውሽት!” በማለት የሰጡትን አጸፋዊ ማላሽ ለዚህ አንቀጽ ማገናዘቢያ ይሁንዎት።
ወጣም ወረደ ወደ ዋና ርዕሳችን እንመለስና ረጅሙን ታሪክ ስናሳጥረው እንደሚከተለው ይመስላል። ራሱን "ማኅበረ ቅዱሳን" በማለት የሚጠራ ስብስብ
ለሀገርም ለትውልድም የማይበጅ ጽንፈኛ የደንቆሮዎች ስብስብ ነው፣
"ማኅበረ ቅዱሳን" የበግ ለምድ የለበሰ ተናጣቂ በላተኛ አውሬ ነው፣
"ማኅበረ ቅዱሳን" አገር አጥፊ ትውልድ ገዳይ ጋንግሬን ነው፣
"ማኅበረ ቅዱሳን" በስመ መንፈሳዊነት ቤተ-ክርስቲያን የማውደምና የማፈራረስ ልዩ ተልዕኮ ያለው ድርጅት ነው፣
"ማኅበረ ቅዱሳን" የብዙሐን ንጹሐን ዜጎች ደም ያለበት ወንጀለኛ ነው፣
"ማኅበረ ቅዱሳን" አታላይ፣ አወናባጅና ነፈሰ ገዳይ ነው፣
ማኅበረ ቅዱሳን" የሀገር ዕድገትና የወገን ለውጥ የማይሻ የሰው መለወጥ ደመ የሚያስቀምጠው ቀናተኛ ነው፣
ማኅበረ ቅዱሳን" ለምንም የማይበጅ ቆርጠህ ሊጣል የሚገባው ትርፍ አንጀት ነው፣
"ማኅበረ ቅዱሳን" በሰላማውያን ወንዶችና ሴቶች መካከል ጸብና ሁከትን ከመጫር ውጪ ፍቅር የማያውቅ ጋንጩር ነው፣
'ማኅበረ ቅዱሳን" ስሙ የማይጠራ መንፈስ የነገሰበት ነቀርሳ ነው፣
ማኅበረ ቅዱሳን" ሊሰርቅ ሊገድልና ሊያጠፋ በመስኮት የገባ ሌባ ነው። በማለት በአደባባይ ስጽፍ ፍጥረታዊ ሰው በሚታይ በሚጨበጥና በሚዳሰስ ያምናልና ለዚህ ሁሉ ቃሌና ሌሎች የማኅበሩ ስውር ማንነት ጭብጦቼንና ማስረጃዎቼን ይዤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በቅዱሳን ስም ሀብተ ንብረቱ እየተዘረፈ ላለውና ለሚገኘው ለኢ / / / / ያን አማኞች እውነቱን አቀርብና አስረዳ ዘንድ ሚዲያው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሩን ይክፈት። " አይደለም ውሸት ነው !” የሚል ማኅበሩን የሚወክል ግልሰብም ሆነ ድርጅት የተገኘ እንደሆነም በድጋሚ እኩል መድረክና ሽፋን ተሰጥቶን መሞገት ይቻል ዘንድ የማወያያ መድረክ ይክፈት። ነጻና ፍትሐፊ ከሆነ መገናኛ ብዙሐን ይህን ማድረግ ይጠበቃል ግዴታም አለበትና። በተረፈ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ኢሳትን እንደ ድርጅት ድርጅቱንም በግልጽም ሆነ በስውር የሚያንቀሳቅሱ ግለሰቦች የዚህ ሁሉ የማኅበሩ እኩይ ምግባር ተባባሪዎች ካልሆኑ በስተቀር ኢሳት "ማህበረ ቅዱሳንን" በማስመልከት ከዚህ ቀደም ለተሰነዘሩ አስተያየትና ለቀረቡ መረጃዎች ማስተባበያ ያቀርብ ዘንድ ለመጠየቅ ነው። ሰው በሰፈረው መስፈሪያ ይሰፈርለት ዘንድ ግድ ነውና!! ሰው ጊዜና ዕድል ገጥሞሎት ለመጠየቅ ሲዳዳው ነገ በተራው ተጠያቄ እንደሆነ ደግሞ ልብ ሊለው ይገባል።
ቁም ነገር እንደዋዛ
"ቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ አውጥቶ ያዋቀረውን ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነት መፈረጅ ቤተ ክርስቲያንን እንደመፈረጅ ነውሲሉ የጅማ ሀገረ-ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ተናገሩ።" የኢሳት ዜና አንባቢ። ከተናጋሪው ተርጓሚው ከተርጓሚው ደጋሚው አትሉም? ደግሞስ ከመቼ ወዲህ ነው "ማኅበረ ቅዱሳን" ማለት ቤተ- ክርስቲያን የሆነው? መቼም "የተባለውን ነው ያስተላለፍነው" በማለት የኢሳት ዜና አንባቢም ሆነች ከስፍራው የዘገበ አካል ማምለጥ እንደማይቻለቸው የሚስቱት አይሆንም። ማዕከሉ የተባለው ሁሉ ሳያጣራና ግራ ቀኙን ሳይል የሚያስተላልፍ እንደሆነ ደግሞ ለስራዎቹና ለዘገባዎቹ አመኔታውን ለሕዝብ የሚተው ይሆናል። ሌላው ግን አንስትዋ የኢሳት አንባቢ ይህን ርዕስ ይዛ ዘገባዋን ስታነብ ቅጽበታዊ በሆነ ፍጥነት ወደ አእምሮዬ የመጣው ማን እንደቀረጸውና በማን ስምም እንደተቀረጸ ባላውቅም እንዲሁ ግን ኢሳት ለማህበረ ቅዱሳን ታቦት ቀርጾ የሰጠው ሁላ ነበር የመሰለኝ።
ደግሞም ንባቡ ከዚህ የተለየ መልዕክት የለውም። እኔ የምለው ግን ኢሳት "ዜና" ከመስራት አልፎ ታቦት እየቀርጸ መስጠትና መሸጥም ከጀመረ በውል ይናገርና ከፈላጊዎች እናገናኘው። ያልሆነ ነገር በመፈብረክና በማሰራጨትም በሰላማውያን ዜጎች መካከል ውዥንብር ከመርፍጠርና ሰላማቸውንም ከመንሳት ወጪ በሌለበት የስራ መስክ መሰማራትም የሚበረታታ ነው።

ማጠቃለያ (ማሳሰቢያ)
አሁንም ቢሆን ግልጽ ለማድረግ የምፈልገው ነጥብ ቢኖር ጽሑፉ የኢሳት አጠቃላይ ስራዎችም ሆነ የድርጅቱ ባልደረቦች በጅምላ የማይወክል ለመሆኑ አጽንዖት ሰጥቼ ራሴን ግልጽ ለማድረግ እወዳለሁ። "ማኅበረ ቅዱሳን" ከኢሳት ጋር አብሮ እንዲሰራ ያስተዋወቀ፣ ያቀራረበ፣ ያደራደራና ያስማማ ድግስም የበላ ከምንም በላይ ደግሞ ይህ ቆማጣጣ እርሾና መራራ ዘር ወደ ኢሳት ያስገባና ኢሳትን የደለለ ግለሰብ/ድርጅት በገባበት በር እስኪወጣ ድረስ ሰላማዊ ቅብብሉ ተጠናክሮ ይቀጥል። የተሰጠውን ርዕስ በተመለከተ ቋንቋን በተገቢ ጊዜና ስፍራ ለአገልግሎት እስከዋለ ድረስ ተገቢ አገላለጽ ነው። "ድን ባለበት በዚያ ዝንቦች ይሰባሰባሉ" እንደሚባለውም ማቅ ልብሱ ያደፈ ጠረኑ ማንንም የማያስጠጋ የገማ የደንቆሮዎች ስብስብ ለመሆኑ ጥያቄ ውስጥ አይገባም። የኢሳት ነገር ግን ከአመፀኛ ጋር የሚተባበር አመፀኛ ነውና ከዚህ ሲያሜም ራሱን ለማንጻት ከተፈለገ ወንጀለኛን ወንጀለኛ ማለት ይጠበቅበታል።
/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E- mail yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America

No comments:

Post a Comment