Monday, August 20, 2012

ሰበር ዜና፡ አቡነ ናትናኤል በአቃቤ መንበርነት ተሾሙ

Click Here to read in PDF: aba natenael 2
·          “ምን አስቸኮላችሁ? አፈር እስኪቀምሱ እንኳ ብትታገሱ ምን ነበረበት?”
                                                                            የአቡነ ጳውሎስ ታናሽ እህት
ለማኅበረ ቅዱሳን ፍላጎቶች ራሱን እያስገዛ የመጣው ሲኖዶስ ብጹዕ አቡነ ናትናኤልን በአቃቤ መንበርነት ሾመ፡፡
ብጹዕ አቡነ ናትናኤል በእድሜ የገፉ ስለሆነ እና የጤናም ችግር አለባቸው በሚል በስራቸው ቋሚ ሲኖዶሱን ጨምሮ 14 አባለት ያሉት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መርጧል፡፡ በዚህ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ የማኅበረ ቅዱሳን የልብ ወዳጅ የሆኑት አቡነ ሉቃስ አቡነ አብርሃም አቡነ ጢሞቴዎስና አቡነ ሳሙኤል አቡነ ገብርኤል እና አቡነ እስጢፋኖስ ይገኙበታል፡፡
ሥራዎች በአጠቃላይ በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በኩል የሚሰሩ ሲሆን የአቡነ ናትናኤል ስራም ስራ አስፋጻሚ ያጸደቀውን ላይ መፈረም ይሆናል፡፡

ከ30 ደቂቃ በፊት ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት አቡነ ፊሊጶስ ሲሆኑ መግለጫውን ሲያሰሙ እየሆኑ ባሉ ነገሮች ግራ የተጋቡ መሆናቸው ያስታውቅ ነበር፡፡ ብጹዕነታቸው ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው  ምን አስቸኮላችሁ? ከቀብር በኋላ ይሆናል አላላችሁም ነበር ወይ? በመካላችሁ ሽኩቻ አለ ይባላል? ለሚሉ እና ሌሎች ጥያቄዎች መልስ ሳይሰጡ ቀርተዋል፡፡ በጋዜጣዊው መግለጫም ወቅት የአቡነ ጳውሎስ ታናሽ እህት “ምን አስቸኮላችሁ? አፈር እስኪቀምሱ እንኳ ብትታገሱ ምን ነበረበት?” ሲሉ ተሰምተዋል፡፡
 
በትናንትናው ዕለት እንዳስታወቅነው አቡነ ፊሊጶስ ለማኅበረ ቅዱሳን በተገቢው ሁኔታ አላጎበደዱም በሚል ከቀብር በኋላ ታስቦ የነበረው የአቃቤ መንበር ሹመት ለዛሬ እንዲሆን  አቃቤ መንበሩም አቡነ ናትናኤል እንዲሆኑ  በማኅበረ ቅዱሳን ተወስኖ የነበረ መሆኑን ዐውደ ምህረት ገልጻ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይኸው ያልነው መሆኑን እና አንባቢ የሚታዘበው እውነት ነው፡፡ ይህም ስለማኅበረ ቅዱሳን የምንጽፈው ከተጨባጭ መረጃ ጋር መሆኑን በበቂ ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment