Friday, August 17, 2012

የአቡነ ጳውሎስ ዜና እረፍት እና ተያያዥ ጉዳዮቹ

Click Here to read in PDF: Abune pawlos 2
የቅዱስ ፓትርያርኩ ዕረፍት ከተሰማ በኋላ በቤተተክርስቲያን አካባቢ ቢያንስ እስከ ቀብር ስርዓታቸው ድረስ እንኳ መጠላለፎች እና ሽኩቻዎች ቀርተው ነገሮች በሰላም ይካሄዱ ይሆናል የሚል ግምት የነበረን ቢሆንም እያየነው ያለው ነገር ግን ከዚህ በተለየ ነው።
በመንበረ ፓትርያርክ ግቢ ውስጥ ያለው ሁኔታ እጅግ የሚያሳዝን ነው። ለቅሶ ሊደርስ የሚመጣ ሰውን እንኳ በአግባቡ ተቀብሎ የሚያስተናግድ ሰው አልተዘጋጀም። ሰዉ ራሱ መሄጃ ሲያጣ የስብከተ ወንጌል አዳረሽ ውስጥ ገብቶ መቀመጥ ጀመረ እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ ያዘጋጀችው ቦታ የለም። በስብከተ ወንጌሉ አዳራሽ ውስጥም አንድም የቤተክርስታኒቱ ተጠሪ አለመኖር የሚያስገርም ሆኗል። ይህ ሁኔታም ለቅሶ ሊደርስ የመጣውን ህዝብ የአባቱን ዕረፍት ሰምቶ የመጣ ሳይሆን በባዳ ለቅሶ የተገኘ እንግዳ ደራሽነት እንዲሰማው አድርጎታል።

አርባ ሚሊየን ህዝብን ለ20 ዓመታት የወከሉ አባት በዚህ ሁኔታ እረፍታቸው እየተስተናገደ መሆኑ ያሳፍራል። ከዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ በመለስ ሰብአዊ ርህራሄ በሚያስፈልግባቸው ጉዳዮች አሁን በመንበረ ፓትርያርክ አካባቢ ያሉ ሰዎች ምንም አይነት ተገቢ እንቅስቃሴ አለማድረጋቸው አሳዛኝ ጉዳይ ሆኗል።
በተለይም በማኅበረ ቅዱሳን አካባቢ የሚታየው ሁኔታ በእጅጉ አሳፋሪ ሲሆን የማኅበሩ አመራሮች የቅዱስነታቸውን ሞት በምን ሁኔታ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው የተወያዩ ሲሆን ከስብሰባው ፍጻሜ በኋለም የቀብር አስፈጻሚው ኮሚቴ ውስጥ ቦታ ለመያዝ ባደረጉት እንቅስቃሴ የማኅበሩ ሰብሳቤ የሆነው ዶክተር ሙሉጌታ የቀብር አስፈጻሚው ኮሚቴ አባል እንዲሆን ተደርጓል። ይህን ተከትሎም በማኅበረ ቅዱሳን ሀሳብ አቅራቢነት የቅዱስነታቸው የቤተክርስቲያን አባትነት ተረስቶ ዘመዶቻቸው ተጠርተው አስከሬኑን ወደ ትውልድ ቦታቸው ወስደው መቅበር የሚፈልጉ ከሆነ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። በዚህ ጥያቄም በጣም ያዘኑት ቤተዘመዶቻቸውን እና የቤተክርስቲያን አባቶች አቡነ ጳውሎስ የዘመዶቻቸው ሳይሆኑ የቤተክርስቲያን አባት ናቸው በማለት ይህ ተዘንግቶ ዘመዶቻቸው ከቤተክርስቲያን በልጠው የአባታችንን አስክሬን ይዘው ይሂዱ መባሉ እጅግ እንዳሳዘናቸው ገልጸው የሚቀበሩት እዚሁ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ቅዱስነታቸው የቤተክርስቲያኒቱ አባት መሆናቸውና ላለፉት ሃያ አመታትም ቤተክርስቲያኒቱን መምራታቸው እየታወቀ እንዲህ ያለ ጥያቄ እንዲነሳ መደረጉ እጅግ አሳዛኝ ነገር ነው።
ምንም ይሁን ምን ቅዱስነታቸው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አባት ናቸው። ይህ አባትነታቸው ደግሞ በተገቢው መንገድ ሊገለጽ ይገባል። ቤተክርስያኒቱም ቢያንስ አለም እንዳይታዘባት አሸኛኘታቸውን ልታሳምር ይገባል። አርፈውም ቂምን እያሳቡ መኖር ግን ክርስትናችን ምን ያህል እንደዘቀጠ ያሳያል።
ከዚህ ተከትሎም እነ ዶ/ር ሙሉጌታ ቀብራቸው ቅዳሜ መፈጸም አለበት የሚል አቋም የያዙ ሲሆን ይህንን ሀሳብ አቡነ ፊሊጶስ ለወዳጆቻቸው መግለጽ በመጀመራቸው ያለሲኖዶሱ ይሁንታ ቀኑን ወመሰን አግባብነት የለውም የሚል ወገን በመነሳቱ ሀሳቡ እንደገና እንዲቀር ተደርጓል። ይህን ተከትሎም የአቡነ ጳውሎስ ቤተሰቦችን ወዳጆች የማኅበረ ቅዱሳን ወኪል ቀብራቸውን አያስፈጽምም እያደረገ ለውም ነገር ተገቢ ያልሆነ ነገር ነው ከኮሚቴው ይውጣልን የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ታውቋል። ይህን ተከትሎም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴሩ አቡነ ፊሊጶስን በስልክ ማናገራቸው ታውቋል።
ቀን ላይ አቡነ ፊሊጶስ መግለጫ ከሰጡ በኃላ የጠቅላይ ቤተክህነቱ ሠራተኞች ለስብሰባ የተጠሩ ሲሆን በዛ ስብሰባ ላይም ሳይጠሩ እና ሳይመለከታቸው የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ተገኝተው አብረው ተሰብስበዋል። ይህ ለምን ሆነ? የሚለው ጥያቄን መልስ ሊሰጥበት የሚችልም አካል አልተገኘም።
የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጉችም ቅዱስነታቸው ባረፉበት ቀን እንኳ ስለእሳቸው መጥፎ ማውራቱን አልተዉትም። ይህም ስር የሰደደ ቂማቸው ምን እንደሚመስል በጉልህ ያሳየ ክስተት ሆኗል። ሌላው እና አነጋጋሪ የሆነው ጉዳይ የቅዱስነታቸው አስከሬን ይመርመር የሚለው ጥያቄ በከፍተኛ ሁኔታ ያስቆጣቸው መሆኑ ነው። የቁጣው ምንጭ ምን ይሆን? የሚል ጥያቄንም አስነስቷል። በርካታ ወገኖችም የአቡነ መርሐ ክርስቶስ እጣ ለቅዱስነታቸው ደረሳቸው እንዴ? ሲሊ ተደምጠዋል። እስከ ረቡዕ ጠዋት ድረስ በቢሮዋቸው ተገኝተው ስራ ሲሰሩ የነበሩን አባት በድንገት መሞት ተከትሎ ለምን ሞቱ የሚለው ጥያቄ ለምን ያስቆጣል የሚል ክርክርን ተከስቷል። አስከሬኑ ይመርመር የሚለው ጥያቄ የመንግስት ሆኖም ሳለ እነ እገሌ ናቸው የሚል ክስ ማንሳቱም ጥቅሙ ምን ይሆን? አስብሏል።
ነግ በኔ በሚባልበት ሞት ከማዘን ይልቅ ቅዱስ ፓትርያርኩን በክፋት ካላነሳች እረፍት የማይሰማት የማቅ ብሎግ ደጀ ሰላም አሁንም እሳቸውን በእርቅ ሒደት አደናቃፊነት ከሳለች።  እንደ እውነቱ ከሆነ ግን አቡነ ጳውሎስ የሚመሰገኑበት ትልቁ ጎናቸው የይቅርታ ልብ ያላቸው መሆኑ ነው። ይህንን ባለፉት 20 ዓመታት የበርካታ ሰዎች ምስክርነት የተሰማበት ጉዳይ ሲሆን አሁን እሳቸው ስላረፉ የእርቅ ሂደቱ ምን ላይ እንደሚደርስ በሂደት የምናየው ነው። የእርቅ ሂደቱን በተመለከተም ችግሩ ምን ል እንደነበር እና እንደሚሆን ጊዜ የሚገልጠው ጉድ ነው። በኛ እምነት እና እውቀት ግን የእርቅ ሂደቱን ከማኅበረ ቅዱሳን እና ከአንዳንድ ጨዋ ጳጳሳት በላይ እንዳይሳካ ተግቶ የሚሰራ የለም። ነገ ከነገ ወዲያ እርቁ መስመር የያዘ ከመሰለ ምን ያህል አደናቃፊ ምክንያቶችን ማቅ እንደምትደረድር ሒደት የሚገልጠው እውነት ነው።

ቅዱስ ሲኖዶሱ በዛሬው ዕለት ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ የሚመርጥ ሲሆን ይህን ተከትሎም የቅዱስነታቸውን የቀብር ቀን ይወሰናል ተብሎ ይጠበቃል።

6 comments:

  1. ገና ብዙ ጉድ እናያለን።ምክንያቱም የማቅና አጃብዎቻቸው በሰው ሞት ደስ የሚላቸው መሆናቸውን እነሆ በግልጥ እያየን ነው።እንዚህ ጨካኝ አውሬዎች ናቸው። ሰብዓዊ ርህራሄ የሌላቸው ዉሾች መሆናቸው ስራቸው እየገለጸ ነው። ለእርሳቸውም ለመሞታቸው የማቅ እጅ አለበት። ሁሉ ከሰው ብደበቅ ከእግዚአብሄር ልደበቅ አይችልም ነገ በተራው ሁሉም ይደረሰዋልና።እውነተኛች ከሆኑ እስት በውጭ ሀገረ ያሉት ኣባቶች በቦታቸው ይመልሱ። አቡነ ጳዉሎስ ከእንግድህ በሗላ አያገኙአቸውም። እውነቱ አሁን ቀርበዋል። ታድያ አቡነ ጳዉሎስ አርፈዋል እና ለምን በስደት ያሉት አባቶችን በቦታቸው አያስቀምጡም? ። እነዚህ የስኖዶስ አባላት ለራሳቸው ጥቅም የምሮጡ በመሆናቸው አይዋጥላቸውም፡፤ ጉዱ አሁን ነው...ድሮ በአቡነ ጳዉሎስ ነበር የተሳበበው አሁን በማነው? መልሱን ከማቅ እንጠብቃለን... ብፁዕነታቸውን ነፍሳቸው በነአብርሃም አጠገብ በመንግስቱ ያድርግላቸው። አንድ ቀን እርሳቸዉን የሚናመሰግንበት ቀን ይመጣል። ለሁሉም ግዜ አለው። ደርግ እንጠላው ነበር የባሰው መንግስት መጣ ......ፍላጎታችን ገድብ የለውም ...... ሁሉን ለእግዚአብሄር መስጠት ከቻል እርሱ መልስ ይሰጣል። በጉልበታችን የሚንመካ ከሆነ ከእኛ የበለጠውን ጉልበተኛ ደግሞ ያስነሳብናል።

    ReplyDelete
  2. እውነት ነው በስደት ያሉት አባቶች በቦታቸው መመለስ አለባቸው።ድሮ ስንሰማ ኣቡነ ጳዉሎስ በጉልበታቸው ቀመተው ነው ስልጣን የያዙት ይባል ነበር።አሁን እርሳቸው ከሞቱ ወዲህ በማን ይሳበብ ይሆን? ለቤተ ክርስቲያንቱ አንድነት ሰላም ፍቅር ከልብ የሚናስብ ከሆነ አንድነቱና መታረቁ ይጠቅማል ግን ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ለራሳቸው ወንበር ዘርና ቡድን የሚታገሉ ከሆነ ግን አሁን የእምነቱ ነገር ቁልቁል እንጅ እድገት አይኖረውም። ስለዚህ ማቅ በቤተ ክህነት አከባቢ ዉር ዉር ማለቱ አንደልማዱ ሰላም አንዳይኖር ለማድረግ ነው። ሰው ስለሞተ ደስተኛ ስለሆን እነዚህ ለሀገር ለወገንም ለሀይማኖትም ካንሰር ናቸው ። ሰው ለመሆኑ እንደ ክርስቲናው ቃል እንዴት አያዚንም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በአልዓዛር ሞት አዘነ አለቀስም ይላል ቅዱስ ቃሉ ዮሐ 11፤33። ለሰማያት አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ብሎ ጌታ አባታችን ተናግሮዋል ማቴ 5 ቁ 46።እነ ማቅ ለመሆኑ የክርስቲና ህይወትና ስነ ምግባር አለቸውን? መልሱ ከእነርሱ ሥራ ስንመለከት የላቸውም።

    ReplyDelete
  3. ማህበረ ቅዱሳን ለእውነተኞች መንፈሳዊያን አባቶች ጠላት የሆነ ድርጅት ነው። ለጥቅሙ የምፈልጋቸውን አባቶች ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል እስከ ሰማይ ጣራም ድረስ ይወስዳቸዋል፡ የፈለገውን ነገር ከተሳካለት በሗላ ግን መቃብር በስኦል ውስጥ ስማቸውን በማጥፋት ይቀብራቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በህዝቡ ዘንድ የተጠላ በመሆኑ የሞት ሽረት እያደረገ ነው ስልጣን ለመጨበጥ። ሁሉም ይመኘዋል ችግሩ ግን ሥልጣኑ ከተያዘ በሗላ ያለው ፈተና ነው። ማቅ ከኢትዮጵያ ምድር ቅርቶቹ መጥፋት አለባቸው ። እግዝአብሔር የብዙሐኑ አምላክ ገና ድል ያደረጋቸዋል። የብጹነተቸው ሞት ብያሳዝንንም ለእርሳቸው ታላቅ እርፍትና ሰላም ነው። በምንም ምክንያት ብሞቱም ለእውነት ከሆነ ታላቅ ሰላም አግኝተዋል። ያታደሉ አባት ናቸው። በዚህ በሱባኤ ወቅት በሰላም ማረፋቸው ምን ያህል ጻድቅ እንደሆኑ ነው የሚያሳየን።መታደል ይሉታል ይህ ነው። በእመቤታችን ሱባኤ እያደረጉ በክብር ማረፋቸው የቅዱሳን መንገድ ነው።

    ReplyDelete
  4. menafik hulu abreh gudiad megbiah derswal

    ReplyDelete
  5. ስጋዬን የሚበላ ደሜንም የኳሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ስጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና ዮሐ 6:54
    whoever eats my flesh & drinks my blood has eternal life. for my flesh is food indeed & my blood is drink indeed. Jhon 6:54 #Tollo kemenigedihe temeles menafike hullu!

    ReplyDelete